የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)
13.3K subscribers
3.59K photos
731 videos
126 files
2.42K links
ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡

አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን!
ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን!
♻: https://api.whatsapp.com/send?phone=
Download Telegram
የዕለቱ መልክት!
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
​"ፍጥረታትን (ሰዎችን) በመኗኗር(መስተጋብር) ውስጥ እውነተኛውን ደስታ (ማግኘት ከፈለግክ)፦ ለአላህ ብለህ በመልካም መስተጋብር ልትኗኗራቸው ይገባል። በእነሱ ጉዳይ አላህን ተስፋ አድርግ፤ በአላህ ጉዳይ ግን እነሱን ተስፋ አታደርግ። በእነሱ ጉዳይ አላህን ፍራ፤ በአላህ ጉዳይ ግን እነሱን ልትፈራ አይገባም። ለእነሱ መልካም የምትውለው የአላህን ምንዳ ፈልገህ እንጂ እነሱ ብድሩን እንዲመልሱልህ ብለህ መሆን የለበትም። እነሱን ከመበደል የምትቆጠበውም አላህን በመፍራት እንጂ እነሱን በመፍራት ሊሆን አይገባም።"

​📚 [መጅሙዕ አል-ፈታዋ (1/51)]

​የመልዕክቱ ዋና ነጥቦች፦
​አላህን ብቻ ተስፋ ማድረግ፦ ለሰዎች መልካም ስትውል ምላሹን ከአላህ እንጂ ከሰዎች አትጠብቅ። ሰዎች ባይመሰግኑህ እንኳ አላህ ስለሚያውቅልህ ደስታህ አይቀንስም።
​አላህን ብቻ መፍራት፦ ሰዎችን የማትበድለው እነሱን ፈርተህ ሳይሆን አላህ ዘንድ መጠየቅን ፈርተህ ይሁን።
​ለአላህ ብሎ መኖር፦
ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ሁሉ አላህን ማዕከል ያደረገ ሲሆን፣ ሰዎች ቢቀየሩም ባይቀየሩም አንተ በአቋምህ ትጸናለህ፤ በዚህም ልብህ ዘላቂ ደስታን ያገኛል።
❤13
የ8000 ነውሮች(ጉድለቶች) መፍትሔ!
ኢማም አን-ነወዊ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
«በጥንት ዘመን የነበሩ ሁለት ጥበበኞች (ቀይስ ኢቢኑ ሳኢዳህ እና አክሠም ኢብኑ ሠይፍ) ተገናኝተው ሳለ፣ አንዱ ሌላኛውን እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ "
በሰው ልጅ ላይ ስንት ጉድለቶችን (ነውሮችን) አገኘህ?"

ጥበበኛውም እንዲህ ሲል መለሰ፦ "ጉድለቶቹ ተቆጥረው አያልቁም፤
እኔ ግን 8000 (ስምንት ሺህ) ጉድለቶችን አግኝቻለሁ። ሆኖም ግን አንድ ባህሪ አለች፤ እሷን ከተጠቀምክ እነዚህን ስምንት ሺህ ጉድለቶች በሙሉ ትሸፍንልሃለች

።"
ያቺ ብቸኛ መፍትሔ ምንድናት? ተብሎ ሲጠየቅ፦ "ምላስን መቆጠብ (መጠበቅ)" በማለት መለሰ።»
* ዑመር ዐብዱል ዐዚዝ እንዲህ ይላሉ፦ «
ቀደምት ደጋግ ሰዎች (ሰለፎች) እውነተኛ (ዒባዳ) በጾምና በሰላት ብቻ እንደሆነ አያስቡም ነበር፤ ይልቁንም ትልቁ ዒባዳ የሰዎችን ክብር ከመንካት ምላስን መቆጠብ እንደሆነ ያምኑ ነበር።»

አንድ ሰው ቀኑን ቢጾም፣ ሌሊቱን ቆሞ ቢያድርም፤ ነገር ግን ምላሱን የማይጠብቅና ሰዎችን የሚሰድብ/የሚያማ ከሆነ፣ የቂያማ ዕለት የለፋበትን ምንዳ የሚያጣ "ከሳሪ" (ሙፍሊስ) ሆኖ ይመጣል።
👍23❤11
ነቢዩ ﷺ ለትዳር እንድንመርጣቸው ያበረታቱን የሴቶች ባህሪያት፦

ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ ﷺ ኡመታቸው ውብ፣ ድንግልና የዲን ባለቤት የሆኑ ሴቶችን እንዲያገቡ ያበረታቱ ነበር።"
1. ምርጥ የተባለችው ሴት፦
አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ ነቢዩ ﷺ "ከሴቶች ሁሉ በላጭ (ምርጥ) የተባለችዋ የትኛዋ ናት?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦
> "
ሲመለከታት ደስ የምታሰኘው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ በራሷም ሆነ በንብረቱ ላይ እሱ የማይፈልገውን ነገር የማታደርግ ናት።

" (ነሳኢ)
>
2. የዲን ባለቤትን መምረጥ፦
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
> "
አንዲት ሴት ለአራት ነገሮች ሲባል ትገባለች፦ ለሀብቷ፣ ለዘር ሐረጓ (ለክብሯ)፣ ለውበቷና ለዲኗ (ለሃይማኖቷ)። አንተ ግን የዲን (የሃይማኖት) ባለቤት የሆነችውን በመምረጥ ስኬትን ተቀዳጅ!"

(ቡኻሪና ሙስሊም)
>
3. አፍቃሪና ወላጅ ሴት፦
ነቢዩ ﷺ የሚወዱና የሚወልዱ ሴቶችን ማግባትን ያበረታቱ ነበር። በአቡ ዳውድ በተዘገበው ሐዲስ ላይ እንደተጠቀሰው፣ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ ﷺ መጥቶ "ቆንጆና የተከበረ ዘር ያላት ሴት አገኘሁ፤ ነገር ግን አትወልድም፣ ላግባት?" ብሎ ጠየቀ። ነቢዩም "አይሆንም" አሉት። ለሁለተኛና ለሦስተኛ ጊዜም ጠይቆ ከለከሉት። በመጨረሻም እንዲህ አሉት፦
> "
አፍቃሪና ወላድ (ብዙ የምትወልድ) የሆኑ ሴቶችን አግቡ፤ እኔ በቂያማ ቀን በእናንተ ብዛት ከሌሎች ህዝቦች ፊት እፎካከርባችኋለሁና (እኩራባችሁለውና!)"

>
❤15
​"ራስህን ከነዚህ አራት ጠንቆች ጠብቅ!" ⚠️
​🤐 አላስፈላጊ ንግግር፦ ቃላትህ ይመዘገባሉና ከመናገርህ በፊት አስብ።
​🍲 ከመጠን ያለፈ ምግብ፦ ለበሽታና ለስንፍና ይዳርጋል።
​😴 ትርፍ እንቅልፍ፦ ጊዜህንና በረከትህን ይበላዋል።
​👥 ከሰዎች ጋር በብዛት መቀላቀል፦ ልብህን ከፈጣሪህ ያርቃል።
​በረከቱ እንዲዛመት ለሌሎችም አጋራው! 🔄

​📲 ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
[https://t.me/sultan_54]
👍7❤3
በዋትስኣፕ ለመከታተል፦👇
Follow the የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ(official) channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbC2qVH6hENvXGwN6U0c
❤3
አሁን መስመር ላይ ያለህ/ሽ... ✨

ለምላስ ቀላል የሆኑ፣ በሚዛኑ ላይ የሚከብዱ፣ በአላህ (አር-ፈሕማን) ዘንድ የተወደዱ የሆኑ ሁለት ቃላት ከኔ ለመደጋገም ዝግጁ?
Anonymous Poll
96%
ሱብሓነሏሂ ወቢሐምዲሂ✨🤎🍁
89%
ሱብሓነላሂ አል ዐዚም✨🤎🍁
👍15❤10👌1
​«አሁን መስመር ላይ ያለህ/ሽ... ከጀነት ግምጃ ቤቶች (ሀብቶች) አንዱ የሆነውን ዚክር አብረኀኝ በል» ✨🤎
Anonymous Poll
95%
​• ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ 🍂🤎
85%
​• ላ ሐውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ 🍂🤎
👍19❤3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
​📌 በነቢዩ (ﷺ) ክብር (ጃህ) ተወሱል ማድረግ የኺላፍ ርዕስ ነውን?
​በዱዓ ወቅት "በነቢዩ ክብር ይሁንብህ!" ብሎ አላህን መጠየቅን ይቻላልን? ተብሎ ተጠይቀው ዶ/ር ሷሊህ አል-ሲንዲ የሰጡት ምላሽ፦
​ማስረጃ የለውም፦
በዚህ መልኩ ተወሱል ለማድረግ የሚያስችል ምንም ዓይነት የሸሪዓ መረጃ (ደሊል) የለም።
​የሰሃቦች መንገድ አይደለም፦
የነቢዩ (ﷺ) ባልደረቦች እንዲህ ዓይነት ተግባር ፈጽመው አያውቁም።

​የልዩነት (ኺላፍ) ጉዳይ አይደለም፦
ይህ ዝም የሚባልለት የሊቃውንት ልዩነት ያለበት ጉዳይ ሳይሆን፣ ማስረጃ የሌለው "ቢድዓ" (አዲስ መጤ ነገር) ነው
።
​ጥንቃቄ፦
ወደ ሽርክ ሊያደርሱ ከሚችሉ መንገዶች አንዱ ስለሆነ ሙስሊሞች ሊጠነቀቁት ይገባል።

​ምንጭ፦ ሸርሕ ከሽፉ-ሹቡሃት (ዶ/ር ሷሊህ አል-ሲንዲ)
​ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
📲 [https://t.me/sultan_54]
❤4👍2
📌 በትዳር ውስጥ የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ጥቅሞችና መቋረጡ የሚያስከትለው ጉዳት!
ታላቁ ዓሊም ኢብኑል ቀዪም (ረሒመሁላህ) «ዛዱል ሚዓድ» በተሰኘው ኪታባቸው ላይ የነቢዩን (ﷺ) ፍኖት እና ቀደምት ሊቃውንት (ሰለፎችን) ምክር እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል፦
> "የነቢዩ (ﷺ) በወሲባዊ ግንኙነት ረገድ የነበራቸው  ፎኖት(ሀድይ) እጅግ የተሟላ ነበር።
(ጂማዕ) ጤናን ይጠብቃል፣ ደስታንና የነፍስ እርካታን ያስገኛል፣ እንዲሁም የተፈለገበትን ዋና ዓላማ ያሳካል።
>
✅ የጋብቻ ግንኙነት (ጂማዕ) ሶስት ዋና ዓላማዎች፦
* ዘርን መተካት፦ የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ አላህ የወሰነለትን ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ዘሩ ቀጥሎ እንዲቆይ ማድረግ።
* ጎጂ ፈሳሽን ማስወገድ፦ በሰውነት ውስጥ ተከማችቶ ቢቆይ በጤና ላይ ጉዳት የሚያመጣውን ፈሳሽ (መኒይ) ከሰውነት ማስወጣት።
* ፍላጎትን ማርካት፦ በተፈቀደው ጸጋ መደሰትና የነፍስ እርካታን ማግኘት። (ይህኛው ነጥብ በጀነት ውስጥ ያለ ብቸኛው ጥቅም ነው፤ ምክንያቱም በጀነት ዘር መተካትም የለምና።)
💡 የሰለፎች (ቀደምት) ምክር፦
አንድ ሰው ሶስት ነገሮችን ዘውታሪ ሊያደርጋቸው ይገባል፦
* መራመድን፦ አንድ ቀን አስገዳጅ ሁኔታ ቢፈጠር እንኳ መራመድ እንዳያቅተው።
* ምግብ መመገብን፦ ምግብ ቢያገኝ እንደልቡ መበላት አይችለረም።(አንጀቱ ስለሚጠብ።)
* የጋብቻ ግንኙነትን (ጂማዕን)፦ ምክንያቱም "የውሃ ጉድጓድ ካልተቀዳ ውሃው እንደሚጠፋ ሁሉ" ይህ ግንኙነትም ሲተው ፍላጎቱና አቅሙ ይጠፋል።
⚠️ ግንኙነትን ለረጅም ጊዜ መተው የሚያስከትላቸው ጉዳቶች፦
ለአምልኮ ወይም ራስን ለመጨቆን በሚል ግንኙነትን ትተው የነበሩ ሰዎች ላይ የሚከተሉት ችግሮች ሲታዩ ተስተውለዋል፦
* የአካል ክፍሎች መዳከም፦ የአካል ክፍሎቹ አቅም ይደክማል፣ የፈሳሽ ማለፊያ ቧንቧዎቹ ይዘጋሉ፣ ብልቱም ይኮማተራል።
*የእንቅስቃሴ መክበድና መቸገር፦ ሰውነታቸው ይቀዘቅዛል (ይዝላል)፣ እንቅስቃሴያቸውም ይቸገራል።
* ያለ በቂ ምክንያት የሚመጣ ድብርት፦ ምንም ግልጽ የሆነ ምክንያት ሳይኖር በጭንቀትና በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ይወድቃሉ።
* የፍላጎትና የምግብ መፈጨት መዳከም፦ የወሲብ ፍላጎታቸውም ሆነ የምግብ መፈጨት (ሀድም) አቅማቸው እጅግ ይቀንሳል።»
📚 ምንጭ፦ ዛዱል ሚዓድ (4/357-358)
ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
📲 [https://t.me/sultan_54]
❤28👍9😱4
*اللهم اجعل لنا في قلوبنا نورًا، وفي صدورنا سكينة، وفي أيامنا بركة، ولا تجعل لنا حاجةً إلا قضيتها، ولا همًّا إلا فرّجته، ولا دعاءً إلا استجبته، يا أكرم الأكرمين.*
صباح الخير
❤8
🖋️ ወሳኝ ማስታወሻ፡
"ወደ አላህ ስትጓዙ እየተንገዳገዳችሁም ቢሆን ሂዱ!"
ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ “
ወደ አላህ (መንገድ) እየተንገዳገዳችሁና እየተሰባበራችሁም ቢሆን ሂዱ፤ ጤናን (ምቹ ሁኔታን) አትጠብቁ፤ ምቹ ሁኔታን መጠበቅ ስንፍና ነውና።

”
ለመሆኑ "ወደ አላህ እያነከሱ (እየተንገዳገዱ) መጓዝ" ማለት ምን ማለት ነው?
* በሱና ሶላቶችህ ላይ፦  (ሱና) ሶላቶችን መስገድ ጀምረህ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ገና የልብ መርጋትና ተመስጦ (ኹሹዕ) አልተሰማህም.. አይዞህ! አታቋርጥ፣ ቀጥል፤ ከአላህም እገዛን ለምን።
* ከቁርኣን ጋር ባለህ ግንኙነት፦ ቁርኣን ማንበብ ጀምረሃል፣ ነገር ግን አንደበትህ ይኮላተፋል ወይም ገና ትርጉሙና መልእክቱ ልብህ ውስጥ አልሰረጸም.. አይዞህ! አታቋርጥ፣ ቀጥል፤ በሚገባ የሚያስተምርህንም ፈልግ፣ ልብህንም እንዲያረሰርሰው ታገል።
* ህይወትህን ለማስተካከል በሚታደርገው ጥረት፦ ህይወትህን በአላህ መንገድ ላይ ለመምራት ወስነሃል፣ ነገር ግን አንዳንዴ ስሜትህ (ነፍስህ) ታሸንፍሃለች.. አይዞህ! አታቋርጥ፣ ቀጥል፤ ወደ አላህ የምታደርገውን ጉዞ አታዘግይ።
💡 ታላላቅ ትምህርቶች፦
* የመታገል (ሙጃሃዳ) ብስራት፦ አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦ “
እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉትን በእርግጥ መንገዳችንን እንመራቸዋለን።”

(አል-ዐንከቡት፡ 69)።
* የኢብኑል ቀይም ምክር፦ "
አንድ ሰው አላህን መታዘዝን (ጧዓን) እስኪለምደውና እስኪወደው ድረስ ይታገላል፤ ከዚያም አላህ ከመኝታውና ከምቾቱ ቀስቅሰው ወደ ጧዓ የሚገፋፉትን መላእክት ያዘጋጅለታል።"

📌 ወደ አላህ ለመመለስ፦ "
ፍጹም" እስክትሆን አትጠብቅ። በድካምህ፣ በመሰባበርህና ባለህ አቅም ወደ እርሱ ተጠጋ፤ እርሱ የተሰበረውን ጠጋኝ፣ ጥቂቱን ተቀብሎ ብዙን የሚመነዳ አዛኝ ጌታ ነውና።
❤19🥰2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢብኑል ቀዪም አል-ጀውዝያ (ረሒመሁላህ) በአድ-ዳእ ወደ-ዳዋእ በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ፣ ብዙ ሰዎች የአላህን እዝነት ብቻ ተገን በማድረግ በወንጀል ላይ የሚዘልቁበትን አደገኛ ሁኔታ በሚከተለው መልኩ ይገልጹታል፦
> "ብዙ አላዋቂዎች በአላህ እዝነት፣ ይቅርታና ቸርነት ላይ ብቻ ተማምነው የአላህን ትዕዛዛትና ክልከላዎች ችላ ይላሉ። አላህ ቅጣቱ ብርቱ መሆኑንና ወንጀለኞችን እንደሚቀጣ፣ ቅጣቱም ከወንጀለኛ ህዝቦች እንደማይመለስ ይዘነጋሉ። በአላህ ይቅርታ ላይ ብቻ ተማምኖ በወንጀል ላይ የሚቀጥል ሰው ልክ እንደ ግትር (አመጸኛ) ነው ተብሎ ይታሰባል።"
* የመዕሩፍ አል-ከርኺ እንዲህ ብለዋል፦"ታዛዥ ላልሆንክለት ጌታ እዝነቱን መመኘት ውርደትና ሞኝነት ነው።"
* ሐሰን አል-በስሪይም እንዲህ ይላሉ፦"
አንዳንድ ሰዎችን 'የአላህ ምህረት ተስፋ' እያታለላቸው ከዱንያ ያለ ተውባ  እስኪወጡ ድረስ ይዘገያሉ። አንዳቸውም፦ 'እኔ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ (ሁስኑ-ዘን) አለኝ' ይላል። ነገር ግን ውሸቱን ነው፤ በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ቢኖረው ኖሮ ስራውን ባሳመረ ነበር።

"
የአላህ መልክተኛ ﷺ በቡኻሪና ሙስሊም ተዘግቦ እንደመጣው እንዲህ ይላሉ፦
> "በቂያማ እለትአ አንድ ሰው ይመጣና ወደ እሳት ይጣላል፤ የሆዱ እቃውም( አንጀቱም) ወደ ውጭ ይዘረገፋል። ልክ አህያ በወፍጮ ዙሪያ እንደሚዞረው እርሱም በአንጀቱ ዙሪያ ይዞራል። የእሳት ሰዎችም በእርሱ ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ ይሉታል፦ 'አንተ እገሌ ሆይ! ምን ሆነህ ነው? አንተ እኮ በመልካም ታዘንና ከመጥፎ ትከለክለን አልነበረም?' እርሱም፦ 'አዎ! በመልካም አዛችሁ ነበር ነገር ግን እኔ ራሴ አልሰራውም ነበር፤ ከመጥፎም እከለክላችሁ ነበር ነገር ግን እኔ ራሴ እሰራው ነበር' ይላል።"
❤15👍6🥰2
እያንዳንዱ ሰው ታሞ እስኪተኛ ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግሮች እንዳሉበት ያስባል፤ ልክ በታመመ ጊዜ ግን ጤና ከሁሉም በላይ አስፈላጊ፣ ውድ እና ታላቅ ጸጋ መሆኑን ይረዳል..
ከዚያ በኋላ ጤና ከታላላቅ ጸጋዎች መሆኑን ትረዳለህ፤
በዓፊያ ማልዳህ፣ በዓፊያ መጓዝህ እና ቀኑን ሙሉ በዓፊያ ማሳለፍህ (ትልቅ ስጦታ ነው)።
ከነቢዩ ﷺ ዱዓዎች መካከልም፦
اللَّهُمَّ إِني أسألك العافية في الدنيا والآخرة،اللهم إني أسألك العفو والعافية في ديني ودنياي وأهلي ومالي).*~*.. ✿ً⃟🌷ً⃟✿..
"አላህ ሆይ! በዱንያም በአኺራም ዓፊያን (ጤናንና ሰላምን) እጠይቅሃለሁ። አላህ ሆይ! በዲኔ፣ በዱንያዬ፣ በቤተሰቤና በገንዘቤ ላይ ይቅርታህንና ዓፊያን እጠይቅሃለሁ" የሚለው ይገኝበታል።
📌 ዛሬ በጤና ተነስተህ መጓዝ መቻልህ ብቻውን ትልቅ "ሀብት" መሆኑን አትዘንጋ። አልሐምዱሊላህ!
👍23❤7👌1
📌 ዛሬ በጤና ተነስተህ መጓዝ መቻልህ ብቻውን ትልቅ "ሀብት" መሆኑን አትዘንጋ።
ታዲያ አልሐምዱሊላህ! አትልም?
Anonymous Poll
96%
አልሐምዱሊላህ
90%
አልሐምዱሊላህ
85%
አልሐምዱሊላህ
👍25❤13
የዒዳችን መጠናቀቂያ ላይ … ሁልጊዜም ይህንን እናስታውስ..

​እውነተኛው በዓላችን (ዒዳችን) በጀነት ውስጥ ይሆናል፤ አላህን በማየትና ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን ጋር በመቀማመጥ የምናሳልፈው። ያኔ ፊቶች በደስታ ያበራሉ፣ ልብሶችም ከሐርና ከዲባጅ የተሰሩ ይሆናሉ። እዚያ አድካሚ ስራ የለም፣ የሚታመምም ሆነ የሚያረጅ አካል የለም፣ የሚያለቅስ ዓይንም ሆነ የመለያየት ስቃይ የለም... አላህ እኔንም እናንተንም፣ እንዲሁም የምንወዳቸውን ሁሉ የጀነት ሰዎች ያድርገን።
👌18❤14👍4
የዘዋጅ (የትዳር )ጥቅሞች
ኢማም ኢብኑ ቁዳማ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ትዳር የተወደደ (ሙስተሐብ) ተግባር ሲሆን ብዙ ትርፎችም አሉት። ከጥቅሞቹም መካከል፦"
* ልጅ ማግኘት፦ የትዳር ዋነኛው ዓላማ የሰው ልጅ ዝርያ እንዲቀጥል ማድረግ ነው፤ በዚህም ውስጥ፦
* የሰውን ልጅ ዘር በማስቀጠል፤
* የነቢዩን ﷺ ፍላጎት መፈጸም፤ እርሳቸው ነገ በመልካም ተከታዮቻቸው ብዛት ይኩራራሉና።
*
በመልካም ልጅ ዱዓእ በረካን መፈለግ እንዲሁም ህፃን ልጅ ቢሞት (ለወላጆቹ) አማላጅ መሆኑን መከጀል።

* ከሸይጣን መጠበቂያ፦ የፍላጎትን (የሸህዋን) አደጋ በመከላከል ራስን ከሸይጣን ጥቃት መጠበቅ።
* ለነፍስ እረፍት መስጠት፦
ከትዳር አጋር ጋር በመቀራረብና በመጨዋወት ለነፍስ መጽናኛንና ደስታን ማግኘት።

* ልብን ከቤት አስተዳደር ስራዎች ነፃ ማድረግ፦ እንደ ምግብ ማብሰል፣ ቤት መጥረግ፣ ዕቃ ማጠብና የኑሮ መሰናዶዎችን በማስተካከል ሴት ልጅ ስለምታግዝ
ወንድ ልጅ ጊዜውን ለዕውቀትና ለዒባዳ እንዲያውል ታግዘዋለች። መልካም ሴት በዚህ መልኩ ለዲን ትልቅ ረዳት ናት

፤ እነዚህ የቤት ውስጥ ስራዎች ባይኖሩ ኖሮ ልብ በጭንቀት ይወጠር ነበርና።
* ነፍስን መገላገልና ማለማመድ፦ ለቤተሰብ ሐላፊነትን በመውሰድ፣ በባህሪያቸው ላይ በመታገስ፣ ከእነሱ የሚመጣን ችግር በመቻል፣ እነሱን ወደ ቀጥተኛው የዲን መንገድ በመምራት፣
ለእነሱ ሲባል ሐላል ሲሳይን ለመፈለግ በመድከም እና ልጆችን በመንከባከብ ነፍስን ማለማመድ። እነዚህ ሁሉ ታላቅ ምንዳ ያላቸው ስራዎች ናቸው።
ሐላፊነትን መሸከምና ቤተሰብን ማስተዳደር በአላህ መንገድ ላይ እንደ መታገል (ጂሃድ) ይቆጠራል።
* ከነቢዩ ﷺ ሐዲስ፦ በኢማም ሙስሊም ዘገባ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
> "አንድ ዲናር በአላህ መንገድ (ለጂሃድ) ብታወጣ፣ አንድ ዲናር ባሪያ ነፃ ለማውጣት ብታወጣ፣ አንድ ዲናር ለምስኪን ሰደቃ ብትሰጥ እና አንድ ዲናር በቤተሰቦችህ ላይ ብታወጣ፤ ከነዚህ ሁሉ ትልቁን ምንዳ የሚያስገኘው በቤተሰቦችህ ላይ ያወጣኸው ዲናር ነው።"
>
ምንጭ፦ ሙኽተሰር ሚንሃጅ አል-ቃሲዲን (ገጽ 161 - 162)

#ትዳርን_ማበረታታት
መልካም አዳር!
❤13👍1