በኢስላም ታሪክ ውስጥ ካሉ ትልልቅ **"የፈላስፎች እና የከላም ምሁራን የቁጭት እምነት ምስክርነቶች"
(اعترافات أهل الكلام والفلسفة)
የታላቁ የከላም (የነገረ-መለኮት) ምሁር እና ተፍሲር አዋቂ የፋኽሩዲን አር-ራዚ (እ.ኤ.አ በ1210 የሞቱት)
እንዲህ ይላሉ፦
> "የከላም (የአመክንዮ) መንገዶችን እና የፍልስፍና ስልቶችን በሙሉ በጥልቀት መረመርኩ፤ ነገር ግን የታመመን ልብ ሲፈውሱም ሆነ የተጠማውን ቀልብ ሲያረኩ አላየኋቸውም። ከሁሉም ይበልጥ ወደ እውነት ቀራቢው መንገድ የቁርአን መንገድ ሆኖ አገኘሁት!"
>
### የዚህ ምስክርነት (اعتراف) ትርጉም እና በጀርባው ያለው ታሪክ
ፋኽሩዲን አር-ራዚ እድሜያቸውን በሙሉ በፍልስፍና፣ በአመክንያታዊ ክርክር (ከላም) እና በግሪክ አመክንዮ ውስጥ ካሳለፉ በኋላ፣ በህይወታቸው ፍፃሜ ላይ የደረሱበትን ፍሬ ነገር ነው የተናገሩት። ይህ ንግግራቸው "አቅሳሙ አል– ለዛት" (أقسام اللذات) በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ የሰፈረ ሲሆን፣ ተከታዩንም ግጥም አካተውበታል፦
وَلَمْ نَسْتَفِدْ مِنْ بَحْثِنَا طُولَ عُمْرِنَا ... سِوَى أَنْ جَمَعْنَا فِيهِ: قِيلَ وَقَالُوا
> *የአእምሮዎች መጨረሻ መረባበሽ (መሸበር) ነው፣*
> *የአለም ምሁራንም ጥረት መጨረሻው ጥፋት ነው።*
> *በአካላቶቻችን ውስጥ ከመንፈሳዊ ስቃይ በቀር አልተጠቀምንም፣*
> *ከዘመናት ፍለጋ ያገኘነውም ቢኖር፡ 'እንዲህ ተባለ' እና 'አሉ' የሚሉ ወሬዎችን መሰብሰብ ብቻ ነው።*
>
ይህ ዓይነቱ የእምነት ኑዛዜ ወይም ምስክርነት በአር-ራዚ ብቻ የተገደበ አይደለም፤ ሌሎችም ታላላቅ የፍልስፍና እና የከላም መሪዎች በህይወታቸው መጨረሻ ላይ ተመሳሳይ የቁጭት ምስክርነት ሰጥተዋል፦
* ኢማም አል-ጁወይኒ (ኢማሙ እል-ሐረመይን)፦
""እናንተ ወዳጆቻችን ሆይ! በከላም (በአመክንዮ/በፍልስፍና) እውቀት ላይ አትጠመዱ። ይህ የከላም እውቀት አሁን ካደረሰኝ (የጥርጣሬና የመዋለል) ደረጃ ላይ እንደሚያደርሰኝ አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ ኖሮ ፈጽሞ በእሱ ላይ ባልተጠመድኩ ነበር። ትልልቅ የትምህርት ተቋማትን በሙሉ አዳረስኩ፣ (የፍልስፍናን) ባህሮች ዋኘሁ፣ የኢስላም ሰዎችንና እውቀቶቻቸውን ንቄ እነሱ ከተከለከሉት ነገር ውስጥ ገባሁ። አሁን ግን አላህ በራህመቱ (በእዝነቱ) ፈጥኖ ካልደረሰልኝ ለጁወይኒ ልጅ ወዮለት! እነሆ እኔ አሁን (ሁሉንም ፍልስፍና ትቼ) በእናቴ እምነት ላይ ሆኜ እሞታለሁ።"
(በሌላ ዘገባ ደግሞ፦ "በነይሳቡር የዋህ አረጋውያን ሴቶች እምነት ላይ ሆኜ እሞታለሁ" ብለዋል)
* አቡ ሓሚድ አል-ገዛሊ፦ ህይወታቸውን በሙሉ በፍልስፍና እና በከላም ካሳለፉ በኋላ፣ በመጨረሻው ዘመናቸው ወደ ሐዲስ ትምህርት በመመለስ የኢማም አል-ቡኻሪን የሐዲስ መጽሐፍ ደረታቸው ላይ አቅፈው እንደሞቱ ይነገራል።
እነዚህ ሁሉ ምስክርነቶች (اعترافات) የሚያረጋግጡት አንድ እውነትን ነው፡- የሰው ልጅ አእምሮአዊ ፍልስፍና ለጊዜው የሚያደናግር እንጂ፣ ልብን በፍጹም እርጋታና እውነተኛ እምነት (የቂን) ሊሞላ የሚችለው ቀጥተኛውና ግልጹ የቁርአን እና የሱና መለኮታዊ ብርሃን ብቻ መሆኑን ነው።

نِهَايَةُ أَقْدَامِ العُقُولِ عِقَالُ ... وَأَكْثَرُ سَعْيِ العَالَمِينَ ضَلَالُ
وَلَمْ نَسْتَفِدْ مِنْ بَحْثِنَا طُولَ عُمْرِنَا ... سِوَى أَنْ جَمَعْنَا فِيهِ: قِيلَ وَقَالُوا
> *የአእምሮዎች መጨረሻ መረባበሽ (መሸበር) ነው፣*
> *የአለም ምሁራንም ጥረት መጨረሻው ጥፋት ነው።*
> *በአካላቶቻችን ውስጥ ከመንፈሳዊ ስቃይ በቀር አልተጠቀምንም፣*
> *ከዘመናት ፍለጋ ያገኘነውም ቢኖር፡ 'እንዲህ ተባለ' እና 'አሉ' የሚሉ ወሬዎችን መሰብሰብ ብቻ ነው።*
>
ይህ ዓይነቱ የእምነት ኑዛዜ ወይም ምስክርነት በአር-ራዚ ብቻ የተገደበ አይደለም፤ ሌሎችም ታላላቅ የፍልስፍና እና የከላም መሪዎች በህይወታቸው መጨረሻ ላይ ተመሳሳይ የቁጭት ምስክርነት ሰጥተዋል፦
* ኢማም አል-ጁወይኒ (ኢማሙ እል-ሐረመይን)፦
"يَا أَصْحَابَنَا لَا تَشْتَغِلُوا بِالكَلَامِ، لَوْ عَرَفْتُ أَنَّ الكَلَامَ يَبْلُغُ بِي إِلَى مَا بَلَغَ مَا اشْتَغَلْتُ بِهِ، لَقَدْ طُفْتُ المَعَاهِدَ الكِبَارَ، وَخُضْتُ البِحَارَ، وَتَرَكْتُ أَهْلَ الإِسْلَامِ وَعُلُومَهُم، وَدَخَلْتُ فِي الَّذِي نَهَوْنِي عَنْهُ، وَالْآنَ فَإِنْ لَمْ يَتَدَارَكْنِي اللهُ بِرَحْمَتِهِ فَالْوَيْلُ لِابْنِ الجُوَيْنِي، وَهَا أَنَا ذَا أَمُوتُ عَلَى عَقِيدَةِ أُمِّي" (وفي رواية: "عَلَى عَقِيدَةِ عَجَائِزِ نَيْسَابُورَ").
""እናንተ ወዳጆቻችን ሆይ! በከላም (በአመክንዮ/በፍልስፍና) እውቀት ላይ አትጠመዱ። ይህ የከላም እውቀት አሁን ካደረሰኝ (የጥርጣሬና የመዋለል) ደረጃ ላይ እንደሚያደርሰኝ አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ ኖሮ ፈጽሞ በእሱ ላይ ባልተጠመድኩ ነበር። ትልልቅ የትምህርት ተቋማትን በሙሉ አዳረስኩ፣ (የፍልስፍናን) ባህሮች ዋኘሁ፣ የኢስላም ሰዎችንና እውቀቶቻቸውን ንቄ እነሱ ከተከለከሉት ነገር ውስጥ ገባሁ። አሁን ግን አላህ በራህመቱ (በእዝነቱ) ፈጥኖ ካልደረሰልኝ ለጁወይኒ ልጅ ወዮለት! እነሆ እኔ አሁን (ሁሉንም ፍልስፍና ትቼ) በእናቴ እምነት ላይ ሆኜ እሞታለሁ።"
(በሌላ ዘገባ ደግሞ፦ "በነይሳቡር የዋህ አረጋውያን ሴቶች እምነት ላይ ሆኜ እሞታለሁ" ብለዋል)
* አቡ ሓሚድ አል-ገዛሊ፦ ህይወታቸውን በሙሉ በፍልስፍና እና በከላም ካሳለፉ በኋላ፣ በመጨረሻው ዘመናቸው ወደ ሐዲስ ትምህርት በመመለስ የኢማም አል-ቡኻሪን የሐዲስ መጽሐፍ ደረታቸው ላይ አቅፈው እንደሞቱ ይነገራል።
እነዚህ ሁሉ ምስክርነቶች (اعترافات) የሚያረጋግጡት አንድ እውነትን ነው፡- የሰው ልጅ አእምሮአዊ ፍልስፍና ለጊዜው የሚያደናግር እንጂ፣ ልብን በፍጹም እርጋታና እውነተኛ እምነት (የቂን) ሊሞላ የሚችለው ቀጥተኛውና ግልጹ የቁርአን እና የሱና መለኮታዊ ብርሃን ብቻ መሆኑን ነው።
👍15❤8
📌 ዙልሒጃ ቀን 07፦
> በዐረፋ ምሽት ላይ ከሰዎች ሁሉ የከፋው ሰው ማን እንደሆነ ያውቃሉ? ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አስ-ሰውሪይ በጉልበታቸው ተንበርክከው ሲያለቅሱ "ከዚህ ስብስብ የከፋው ማነው?" ተብለወወ ሲጠየቅኘቁ፦ "አላህ አይምረኝም ብሎ የሚያስበው ሰው ነው" ሲል መለሱ። በአላህ ላይ መልካም ጥርጣሬ ይኑረን! 💫 #ዐረፋ #ተስፋ #የአላህ_እዝነት

❤9
የታላቁ ዓሊም የኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) ዕንቁ ምክር፦
“ኢማን በልብ ውስጥ የሚገኝ ደስታ፣ ጥፍጥና እና እርካታ አለው።
አንድ ሰው የአምልኮ ተግባራትን በሚፈጽምበት ጊዜ ያንን ጣፋጭና መንፈሳዊ የደስታ ቃና ካላገኘ፣ ኢማኑን አጥቷል ወይም ጎድሏል ማለት ነው!»

📔 አር-ሪሳላህ አት-ተቡኪይያህ (7)*
👍7❤1
ዐላመቱ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ
### ጥያቄ (ከአድማጭ)፦
> "ጥያቄ አቅራቢው እንዲህ ይላል፦ 'እኔ መልካም ነገርን የምትወድ ነፍስ አለችኝ፤ ነገር ግን ደካማ ናት፣ ከወንጀልና ከጥፋት ፊት መቆም አትችልም። ወንጀልን ባየሁ ቁጥር ከፊቱ እደክማለሁ። ታዲያ ለዚህ የሚሆን፣ የሚመሩኝ መድኃኒት ወይም ፈውስ አለን?'"
>
### የሸይኽ ኢብን ባዝ ምላሽ፦
"አዎ! አላህ (ሱብሐነሁ ወተዓላ) *'ሰውም ደካማ ሆኖ ተፈጠረ'* ብሏል። ነገር ግን እንድትጠነክር አላህ መሣሪያዎችን ሰጥቶሃል።
ልብህ በእነርሱ እንዲጠነክር ያደረገልህን መሣሪያዎች ሰጥቶሃል፤ እነርሱም፦
* አላህን መታዘዝ፣ * ዚክርን (እርሱን ማውሳትን) ማብዛት፣ * በእርሱ ታላቅነት ላይ ማስተንተን እና በአንተ ላይ ስላለው መብት ማሰብ ናቸው።
አንተ ወደ እርሱ ተመላሽ መሆንህን፣ ተጠያቂ መሆንህንም አስብ፤ *'በጌታህ እምላለሁ! ከሚሠሩት ነገር በሙሉ በእርግጥ እንጠይቃቸዋለን'* ተብሏል።
አንተ በጥፋቶችህ ምክንያት ቅጣት የሚገባህ መሆንህን፣ በታዛዥነትህ ደግሞ ምንዳ (አጅር) የምታገኝ መሆንህን አስብ። ስለዚህ (ነፍስህን) አስታውሳት፤ ስሜትንም አትከተል፤ ከአላህ መንገድ ያሳስትሃልና። ነፍስ በአላህ እዝነት ካልተጠበቀች በስተቀር ሁልጊዜም ወደ መጥፎ ነገር አዛዥ መሆንዋን እወቅ። ስለዚህ ለስሜቷ አትታዘዝላት።
አላህ እንዲህ ብሏል፦
> *'ያ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ፣ ነፍሱንም ከክፉ ስሜቷ የከለከለ፤ በእርግጥ ጀነት እርሷ መጠጊያው(መኖሪያወ) ናት።'*
>
ስለዚህ ነፍስህ ወደ ወንጀል ስትጠራህ፦ ነገሩ ከባድ መሆኑን፣ አላህ ከወንጀል መከልከሉን፣ በአላህ ቁጣና ቅጣት የተዛተበት መሆኑን አስታውሳት፤ (አላህ ካልማረው በስተቀር)። አንተ ደግሞ በዚያው ወንጀል ላይ እያለህ ልትሞት ትችል እንደሆነ፣ ይቅርታ ይደረግልህ ወይም ትቀጣ እንደሆነ አታውቅም።
ስለዚህ ታገላት፣ አስታውሳት፣ ነገሮችን አቅልሎ ከመመልከት (ቸልተኝነት) ተጠንቀቅ። በዚህ ላይ ከተሳካልህ አላህ ያግዝሃል፤ ከዚህችም ነፍስ ክፋት ትድናለህ።"

❤4👍4
## 🌟 የዓረፋ ቀን እና የዕርድ ቀን (የዒድ ዕለት) ታላቅነት!
ምስጋና ለአላህ ይሁን። የዓረፋ ቀን በአላህ (ዓዘ ወጀል) ዘንድ እጅግ ታላቅ ቀን ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም) በትክክለኛ ሐዲሳቸው እንዲህ ብለዋል፦
> *“አላህ በዓረፋ ቀን ከእሳት ነፃ የሚያወጣቸውን ያህል ባሮችን (ከእሳት) ነፃ የሚያወጣበት ሌላ ምንም ቀን የለም።”*
>
የአንዳንዶቹ የዓሊሞች አባባል እንደሚያመለክተው፣ አላህ በቁርአኑ “በመስካሪውና በተመሰከረበትም እምላለሁ” (وشاهد ومشهود) ሲል የፈለገበት ‘የተመሰከረበትን ዕለት’ ማለትም የዓረፋን ቀን ነው። እሱ ፀሐይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጩ ቀን ነው። በዚህ ዕለት ከሚደረግ ዱዓእ የበለጠ በአላህ ዘንድ ታላቅ የሆነ የለም። የአላህ መልዕክተኛም ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም))፦ *“ከዱዓእ ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን ዱዓእ ነው”* ብለዋል።
የዓረፋ ቀን ትሩፋትና የአላህን ችሮታ ማግኘት ሑጃጁንም (ሐጅ ላይ ያለውን) ሆነ ሀገር ላይ ያለውን (ሐጅ ያላደረገውን) እኩል ያጠቃልላል። ሑጃጆች በዓረፋ ሜዳ ላይ በመቆም ታላቁን የሐጅ (ሩክን) ማዕዘን ይፈጽማሉ፤ ነቢዩ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም)) *“ሐጅ ማለት ዓረፋ ነው”* እንዳሉት። ሐጅ ያላደረጉት ደግሞ የዓረፋን ቀን በመጾም ወደ አላህ መቃረቢያን ይሻሉ። ይህንንም ጾም የአላህ መልዕክተኛ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም)) እንደተናገሩት፦ ያለፈውን አንድ ዓመትና የሚመጣውን አንድ ዓመት (በድምሩ የሁለት ዓመት) ወንጀል ያስተሰርያል ብለው ከአላህ ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉ።
ስለሆነም እሱ በረከቱ አጠቃላይ፣ ትሩፋቱ ታላቅ፣ ምሕረቱና እዝነቱ የሰፋ፣ ከእሳት ነፃ የመውጫ ቀን ነው። ይህ ቀን ከዱንያ ቀናት ሁሉ በአላህ ሚዛን ዘንድ እጅግ ከባድ ቀን ነው። ወደ ዓረፋ ቀን ከተመለከትክና “በነዚህ አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ውስጥ ከዓረፋ ቀን በስተቀር ሌላ ቀን ባይኖር እንኳ፣ የአስሩን ቀናት በላጭነት ከሌላው የዓመቱ ቀናት ሁሉ በላይ ለማስበለጥ በቂ በሆነ ነበር” ብትል እውነት ነው። ታዲያ ከላይ የተጠቀሱት ታላላቅ ትሩፋቶች ሁሉ ተደምረውበትማ እንዴት አይበልጥ?! እነኚህ ቀናት አላህ ሐጅን ያዘዘበትና ሑጃጆች የአምልኮ ሥርዓታቸውን የሚፈጽሙባቸው የታወቁት ቀናት ማጠቃለያ ናቸው። ይህም አላህን ለማውሳትና በነዚህ ቀናት ውስጥ ያሉትን ጥቅሞች ለመታደም የተደነገገ ነው።
በመቀጠልም የአስሩ ቀናት ማሳረጊያ (አሥረኛው ቀን) የሆነው የዕርድ ቀን (يوم النحر) ይመጣል። እሱም በምሥራቅም ሆነ በምዕራብ ያሉ የሙስሊሞች ኡማህ በደስታ የሚሞሉበት ታላቅና የተባረከ የዒድ ቀን ነው። ይህ ቀን በአላህ ዘንድ እጅግ ታላቅ ከሆኑ ቀናት ውስጥ አንዱ ነው። ነቢዩ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)) እንዲህ ብለዋል፦
> *“በአላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ ታላቁ ቀን የዕርድ ቀን (የዒድ ዕለት) ነው።”*
>
ይህ የአላህ መልዕክተኛ ((ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)) የተናገሩት ፍፁም የሆነ ማበላለጥ (تفضيل مطلق) ነው። ይህ ፍፁም ማበላለጥ የዒድ ቀንን በናፍቆት የምትጠብቀው ታላቅ ቀን አድርገህ እንድትይዘው ያደርግሃል። ይህ በታላቁ ጌታህ ዘንድ ከሁሉ የበላይ የሆነ ታላቅ ቀን ከሆነ፣ በአላህ ይሁንብህ! አንተ በዚህ ቀን ምን ልትሠራ ተዘጋጅተሃል?! በአላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ በላጭ በሆነው ቀን ምን ታደርጋለህ?
አላህ በዚህ ቀን ተክቢራን ደንግጎልሃል፣ የዒድ ሰላትን ደንግጎልሃል፣ የምታርደውን ኡድሒያ (ዕርድ) ደንግጎልሃል። ለሙስሊሙ ኡማህ በሙሉ፤ ሑጃጁንም ሆነ ሌላውን፣ አላህን በማክበር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አላህን እንዲያወድሱ፣ ተክቢራ፣ ተህሊልና ተሕሚድ እንዲያደርጉ ደንግጓል።
የሙስሊሙ ኡማህ ሑጃጁም ሆነ በሀገሩ ያለው ሁሉ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንድ ድምፅ ይሰበሰባል። ምድር በሙሉ ለታላቁ ጌታችን በምናደርገው ተክቢራ፣ ተህሊልና ተሕሚድ ትናወጣለች፣ በድምፅም ትሞላለች። በእርግጥም የሙስሊሙ ኡማህ የዚህን ቀን ታላቅነት በአምልኮ ሥርዓቱ፣ በሸሪዓው፣ በዓቂዳውና በባህሉ ላይ ያንጸባርቃል። በዚህም የሙስሊሙ ኡማህ አረብም ሆነ አረብ ያልሆነው፣ ታናሹም ታላቁም፣ ወንዱም ሴቱም ሁሉ በአንድ ሰው ልብ ላይ ሆነው በአንድ ድምፅ እንዲህ ይላሉ፦
> الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله
> الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
> *(አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሀ ኢልለላህ፣ አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ)*
>
🚩 @ https://t.me/sultan_54

❤14👍1
ቃላት ፍርድ አላቸው።
በሸሪዓ ሚዛን "ሙስሊም አይደለሁም" የሚሉ ግልጽ ቃላት እንደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ወይም እንደ ምሳሌያዊ አነጋገር አይታዩም። ይልቁንም ቀጥተኛ የእምነት ክህደት መግለጫ ናቸው። አንድ ሙስሊም ከእውነተኛ ማስገደድ ውጭ ይህንን ለማድረግ መብት የለውም።

👍11
የአእምሮና የሃሳብ ጥንካሬ የሚገለጠው መርህን ግልጽ በማድረግና ማንነትን ጠብቆ በማስረዳት ላይ እንጂ፣ የሰሚዎችን ስሜት ለመከተልና የአስተሳሰብ ግጭትን ለመሸሽ ሲሉ በማንነት ውስጥ መለዘብ አይደለም።
👍14❤2
##"የዓረፋ ቀን በዓል (ዒድ) መሆኑን ያውቃሉን? አዎ!
እሱማ አላህ ዲኑን የሞላበት፣ ጸጋውንም ያጠናቀቀበት ቀን አይደለምን? ይህ የሆነው ደግሞ ከብዙ የተውሂድ አንቀጾች፣ ከታሪኮች፣ ከሕግጋቶችና ከነቢያዊ ሐዲሶች ረጅም ሰንሰለት በኋላ ነው።
ይህ በዓል ለሙስሊሞች ዘንድ እጅግ ታላቅ መሆኑን ማስታወስና ማስተንተን ይገባል። እንዲያውም አንድ አይሁዳዊ (ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ) እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ *‘እኛ የይሁዳ ማኅበረሰቦች ላይ እንዲህ ዓይነት አንቀጽ (አያህ) ወርዶ ቢሆን ኖሮ፣ ያንን ቀን የበዓል ቀን (ዒድ) አድርገን እንይዘው ነበር።’* ዑመርም (ረዲየሏሁ.ዐንሁ) እንዲህ ሲል መለሱለት፦ *‘እኔ ይህች አንቀጽ( ማለትም፦"...ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፤ ለእርናንተም እስልምናን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ..." (አል-ማኢዳህ: 3)
በየትኛው ቀን በነቢዩ (ﷺ) ላይ እንደወረደች ጠንቅቄ አውቃለሁ፤ እሷም የወረደችው በዓረፋ ቀን ነበር።’*"
#ዒድ_ዐረፋ#ዙልሒጃ

👍13❤3
ዙልሒጃ 8(የውሙ ተርዊያህ)
ከሚና ጥሪው(ተልቢያው) ይጀምራል፣
በአረፋም እለት ዱዓዎች ወደ ላይ ይውጣሉ፣
በመቀጠል በሰከነ መንፈስ ወደ ሙዝደሊፋ፣
በጀመራትም የኢማን እርምጃዎች ይፈጸማሉ..
የሐጅ ትዕይንቶች በቅዱሳን ቦታዎች መካከል መዘዋወር ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የልብ ወደ አላህ የመጓዝ ጉዞ እንጂ።
#ሐጅ
#ሐጅ_1447ዓ_ሂ

👍6❤4
ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል!
አቡ–ቀታዳ ረዲየላሁ ዓንሁ እንዳስተላለፉት:‐ «የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ ዓረፋ ጾም ተጠየቁ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል" አሉ።» (ሙስሊም ዘግበውታል)
ያስታውሱ ዛሬ ከዙል–ሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን (የውሙ አት–ተርዊያ) ሑጃጆች የሐጅ ስራቸውን የሚጀምሩበት እለት ነው።
የነገው ዘጠነኛው ቀን የውሙ ዓረፋ ነው። ሑጃጆች በዓረፋ ምድር የሚቆሙበት ለነሱም ይሁን ለሌላው ሙስሊም ማህበረ–ሰብ እጅግ ልዩ የዒባዳ ቀን ነው።
በጾም፣ በዚክር በተለይ ተክቢራ እና ዱዓእ እንድንጠቀምበት ልንተዋወስ እና አንዳችን ሌለኛውን ሊያበረታታ ይገባል።
የነገውን ቀን ጾም በተመለከተ ከላይ በጠቀስነው ሀዲስ ላይ መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ያለፈውን እና የመጪውን አመት ወንጀል ያሰምራል ማለታቸው ይህን እለት በጉጉት እንድነጠብቀው ያደርጋል።
ከጾም ውጪ በዚህ ቀን ልዩ በሆነ መልኩ ልናደርጋቸው የሚወደዱ ነገሮችን በተመለከተ በተከታይ ጽሁፎች ኢንሻ አላህ ለመጠቆም እሞክራለሁ።
ወደ መልካም አመላካች እንደ ሰሪው ምንዳ አለው!!
ለሌሎችም መልእክቱን እናስተላልፍ
✍️ ጣሀ አህመድ
🌐 https://t.me/tahaahmed9

👍12❤6
#Eid_Aladha1447
🌺 عيدكم مبارك! 🌺
🔶 🌸Eid Mubarak! 🌸 🔶
🌹 ዒድ ሙባረክ! 🌹
🤲تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🤲
🤲ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን🤲
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
@sultan_54
🌺 عيدكم مبارك! 🌺
🔶 🌸Eid Mubarak! 🌸 🔶
🌹 ዒድ ሙባረክ! 🌹
🤲تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال🤲
🤲ከእኛም ከእናንተም አሏህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን🤲
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
@sultan_54
🥰16❤10👍5
📌 ዙልሒጃ ቀን 10 (የዒድ ቀን)፦
> በተለያዩ ምክንያቶችና በህመም ሳይጓዙ የቀሩ፣ ልባቸው ግን ከመካ ያልተለየ ብዙ ወገኖች አሉ።
يا راحلين إلى البيت العتيق * سرتم جسوما وسرنا نحن أرواح إن أقمنا عن عذر وعن قدر * ومن أقام عن عذر كمن راحا
"እናንተ በአካላችሁ ተጓዛችሁ፣ እኛ ግን በነፍሳችን ተጓዝን፤ በእውነተኛ ምክንያት የቀረ ሰው ግን እንደተጓዘ ይቆጠራል።" አላህ (በኡዝር) የቀሩትን የሑጃጆችን አጅር ይመንዳቸው! 🕊️❤️ #ዙልሒጃ #የዒድ_ቀን

❤10
### ግንዛቤ ማስተካከያ!
የሰው ልጅ ለሰዎች የመጸወተውና በአላህ መንገድ ላይ የሰጠው ነገር ሁሉ ለአኼራው የሚቀረው እውነተኛው ሀብቱ ሲሆን፣ ለራሱ አስቀርቶ የበላውና የተጠቀመበት ግን አላፊና ጠፊ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
የአላህ መልእክተኛም ﷺ አንድ የበግ ጠቦት አረዱና፤(ዓኢሻን) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ፦
(“ከበጓ ላይ ምን የቀረ ነገር አለ?”)
*(እናታችን ዓኢሻም* እንዲህ አሏቸው፦ “ከትከሻዋ በስተቀር ምንም የቀረ ነገር የለም።”
የአላህ መልእክተኛም ﷺ እንዲህ አሉ፦
“ከትከሻዋ በስተቀር ሙሉዋ ቀርታለች እንጂ!”
*[ቲርሚዚ የዘገቡት ሲሆን፣ አልባኒ ሰሒሕ ነው ብለውታል]*

👍15❤7