## ህይወትዎን በአምስት ነገሮች ያድሱ
### 1. የዕለት ተዕለት ትምህርት (ራስን ማሳደግ)
በቀን ውስጥ 30 ደቂቃ ብቻ በቂ ነው። መጽሐፍ ያንብቡ፣ ጠቃሚ የፖድካስት ፕሮግራሞችን ያዳምጡ ወይም በማንኛውም መንገድ ራስዎን ያሻሽሉ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአስተሳሰብዎ እና በራስ መተማመንዎ ላይ ትልቅ ለውጥ ያስተውላሉ።
### 2. ቀንን ማደራጀት
በየቀኑ ጠዋት ግልጽ እና ሊተገበሩ የሚችሉ 3 ዋና ዋና ተግባራትን በመለየት ይጀምሩ። ይህ ልማድ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ብዙ ነገሮችን እንዲያከናውኑ ያደርግዎታል።
### 3. አካባቢን ማጣራት (ማፅዳት)
ጉልበትዎን ከሚመጥጡ ወይም አሉታዊ ጫና ከሚፈጥሩብዎት ሰዎች ሁሉ ይራቁ። ይህንን ሲያደርጉ መረጋጋትዎ እና ስነ-ልቦናዊ ሰላምዎ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
### 4. ለራስ እንክብካቤ መስጠት
በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እና እውነተኛ የእረፍት ጊዜያትን መውሰድ ያስፈልጋል። እነዚህ ቀላል የሚመስሉ ነገሮች የተለየ የስነ-ልቦና እና የአካል ብቃት ጥንካሬ ይፈጥሩልዎታል።
### 5. አዳዲስ ነገሮችን መሞከር
በየወሩ አዲስ ነገር ይሞክሩ፤ አዲስ ቋንቋ፣ ክህሎት ወይም የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ (ሆቢ) ሊሆን ይችላል። እነዚህን ልማዶች ጠብቀው ከቀጠሉ፣ ከሶስት ወር በኋላ ሙሉ በሙሉ አዲስ ሰው መሆንዎን ያገኟታል።

👍13❤9
الشيخ سعد الغامدي تكبيرات عيد الأضحى
<unknown>
ተክቢራ
በቃሪእ ሰዕድ አልጋሚዲይ ድምፅ
احيوا سنة التكبيــــــــــر
وذكــــــــــروا بها
الله اكبر ، الله أكبر ، الله أكبر
🍃 لاإله إلا الله 🍃
الله أكبـــــــر ، الله أكبـــــــر
🍃 ولله الحمد 🍃
🌸🍃
https://t.me/sultan_54
በቃሪእ ሰዕድ አልጋሚዲይ ድምፅ
احيوا سنة التكبيــــــــــر
وذكــــــــــروا بها
الله اكبر ، الله أكبر ، الله أكبر
🍃 لاإله إلا الله 🍃
الله أكبـــــــر ، الله أكبـــــــر
🍃 ولله الحمد 🍃
🌸🍃
https://t.me/sultan_54
❤4👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሕዩ ወንሽሩ ሱነተ-ትተክቢር**
> *"የተክቢራን ሱና ሕያው አድርጉ፤ አሰራጩም!"*
> *"እኛ አሁን እንግዲህ በዱንያ ላይ ካሉት ታላላቅና አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ከሆኑት ቀናት ውስጥ ነው ያለነው።"*
>
አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ

👍9❤4
### በጊዜ ያልተገደበ (ሙጥለቅ) እና በጊዜ የተገደበ (ሙቀየድ) ተክቢራ
1 አት-ተክቢር አል-ሙጥለቅ (በጊዜ ያልተገደበ)፦ በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ የሚባል፣ በአንድ የተወሰነ ወቅት ወይም ከፈርድ ሶላት ማግስት ብቻ የማይገደብ ተክቢራ ነው።
* አት-ተክቢር አል-ሙቀየድ (በጊዜ የተገደበ)፦ ከአምስቱ ግዴታ (ፈርድ) ሶላቶች (ከማሰላመት በኋላ) ብቻ ተያይዞ የሚባል ተክቢራ ነው።
2. የሚጀምሩበትና የሚያበቁበት ጊዜ፦
* በጊዜ ያልተገደበው (ሙጥለቅ) ተክቢራ፦ በሁለቱ የዒድ ሌሊቶች (የረመዳን እና የሐጅ ዒድ ዋዜማ ላይ) ይባላል። እንዲሁም የዙልሒጃህ አስር ቀናት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የመጨረሻው የተሽሪቅ ቀን ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ በማንኛውም ሰዓት ይባላል።
* በጊዜ የተገደባው (ሙቀየድ) ተክቢራ፦ * ሐጅ ላላደረገ ሰው ከአረፋ ቀን የፈጅር (ሱብሒ) ሶላት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተሽሪቅ ቀን የአስር ሶላት ማግስት ድረስ ይባላል።
* ሐጅ ለሚያደርግ ሰው (ሑጃጅ)፦ በዒድ ቀን (የእርድ ቀን) ከዙህር ሶላት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተሽሪቅ ቀን የአስር ሶላት ማግስት ድረስ ይባላል።
3. ሁለቱ ተክቢራዎች የሚገናኙባቸው ቀናት፦
ሐጅ ላላደረገ ሰው ሁለቱ የተክቢራ ዓይነቶች (ሙጥለቅ እና ሙቀየድ) ከአረፋ ቀን ሱብሒ ሶላት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተሽሪቅ ቀን(ዙልሂጃ 13) ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይገናኛሉ (በአንድ ላይ ይከሰታሉ)። ለሑጃጅ (ሐጅ ለሚያደርግ ሰው) ደግሞ ከእርድ ቀን (የዒድ ቀን) ዙህር ሶላት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የተሽሪቅ ቀን ፀሐይ መግቢያ ድረስ ይገናኛሉ።
4. የተክቢራው አባባል (ዘይቤ፦
የተክቢራው አገላለጽ፦
> *«አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ»*
>
የፈለገ ሰው ተክቢራውን ሶስት ጊዜ በማድረግ (በመደጋገም) እንዲህ ሊል ይችላል፦
> *«አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ»*
>
5. የተክቢራ ታላቅነትና የማስታወሻ ጥሪ፦
በጊዜ ያልተገደበው ተክቢራ የዙልሒጃህ አስር ቀናት ሲገቡ የሚጀምር ሲሆን፣ ሰዎች በሚሰበሰቡባቸው ቦታዎች ላይ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማለቱ ይበልጥ የተወደደ ነው። ይህንን ሸሪዓዊ ሥነ-ሥርዓት (ሸዒራህ) ግልጽ ለማድረግ ከሚመቹ ወቅቶች መካከል በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ በአዛንና በኢቃማ መካከል ያለው ጊዜ አንዱ ነው።
አረቦች «አላሁ አክበር» የሚለው ቃል አላህን ለማላቅና ለማክበር ከተነገሩ ንግግሮች ሁሉ እጅግ ጥልቅና ላቅ ያለ መግለጫ እንደሆነ ይናገራሉ። ትርጉሙም «አላህ ከማንኛውም ነገር በላይ ታላቅ ነው፤ አላህ በልቦና ውስጥ ከሚመላለስና ከሚታሰብ ነገር ሁሉ በላይ ታላቅ ነው» ማለት ነው።
በመጨረሻም፣ እያንዳንዱ ሙስሊም ይህንን ታላቅ ሱና ሕያው ማድርግና ይህንን ሸሪዓዊ መለያ (ሸዓኢር አድ–ዲን)በየቦታው ይፋ ማድረግ ተገቢ ነው።
(ከሸይኽ ሰዐድ ኸሥላን ትምህርት የተወሰደ)

❤6👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአላህ እምላለሁ! እንደነዚህ ያሉ (የዙልሒጃህ አስር) ቀናት በፍጹም አይገኙም። ከበጎ ሥራዎች ማከናወን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ! ከበጎ ሥራዎች ማከናወን የምትችሉትን ሁሉ ፈጽሙ!
ዚክሮችን፣ ዱዓዎችን፣ ቁርኣን መቅራትን፣ ማስተንተንን፣ ማሰላሰልን፣ ወላጆችን መንከባከብን (ቢሪል ዋሊደይን)፣ ዝምድናን መቀጠልን፣ ለጎረቤት መልካም መዋልን፣ እንዲሁም የተለያዩ የሰደቃ ዓይነቶችን ሁሉ አዘውትሩ።
ማከናወን የምትችሉትን ማንኛውንም በጎ ነገር ሁሉ አድርጉ፤ ለዲንና ለዕውቀት የሚሆኑ መልዕክቶችን መጻፍና ማሰራጨት፣ ሰዎችን ወደ በጎ ነገር ማነቃቃትን ጨምሮ። የአላህ ባሪያ ሆይ! ከበጎ ሥራዎች አንዳች ነገር እንኳ እንዳታስቀር! ይልቁንም ያለህን አቅምና ጉልበት ሁሉ አስተባብረህ ተጠቀምበት።
የሌሊት ሶላትን (ቂያሙል ለይል)፣ የዱሐ ሶላትን፣ የተለያዩ የነዋፊል (የትርፍ) ሶላቶችን ስገድ። ወደ መስጂዶች ቀድሞ መግባትን፣ ከአንድ ሶላት በኋላ ሌላኛውን ሶላት በጉጉት መጠባበቅን አዘውትሩ። በነዚህ አስር ቀናት ውስጥ ቁርኣንን አክትመሃልን? ዘጠኙን ቀናት ወይም ከፊሉን ጾመሃልን?
ማከናወን የምትችለውን መልካም ነገር ሁሉ አድርግ! በአላህ እምላለሁ፣ እንደነዚህ ያሉ የተከበሩ ቀናት በፍጹም አይገኙም! በአላህ እምላለሁ፣ እንደነዚህ ያሉ ቀናት በፍጹም አይገኙም!"
ሸይኽ ሷሊሕ አል ሙነጂድ
❤11👌3👍1
📌ዙልሒጃ ቀን 02፦
> የአላህ ቅን ባሪያዎች አላህ ፊት ያላቸው መተናነስ ድንቅ ነው። ታላቁ ዓሊም ሙጠሪፍ ኢብኑ ዐብዲላህ በዐረፋ መድረክ ላይ ቆመው፦ "አምላኬ ሆይ! በእኔ ወንጀል ምክንያት የዚህን ሁሉ ሁጃጅ ዱዓእ እንዳትመልስባቸው!" እያሉ ያለቅሱ ነበር። ራሳችንን ዝቅ አድርገን ምሕረትን የምንለምንበት ወቅት ይሁንልን። 🌙 #ዙልሒጃ #ኢስላማዊ_ማስታወሻ

❤14👍1
«ولا نُزِيلُ صِفَةً مِنْ صِفَاتِهِ لِشَنَاعَةٍ شُنِّعَتْ»
> "ተቺዎች ስላሸማቀቁበት ወይም ስላስፈራሩበት ብቻ ከአላህ ባህሪያት መካከል አንዳቸውንም ባህሪ ውድቅ አናደርግም (አንሰርዝም)።"
(ኢማሙ አሕመድ)
>
ኢማም አሕመድ ይህንን የተናገሩት የአላህን ስሞችና ባህሪያት (አስማእ ወስ-ሲፋት) በሚመለከት የጥመት አንጃዎች (እንደ ጃሕሚያህና ሙዕተዚላህ ያሉ) የሱና ሰዎችን ለማጥቃትና ለማሸማቀቅ ይጠቀሙበት የነበረውን ስልት ለመመከት ነው።
* የተቺዎች ስልት (ሽናዓህ)፦ እነዚህ ቡድኖች አህሉስ ሱናዎች በቁርኣንና በሐዲስ የመጡትን የአላህ ባህሪያት (ለምሳሌ፦ ማየቱን፣ መስማቱን፣ ከዐርሽ በላይ መሆኑን፣ መውረዱን፣ ፊቱን...) እንዳለ ሲያጸድቁ፣ እነርሱ «ይህ እኮ አላህን ከፍጡር ጋር ማመሳሰል (ተሽቢህ) "ተጅሲም" ነው» እያሉ በተራው ሕዝብ ዘንድ ያስፈራሩበት ነበር።
* የኢማም አሕመድ ጽናት፦ ኢማሙ ምን አሉ። አላህ ለራሱ ያጸደቀውን ወይም መልእክተኛው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያጸደቁለትን ባህሪ፣ ሰዎች ስም ስላወጡለት ወይም ስላስፈራሩን ብቻ «ሰዎች እንዳይገምቱን» ብለን አንክድም፣ አንደብቅም፣ አንሰርዝምም።
ባጭሩ፦ በዲንና በአቂዳ ጉዳይ ላይ የሰዎች ትችትና ማጠልሸት ሳይሆን መከተል ያለብን በቁርኣንና በሐዲስ የመጣውን ቀጥተኛውን መረጃ ብቻ ነው።

👍12❤4
📌 ዙልሒጃ ቀን 03፦
> "ጌታዬ ሆይ! አረጀሁ እኮ፤ ስለዚህ ከእሳት ነፃ አውጣኝ!" — አቡ ዑበይዳህ አል-ኸዋስ በዐረፋ ቀን ላይ ዕድሜያቸው ገፍቶ ፂማቸው በፈካ ጊዜ ፂማቸውን ይዘው አላህ ፊት ይንበረከኩ ነበር። ባሪያዎች ሲያረጁ ጌቶቻቸው(አሳዳሪዎቻቸው) በነፃ እንደሚለቋቸው ሁሉ፣ አላህም በእርጅናቸው ከእሳት እንዲጠብቃቸው ይማጸኑ ነበር። 🕊️ #የአላህ_እዝነት #ዙልሒጃ

👍10❤8
> "የአእምሮን ጥንካሬ (ማሰብን) መጀመሪያ የሚያዳክመው ነገር... እነዚህ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የምታዩዋቸው አጫጭር ቪዲዮዎች (Shorts/Reels) ናቸው። እነዚህ በፍጥነት የሚቀያየሩት አጫጭር ቪዲዮዎች አእምሮን ይበታትኑታል። አእምሮ ከ5 ደቂቃ በላይ ዘልቆ በጥልቀት እንዳያስብ ያደርጉታል። በአንድ ነገር ላይ መቆየትና ማተኮር አይችልም።
> ንቃትና ማስተዋል መሰልቸት(ትዕግስት ማጣት)፣ ከአእምሮ መዳከም እና ከትዕግስት ማነስ ጋር አብረው ሊሄዱ አይችሉም፤ በፍጹም አይቻልም!
> ንቁና አስተዋይ ለመሆን ከነዚህ ነገሮች መራቅ አለብህ። ከነሱ የምትወስደው ለአስፈላጊ ጉዳይ ያህል ብቻ መሆን አለበት። ነገር ግን በእነሱ ሱሰኛ መሆን ንቃትንና ማስተዋልን ያርቃል።
> (በዚህ ሱስ ከተጠመድክ) ዝም ብለህ የምትቀበል( ተመልካች)፣ ጥልቀት የሌለው፣ በስሜት ብቻ የምትነዳ፣ የማታስተውልና የማታሰላስል ሰው ትሆናለህ።"
> — አሽ–ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ኣሊ ሸይኽ

❤28👍17
በቃዲ ዐብዱልጀባር አል-ሙዕተዚሊ እና በአቡ ኢስሃቅ አል-ኢስፈራዪኒ መካከል በቀደር ዙሪያ የተደረገ ክርክር
የሙዕተዚላህ መሪዎች አንዱ የሆነው ቃዲ ዐብዱልጀባር አል-ሀመዳኒ፣ ሳሒብ ኢብኑ ዐባድ ዘንድ ገባ። እዚያም የአህሉ-ሱናህ መሪ ከሆኑትና "አል-ኡስታዝ" ተብለው ከሚጠሩት አቡ ኢስሃቅ አል-ኢስፈራዪኒ ጋር ተገናኙ። ቃዲ ዐብዱልጀባር ኡስታዝ አል-ኢስፈራዪኒን ባየው ጊዜ (የራሱን የሙዕተዚላህ እምነት ለማንጸባረቅ ፈልጎ) እንዲህ አለ፦
(ማለትም፦ አላህ መጥፎ ነገሮች እንዲከሰቱ ፈቃድ ከመስጠት የጠራ ነው፤ መጥፎ ነገር በአላህ ፍቃድና ውሳኔ አይከሰትም ማለቱ ነበር።)
ኡስታዝ አል-ኢስፈራዪኒም ወዲያውኑ (የአህሉ-ሱናህን እምነት በማረጋገጥ) እንዲህ ሲል መለሰለት፦
ቃዲ ዐብዱልጀባርም ጠየቀ፦ "ለመሆኑ ጌታችን ሊያምጹት (ሊያምፁበት) ይሻልን?"
ኡስታዝ አል-ኢስፈራዪኒም መለሰ፦ "ለመሆኑ ጌታችን በግዴታና በኃይል (ያለ እርሱ ፍቃድ) ይታመጻልን?" (ማለትም፦ በፈጠረው ዓለም ላይ በእርሱ ቁጥጥርና ፍቃድ ስር ያልሆነ ነገር በግዴታ ይከሰታልን?)
ቃዲ ዐብዱልጀባርም (ሊሞግተው በመፈለግ) እንዲህ አለ፦ "እስኪ ንገረኝ! ቅኑን መንገድ (ሂዳያን) ቢከለክለኝ፣ በጥፋትና በክህደት ላይ ከወሰነብኝ፤ መልካም አደረገልኝ ወይስ በደለኝ?"
አል-ኢስፈራዪኒም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "የከለከለህ ያንተ የሆነውን መብትህን ከሆነማ በድሎሃል። ነገር ግን የከለከለህ የእርሱ የሆነውን (ችሮታውን) ከሆነ፣ እርሱ እዝነቱን ለሻው ሰው ይመርጣል።"
በዚህ ጊዜ ቃዲ አብዱልጀባር የሚመልሰው አጥቶ አፉ ተለጎመ (ተረታ)። ይሁን እንጂ እስከወዲያኛው በሙዕተዚላህ እምነቱ ላይ ጸንቶ ቀጠለ፣ መልስም መስጠት አልቻለም።

"ከመጥፎና ጸያፍ ነገር ሁሉ የጠራው (አላህ) ጥራት ይገባው።"
(ማለትም፦ አላህ መጥፎ ነገሮች እንዲከሰቱ ፈቃድ ከመስጠት የጠራ ነው፤ መጥፎ ነገር በአላህ ፍቃድና ውሳኔ አይከሰትም ማለቱ ነበር።)
ኡስታዝ አል-ኢስፈራዪኒም ወዲያውኑ (የአህሉ-ሱናህን እምነት በማረጋገጥ) እንዲህ ሲል መለሰለት፦
"በግዛቱ ውስጥ እርሱ ከሻው (ከፈቀደው) ውጭ ምንም ነገር የማይከሰተው አምላክ ጥራት ይገባው።"
ቃዲ ዐብዱልጀባርም ጠየቀ፦ "ለመሆኑ ጌታችን ሊያምጹት (ሊያምፁበት) ይሻልን?"
ኡስታዝ አል-ኢስፈራዪኒም መለሰ፦ "ለመሆኑ ጌታችን በግዴታና በኃይል (ያለ እርሱ ፍቃድ) ይታመጻልን?" (ማለትም፦ በፈጠረው ዓለም ላይ በእርሱ ቁጥጥርና ፍቃድ ስር ያልሆነ ነገር በግዴታ ይከሰታልን?)
ቃዲ ዐብዱልጀባርም (ሊሞግተው በመፈለግ) እንዲህ አለ፦ "እስኪ ንገረኝ! ቅኑን መንገድ (ሂዳያን) ቢከለክለኝ፣ በጥፋትና በክህደት ላይ ከወሰነብኝ፤ መልካም አደረገልኝ ወይስ በደለኝ?"
አል-ኢስፈራዪኒም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "የከለከለህ ያንተ የሆነውን መብትህን ከሆነማ በድሎሃል። ነገር ግን የከለከለህ የእርሱ የሆነውን (ችሮታውን) ከሆነ፣ እርሱ እዝነቱን ለሻው ሰው ይመርጣል።"
በዚህ ጊዜ ቃዲ አብዱልጀባር የሚመልሰው አጥቶ አፉ ተለጎመ (ተረታ)። ይሁን እንጂ እስከወዲያኛው በሙዕተዚላህ እምነቱ ላይ ጸንቶ ቀጠለ፣ መልስም መስጠት አልቻለም።
❤10
"እናንተ ሰዎች ሆይ! በቁርአን በወረደበትና በዓረብኛ ቋንቋ የታወቀውን ትርጉም—ይኸውም 'ላይ መሆን እና ከፍ ማለት' የሚለውን ትተው—አላህ ከዙፋኑ (ከዓርሹ) በላይ ሆኗል (*ኢስተዋ*) ማለትን ለምን ትቃወማላችሁ?
እነሱም፦ *'ምክንያቱም ከፍ ማለት (ኢስቲዋእ) የፍጡራን ባህሪ ነው፤ ከፍ የሚልን ማንኛውንም አካል ፍጡር መሆኑን እንጂ ሌላ አናውቅም'* አሉ።
እሺ ችግር የለውም፤ ታዲያ ፦
الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى [طه:5]
የሚለውን የቁርአን አንቀጽ ምን ልናደርገው ነው?
'በቁጥጥር ስር ማዋል ወይም መቆጣጠር (*ኢስቲላእ*) በሚለው ትርጉም እንፈታዋለን (እንተረጉመዋለን)' አሉ።
እኛም እንላቸዋለን፦ በእናንተ ህግና መርህ መሰረት፣ እኮ ማንኛውንም የሚቆጣጠርና በቁጥጥር ስር የሚያውልን አካል ፍጡር መሆኑን እንጂ ሌላ አናውቅም።
ታዲያ እናንተ አላህን ከፍጡር ጋር ማመሳሰል (*ተሽቢህ*) ውስጥ አልገባችሁምን? በዚያ በተቀጠፈው የቅኔ ስንኝ ውስጥ ገጣሚው ያላችሁን አታወሱም?
قَدِ اسْتَوَى بِشْرٌ عَلَى العِرَاقِ ... مِنْ غَيْرِ سَيْفٍ وَدَمٍ مُهْرَاقِ
*'ቢሽር (የተባለው ሰው) ያለምንም ሰይፍና ደም መፋሰስ በኢራቅ ላይ የበላይነቱን አረጋገጠ (ተቆጣጠረ)'* የሚለውን። በእነሱ ዘንድ እዚህ ጋ 'ኢስተዋ' ማለት 'ኢስተውላ' (በስልጣኑ ተቆጣጠረ) ማለት ነው።
እንግዲህ 'ቢሽር' የተባለው ፍጡር ተቆጣጠረ ከተባለ፣ እናንተም አላህን 'ተቆጣጠረ' ስትሉ ፍጡርን አላህ ጋር አመሳሰላችሁ ማለት ነው። ስለዚህ እናንተ ራሳችሁ አላህን ከፍጡር ጋር ወደ ማመሳሰል ተግባር ውስጥ ወድቃችኋል።
እነሱም፦ *'አይ ወንድሜ ሆይ! አንተ በስህተት ነው የተረዳኸን፤ እኛ ማለቱ የፈለግነው ከአላህ ታላቅነት ጋር የሚመጥን ቁጥጥር (ኢስቲላእ) ነው እንጂ እንደ ፍጡር ቁጥጥር አይደለም'* ካሉ፤
እኛም፦ 'ለአላህ ጥራት ይገባውና!)' እንላለን።
እኛስ የምንለው ምንድን ነው? ከአላህ ታላቅነትና ልቅና ጋር የሚመጥን ከፍ ማለት (*ኢስቲዋእ*) ነው እንላለን። በእኛ አባባል ላይ የምትሰጡትን ማንኛውንም ምላሽ፣ እኛም በእናንተ ቃል ላይ መልሰን እንመጣባችኋለን።"
ሸይኽ ሷሊሕ አስ–ሲንዲይ

👍13❤7
🔹 የዘመኑን የክህደት (ኢልሃድ) ፈተና መጋፈጥ
ይህ የአላህ መኖር እውነት እጅግ ግልፅ ቢሆንም፣ በዘመናችን የወጣቱን ትውልድ እምነት (አቂዳ) እና ስነ-ምግባር ለመበከል የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ጠማማዎች አሉ።
ይህንን የሃሳብ ወረራና የኢልሃድ ፈተና መጋፈጥ፣ የወጣቶችን እምነት መጠበቅ በአላህ መንገድ ላይ ከሚደረጉ ትላልቅ ጂሃዶች (ትግሎች) አንዱ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ትግል ዲናችንንም ሆነ ዱንያችንን ከጥፋት የመከላከል ስራ ነው።
🔗 የኪታቡን ሊንክ ለመጫን፦
كتاب الإلحاد وسائله و خطره و سبل مواجهته
https://t.me/amaliketeladab/8319

❤10👍2
📌ዙልሒጃ ቀን 05፦
> "እነዚህ ባሪያዎቼ አቧራ ለብሰው፣ ፀሐይ እየመታቸው ወደእኔ መጡ።" ጌታ ሆይ! ዛሬ ያንተን ውዴታ፣ ችሮታና እዝነት እንጂ ሌላ ምንም አልፈለጉም። ዛሬ በአንድ የውዴታ እይታ እንድትመለከታቸውና ዳግመኛ የማትቆጣበትን ውዴታ እንድትለግሳቸው ብቻ ነው የፈለጉት። 🤲❤️ #የዙልሒጃ_አስር_ቀናት #ዱዓእ

❤7
قال ابن الجوزي رحمه الله :
الليالي والأيام الفاضلة لا يصلح أن يغفل عنها، لأنه إذا غفل التاجر عن موسم الربح فمتى يربح؟!"
(منهاج القاصدين ١/٣٤٣)

ኢብኑል ጀውዚ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
" ታላቅ ደረጃ ያላቸው (ቅዱሳን) ሌሊቶችና ቀናትን በቸልተኝነት ማሳለፍ በፍጹም አይገባም። ምክንያቱም አንድ ነጋዴ የትርፍ ወቅቱን በቸልተኝነት ካሳለፈ፣ ታዲያ መቼ ሊያተርፍ ነው?!"
(ሚንሃጁል ቃሲዲን፣ 1/343)
❤4👍3
## የዒልም መብት ከዓሊም መብት ይቀድማል!
* **ከአላህ ዘንድ የወረደውን መከተልና ከእሱ ውጭ ያሉትን አለመከተል ግዴታ ነው።
** ማንኛውም ዓሊም ለእኛ ተወዳጅ ቢሆንም፣ እውነት ግን ከእሱ የበለጠ ለእኛ የተወደደች መሆን አለባት።
*የአንድ ዓሊም ትልቅ ደረጃና ክብር እሱን ለማመካኛነትና ስህተቱን ለማረም የሚጠቅም እንጂ፣ የሰራውን ስህተት ትክክል ነው ለማለት ማስረጃ ሊሆን አይችልም።
እውነት ከተናጋሪው ማንነት ሳይሆን ከራሱ ከንግግሩ ተነስተን የምንቀበለው ነው፤ ውሸትም (ባጢል) በተመሳሳይ መልኩ ተናጋሪው ማንም ይሁን ማን ውድቅ የሚደረግ ነው። እውነቱን የተናገረው ወይም ውሸቱን ያወራው ሰው ያለው ማዕረግ የእውነትን ወይም የውሸትን ምንነት አይቀይረውም።

❤11👍2
## የኢማም አል-ሙዘኒ እና የኢማም አሽ-ሻፊዒ ውይይት
ኢማም አል-ሙዘኒ (አላህ ይዘንላቸውና) ሸይኻቸው የሆኑትን ኢማም አሽ-ሻፊዒን የጠየቁት ጥያቄ ኢማም አዝ-ዘሃቢ "ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ" በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ ዘግበውታል።
ታሪኩም እንደሚከተለው ነው፦ በኢማም አል-ሙዘኒ ልብ ውስጥ ከተውሒድ (አስማኡ ወሲፋት) ጉዳዮች መካከል በአንዱ ላይ ጥርጣሬ ወይም አሻሚ ነገር ተፈጠረባቸው።
ዋናው ፍሬ ነገር ግን፤ አል-ሙዘኒ ወደ ኢማም አሽ-ሻፊዒ መጥተው ስለዚህ ጉዳይ ጠየቋቸው። ኢማም አሽ-ሻፊዒም (አላህ ይዘንላቸውና) ካሏቸው ነገሮች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል፦
> ኢማም አሽ-ሻፊዒ፦ "በሰማይ ላይ ስንት ከዋክብት እንዳሉ ታውቃለህ?"
> አል-ሙዘኒ፦ "አላውቅም" (አል-ሙዘኒ ታሪኩን ሲያወራ እንዲህ ነው ያለው)።
> ኢማም አሽ-ሻፊዒይ፦ "መልካም! ከእነሱ ውስጥ ስለ አንዱ ኮከብ፤ የወጣበትን አቅጣጫ፣ የሚጠልቅበትን ቦታ እና ከምን እንደተፈጠረ ታውቃለህ?"
> አል-ሙዘኒ፦ "አላውቅም" አልኳቸው። ይላሉ
> ኢማም አሽ-ሻፊዒ፦ "እንግዲህ በአይንህ የምታየውንና ከፍጡራን ወገን የሆነን ነገር እንኳን ምንነቱንና እንዴትነቱን የማታውቅ ከሆነ፤ እንዴት ብለህ ነው ስለ ፈጣሪህ እውቀት (ስለ ባህሪያቱ እንዴትነት) ልትናገር የምትደፍረው?!"
> ሲየር አዕላም አንኑበላእ
### ዋናው መልእክት💡
በአይንህ የምታየውን፣ ፈጽሞ የማትስተውንና የምታውቀውን ፍጡር እንኳን እንዴትነቱን(ከይፊያውን) የማታውቅ ሆነህ ሳለ፤ ታዲያ አንድ ሰው ከዚህ በኋላ እንዴት ደፍሮ ስለ ፈጣሪው (የላቀና የከበረው አላህ) ማንነትና ባህሪያት 'እንዴትነት' (ከይፊያህ) ሊናገር ይችላል?!
🔴 ይህ ዓይነቱ አካሄድ (ስለ አላህ ባህሪያት እንዴትነት በጥልቀት መመርመር) ፍጹም አስተማማኝና ሰላማዊ ያልሆነ መንገድ እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

❤5