## የአያሙ አት-ትሽሪቅ (ሑጃጆች ሚና ላይ የመቆያ ቀናት) ትርጉምና ደረጃ
ምስጋና ለአላህ ይሁን። የአያሙ አት-ትሽሪቅ ቀናት ማለት አላህ በቁርኣኑ፦ "አላህንም በታወቁት (በተቆጠሩት) ቀናት ውስጥ አውሱት" (አል-በቀራህ፡ 203) በማለት የጠቀሳቸው ቀናት ናቸው። እነሱም ከዕርዱ ቀን (ከዒድ አል-አድሃ) በኋላ ያሉ ሶስት ቀናት ሲሆኑ፤ 11ኛው፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀናት ናቸው።
ከእነዚህ ቀናት ውስጥ በላጩ መጀመሪያው ቀን (11ኛው ቀን) ነው። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
> "አላህ ዘንድ ከቀናት ሁሉ የላቀው ቀን የዕርዱ (የዒድ) ቀን ነው፣ ከዚያም ‘የቀር’ር’ (ሑጃጆች ሚና ላይ የሚቆዩበት ቀናት) ቀን ነው"
>
እሱም 11ኛው ቀን ነው።
## የእነዚህ ቀናት ትሩፋት እና ተግባራት
የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
> "የዐረፋ ቀን፣ የዕርዱ ቀን እና የአያሙ አት-ትሽሪቅ ቀናት ለእኛ ለኢስላም (ህዝቦች) በዓሎቻችን ናቸው፤ እነሱም የመብያና የመጠጫ ቀናት ናቸው።"
>
ስለሆነም በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚከተሉትን ማድረግ ይደነገጋል (ይወደዳል)፦
* አላህን ማውሳት (ዚክር ማድረግ)፦ የእስልምናን መገለጫዎች ማሳየት፣ መደሰት እና ሀሴት ማድረግ።
* ዝምድናን መቀጠል፦ ከቤተሰብና ከዘመድ ጋር መዘያየር።
* የተገደበ ተክቢራ (አት-ተክቢር አል-ሙቀየድ)፦ ከግዴታ ሶላቶች በኋላ የሚደረገው ተክቢራ እስከ 13ኛው ቀን የዐስር ሶላት ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል።
* አጠቃላይ ተክቢራ (አት-ተክቢር አል-ሙጥለቅ)፦ በማንኛውም ሰዓት፣ ሁኔታ እና ቦታ ላይ የሚደረገው ተክቢራም እንዲሁ ይቀጥላል።
* የኡድሂያ እንስሳትን ማረድ፦ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የዒድ መሥዋዕት ይታረዳል።
* መጾምን መከልከል፦ በእነዚህ ቀናት መጾም አይፈቀድም፤ ነገር ግን (በሐጅ ላይ ሆኖ) የመሥዋዕት (ሀድይ) እንስሳ ማቅረብ ላልቻለ ሰው ብቻ መጾም ይፈቀድለታል።

❤11👍1
## 📌 ጠቃሚ ምክር!
በአካሉ፣ በንግግሩ፣ በጽሑፉ እና በሁሉም ጉዳዮቹ ላይ ጥንካሬን ለሚሻ ሰው፦
👇👇
ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህን ማውሳት (ዚክር) ለሚያዘወትረው ሰው ጥንካሬን ይሰጠዋል። አልፎ ተርፎም ያ ሰው በዚክር አማካኝነት ያለ ዚክር ሊያደርገው የማይችለውን ከባድ ነገር ሁሉ በቀላሉ ይከውናል።
እኔ ራሴ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያን (ረሒመሁላህ) ብርታት በተመለከትኩ ጊዜ በአካሄዳቸው፣ በንግግራቸው፣ በጀግንነታቸውና በጽሑፋቸው ላይ የሚገርም ነገር አይቻለሁ። አንድ ጸሐፊ በአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ሊጽፈው የሚችለውን የኪታብ ዝግጅት እሳቸው በአንድ ቀን ውስጥ ይጽፉት ነበር። የጦር ሠራዊቱም በጦርነት ወቅት የነበራቸውን ታላቅ ጥንካሬና ጀግንነት በተግባር መስክሯል።
●● የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለልጃቸው ፋጢማ እና ለዐሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ወደ መኝታቸው በሚሄዱበት ጊዜ፦
* 33 ጊዜ ‘ሱብሐነላህ’
* 33 ጊዜ ‘አልሐምዱሊላህ’
* 34 ጊዜ አላሁ አክበር ፣ ብለው እንዲያወሱ አስተምረዋቸዋል።
ይህንን ያስተማሯት ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ስንዴ ፈጭቶ ማዘጋጀትና የቤት ውስጥ ሥራ ደክሟት አገልጋይ እንዲሰጧት በጠየቀቻቸው ጊዜ ነበር። ይህንን አስተምረው ማጠቃለያው ላይ፦ '(ይህ ዚክር) ለእነሱ ከአገልጋይ ይበልጥ በላጭ ነው' አሏት።
👈 በመሆኑም ይህንን ዚክር አዘውትሮ ያደረገ ሰው በአካሉ ላይ አገልጋይ ከመፈለግ የሚያብቃቃውን (የሚተካውን) ጥንካሬ ያገኛል ተብሏል።"
> 📚 ምንጭ፦ አል-ዋቢል አስ-ሰዪብ፣ ገጽ (185)

👍12❤7
ቁርኣንን በተሳሳተ መንገድ መረዳት የሚያስከትለው አደጋ!
ቁርዓንን በትክክል የመረዳትን እጅግ አንገብጋቢ አስፈላጊነት መገንዘብ ግድ ይላል።
ቁርኣንን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ለኡማው (ለህዝበ ሙስሊሙ) መጥፋት፣ መከፋፈል፣ መናቆር፣ እና ከመስመር መውጣት ምክንያት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።
ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር፤ አህሉ-ሱናዎች ቁርዓኣንን በሱና (በነብዩ ሐዲስ) እንደሚተረጉሙ ነው፤ ለዚህም ነው "አህሉ-ሱና" ተብለው የተሰየሙት።
በተለየ ቡድን ስም አልተጠሩም፤ "ሙተከሊሚን" (የከላም/የፍልስፍና ሰዎች)፣ "አሽዓሪያ"፣ "ማቱሪዲያ" ወይም "ሱፊያ" ተብለው አልተሰየሙም። በፍጹም! ከ"ሱና" ውጪ ሌላ ስም የለንም።
> ኢማሙ ማሊክ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
> *"አህሉ-ሱና ማለት የሚታወቁበት ምንም ዓይነት (የተለየ) ቅጽል ስም የሌላቸው ናቸው፤ ጃህሚያም፣ ቀደሪያም፣ ራፊዲያም አይደሉም።"* > —
[አል-ኢንቲቃእ ሊኢብኒ ዓብዲልበር፣ ገጽ 35]

قال الإمام مالك رحمه الله: أهل السنة الذين ليس لهم لقب يعرفون به، لا جهمي ولا قدري ولا رافضي."
— [الانتقاء لابن عبد البر، ص 35]
> ኢማሙ ማሊክ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
> *"አህሉ-ሱና ማለት የሚታወቁበት ምንም ዓይነት (የተለየ) ቅጽል ስም የሌላቸው ናቸው፤ ጃህሚያም፣ ቀደሪያም፣ ራፊዲያም አይደሉም።"* > —
[አል-ኢንቲቃእ ሊኢብኒ ዓብዲልበር፣ ገጽ 35]
>
👍8❤1
የሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) ወርቃማ ምክር!
> 🔴 "በዲን ውስጥ ማጥበቅና ወሰን ማለፍም ሆነ፤ ቸልተኝነትና ግድየለሽነት አይፈቀድም። ይልቁኑ በዚህና በዚያ መካከል መካከለኛ (ሚዛናዊ) ሁን።"
> — አሽ–ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን፣ ፈታዋ (9/367)

❤7👍6
🛡️ የአማኞች ጋሻ፦ የአላህን ባህሪያት በቃላት ጨዋታ የማደብዘዝ ሴራ!
ሽብር!
### 📌 “እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባ ታላቅ ነጥብ አለ!
💡በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡትን የጌታችንን (ሱብሐነሁ ወተዓላ) ባህሪያት በሚያጠራጥር ወይም በሚያሳቅቅ ቃል መግለፅ እውነታውን በፍጹም አይቀይረውም!
ኢማም አሕመድ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለው ነበር፦
> « ..وَلَا نُزِيلُ عَنْهُ صِفَةً مِنْ صِفَاتِهِ لشَنَاعَةٍ شُنِّعَتْ.. »
> *“የሚፀየፍ ተፀይፎ ስላወገዘ (ብለን) ከባህሪያቱ አንዱንም አንገፍፍም (አናስወግድም)!”*
> 📄 [“አል-ኢባና” ሊ’ብኒ በጣህ (3/326)፤ “ዘም-ሙ’ት-ተእዊል” ሊ’ብኒ ቁዳማህ፣ ገፅ 22]
>
### 🔍 የ“ተዕጢል” (የአላህን ባህሪያት አስተባባዮች) ስልት ምንድን ነው?
በአቀንቃኞቹ ንግግር ላይ *“አላህ ለራሱ ያፀደቃቸውን ባህሪያት አንቀበልም!”* የሚል ቀጥተኛ የማስተባበያ ገለፃ ላይገኝ ይችላል። ሆኖም አብዛኛውን ጊዜ ለዚህ ዓላማ መንገዱን የሚደለድሉት ባህሪያቱን ያለ አደብ በተለያዩ ፍልስፍናዊ ቅፅላዎች እየጠሩ እውነታውን በማድበስበስ ነው!
*(በሀገራችን ብሂል፦ «ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ‘ጅግራ’ ይሏታል» እንደሚባለው!)*
ባህሪያቱን ለማስተባበልና ሰዎችን ለማሸበር የሚጠቀሙባቸው ስያሜዎች፦
* አዕራድ (أَعْرَاض)፦ እንደ መስማትና ማየት ያሉትን የአላህ ባህሪያት።
* አዕዷእ (أَعْضَاء) ወይም ጀዋሪሕ (جَوَارِح)፦ እንደ ፊትና እጅ ያሉትን ባህሪያት።
* ሐዋዲሥ (حَوَادِث)፦ እንደ ንግግር ያሉ ሲፈልግ የሚፈፅማቸውን አድራጎቶች።
* ተሐይ-ዩዝ (تَحَيُّز)፦ “አስቲዋእ”ን (በዐርሹ ላይ መሆኑን) እና ከፍጥረተ ዓለሙ በላይ መሆኑን።
* አግራድ (أَغْرَاض)፦ ከውሳኔውና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉትን ጥበቦችና ዓላማዎች።
### ⚠️ የማደናገሪያው ጥግ
እነዚህን ቃላትና መሰሎቻቸውን የሚተረጉሙት በመሠረታዊው ቋንቋዊ መልዕክታቸው ሳይሆን፣ በተምታታ ፍልስፍናዊ ይዘታቸው ነው።
በዚህም ሳይበቁ፤ የአላህን ባህሪያት ከማመሳሰል (ተሽቢህ) በፀዳ መልኩ በቁርኣንና በሐዲሥ እንደተገለፁት በቀጥታ የሚቀበሉትን የሐቅ ባለቤቶች (አህሉስ-ሱናህን)፦ *“አላህን በእነዚህ አሸማቃቂ መገለጫዎች ይገልፃሉ!”* እያሉ በቅጥፈት ይወርፋሉ።”
📚 ምንጭ፦ የአማኞች ጋሻ — ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ (ገፅ 93)
*
https://t.me/sultan_54

❤7
> ለ1447ኛው ሂጅሪያ አ/ ሂ ምርጥ የሐጅ ልዑካን ምደባ ላይ ቀዳሚ ደረጃዎችን በመያዝ፣ በከፍተኛ ሥርዓትና ለሐጃጆቻቸው በማሳየት ረገድ ግሩም ምሳሌ ለሆኑት ሕዝቦች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! 🏆
>
ምርጥ የሐጅ ልዑካን (ልኡካን ቡድኖች)
### 💎 የአልማዝ ሽልማት
* 🇲🇾 ማሌዢያ
* 🇪🇹 ኢትዮጵያ
* 🇮🇶 ኢራቅ
### 🥇 የወርቅ ሽልማት
* 🇹🇷 ቱርክ
* 🇰🇲 ኮሞሮስ (ጁዝሩል ቀመር)
* 🇩🇯 ጅቡቲ
### 🥈 የብር ሽልማት
* 🇪🇬 ግብፅ
* 🇴🇲 የኦማን ሱልጣኔት
* 🇲🇦 ሞሮኮ
### 🥉 የነሐስ ሽልማት
* 🇸🇬 ሲንጋፑር
* 🇹🇳 ቱኒዚያ
* 🇩🇿 አልጄሪያ
>
ምርጥ የሐጅ ልዑካን (ልኡካን ቡድኖች)
### 💎 የአልማዝ ሽልማት
* 🇲🇾 ማሌዢያ
* 🇪🇹 ኢትዮጵያ
* 🇮🇶 ኢራቅ
### 🥇 የወርቅ ሽልማት
* 🇹🇷 ቱርክ
* 🇰🇲 ኮሞሮስ (ጁዝሩል ቀመር)
* 🇩🇯 ጅቡቲ
### 🥈 የብር ሽልማት
* 🇪🇬 ግብፅ
* 🇴🇲 የኦማን ሱልጣኔት
* 🇲🇦 ሞሮኮ
### 🥉 የነሐስ ሽልማት
* 🇸🇬 ሲንጋፑር
* 🇹🇳 ቱኒዚያ
* 🇩🇿 አልጄሪያ
❤27👍4🥰4💔1
በሱጁዱ አስ– ሰህው (የመርሳት ሱጁድ) አራት አስፈላጊ መርህዎች
የመጀመሪያው መርሆ፡(ቃዒዳህ) በሶላት ውስጥ ዋጅብ የሆኑ ነገሮችን በመርሳት ሳያደርጉ ካለፉ፤ ከማሰላመት በፊት ሱጁድ ይደረጋል።
ሁለተኛው መርህ(ቃዒዳህ)፡ ሩክን የሆኑ ነገሮችን በመርሳት ሳያደርጉ ካለፉ፤ ያን የረሱትን ሩክን አሟልተው ከዚያ ሶላቱን ጨርሰው ከሰላምታ በኋላ ሱጁድ ያደርጋሉ።
ሦስተኛው መርህ(ቃዒዳህ)፡ በመጠራጠር ላይ የተመሰረተ ሱጁድ ሲሆን በዋነኛው በመጠራጠር (በገመትነውን በመመስረት) ከሰላም በኋላ ሱጁድ ይደረጋል። በትንሹ በመመስረት (የተረጋገጠውን አነስተኛ በመመስረት) ከማሰላመት በፊት ሱጁድ ይደረጋል።
አራተኛው መርሆ(ቃዒዳህ)፡ በሶላት ውስጥ ማንኛውም በመርሳት የተነሳ መጨመር ከሆነ፤ ከማሰላመት በኋላ ሱጁድ ይደረጋል።

# ጃሚዑል መሳኢል (جامِعُ المَسَائِلِ)
ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢቢን ዐብዱልሐሊም ኢቢን ዐብዱሰላም ኢብኑ ተይሚያህ
“ነገር ግን ይህ ማለት አላህ በሰማይ ውስጥ ነው፣ ሰማያትም ይከቡታል ወይም ይይዙታል ማለት አይደለም። ይህንንማ ከቀደምት (ሰለፎች) እና ከዑለማኦች መካከል ማንም አላለውም። ይልቁንም አላህ ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፣ ከፍጡራኑ የተለየ (ያለተነካካ) መሆኑን፣ በፍጡራኑ ውስጥ የእሱ ማንነት (ዛቱ) ምንም ነገር እንደሌለ፣ በእሱም ማንነት ውስጥ ከፍጡራኑ ምንም ነገር እንደሌለ ተስማምተዋል።
* ማሊክ ኢቢኑ አነስ እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ በሰማይ ነው፤ እውቀቱ ግን በየቦታው ነው።»
* ለዐብዱላህ ኢቢኑ አል-ሙባረክ፦ «ጌታችንን በምን እናውቀዋለን?» ተብለው ሲጠየቁ፤ «ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ የላቀ፣ ከፍጡራኑ የተለያየ መሆኑን በማወቅ» አሉ።
* አሕመድ ኢቢኑ ሐንበልም፦ ልክ ይህና ይህ (የተባለው) ዓይነት ነው ብለዋል።
* አሽ-ሻፊዒይም እንዲህ ብለዋል፦ «የአቡ በክር ኸሊፋነት አላህ በሰማዩ የወሰነው እውነተኛ ውሳኔ ነው፤ የኡለማኦች ልቦችም በዚህ ላይ ተስማምተዋል።»
* አል-አውዛዒይም እንዲህ ብለዋል፦ «እኛና ታቢዒዮች በብዛት በነበርንበት ጊዜ አላህ ከዐርሹ በላይ መሆኑን እናረጋግጥ ነበር፤ በሱና ላይ በመጡት ባህሪያቱ ሁሉ እናምናለን።»
ስለሆነም አላህ በሰማይ ውስጥ የተከበበ፣ የተያዘ ነው ብሎ የሚያምን፣ ወይም ወደ ዐርሽና ወደ ሌላ ፍጡር ፈላጊ ነው ብሎ የሚያምን፣ ወይም በዐርሹ ላይ ከፍ ማለቱ (እስቲዋእ) ልክ ፍጡር በወንበሩ ላይ እንደሚደላደለው ዓይነት ነው ብሎ የሚያምን ሰው፤ እሱ የተሳሳተ፣ ቢድዓ አራማጅና መሃይም ነው።
(3/198)

👌5❤3
## በ (ሰላት) ላይ የሚታዩ ስድስት የሙናፊቆች (መናፍቃን) ባህሪያት
ኢማም እብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸውና) መናፍቃን ሰላት በሚሰግዱበት ጊዜ የሚታዩባቸውን ስድስት መጥፎ ባህሪያት እንደሚከተለው አስቀምጠውታል፡
### 1. ለመስገድ በሚነሱበት ጊዜ ስንፍና ማሳየት (الكسل عند القيام إليها)
ሰላትን ለመስገድ መነሳሳት ማጣት፣ መክበድ እና መዘግየት።
አላህ تعالى
በቁርአኑ ላይ እንደገለጻቸው፡
{وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ} (ወደ ሰላትም በቆሙ ጊዜ ሰነፎች
ሆነው ይቆማሉ)።
### 2. ለይዩልኝ (ሪአእ) መስገድ (الرياء ومراءاة الناس)
ሰላትን የሚሰግዱት ወይም አሳምረው የሚያደርጉት ሰዎች እንዲያዩላቸውና እንዲያደንቋቸው ብቻ ነው፤ የአላህን ውዴታ ፈልገው አይደለም።
### 3. ሰላትን ከወቅቱ ማዘግየት (تأخيرها عن وقتها)
ሰላት የመስገጃው ጊዜ አልፎ እስኪቃረብ ድረስ ሁል ጊዜ ማሳደር እና ማዘግየት፤ ለምሳሌ የዐስርን ሰላት ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል (ወደ ዳልቻ ስትቀይር) ማዘግየት።
### 4. ሰላትን ማጣደፍ (نقرها)
በሰላት ውስጥ የመረጋጋት (ጡማእኒናህ) እጥረት ማሳየትና በጣም ማጣደፍ። ነቢዩ ﷺ ይህንን ድርጊት "ቁራ መሬት ላይ እንደሚጭረው" (ንቅረል ጉራብ) በማለት መስለውታል። በዚህ አይነት ስግደት ውስጥ እውቅናም ሆነ ኹሹዕ (ተመስጦ) አይገኝም።
### 5. አላህን ማውሳት (ዚክር) ማነስ (قلة ذكر الله فيها)
ልብ ሳይገኝ (ሳይተኮር)፣ የቁርአን አንቀጾችንና ዚክሮችን ሳይገነዘቡ እንዲሁ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ብቻ ማድረግ።
### 6. የጀማዐ ሰላትን መተው (التخلف عن جماعتها)
ያለ ምንም (ሸሪዐዊ) ምክንያት እና አቅም እያላቸው የጀማዐ ሰላትን በመስጂድ ከመስገድ ወደ ኋላ ማለት።
> ኢማም እብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፡ "እነዚህ በሰላት ውስጥ የሚታዩ ስድስት ባህሪያት የንፍቅና (መናፍቅነት) ምልክቶች ናቸው።"
📚ኪታቡ አስ–ሰላት ገፅ(80)

❤10
ከቀደምት ደጋግ ሰዎች (ሰለፎች) አንዱ እንዲህ ብሏል፦
> "እጆቼን ወደ ላይ አንስቼ አላህን ስለምንና ዱዓዬን ሲመልስልኝ ደስ ይለኛል። ነገር ግን ዱዓዬን ካልመለሰልኝ ደስታዬ እጅግ የላቀ ይሆናል።"
>
"ለምን?" ተብሎ ሲጠየቅም እንዲህ ሲል መለሰ፦
> "ምክንያቱም እሱ (አላህ) የራሱን ፍላጎት ነው የሰጠኝ እንጂ እኔ የፈለግኩትን አይደለም። በእሱ ፍላጎትና ውሳኔ ላይ ያለኝ እምነት፣ እኔ ለራሴ መልካም ነው ብዬ ካሰብኩት በላይ ነው።"
>
ገባችሁ? አላህን አንድ ነገር ጠይቃችሁት ሳይመልስላችሁ ሲቀር፤ እወቁ፣ ከእናንተ ላይ አንድን መጥፎ ነገር እንዳራቀላችሁ። እሱ ባለው ጥበብና እውቀት፣ እናንተ ለራሳችሁ ያላያችሁትን መልካም ነገር ለእናንተ አይቶላችኋል።
እወቅ! በአላህ እዝነትና እውቀት የምታምን ከሆንክ፣ የደረሰብህ ነገር ሊስትህ እንደማይችልና የሳተህም ነገር ሊደርስብህ እንደማይችል እወቅ።

👍16❤7
ከኃጢአት ለመራቅ ከሚረዱህ ነገሮች አንዱ የአላህን ጸጋዎች ማስታወስ እና ማስተንተን ነው፤ ለመሆኑ የምታምጸው ማንን ነው?
አንተ የምታምጸው ሳትጠይቀው የረዘቀህን ፣ ነውርህን የሸፈነልህን፣ በሰዎች መካከል ያከበረህን እና በቁጥር ስፍር በሌላቸው በርካታ ጸጋዎች የከበበህን አላህን ነው።
አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦
> "የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትጨርሷትም፤ ሰው በእርግጥ በጣም በደለኛ ከሃዲ ነው፡፡" (ሱረቱ ኢብራሂም: 34)
>
እስቲ አስበው... በምድሩ ላይ ትኖራለህ፣ ከሲሳዩ ትመገባለህ፣ በጸጋዎቹ ውስጥ ትገለባበጣለህ፣ ከዚያም ታምጸዋለህ!
የአላህን ጸጋዎች ባስታወስክ ቁጥር፣ ልብህ እርሱን ለመታዘዝ ያፍራል፤ ይህ ፍርሃት ብቻ ሳይሆን፣ ለአላህ ካለህ ክብርና ሀፍረት የመነጨ ነው። አላህን በረሳህ ጊዜ ካመጽከው ደግሞ፣ ምሕረትን (ኢስቲግፋርን) አብዛ፣ ይቅርታውንና ምሕረቱንም ለምን።

👍12❤6👌2
:
### በአላህ መገለጫ ባህሪያት (ሲፋት) በተመለከተ ትልቅ መርሆ (ቃዒዳህ)
"ማስጠጋቱ (ኢዳፋህ) ከተለያየ፥ የባህሪያቱ ሁኔታ (ከይፊያህ) ይለያያል።"
ይህ ማለት አንድን ባህሪ ወደ አንድ አካል ስናስጠጋ እና ወደ ሌላ አካል ስናስጠጋ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ግልጽ ይሆናል፦
* የአላህ ፊት እና የፍጡር ፊት፦ "የአላህ ፊት" ስንል ወደ አላህ አስጠጋነው፤ "የፍጡር ፊት" ስንል ደግሞ ወደ ፍጡር አስጠጋነው። ማስጠጋቱ ስለተለያየ የአላህ ፊት በምንም መልኩ ከፍጡር ፊት ጋር አይመሳሰልም።
* የአላህ እጅ እና የፍጡር እጅ፦ ማስጠጋቱ የተለያየ ስለሆነ ፍጹም የተለያዩ ናቸው።
* የአላህ (ዐይን) እና የፍጡር አይን፦ በተመሳሳይ መልኩ ማስጠጋቱ ስለተለያየ አይመሳሰሉም።
* የአላህ ከዐርሽ በላይ መሆን (ኢስቲዋእ) እና የፍጡር በሆነ ነሀር ላይ መደላደል፦ ሁለቱም የተለያዩ ናቸው።
ይህንን ይበልጥ ለማስረዳት በዱንያ እና በጀነት መካከል ያለውን ምሳሌ ወስደናል። ለምሳሌ፦ የጀነት የቴምር ዛፍ እና የዱንያ የቴምር ዛፍ ስንል ስማቸው አንድ ቢሆንም፥ አንደኛው ወደ ጀነት ሌላኛው ወደ ዱንያ በመጠጋታቸው ምክንያት ሁነታቸውና ባህሪያቸው ፍጹም የተለያየ ነው። የጀነት ወንዞች እና የዱንያ ወንዞችም እንዲሁ።
> ዋናው መልዕክት (ማጠቃለያ)፦
> "ማስጠጋቱ (ኢዳፋህ) ከተለያየ፥ የባህሪያቱ ሁነታም ይለያያል።" አላህ ለእርሱ የሚገቡ የላቁ እና ምሉዕ ባህሪያት አሉት፤ ፍጡርም ለእርሱ የሚሆኑ ደካማ ባህሪያት አሉት። በመሆኑም የአላህ ባህሪያት ከፍጡራን ባህሪያት ጋር በፍጹም አይመሳሰሉም።

❤5👌3
የነቢዩን(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ሐዲስ መከተል በንፁህ ሸሪዓ ወሰኖች ላይ መቆም ነው። 🕯️
📜 የአላህ መላክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁንና) የዚህ ዘመን ጠማማ ጥሪ አቅራቢዎችን (አሳሳቾችን) ያስጠነቀቁበት ግልጽ የሆነ የነቢይነት ሙዕጂዛ፤ እንዲህ አሉ። «አንድ ሰው በአልጋው ላይ ተደግፎ እያለ፣ ከእኔ ከሆኑት ሐዲሶች አንዱ ተወርቶለት፡ "በእኛና በእናንተ መካከል የአላህ መጽሐፍ (ቁርአን) አለ.." የሚልበት ጊዜ ሊመጣ ተቃርቧል። ንቁ! የአላህ መላክተኛ እርም ያደረጉት ነገር አላህ እርም እንዳደረገው ሁሉ ነው።»
#የነቢዩ_ሱና

🥰3
‘#ቁርኣኒዩን" ትክክለኛ ስያሜያቸው
#منكروا_السنة
(#ሐዲስን_አስተባባዮች) ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ይህ አስተሳሰብ የሚመነጨው የሐዲስ ሊቃውንትን (የሙሐዲሶችን) ጥብቅ “ዒልሚይ” አካሄድ ከመረዳትና ከመከተል በመስነፍ፣ ወይም ሱና በዝርዝር ካስቀመጣቸውና የቁርኣንን አጠቃላይ ትዕዛዛት ካብራራባቸው ሸሪዓዊ ግዴታዎች ለመሸሽ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው።
አሚሩል ሙእሚኒን ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረ.ዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
"የግል አስተያየትን (አስሓቡር-ራእይን) ከሚከተሉ ሰዎች ተጠንቀቁ፤ እነሱ የሱና ጠላቶች ናቸውና። ሐዲሶችን መሸምደድና መረዳት ባሰለቻቸው ጊዜ በግል አስተያየታቸው ተናገሩ፤ በዚህም እራሳቸው ጠመሙ፣ ሌሎችንም አጠመሙ።"
📚ابن عبد البر في ((جامع بيان العلم وفضله)) (1123)

👍18
ሸይኽ ወሊድ አስ-ሱዓይዳን በጋራ (በአንድ ድምፅ) ዚክር ማድረግን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦
"አንድ ወቅት በአቅራቢያችን ከሚገኙ አገሮች በአንዱ ነበርኩ። ያኔ አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፦ *'እናንተ የሳውዲ አረቢያ ሰዎች ነቢዩ ፦ﷺ «ሰዎች በአላህ ቤቶች (መስጊዶች) ውስጥ ተሰብስበው አላህን ሲያወሱ...» ማለታቸውን እየወቃችሁ፣ እንዴት በጋራ (በአንድ ድምፅ) ዚክር ማድረግን ትቃወማላችሁ?'* አለኝ።
እኔም ነቢዩ ﷺ የተናገሩትን ይህንን ሐዲሥ እንደሚያጣቅስ ወዲያውኑ ገባኝ። ይህ ሐዲሥ በኢማም ሙስሊም የሐዲሥ መጽሐፍ ውስጥ ከአቡ ሁረይራ የተዘገበ ትክክለኛ (ሶሒሕ) ሐዲሥ ነው።
ለመሆኑ አንተ ብትሆን ለዚህ ሰው ምን ብለህ ትመልስለት ነበር? ሐዲሡ ትክክለኛ ስለሆነ 'ሐዲሡ ላይ ጥርጣሬ አለ' ማለት አትችልም። እርሱ ለራሱ አመለካከት ከሱና ማስረጃ አቅርቧል።
እኔም እንዲህ አልኩት፦ 'ይህ ሐዲሥ በዕውቀትም ሆነ በተረካቢነት ከእኔም ከአንተም ለበለጡት (ለሰሐባዎች) አልደረሰም ነበርን?'
እርሱም፦ *'ሰሐባዎችን ማለትዎ ነውን?'* አለኝ። 'አዎ' አልኩት።
እርሱም፦ *'አዎ፣ ደርሶዋቸዋል'* አለኝ።
እኔም፦ 'ታዲያ ሰምተውት ተረድተውታል ወይስ ሰምተውት አልተረዱትም?' አልኩት።
እርሱም፦ *'አይ፣ ሰምተውት ተረድተውታል'* አለ። (ምክንያቱም ሌላ ራፊዳ(ሺኣ) ሰው በስተቀር ማንም ሰሐባዎች አልተረዱትም ሊል አይችልም)።
እኔም፦ 'እሺ፣ እነርሱ ይህንን ሐዲሥ ሰምተውትና በልባቸው ይዘውት እያለ፣ በተወሰነ ጊዜ ተሰብስበው፣ ከበሮና የመሳሰሉትን እየመቱ፣ ራሳቸውን እየወዘወዙና በአንድ ላይ ድምፃቸውን አስተካክለው (በአንድ ድምፅ) ዚክር ያደርጉ እንደነበር ከእነርሱ የተላለፈ አንድም ነገር አለን?' አልኩት።
መልሱ፦ የለም፣ ከእነርሱ የተላለፈ ምንም ነገር የለም።
በመቀጠልም እንዲህ አልኩት፦ 'እንግዲህ አንተ የተረዳኸው መረዳት እነርሱ ከተረዱት ውጪ ነው። ይህ አንተ የምታደርገው ነገር ትክክለኛ አምልኮ ቢሆን ኖሮ፣ በዚህ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ለምትገኘው ለአንተ ተገልጦ፣ ከእኔና ከአንተ በዕውቀት፣ በግንዛቤ በነቢዩ ﷺ
ንግግር መረዳት ከበለጡት ከሰሐባዎች ሊሰወር አይችልም ነበር።' በዚህ ጊዜ እርሱ ምንም ሊመልስልኝ አልቻለም።"

👍11❤6