Rufael is the Ethiopic and Eritrean form of the ancient Hebrew name Raphael, meaning "God has healed"
🔥4
የቅዱስ ሩፋኤል በዓል ዋና ዋና ነጥቦች (ጳጕሜን ፫)
የበዓሉ ምክንያት እና የስሙ ትርጓሜ፦ በዓሉ የሚከበረው የሢመቱን እና የቅዳሴ ቤቱን መታሰቢያ በማድረግ ነው፡፡ «ሩፋኤል» ማለት «ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን፣ የዋህ» ማለት ነው፡፡
የፈውስ መልአክ፦ በሰው ልጆች ደዌና ቍስል ላይ የተሾመ በመኾኑ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሥልጣን ሕመምና ቍስልን ይፈውሳል (ሄኖክ ፲፥፲፫)፡፡
የነፍሰ ጡሮችና ሕፃናት ረዳት፦ «ፈታሔ ማኅፀን» በመኾኑ ነፍሰ ጡር ሴቶችን ከፅንስ እስከ ወሊድ በጥበቃው አይለያቸውም፤ በመውለጃቸው ቀን በሚደርስባቸው ጭንቀት ደርሶ ሕመማቸውን ያቀልላቸዋል፡፡
አጋንንትን የሚያስር እና ጥበቃ የሚያደርግ፦ አስማንድዮስ የተባለውን ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ሲያሣቂያት አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫)፤ አዛዝኤል የተባለውንም ጋኔን በእሳት ሰይፍ ቀጥቶ አስሮታል (ሄኖክ ፫)፡፡
የቅዱሳን ጸሎት አሳራጊ፦ የቅዱሳንን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያቀርቡት ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡
የእስክንድርያ ደሴት ተአምር፦ በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የተሠራችው ቤተ ክርስቲያን በሰይጣን ተንኮል ልትፈርስ ስትል፣ ምእመናን በስሙ ሲማጸኑ ቅዱስ ሩፋኤል አንበሪውን በጦሩ ወግቶ «ጸጥ ብለህ ቁም» በማለት ማዕበሉን አረጋግቶ ምእመናኑን አድኗቸዋል፡፡

❤8
‹‹የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው›› (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡
❤7
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ 🌼🌼🌼
አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ዓመት እንዲሆን፣ ከልብ እንመኛለሁ::
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት!🌼🌼🌼

❤5
🌼 ዳንኤል 3:18 🌼
ለእግዚአብሔር መታመን ያለብን እርሱንም ማመስገን ያለብን ስላደረገልን ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ቢያደርግልንም ይመስገን ፤ ባያደርግልንም ይመስገን።
በትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውም ይህ ነው
። ሶስቱ ወጣቶች ወደ እሳቱ ሊጣሉ ባሉ ጊዜ እግዚአብሔር ባያድነን እንኳ ለእርሱ ታምነን እንሞታለን ነው ያሉት። ግን እግዚአብሔር ከእሳቱ አዳናቸው።
ዳንኤል 3:18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል ...
ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል፣ ላቆምኸውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።

❤2
'' የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።'' (2 ቆሮ 8:9)
❤5
የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል አድኗል ያድናልም። እኛ ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስ የሆነው ሁሉ በራሱ በክርስቶስ ሃይል ያድናል ብለን እናምናለን።
መልካም በዓል።
መልካም በዓል።
🔥3❤1
ራስን ማየት፡ የራሳችንን ስህተት ማየት ስንጀምር ሌሎችን ለመውቀስና ለመፍረድ ጊዜም ሆነ የሞራል ብቃት አይኖረንም።
❤4
ወንድሜ ሆይ እግዚአብሔር ለአላማው ካዘጋጀህ ልክ እንደ ነቢዩ ዮናስ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ብትገባ እንኳ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፤ እንደ ነቢዩ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ብትጣል እርሱ ከእንተ ጋር ነው ፤ እንደ ዮሴፍ ዘመንድና ወዳጅ ቢከዳህ እርሱ ከአንተ ጋር ነው።
“በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።”
— መዝሙር 23፥4

❤3🔥2👍1
ቤተልሔም ማለት ቤተ ህብስት፣ የህብስት ቤት፣ የእንጀራ ቤት ማለት ነው። ይህም ካሌብ እስራኤል ዘሥጋ ምድረ ርስት፣ ኢያሪኮን “ሃይል ዘእግዚአብሔር ኲናት ዘኢያሱ” ብለው በኢያሱ መስፍንነት ሲወርሱ ከኢያሱ የተሰጠችው ምድር፣ ኬብሮን ነበረች። ይህችም የይሁዳ ምድር በኋላም የቅዱስ ዳዊት ከተማ የሆነች ናት። አስቀድሞ ካሌብ ከብታ የምትባል ሚስት አግብቶ በሚስቱ ከብታ አላት ትርጓሜውም የምስጋና ቤት ማለት ነው፤ ይህም ካሌብ በመንፈሰ እግዚአብሔር በዚህች ምድር የሚገለጠውን የክርስቶስ የልደቱን ነገር፣ እና የመላእክትን ምስጋና ስለተረዳ ነበር። በኋላም ካሌብ ኤፍራታ የምትባል ሚስት አገባ ቦታዋን በዚህች ሚስቱ እንደገና ኤፍራታ ብሎ ጠራት። ኤፍራታ ማለት ፀዋሪተ ፍሬ፣ ፍሬ በውስጧ ያለባት ማለት ነው። ይህችውም የእመቤታችን ምሳሌ ናት የህይወት ፍሬ ክርስቶስን ወልዳልናለችና፤ አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ፍሬኪኒ ፍሬ ሕይወት እንዳለ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን። ቤተልሔም ይህን ስያሜዋን ያገኘችው ካሌብ ከኤፍራታ ባገኘው ልጁ በልሔም ነው፤ ልሔም ማለት ህብስት፣ እንጀራ ማለት ነው ይህም ምሳሌነቱ የጌታ ነው፤ ይኸውም አማናዊ፣ እውነተኛ የሕይወት እንጀራ፣ህብስት ክርስቶስ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሊያድነን የመወለዱ ምሳሌ ነው። “ከሰማይ የወረደ ህያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለዓለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።” እንዲል /ዮሐ 6፥51/።
🔥3❤1
ሰይጣን ( እርኩስ መንፈሱ ) ተጠምቆ ክርስቲያን ሆነና ገነት ገባ የሚል የቤተክርስቲያን ትምህርት የለም። ታዲያ በገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ላይ የተጠቀሰው ምንድን ነው ቢሉ :-
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁት የሰው ልጅን ነው። ነገር ግን ያ ሰው ከምግባሩና ከውሎው የተነሳ ሰይጣን ተባለ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በምትሓት በእሳት ላይ ይራመዳሉ ፤ እሶኸ ላይ ይተኛሉ ፤ ባህር ውስጥ ይኖራሉ ወዘተ...
ስለዚህ እንዲህ ከእርኩስ መንፈስ ጋር ይኖር የነበረውን ሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጠመቁትና ክርስቲያን አደረጉት። አንዳንዶች ግን ይህንን ታሪክ በመቀየር ለራሳቸው አላማ ሲጠቀሙ እናያለን። እኛ ግን እውነትን እንመሰክራለን።
የጻድቁ በረከት አይለየን።

❤9
———-በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ ትምህርት መሠረት፦
የሰይጣን (የአጋንንት) ተፈጥሮና ውደቀት፦ አጋንንት ረቂቃን መናፍስት ሲሆኑ፡ በፍቃዳቸው ኮርተው ከወደቁ በኋላ ንስሐ መግባት ወይም መጠመቅ አይችሉም። ማዳን የተዘጋጀው ለሰው ልጅ ብቻ ነው።
የቃላት ዘይቤያዊ አጠቃቀም፦ በቅዱሳት መጻሕፍትና በገድላት ላይ "ሰይጣን"፣ "አጋንንት" ወይም "አራዊት" የሚሉ ቃላት አንዳንደ ጊዜ ለክፉ ምግባራቸው ወይም እርኩስ መንፈስ አድሮባቸው ለሚኖሩ ሰዎች ምሳሌ ሆኖ ይሠጣል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ ይሁዳን «ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው» (ዮሐ. 6፥70) እንዳለው ወይም ጴጥሮስን «አንተ ሰይጣን ከበስተኋላዬ ሂድ» (ማቴ. 16፥23) እንዳለው ሁሉ፡ ምግባረ አጋንንት የሚያደርጉ ሰዎችን በስም መጠራት የተለመደ ነው።
ስለሆነም ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያጠመቁትና ወደ አምላክ ያመጡት በአጋንንትና በምትሐት ተይዞ ይኖር የነበረውን ያንን የሰውን ልጅ ነው

በዚያን ዘመን ተጠንቀቁ
ሄኖክ ፴፰÷፲፯ ^ ዮሐ ፭÷፵፬
'' በዚያን ዘመን ሴቶች ለባሎቻቸው አይታዘዙም ባሮችም ለጌቶቻቸው አይገዙም ሴቶች በመኳንንት ወንበር ቢቀመጡ ይወዳሉ። በወንድ መሣሪያ ያጌጣሉ እንዲህም ይላሉ በዳኝነት ተቀምጠን ፍርድ እንፍረድ ይላሉ። ሴት የተናገረችው ለባሏ አይጥመውም ባልዋ የተናገረውም ለሚስቱ አይጥማትም። የባልዋን ፈቃድ አትሠራውም። ባልዋ ስለ ንብረቱ ይታገሣታል። ፈቃዱን ታደርግ ዘንድ እሺ ብትለው ለጊዜው ደስ ይለዋል። እምቢ ብትለውም ስለ ንብረቱ እያዘነ ይኖራል።''
(ፍካሬ ኢየሱስ )

❤1
የምስጋና (የስብሐት) ዓይነቶች ልዩነት
በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ምስጋና/ስብሐት እንደ ባለቤቱ ማንነትና ደረጃ በሁለት አበይት ክፍሎች ይከፈላል፦
የአምልኮ ምስጋና (Latria / Worship)፦
ባለቤቱ፦ ለሥላሴ (ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ) ብቻ የሚቀርብ ነው።
ምክንያቱ፦ ስለ ፈጣሪነቱ፣ ስለ አዳኝነቱ፣ ስለ ባሕርይ አምላክነቱ እና ለፍጥረታት ሁሉ ሕይወትንና ህልውናን በመስጣቱ የሚቀርብ ፍጹም አምልኮ ነው።
የአክብሮትና የጸጋ ምስጋና (Dulia / Venerations)፦
ባለቤቱ፦ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም (የላቀ የአክብሮት ምስጋና - Hyperdulia)፣ ለማላእክት እና ለቅዱሳን የሚቀርብ ነው።
ምክንያቱ፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ስላገኙት ባለሟልነት፣ ቅድስና፣ እና ፈጣሪን በድንግልና ወልዳ ስለ አበቃችው ታላቅ የድንቅ ሥራ የሚሰጥ አክብሮት ነው።
ስለዚህ “ስብሐት ለእግዚአብሔር” ሲባል የአምልኮ ምስጋና ሲሆን፤ “ስብሐት ለማርያም” ሲባል ደግሞ የፈጠራትን አምላክ ያከበረች እና የወለደች በመሆኗ የሚሰጥ የጸጋና የአክብሮት ምስጋና ነው።
2. የመጽሐፍ ቅዱስ ምስክሮች
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የፈጣሪና የፍጡር ስም አብሮ መጠራት ወይም ተመሳሳይ ቃላት ጥቅም ላይ መዋል ፍጡሩን ከፈጣሪ ጋር እኩል አያደርገውም፦
የሐዋርያት እና የመንፈስ ቅዱስ ስም አብሮ መጠራት (ሐዋርያት 15፥28)፦
እመቤታችን ራሷ የተናገረችው (ሉቃስ 1፥48-49)፦
የእግዚአብሔር እና የቅዱሳን ስም አብሮ መጠራት (መጻሕፍተ ነገሥት/መሣፍንት)፦
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የእግዚአብሔር እና የጌዴኦን ሰይፍ” (መሣፍንት 7፥20) ወይም “እግዚአብሔርንና ንጉሡን አመሰገኑ” የሚሉ አበዋዋሎች አሉ። ይህም ፍጡራን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫና አገልጋዮች በመሆናቸው የተነገረ እንጂ ፈጣሪና ፍጡር እኩል ሆነው አይደለም።
ማጠቃለያ
“ስብሐት ለማርያም” ሲባል የእግዚአብሔርን አምልኮና ምስጋና ለሌላ መስጠት ሳይሆን፣ ይልቁንም የሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነችውንና የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን የተመረጠችውን እመቤት ማክበር ነው። እመቤታችንን ማመስገን በራሱ በእርሷ ላይ ታላቅ ሥራ ያደረገውን እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር ነው።

“እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና...”
ሐዋርያት ራሳቸውን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብረው ስለጠቀሱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ባሕርይ አላቸው ማለት አይደለም። ይልቁንም የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያና አገልጋዮች በመሆናቸው መንፈስ ቅዱስ በመራቸው መሪነት መወሰናቸውን ለማሳየት ነው።
እመቤታችን ራሷ የተናገረችው (ሉቃስ 1፥48-49)፦
“እነሆ፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና፤”
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ጸጋን የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ” ብሎ እንዳመሰገናት ሁሉ፣ ትውልድ ሁሉ እርሷን የሚያመሰግኗት እግዚአብሔር በእርሷ ላይ ስላደረገው ታላቅ የድኅነት ሥራ ነው።
የእግዚአብሔር እና የቅዱሳን ስም አብሮ መጠራት (መጻሕፍተ ነገሥት/መሣፍንት)፦
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “የእግዚአብሔር እና የጌዴኦን ሰይፍ” (መሣፍንት 7፥20) ወይም “እግዚአብሔርንና ንጉሡን አመሰገኑ” የሚሉ አበዋዋሎች አሉ። ይህም ፍጡራን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫና አገልጋዮች በመሆናቸው የተነገረ እንጂ ፈጣሪና ፍጡር እኩል ሆነው አይደለም።
ማጠቃለያ
“ስብሐት ለማርያም” ሲባል የእግዚአብሔርን አምልኮና ምስጋና ለሌላ መስጠት ሳይሆን፣ ይልቁንም የሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነችውንና የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን የተመረጠችውን እመቤት ማክበር ነው። እመቤታችንን ማመስገን በራሱ በእርሷ ላይ ታላቅ ሥራ ያደረገውን እግዚአብሔርን ማመስገንና ማክበር ነው።
❤2
መጽሐፍ ቅዱስ :- 2ኛ ነገሥት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ኤልሳዕም ሞተ፥ ቀበሩትም። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።
²¹ ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ።
ቅዱሳን በሥጋ ቢለዩም ይፈውሳሉ ያድናሉ።