Times መረጃ | Times Mereja
120K subscribers
1.97K photos
58 videos
224 links
ያልቀዘቀዙ ትኩስ መረጃዎች።

በዚህ ያግኙን ፡ https://t.me/TimesMereja
Download Telegram
በትግራይ ክልል የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት የባንክ፣ የኤቲኤም፣ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር ሙሉ በሙሉ ከመቋረጡ ጀርባ ያለው ማን ነው?

በትግራይ ክልል ሐሙስ ምሽት ከ4 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ጀምሮ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ተደርጓል የቴሌኮም አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ጫና ያደረጉት የቀድሞው የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ ቃል አቀባይና የአሁኑ የሚዲያ ጉዳዮች ኃላፊ ገብረ ገብረጻድቅ (ገብረ አዴት) እንዲሁም የትግራይ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ገብረስላሴ መሆናቸው ታውቋል።

የኔትወርክ አገልግሎቱን የማቋረጥ ጥረት ከማክሰኞ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም ቴክኒሻኖች አገልግሎቱን ከመቀሌ ማቋረጥ እንደማይቻል እና ከአዲስ አበባ መከናወን እንዳለበት ምላሽ ሰጥተው ነበር። ይህን ተከትሎ ባለስልጣናቱ ወደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በማምራት ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ የኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎችን ግን ከማክሰኞ ጀምሮ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።

ምንጮች እንዳመለከቱት የታሰሩት ባለሙያዎች ሐሙስ ምሽት ላይ የሞት ዛቻ ተሰጥቷቸው ወደ ቴክኒክ መቆጣጠሪያ ክፍል እንዲገቡ የተገደዱ ሲሆን፣ ምክትል ኮሚሽነር ገብረስላሴ በላይም አንዱን ባለሙያ ማስፈራራታቸው ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ሂደቱ ጥቂት ሰዓታት እንደሚወስድ ከገለጹ በኋላ በዚያው ምሽት አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል። የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡን ተከትሎ ተጠቃሚዎች መደወልም ሆነ የኢንተርኔት መልዕክቶችን መጠቀም ያልቻሉ ሲሆን፣ ይህም በክልሉ የሚገኙ የባንክ፣ የኤቲኤም፣ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል መፍጠሩ ተመላክቷል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤14👍4
የኤርትራ ጦር ድንበር ጥሶ ሰፊ የአፋር መሬት መቆጣጠሩን አቶ አወል አርባ አስታወቁ

የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ጥሶ በመግባት በክልሉ ዞን ሁለት ሥር የሚገኙ ሰፊ ቦታዎችን መቆጣጠሩን የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ለአልጀዚራ በሰጡት ቃል ገለጹ። አቶ አወል በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ውጥረት ከተቀሰቀሰ ወዲህ አስመራን በቀጥታ ወረራ በመፈጸም በይፋ የከሰሱ የመጀመሪያው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ሆነዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳስታወቁት የኤርትራ ኃይሎች የእረብቲ ከተማን ጨምሮ በዞን ሁለት ሥር የሚገኘውን ሁለት ሦስተኛ ወይም ወደ 36 ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር የሚጠጋውን የአፋር መሬት ተቆጣጥረዋል። በተጨማሪም ኃይሎቹ ወደ አፍዴራ ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤርትራ እና ጅቡቲ የሶስትዮሽ ድንበር አቅጣጫ እየገሰገሱ መሆናቸውን ጠቁመው ድርጊቱ ድንበርን በኃይል የመቀየር ስትራቴጂካዊ ዓላማ ያለው መሆኑን አመልክተዋል።

የኤርትራ ሠራዊት ይህን ያህል ርቀት ዘልቆ የገባበት ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር እና ወደ ዓሰብ ወደብ ለመድረስ ያላትን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እንደሆነ ተናግረዋል። ኃይሎቹ ወደፊት መግፋታቸው ኢትዮጵያ ወደ ወደቡ ለመድረስ የነበራትን የ90 እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደ 200 እና 300 ኪሎ ሜትር በማስፋት የባሕር በር ፍላጎቷን የማደናቀፍ ስሌት ያለው መሆኑንም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል፣ ከዚህ ቀደም በትግራይ ጦርነት ወቅት ክልሉን ደግፈው የነበሩ አንዳንድ ኃይሎች አሁን ላይ አቋማቸውን በመቀየር በአፋር ላይ ጥቃት እንደከፈቱ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ውጊያ ከአካባቢው የጸጥታ መዋቅር አቅም በላይ የሆነ «ተመጣጣኝ ያልሆነ ጦርነት» ነው ሲሉ ገልጸውታል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤9🙉1
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ባገረሸው ግጭት ጎረቤት አገራት ጣልቃ እንዳይገቡ ዴንማርክ አሳሰበች።

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ውጥረት እጅግ እንዳሳሰባት ያስታወቀችው ዴንማርክ ጎረቤት አገራት ግጭቱን ይበልጥ ከማባባስ እና ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠች።

የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው መግለጫ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ እየታየ ያለው የጸጥታ መበላሸት አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሶ፣ ሁሉም ወገኖች ውጥረቱን በአስቸኳይ እንዲያረግቡ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። መግለጫው አክሎም፣ ጎረቤት አገራት ሁኔታውን ከማባባስ እንዲታቀቡ በማሳሰብ፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እና በአፍሪካ ኅብረት የሚመራው የሽምግልና ጥረት ለቀጣይ ሰላም ብቸኛው መፍትሔ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥቷል።

ይህ የአውሮፓዊቷ አገር ማሳሰቢያ የተደመጠው፣ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደ ኤርትራ እና ሱዳን ያሉ ጎረቤት አገራት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎች ድጋፍ በመስጠት ቀጠናውን እያተራመሱ ነው ሲሉ ከሰሱትን መግለጫ ተከትሎ ነው። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ውጊያ ወደ ሙሉ ቀጠናዊ ጦርነት እንዳያመራ ስጋቱን እየገለጸ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ዴንማርክ ጎረቤት አገራት ከጣልቃ ገብነት እንዲታቀቡ ያስተላለፈችው ጥሪ ተፋላሚዎች ወደ ሰላም ንግግር እንዲመለሱ የሚደረገውን ዓለም አቀፍ ግፊት የሚያጠናክር ሆኗል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤11👍10
የፓርላማ አባሉ በግብጹ ሚዲያ የተፋጠጡበት የሰሞኑ የፊማ ብርሃኑ ጁላ ጠንካራ ክስ። ፊማ ብርሃኑ ጁላ ግብጽ ሱዳን እና ኤርትራን ታጣቂ ሀይሎችን እየረዱ ነው ሲሉ ከሰሞኑ በይፋ ጠንካራ ክስ ማቅረባቸው ይታወሳል ሱዳን በይፋ ምላሽ ብትሰጥም ኤርትራ እና ግብጽ ግን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መርጠዋል ሆኖም ግን ታዋቂው የዓረብኛ የዜና አውታር አል አረቢያ ‘ካሪጅ አል-ሱንዱቅ’ በተሰኘው ፕሮግራሙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉን አቶ መሐመድ አል-አሩሲን በመጋበዝ በፊ/ማ ብርሃኑ ጁላ ንግግር ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጋብዞት ነበር።

በዚህም የፕሮግራሙ አዘጋጅ ናይፍ አል-አሕመሪ የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊ/ማ ብርሃኑ ጁላ በጎረቤት ሀገራት ላይ ላቀረቡት ከባድ ወታደራዊ ክስ ማረጋገጫ የሚሆን ተጨባጭ ማስረጃ ለምን ይፋ እንዳልተ

የፓርላማ አባሉ አቶ መሐመድ አል-አሩሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊ/ማ ብርሃኑ ውንጀላውን ያቀረቡት በዘፈቀደ ሳይሆን በእጃቸው ባለው ተጨባጭ የደኅንነት መረጃ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል። ወታደራዊና የደኅንነት መረጃዎች የሚዲያ ፍጆታ ባለመሆናቸው ኢታማዦር ሹሙ ማስረጃውን በተገቢው ቦታና ወቅት ይፋ እንደሚያደርጉት የተናገሩት አቶ መሐመድ፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ለቀረበው ክስ ግልጽ ማሳያ እንደሆነ አስረድተዋል።

በተለይም በሱዳን ድንበርና በተለያዩ ከተሞች ተደራጅተው ኢትዮጵያን የሚያስፈራሩ የህወሓት ታጣቂዎች የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ ማድረጋቸው፣ እንዲሁም ግብፅ የሚዲያ ተቋሞቿን ተጠቅማ ፀረ-ኢትዮጵያ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላትን በማስተናገድ የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ የምታደርገው እንቅስቃሴ ክሱን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ አመልክተዋል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤15
ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚገኙ ከ3 ሺህ በላይ ወታደሮቿን ወደ ሀገር ቤት ልትመልስ መሆኑ ተገለጸ

ትናንት በስፋት የተሰራጨውን "ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ (አውሶም/AUSSOM) ስር ያልተካተቱ የሰራዊት አባላቷን ከሶማሊያ ልታስወጣ ነው" የሚለውን መረጃ ዛሬ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ጭምር በስፋት እየዘገቡት ይገኛሉ። በአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ያልተካተቱ ቁጥራቸው ከ3 ሺህ በላይ የሚሆን የሰራዊቱ አባላት በቀጣዮቹ ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ከሶማሊያ እንደሚወጡና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ወዳለባቸው የሰሜኑ አካባቢዎች ማለትም በአማራ፣ በትግራይና በአፋር ክልሎች ሊሰማሩ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደገለጹት ከሆነ የጠሚ አቢይ አሕመድ አስተዳደር በሀገር ውስጥ ከተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች ጋር እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለመመከት ወታደራዊ አቅሙን ወደ ሀገር ውስጥ ለማዞር ተገድዷል። በዚህም መሠረት በሶማሊያ ባይ ባኮል እና ሒራን ክልሎች ተሰማርተው የነበሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በቅርቡ አካባቢዎቹን ለቀው ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ታውቋል። እስካሁን ባለው ሁኔታ፣ ስለተባለው የወታደሮችን የማስወጣት እቅድ ከኢትዮጵያም ሆነ ከሶማሊያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫም ሆነ ማረጋገጫ የለም።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤13😁2💔1
የመከላከያ ሠራዊት የመልሶ ማጥቃት እና የትብብር ኃይሎች የድሮን ጥቃት ሙከራ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ መቀሌ የሚያደርገው ግስጋሴ እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል፤ አሁን ላይ ሠራዊቱ በሦስት አቅጣጫዎች ወደ መቀሌ እያመራ ነው። መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ኢትዮጵያ በትብብሩ ኃይሎች የተከፈተውን መጠነ-ሰፊ ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመመከት በህወሓት ስር ወደምትገኘው የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ አቅጣጫ በሦስት ግንባሮች የተቀናጀ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ከፍቷል።

ትናንት ድንገት ብቅ ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫ፣ የወቅቱ የውጊያ ስልታቸው ከዓመታት በፊት እንደነበረው ፊት ለፊት ቆሞ የመፋለም ሳይሆን «ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልት» መሆኑን ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ በመግለጫቸው ላይ "አላማጣ ላይ እየተዋጋን እንገኛለን" ማለታቸው መግለጫው አስቀድሞ የተቀረጸ መሆኑን ግልጽ ማሳያ ሆኗል ምክንያቱም አላማጣ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከዋለች ሁለት ቀናት አልፈዋታል።

በተያያዘም መሬት ላይ ሽንፈት የገጠማቸው የትብብር ኃይሎች ድሮንን በስፋት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። ‹የትብብር ለህልውና› የተሰኘው ጥምረት የመከላከያ ሠራዊቱን ኃይል ለመበታተን፣ ትኩረቱን ለመከፋፈል እና ግጭቱን ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የማስፋፋት አቅም እንዳላቸው ለማሳየት በማሰብ በመላ አገሪቱ፣ በተለይም በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ጭምር ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት ዘመቻ ከፍቷል።
ይሁን እንጂ መከላከያ ሠራዊቱ መቀሌ የሚያደርገውን የማጥቃት ዘመቻ በተያዘለት እቅድ መሰረት እያስቀጠለ ይገኛል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤19👍1🕊1
ጀነራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ካቀረበላቸው የኡጋንዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ለማሰማራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።

አነጋጋሪው የኡጋንዳ ጦር ኃይል ከፍተኛ አዛዥ ጀነራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እና ጥያቄ ከቀረበላቸው ሠራዊታቸውን በኢትዮጵያ በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ ለማሰለፍ ፈቃደኛ መሆናቸውን በተለመደው የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ኤክስ/ትዊተር ላይ አስፈረዋል።
ጀነራሉ ባጋሩት መልዕክት “በዚህ የቅርብ ጊዜ ግጭት የኢትዮጵያ ወንድሞቻችንን ለመደገፍ ቆርጠን ተነስተናል። የኢትዮጵያ አመራር የእኛን እገዛ ከጠየቀ የማይበገረውን የኡጋንዳ ሕዝቦች መከላከያ ሠራዊት (UPDF) እናሰማራለን” ሲሉ በግልጽ አስታውቀዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በይፋ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ፣ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ሲገልጹ የቆዩት እና በኢትዮጵያ የኡጋንዳ ኤምባሲ አምባሳደሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጋር ስለ ወቅታዊው ሁኔታ ገለጻና ውይይት የተደረገላቸው የፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ልጅ ጀነራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ፣ አሁን ባጋሩት ጽሑፍ የኢትዮጵያ መንግሥት ፍላጎት ካለው እና ጥያቄ ካቀረበ ኡጋንዳ ወታደሮቿን ለመላክ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ጀነራል ሙሆዚ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚያጋሯቸው ያልተለመዱ እና ቀጥተኛ ፖለቲካዊ አስተያየቶች በምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ በተደጋጋሚ መነጋገሪያ የሚሆኑ ግለሰብ ናቸው። ቀደም ሲል በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት የመጀመሪያ ወቅት ለትግራይ ኃይሎች (ሕወሓት) ድጋፍ የሚመስሉ እና የፌደራል መንግሥቱን አካሄድ የሚተቹ መልዕክቶችን በማጋራታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከበርካታ ታዛቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና አለመግባባት አስከትለው ነበር።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
😁14❤12
መከላከያ መቀሌ ለመግባት ተቃርቦ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሕወሓት አመራሮችና ታጣቂዎች መቀሌን መልቀቅ መጀመራቸው እና በከተማዋ ዝርፊያ መባባሱ ተገለጸ።

የመከላከያ ሠራዊቱ ወደ መቀሌ ለመግባት መቃረቡ የተሰማ ሲሆን ከመቀሌ ከተማ መግቢያ በስተደቡብ የሚገኘውን ኤርፖርት ጨምሮ በትግራይ የሚገኙ ኤርፖርቶችን መንግሥት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠርና መደበኛ በረራዎች ሊመለሱ እንደሚችሉ ተመላክቷል።
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ወደ መቀሌ እየገሰገሱ ባሉበት በዚህ ወቅት የሕወሓት ታጣቂዎችና አመራሮች ከተማዋን ለቀው እየወጡ ይገኛሉ። ምንም እንኳን የፌደራል ሠራዊቱ እስካሁን በከተማዋ እምብርት ውስጥ ባይታይም፣ የመንግሥት ቢሮዎች እና የፖሊስ ጣቢያዎች ያለምንም ጥበቃና የጸጥታ ኃይል ክፍት ሆነው ቀርተዋል።
ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ በመቀሌ ከተማ የጸጥታ ኃይሎች በግዳጅ ላይ ባለመሆናቸው ምክንያት ዝርፊያ በከፍተኛ ደረጃ መባባሱ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የመንግሥት ተቋማት አስተዳደራዊ ቢሮዎች እና የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለከፋ ዘረፋ ተጋላጭ ሆነው እንደሚገኙ ተጠቁሟል። ሁኔታው ያሳሰባቸው ነዋሪዎችም ሕገ-ወጥነት እንዳይሰፋፋ እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ፈጣን የሆነ የሕግና ሥርዓት መከበር እንዲሰፍን ጠይቀዋል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤12👍3
የመከላከያ ሠራዊት ልዩ የኮማንዶ ክፍሎች መቀሌ ከተማ መግባታቸው ታውቋል ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ልዩ የኮማንዶ ኃይል ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ መግባቱ ታውቋል። ሠራዊቱ ወደ ከተማዋ የገባው ያለምንም ውጊያ እና ተኩስ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ሳይስተጓጎል መቀጠሉ ተዘግቧል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት በመቀሌ ከተማ "የትብብር ለህልውና ኃይሎች" በሚል አዲስ ጥምረት በይፋ መመስረቱ መገለጹን ተከትሎ፣ የፌደራል መንግሥቱ በተመረጡ ኢላማዎች ላይ ተከታታይ የአየር ላይ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።

የአየር ጥቃቱን ተከትሎ በራያ እና በአፋር አቅጣጫዎች በእግረኛ ሠራዊት መካከል ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ የሰነበተ ሲሆን፣ የፌደራል ሠራዊቱ በአፋር በኩል ወደ ክልሉ መግባቱ ታውቋል። በራያ ግንባር በኩል እስከ ማይጨው ከተማ ድረስ ያለው አካባቢ አሁንም በከፊል ውጥረት እና ቁጥጥር ስር ያለ ቢሆንም፣ የኮማንዶ ኃይሉ ወደ መቀሌ ከተማ እንዲገባ መንገድ የከፈቱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መካሄዳቸው ተመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከነበሩት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በተለየ መልኩ የሠራዊቱ መቀሌ መግባት በነዋሪው ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤ አለመፍጠሩ ታውቋል። የከተማዋ መንገዶች ክፍት ሆነው የሚገኙ ሲሆን የባጃጅ ትራንስፖርትን ጨምሮ ሌሎች የንግድ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ሳይቆራረጡ እንደቀጠሉ መሆኑን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።
የመከላከያ ሠራዊት ወደ ከተማዋ እየተቃረበ መምጣቱን ተከትሎ፣ የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣ የጦር አዛዦች እንዲሁም የከተማዋ የፀጥታ ኃይሎች ባለፉት ጥቂት ቀናት መቀሌን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። ይህም የመከላከያ ሠራዊቱ ልዩ የኮማንዶ ክፍል ያለምንም ውጊያ እና የከፋ ግጭት ከተማዋን እንዲቆጣጠር ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የመከላከ
❤11👍7👏2
አሜሪካ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት አስመልክቶ ጠንካራ መግለጫ አወጣች።

ሁለቱ አገራት ኤምባሲዎቻቸውን በዘጉ እንዲሁም አምባሳደሮቻቸውንና ዲፕሎማቶቻቸውን ከየአገራቱ ባስወጡበት ወቅት፣ አሜሪካ ነገሮች በዚህ ከቀጠሉና ሁኔታዎች ካልተለወጡ ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ በመጠቆም በቃል አቀባይዋ በኩል ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቶማስ ፒጎት ባወጡት ይፋዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር አካባቢ እየተባባሰ የመጣው አለመግባባት መላውን ቀጣና የማወክ ከፍተኛ አቅም አለው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም የአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ ወታደራዊ ግጭትንም ሆነ ሰብዓዊ ቀውስ የመሸከም አቅም እንደሌለው በግልጽ አስገንዝበው እየተፈጠረ ያለው አለመረጋጋት ዋሽንግተን ከሁለቱም አገራት ጋር በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ እያከናወነች ያለችውን ትብብር አደጋ ላይ እንደሚጥለው የገለጸው መግለጫው አሜሪካ ሁለቱም ወገኖች የጎረቤቶቻቸውን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርባለች።

በተጨማሪም ኢትዮጵያና ኤርትራ ከፍተኛ ራስን የመግዛት እርምጃ እንዲወስዱ፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ2018 በተፈረመው የሰላም ማዕቀፍ መሠረት ወደ ውይይትና ትብብር እንዲመለሱ ዋሽንግተን በጥብቅ አሳስባለች። በመግለጫው ማጠቃለያ ላይም «ዘላቂ ጸጥታን የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ በውይይት የሚገኝ ሰላም ብቻ ነው» ሲሉ ቃል አቀባዩ አስምረውበታል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤12
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዓድዋ ከተማ ሆቴሎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተዘገበ

የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራሮች መቀሌን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ይገኙበታል ተብለው ከሚጠረጠሩባቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መካከል አንዷ በሆነችው የዓድዋ ከተማ ላይ የመከላከያ ሠራዊቱ የአየር ኃይል ዛሬ ምሽትም ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን ፈጽሟል።

እንደተገኘው መረጃ ከሆነ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በምትገኘው በዚሁ የዓድዋ ከተማ ላይ ዛሬ ምሽት እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በትንሹ አራት የድሮን ጥቃቶች ተፈጽመዋል። የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት የፈጸማቸው እነዚህ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች እና የሕዝብ አገልግሎት መስጫ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ እንደነበሩ ተጠቁሟል።

ይህ እርምጃ የተወሰደው በክልሉ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ በተለይም የህወሓት አመራሮችና ወታደራዊ ይዞታዎች ያሉባቸውን አቅጣጫዎች ዒላማ ያደረገ የአየር ላይ ክትትል እና እርምጃ ተጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል። በዚህ የዛሬ ምሽት ጥቃት የደረሰውን ዝርዝር የሰው እና የንብረት ጉዳት መጠን በተመለከተ እስካሁን በይፋ የወጣ መረጃ የለም።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤11👍4🕊2
በዓድዋ ከተማ በሶሎዳ ሆቴል ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የዶ/ር ደብረጽዮን ጠባቂዎችን ጨምሮ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ከመቐለ ከተማ መውጣታቸውን ተከትሎ በዓድዋ ከተማ በሚገኘው "ሶሎዳ ሆቴል" ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ዘግይተው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ዒላማ ያደረገ ነበር። በጥቃቱ ወቅት የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በሆቴሉ ውስጥ ስለመኖራቸው እስካሁን በይፋ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፣ የእርሳቸው ጠባቂዎች ግን በዚሁ የድሮን ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።

በጥቃቱ በአጠቃላይ የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የታጠቁ የጥበቃ አባላት መሆናቸው ታውቋል። ቀሪዎቹ ሦስቱ በወቅቱ በሆቴሉ ያረፉ/ሲስተናገዱ የነበሩ ሲቪሎች ሲሆኑ፣ ከጥቃቱ በኋላ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ቅጽበት ዶ/ር ደብረጽዮንን ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ከፍተኛ ኃላፊዎች በሆቴሉ ስለመኖራቸው እስካሁን የወጣ ይፋዊ መረጃ የለም።
የዘገባው ዳራ (የመከላከያ ሠራዊት የአየር ኃይል እሁድ ለሰኞ አጥቢያ በዓድዋ ከተማ ሆቴሎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ከ4 ጊዜ በላይ ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ይህም እርምጃ አመራሮቹ ያሉባቸውን አቅጣጫዎች ዒላማ ካደረገ የአየር ላይ ክትትል ጋር ተያይዞ የተወሰደ መሆኑ ተገልጿል።)

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤11
ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኤርትራ ሰራዊት ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ዘልቆ መግባቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተረጋገጠ ቢሆንም፣ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት በኤርትራ ላይ ጦርነት ለመክፈት ሰበብ እየፈለገ ይገኛል ሲሉ አስታውቋል።
ከሳምንታት በፊት በአፋር ክልል ዞን ሁለት አካባቢዎች ከታየው ሰፊ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በተጨማሪ አሁን ላይ በዛላምበሳ ድንበር በኩል የገቡ በርካታ የኤርትራ ወታደራዊ ኮንቮዮች በዓዲግራት፣ በዕዳጋ ሓሙስ እና በውቅሮ በኩል በግልጽ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የአይን እማኞች እንደሚገልጹት፤ ከባድ የጦር መሣሪያዎችንና ፀረ-አውሮፕላን ተሽከርካሪዎችን የጫኑ ከ40 እስከ 60 የሚደርሱ ወታደራዊ የጭነት መኪኖች በደቡባዊ ትግራይ አቅጣጫ ሲንቀሳቀሱ ተስተውለዋል።

ይሁን እንጂ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በኤርትራ ላይ የሚቀርቡት ውንጀላዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ሊከፍተው ላሰበው የጥቃት ጦርነት "ራስን የመከላከል" ሽፋን ለመስጠት ሆን ተብለው የተፈበረኩ ናቸው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
አቶ የማነ ጨምረውም የኢትዮጵያ ገዥ አካል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የጦርና የፖለቲካ አመራሮች ድረስ በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት የጦርነት ከበሮ ሲደልቁ መቆየታቸውን ገልጸዋል። የዚህም ዋነኛ ዓላማ "ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት" እና በደቡባዊ የኤርትራ የባህር ዳርቻዎች ላይ "የባህር ኃይል መገኘትን" እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑን አመልክተዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ፣ በአካባቢው አዲስ መጠነ-ሰፊ ቀጣናዊ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለው ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

@times_mereja
❤8🕊1🙉1
"የኤርትራ ጦር በአፋጣኝ ለቆ እንዲወጣ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ መብቷ የተጠበቀ ነው" ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ የያዛቸውን አካባቢዎች በአፋጣኝ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣ እጅግ ጠንከር ያለ አስቸኳይ ማሳሰቢያ አስተላለፉ። ሚኒስትሩ ባስተላለፉት በዚህ ያልተለመደ ጠንካራ መልእክት አስመራ ጦሯን የማታስወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ሙሉ መብት ያላት መሆኑን በጽኑ አረጋግጠዋል። ይህም አገሪቱ ድንበሯን ለማስከበር ወደ ቀጥተኛ እርምጃ ለመግባት እንደማታመነታ ግልጽ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ዶ/ር ጌዲዮን ይህን ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሐመድ ጋር ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ወቅት ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኤርትራ ግልፅ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እና ትንኮሳ ፈጣን እና ግልጽ ምላሽ እንዲሰጥም በይፋ ጠይቀዋል።

የዶር ጌዲዮን እና የተመድ ተወካዮ ውይይት የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊት ይፋ በማድረግ ያስቀመጠው አቋም ዲፕሎማሲያዊ አማራጮች ፈጣን ምላሽ ካላገኙ ድንበሯን በኃይል የማስከበር እርምጃ ሊከተል እንደሚችል የተሰጠ የመጨረሻ ግልፅ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተገምግሟል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤21👍9🕊2
የሱዳን መከላከያ ሠራዊት “ኢትዮጵያ ለፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) የጦር ካምፕ ሰጥታለች፣ ድሮኖችንም በእኛ ላይ ታዘምታለች” በሚል በኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ውንጀላዎችን ካቀረበ በኋላ በተጨባጭ ግን እራሱ ህወሓትን በላቀ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ እና ሎጅስቲክስ እያስታጠቀ መሆኑን የሚያጋልጡ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ ሆነዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በቅርቡ ከህወሓት እጅ የማረከው የቱርክ ሰራሹ ‘Sivrisinek S-389’ ካሚካዜ ድሮን የመረጃዎቹ ማረጋገጫ ሆኖ የቀረበ ሲሆን፣ አሁን የወጡት ይፋዊ ወታደራዊ ሰነዶችም ትስስሩን ይበልጥ አጋልጠውታል።

በቅርቡ የተገኙ ሰነዶች የሱዳን ጦር ከፍተኛ አመራሮች በቀጥታ የተሳተፉበት ስምምነት መኖሩን ያሳያሉ። ከወጡት ሰነዶች አንዱ ከሱዳን ጦር ጠቅላይ የወጣ እና “ሚስጥራዊ/የተከለከለ” የሚል ማህተም ያረፈበት ይፋዊ ደብዳቤ ነው። ደብዳቤው በሱዳን ጦር የሞባይል ኦፕሬሽን ድጋፍ አዛዥ ስም በሌተና ኮሎኔል መሀንዲስ አህመድ አደም አህመድ ተፈርሞ “ለሚመለከተው አካል ሁሉ” የተጻፈ ሲሆን፣ ለእንቅስቃሴው አገልግሎት የሚውሉ የቶዮታ ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን የይለፍ እና የባለቤትነት ፈቃድ የሚሰጥ የሎጅስቲክስ ድጋፍ ማረጋገጫ ነው።

ከዚህም ባሻገር የወጣው ሁለተኛው የወታደራዊ ስምምነት ዝርዝር ደግሞ የሱዳን ጦር ለህወሓት ያቀረባቸውን እጅግ ዘመናዊ የድሮን መገጣጠሚያ እና የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂዎችን ያካተተ ነው። ከተዘረዘሩት ቁልፍ ወታደራዊ ቁሳቁሶች መካከል የድሮን አቅጣጫ ጠቋሚ ፣ የጠላት ጃሚንግ መከላከያ ሲስተሞች የከፍታ መለኪያ ሌዘር ሴንሰሮች ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የቪዲዮና ዳታ ማስተላለፊያ እና መቀበያ መሬት ላይ የሚተከሉ ሲስተሞች ፣ እንዲሁም የድሮን ባትሪዎችና የአየር ላይ ካሜራ መቆጣጠሪያዎች ይገኙበታል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤11
ተመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያገረሸው ውጊያ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቀ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች ግጭቱን ባስቸኳይ በማቆም ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሐፊው ትናንት ዓርብ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም በቃል አቀባያቸው በኩል ባወጡት ይፋዊ መግለጫ በትግራይ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በድጋሚ ባገረሸው ግጭትና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ላይ "ጥልቅ ሥጋት" እንዳደረባቸው አስታውቀዋል።
የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረሙ አካላት በስምምነቱ ማዕቀፍ ሥር ወደ ንግግር እንዲመለሱ ያሳሰቡት ጉቴሬዝ ግጭቱ እየተባባሰ ከሄደ መላውን የቀጠናውን መረጋጋት አደጋ ላይ እንደሚጥል አስጠንቅቀዋል።
ዋና ጸሐፊው በመግለጫቸው ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ውጊያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲያቆሙ እና ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ስለመገኘታቸው የሚወጡ ዘገባዎች እንዳሳሰቧቸው የገለጹት ዋና ጸሐፊው የቀጠናው አገራት የተመድ ቻርተርን በማክበር የሌሎች አገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዳይጋፉ አሳስበዋል።በተፋላሚ ወገኖች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉ አገራትና አካላት ውጥረቱን ለማርገብ እንዲረዱ እንዲሁም ሁኔታውን ይበልጥ ከሚያባብስ ማናቸውም ድርጊት እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤6
«የኢትዮጵያን ምድር ለቆ ካልወጣ የከፋ ክንድ ይጠብቀዋል» — ጀነራል ባጫ ደበሌ

የኤርትራ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበር ጥሶ አዲግራትን በማለፍ እስከ ኢዳጋ ሐሙስ ድረስ ዘልቆ መግባቱንና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዘመናዊ ክንድ ከባድ ምት እንደደረሰበት ጀነራል ባጫ ደበሌ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
ጀነራል ባጫ በይፋዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ በአርባዎች በሚቆጠሩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የተንቀሳቀሰው የኤርትራ ጦር ከድሮን ጥቃት ራሱን ለመሰወር ተሽከርካሪዎቹን በቅጠላ ቅጠል ሸፍኖ መንቀሳቀሱን ገልጸዋል። ይህንን አካሄድ የቴክኖሎጂውን ዘመን ያላገናዘበ «የድንጋይና የአናሎግ ዘመን አስተሳሰብ» ሲሉ የጠሩት ጀነራሉ ሠራዊቱ ያደረገው የመሰወር ጥረት ሳይታደገው በኢትዮጵያ ሰራዊት ዘመናዊ አቅም መመታቱን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንኑ የድንበር ጥሰት አስመልክቶ በሳተላይትና በቪዲዮ የተደገፉ አሳማኝ ማስረጃዎችን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማቅረቡን ያሳወቁት ጀነራል ባጫ የኤርትራ መንግሥት ግን እውነታውን በመካድ «ኢትዮጵያ ለባህር በር ስትል ልትወረኝ ነው» በሚል የሀሰት ሰበብ ጥሰቱን ለማስተባበል መሞከሩን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ጀነራል ባጫ ደበሌ ባስተላለፉት ጠንካራ ማስጠንቀቂያ የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ምድር በአስቸኳይ ለቆ ካልወጣ በኢዳጋ ሐሙስ ከገጠመው በላይ እጅግ የከፋ ወታደራዊ ምት እንደሚጠብቀው በጥብቅ አሳስበዋል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
❤24👍6
🇪🇹

በአዲስ አበባ የተቋቋመውና አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን ያካተተው «የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» ክልሉን በጊዜያዊነት ለመረከብና ለማስተዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የፌደራል መንግሥት ሳይቀበለው መቅረቱ ታውቋል።
ምክር ቤቱ ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው ህወሓት መቀሌን ለቆ ከወጣ በኋላ የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት በሚል ፤ አምስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪል ማኅበራትንና ታጣቂዎችን በማካተት የተመሠረተ ነው። ይህ ስብስብ «የድህረ-ህወሓት ስትራቴጂ ሰነድ» በማዘጋጀት ህጋዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ክልሉን በጊዜያዊነት የማስተዳደር ሐሳብ ለመንግሥት ቢያቀርብም፣ የፌደራል መንግሥቱ ግን ሰነዱን ከመረመረ በኋላ ውድቅ ማድረጉን የምክር ቤቱ አመራሮች ገልጸዋል።

የፌደራል መንግሥቱ ዕቅዱን ያልተቀበለው በምክር ቤቱ አባል ድርጅቶች መካከል ባሉ የውስጥ ልዩነቶች ምክንያት እምነት በማጣቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ከውሳነው በኋላ ከቀናት በፊት መቀሌ ለሚዲያ ቃላቸውን የሰጡት የጠ/ሚ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ክልሉን በቀጥታ የፌደራሉ መንግሥት እንደሚያስተዳድረው መግለፃቸው ይታወሳል።

📢 @times_mereja_ethiopia
👇 Join US
👍12❤7😁2😡1
ኤርትራ የኢትዮጵያን እርምጃ በመቃወም አቤቱታ አቀረበች
የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ከቀናት በፊት መወሰኑን ተከትሎ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውሳኔውን በመቃወም ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ይፋዊ የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ።

የኤርትራ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በአዲስ አበባ በሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ እንዲሁም በአፍሪካ ህብረትና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑትን ጨምሮ 10 ዲፕሎማቶች ሀገር ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ ሀገሪቱ በህብረቱ ውስጥ ያላትን የመወከል እና የመሳተፍ የአባልነት መብት የሚያሳጣት ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተቋማትን የማስተናገድ ግዴታ እንዳለባት ያስታወሰው መግለጫው፤ እርምጃው ህብረቱ መቀመጫውን በአዲስ አበባ እንዲያደርግ የተፈረመውን የመቀመጫ ስምምነት እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ መርሆችን የጣሰ ነው ሲል ከሷል። በመሆኑም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን፣ የስራ አስፈፃሚው ምክር ቤት እና የህብረቱ ጉባኤ ጉዳዩን በአስቸኳይ ተመልክተው የኤርትራ ሕጋዊ ውክልና እንዲመለስ የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።
የበለጠ መረጃ t.me/times_mereja_ethiopia
❤20👍7😁3