telebirr
✔
338K subscribers
7.67K photos
210 videos
122 files
2.88K links
Download Telegram
ሦስተኛው የዲጂታል ቅዳሜ መድረክ ተካሄደ!

ኩባንያችን ከ Urban Center ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ሦስተኛው የዲጂታል ቅዳሜ መድረክ በዲጂታል ክፍያዎች፣ በዲጂታል ፋይናንስ አማራጮች እና በደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ተካሄዷል።

ቀደም ሲል በ Home Connectivity እና በዲጂታል ደኅንነት ዙሪያ የተካሄዱ ውጤታማ መድረኮችን ተከትሎ የተዘጋጀው ይህ መርኅ-ግብር፤ የኩባንያችንን የዲጂታል ፋይናንስ መፍትሔዎች ለማስተዋወቅ፣ ከደንበኞቻችን ጋር በቀጥታ ለመወያየት እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቶችን ግንዛቤና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምቹ ዕድል ፈጥሯል።

ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም አካታች፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የዲጂታል ፋይናንስ ሥነ-ምኅዳርን በመገንባት የደንበኞቻችንን የዕለት ተዕለት ሕይወት ለማቅለል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል!

መድረኩ ላይ በመገኘት ገንቢ ሀሳባቸውን፣ ተሞክሯቸውንና ዕውቀታቸውን ላካፈሉ ተሳታፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ክቡራን ደንበኞቻችን የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

#Ethiotelecom #UrbanCenter #DigitalSaturday #telebirr #DigitalPayments #DigitalFinancialSolutions #CustomerExperience #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
❤24👍7🙏2
💸 በ35 ብር የ2 ሰዓት ያልተገደበ ዳታ ጥቅል ገዝተው ከወዳጅዎ ጋር በቪዲዮ ኮል መደዋወል ይችላሉ!

📲 በ*999#፣ በአርዲ ቻትቦት ወይም በማይ ኢትዮቴል ይግዙ!

🎁በቴሌብር https://onelink.to/telebirr ሲገዙ ቅናሽ ያገኛሉ!

#2HoursUnlimitedPackages
#Ethiotelecom
#telebirr
#DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
❤35👍17😁7🤩2