ደርግ በሚግ እንዳልተረፈ ሁሉ
ብልፅግናም በድሮን አይድንም!
2019 አገዛዙ የሚገረሰስበት ያድርግልን!
መልካም አዲስ አመት
ብልፅግናም በድሮን አይድንም!
2019 አገዛዙ የሚገረሰስበት ያድርግልን!
መልካም አዲስ አመት
👍27🔥20🥰5😁3
እርሱ ባያፈር.....
ተብሎ ምን ነበር የሚባለው!!
ከተገንጣይ ቡድኖች ጋር ትብብር አደረኩ ማለት አንድም እኔም ተገንጣይ ነኝ ማለት ነው። ሁለትም በራሴ ማሳካት አልችልም ማለት ነው።
በነገራችን የዚህ ትብብር ፊት አውራሪ ማን ነው?? ከተባበሩት ውስጥ የትኛው የበለጠ ጠንካራ አደረጃጀት አለው? በሚዲያ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መለኪያዎች!
ተመሳሳያ ዓላማ ካላቸው የራስ ወንድሞች ጋር ተባብሮ መስራት ሳይቻል ያልተመጣጠነ አቅም ካላቸው አካላት (የህዝባችን የችግር ሁሉ ምንጭ) ጋር አንሶላ መጋፈፍ ትግሉን ስንት ሜትር ጉድጓድ ውስጥ ይቀብረዋል!?
ጥያቄ፦ የፅምዶ ፊት አውራሪ ድርጅት (ግለሰብ አላልኩም) ማን ይመስላችኋል!?

👎13❤12👏2😁1
የዘመነ ታጣቂስ ምን ላይ ይሆን!?
ትክክለኛው ፋኖስ?
የአማራ ፋኖ እንዳለው ትልቅ የእግረኛ ሰራዊት፤ እንዳለው ሰፊ ቀጠና፤ እንዳለው የፋይናንስ ድጋፍ የፀረ ፋሽስቱ ትግል ፊት አውራሪ መሆን ነበረበት!! የራሱ ሚዲያ፣ የራሱ የፕሮፖጋንዳ ክፍል፣ ሜካናይዝድ እና ፀረ ድሮን units ሊኖሩ ይገባ ነበር። አሁን እንደተመሰረተው አይነት ታክቲካል አሊያንስ ሲፈጠር መሪ መሆን የነበረበት ራሱ ነበር!! ግን ክብር ለዘመነ ካሴና ጃግሬዎቹ ይሁንና የወያኔ አሽከር ለመሆን በቃን😭

👎20❤6👍5😭2👏1😱1
ጎበዝ
እስቲ የዚህን ጦርነት ስም አውጡለት!
1) የህውሃት የብልፅግና ጦርነት (ግቡ አማራን ለማጥፋት)
2) የትብብሩና የብልፅግና ጦርነት (ግቡ ግራ የሚያጋባ)
3) የኢሱ-አቢቹ ግጥሚያ ( ግቡ ባህር ለመቀማማት)
ምረጡ
እስቲ የዚህን ጦርነት ስም አውጡለት!
1) የህውሃት የብልፅግና ጦርነት (ግቡ አማራን ለማጥፋት)
2) የትብብሩና የብልፅግና ጦርነት (ግቡ ግራ የሚያጋባ)
3) የኢሱ-አቢቹ ግጥሚያ ( ግቡ ባህር ለመቀማማት)
ምረጡ
👎33👍6👏2🤔2❤1🔥1
ፋሽስታዊ ሀይሉ እንዳያንሰራራ ተደርጎ እንደተደቆሰ መረጃዎች ቢያሳዩም የአገዛዙ የሀሰት የፕሮፓጋንዳ ክንፍ ግን ብልጫ ወስዶ ውሏል!!
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የስልክ የኢንተርኔት አግልግሎት እንደተቋረጠ እየተሰማ ነው። እንዲሁም በደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ባንኮች ውስን የሆነ ካሽ ብቻ ለደንበኞች እየሰጡ መሆኑን ምንጮቼ አረጋግጠዋል!
የሁለት ዶክተሮች ግጥሚያ የሚገርም እንደሚሆን እሙን ነው!

❤12😁5👍1
በራያና ዋግ ቀጠናዎች በተደረጉ ውጊያዎች በሁሉም ተፋላሚዎች በኩል በንፁሓን ላይ የታየው ደንታ-ቢስነት በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ነው!! በእነዚህ ውስን አውደ ውጊያዎች ላይ የደረሰው የበዛ የንፁሓን ጭፍጨፋ አስፈላጊውን ትኩረት ካልሰጠነው በቀጣይ በሚደረጉ ውጊያዎች የሚደርሰውን እልቂት አስቡት!
👍10🤔5❤3👎1😱1
✅በሰሌን ውሃ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ በአረፈ ከባድ መሳሪያ ምክንያት 6 የአንድ ሰው ቤተሰቦች ሙተዋል!
✅በሰቆጣ በተመሳሳያ መኖሪያ ቤት ላይ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የአንዲት እናት ህይወት ወዲያውኑ ሲያል በሶስት የቤተሰቡ አባላት ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል!!
✅በአላማጣ ከተማ በተመሳሳይ በርካታ ሰዎች የተገዱ ሲሆን አቶ ረዳ ካህሳይ (የአቶ ጌታቸው ረዳ ወላጅ አባት) አንዱ ናቸው።
በአጠቃላይ በሰባት ቀናት ውስጥ በ4 ግንባሮች በተደረገ ውጊያ ቢያንስ 70 ንፁሓን ተገድለዋል!!
በንፁሓን ላይ የሚታየው ግዴለሽነት በጣም ያስፈራል!!

😢12❤4👍1
ድል ቁርሱ ግን የተጨነቀ ይመስላል!! ዛሬ ሉሉ ሳያደርግ ያደረገው ቃለ መጠየቅ እንደይተላለፍ ተደርጓል!
የሚያሳዝነኝ በእነዚህ ቀሽሞ ሰዎች መዋቅር ገብተው ውድ ህይወታቸውን ለሚገብሩ የሀገሬ ልጆች ነው!!
ቀይ ባህርን ሲመኙ
ተሻግረው እንደይሔዱ

👍13😁2
የደብረዘይት አየር ሀይል
የሰመራ ኤርፖርት
የባህርዳር አየር ሀይል
ኮምቦልቻ ኤርፖርት
ሑመራ ኤርፖርት
በአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች የተመቱ ሲሆን
መቀሌ ኤርፖርት
ላሊበላ ኤርፖርት
አክሱም ኤርፖርት
ሽሬ ኤርፖርት
አገልግሎት አቁመዋል!!
ሰማዩ ግን የነሱ ነው¡
የሰመራ ኤርፖርት
የባህርዳር አየር ሀይል
ኮምቦልቻ ኤርፖርት
ሑመራ ኤርፖርት
በአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች የተመቱ ሲሆን
መቀሌ ኤርፖርት
ላሊበላ ኤርፖርት
አክሱም ኤርፖርት
ሽሬ ኤርፖርት
አገልግሎት አቁመዋል!!
ሰማዩ ግን የነሱ ነው¡
❤21😱4😁2
6:30
7:11
7:31
ሆነ ተከናወነ!! ጦር ሀይሎ ሆስፒታል በቁስለኛ ተሞልቷል!
ሰማዩ የኛም ነው 😂
7:11
7:31
ሆነ ተከናወነ!! ጦር ሀይሎ ሆስፒታል በቁስለኛ ተሞልቷል!
ሰማዩ የኛም ነው 😂
👍21❤9
ኸየ ብልፄ!!
በመጀመሪያ ደረጃ የኤርትራ ዲፕሎማቶች አዲስ አበባ የመጡት የሀገራቸውን ጥቅም ለማስከበር ነው፤ (እንደኛዎቹ ሆዳማች አይደለም! ታዲያ ቀይ ባህር፤ አሰብ ገለመኔ እያልክ ስታለግ ዝም ብለው እንዲያዩህ ነበር የፈለከው!!? ኸየ ኦሮሞ

👍20
አንዱ ወንጌል የሚቀላቅል ካድሬ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው..."የሰሜኑን ድግምት እያፈራረስነው ስለሆነ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከአጋንንት አሰራር ወጥታ ሰላም ትሆናለች።"
ይህ ሰው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ኃላፊነት ያለው ነው።
ዘይገርም

😱9❤7🥱5
በእሳት ዳር ቤንዚን፦ የቀይ ባሕር ዛቻና የአስመራ ስትራቴጂካዊ ሥጋት
____________
የአፍሪካ ቀንድ ወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ የፕሮፓጋንዳ ቀረርቶ እና የቀጣናው የደህንነት ስጋት አዙሪት
(ጂኦ-ፖለቲካ & ወታደራዊ)
በቀይ ባሕር አካባቢ እየተካሄደ ያለው የጂኦ-ፖለቲካ እና የወታደራዊ እንቅስቃሴ፣ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን ወደ አዲስና አደገኛ የፖለቲካ ምዕራፍ እያሸጋገረው ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግሥት በከፍተኛ ባለሥልጣናትና በወታደራዊ አዛዦች አማካይነት የሚያስተላልፏቸው ተከታታይ ሀገራዊ ብሔርተኝነትን ለመቀስቀስ የታለሙ የሚመስሉ እና ቀይ ባሕርን የሚመለከቱ ንግግሮች፣ የአስመራን ስትራቴጂካዊ ሥጋት አብዝተው በመቀስቀስ የሁለቱን ሀገራት የወደፊት ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከተውታል።
የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች እና የጦር አዛዦች «አሰብን ሳንይዝ አንመለስም»፣ «ከብታችንን አሰብ ላይ ነው የምናጠጣው»፣ «እሬቻን ቀይ ባህር ላይ ነው የምናከብረው»... በሚሉ እና መሰል የነጋ-ጠባ ቀረርቶዎች በሚያዥጎደጉዱበት ወቅት፣ የኤርትራ መንግሥት ሁኔታውን እንደ ዝምተኛ ተመልካች እንዲያየው መጠበቅ የዋህነት ነው።
እነዚህ የፕሮፓጋንዳ ዛቻዎች በአስመራ እይታ ውስጥ እንደ ተራ ፖለቲካዊ ፉከራ ሳይሆን፣ አገዛዙንና ሉዓላዊነቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ እውነተኛና አፋጣኝ የደህንነት ሥጋቶች (real and imminent threats) ተደርገው ይወሰዳሉ።
ለዚህ ስጋት ዋነኛው ምክንያት የኤርትራ የደቡባዊ ቀይ ባሕር ዞን የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ነው። ከምፅዋ እስከ አሰብ ተዘርግቶ የሚገኘው ይህ ጠባብና ረጅም የባሕር ዳርቻ ኮሪደር (የበሬ ምላስ)፣ ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር ወደ 500 ኪሎሜትር በሚደርስ ርዝመት የተገናኘ በመሆኑ ለወታደራዊ ጥቃት እጅግ ተጋላጭ ነው።
ይህ ዓይነቱ አቀማመጥ በየትኛውም ነጥብ ላይ በፈጣን ወታደራዊ ወረራ ተቆርጦ ከአስመራ የመነጠል እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣ በአስመራ ወታደራዊ እቅድ አውጪዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን መፍጠሩ አይቀርም።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፌደራል ጦር በሕወሓትና በፋኖ ኃይሎች ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ዘመቻ ወደ ሰሜን አካባቢ ማድረጉ ይታወቃል። ነገር ግን ከአመራሮቹ የዕለት ተዕለት ዛቻ አንጻር፣ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጦር በማንኛውም ቅጽበት አቅጣጫውን ወደ ምሥራቅ በመቀየር አሰብን ለመቁረጥ ሊንቀሳቀስ ይችላል የሚል ስጋት አለ።
በመሆኑም ኤርትራ የፌደራሉን ጦር እንቅስቃሴ በከፍተኛ ጥንቃቄና በአንክሮ እየተከታተለች፣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ኃይሏን በተጠንቀቅ ማቆየቷ የማይቀር የተፈጥሮ የመከላከል እርምጃ ነው።
የስነ-ልቦና እና የደህንነት ተመራማሪዎች እንደሚገልፁት፣ ረጅም ድንበር እና ቀጭን የኮሪደር አቀማመጥ ያላቸው ሀገራት የከበባ ወይም የመቁረጥ ስጋት ሲደቀንባቸው፣ ሁኔታውን እንደ "ቀጥተኛና አጣዳፊ ስጋት" የመመልከት እድላቸው ከፍተኛ ነው።
አሌክስ ደ ዋል (Alex de Waal) Real Politics of the Horn of Africa በተሰኘው ጥናታቸው እንደሚያስረዱት፣ በቀጣናው የሚገኙ ሀገራት ድንገተኛ ጥቃትን ለመከላከል ሲሉ ቀድሞ የመስጋት እና የመከላከል (pre-emptive) እርምጃዎችን የመውሰድ ልምድ አላቸው በማለት ያስረዳሉ። ይህም አሁን ባለው አያያዝ የጂቡቲን የንግድ መስመር እስከ መቁረጥ ሊደርስ ይችላል ብሎ መገመት ፍፁም ስህተት ተብሎ ሊወሰድ አይችልም።
ይህንን ሁኔታ የበለጠ የሚያወሳስበው ለፕሮፓጋንዳ ሲባል በግድየለሽነት የሚወረወሩ አደገኛ የቃላት ጦርነት እና የፖለቲካ ቃላት፣ ንግግሮችና መግለጫዎች መበራከት ነው።
ሮበርት ጄርቪስ (Robert Jervis) Perception and Misperception in International Politics በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንደሚያብራሩ፣ ተከታታይ የሆኑ ማስፈራሪያዎች እና ስትራቴጂካዊ ምልክቶች በሁለት ወገኖች መካከል ያለውን መተማመን በማሳጣት የስጋት አዙሪት (security dilemma) ይፈጥራሉ።
በእሳት ዳር ቤንዚን እንደሚረጭ ያህል አደገኛ የሆነውን ይህንን ያልተገደበ የፕሮፓጋንዳ እና የዛቻ አካሄድ የብልፅግና አመራሮች አደብ ሊያስገቡት ይገባል። አለበለዚያ ያላሰለሰና ለከት የሌለው ቀረርቶ የኤርትራን ጦር በገዛ እጁ ወደዚህ ውጊያ በመጎተት በቀጣናው ላይ በቀላሉ ሊወጡት የማይቻል መዓት የመጋበዝ አቅም አለው።
የቀይ ባሕር ቀጠና ውጥረት በሁለቱ ሀገራት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን የዓለም አቀፍ ንግድ እና የደህንነት መስመርን የሚነካ በመሆኑ፣ ሌሎች ያልተጠበቁ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ኃይሎችን ወደ ግጭቱ ሊስብ የሚችል አደገኛ አካሄድ ነው።
ይህንን ስጋት ለመቀነስ ከአላስፈላጊ ዛቻ እና ቀረርቶ ይልቅ የራስን ምላስ በመግታት፣ በዲፕሎማሲያዊ እና ሕጋዊ መንገድ ውይይት ማድረግ ብቸኛው አወንታዊ መፍትሔ ነው።
@Assaf Hailu

❤17