ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
ማንም ማንንም ሃጢያተኛ የማለት መብት የለውም

“በዓይንህ ያለውን ምሰሶ ራስህ ሳታይ፥ እንዴት ወንድምህን፦ ወንድሜ ሆይ፥ በዓይንህ ያለውን ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ ልትል ትችላለህ? አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ ከዚያም በኋላ በወንድምህ ዓይን ያለውን ጉድፍ ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።”
— ሉቃስ 6፥42
❤2
"Repentance opens the gates of heaven for us." (St John Chrysostom) "ንስሐ የገነትን ደጆች ይከፍትልናል" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
👍1
"You have made us for Yourself, O Lord, and our heart finds no peace until it rests in You." (Saint Augustine) " አቤቱ ለራስህ ፈጠርከን ልባችንም በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ሰላም አላገኘም።" (ቅዱስ አውጉስቲን)
🥰4
ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል የሚገኝበት ጉባኤ ቅዳሴ የተባለው የቤተክርስቲያን የምሳጋና ጊዜ ነው።
❤3
🌼 ዳንኤል 3:18 🌼

ለእግዚአብሔር መታመን ያለብን እርሱንም ማመስገን ያለብን ስላደረገልን ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ቢያደርግልንም ይመስገን ፤ ባያደርግልንም ይመስገን።

በትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውም ይህ ነው
። ሶስቱ ወጣቶች ወደ እሳቱ ሊጣሉ ባሉ ጊዜ እግዚአብሔር ባያድነን እንኳ ለእርሱ ታምነን እንሞታለን ነው ያሉት። ግን እግዚአብሔር ከእሳቱ አዳናቸው።

ዳንኤል 3:18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል ...
ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል፣ ላቆምኸውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።”
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ"

#እንኳን ለእመቤታችን የልደት ቀን መታሰቢያ በዓል አደሰሳችሁ።
❤1
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬ ተወለደች። ይህቺ የተወለደችው ሴት ልጅ የአዳም ተስፋው ለሄዋንም መጽናኛዋ ነች።
❤3
እመቤታችን አምላክን ለመውለድ ተወለደች
አምላክ ሰው የሆነባት ትልቁን የመዳን ምስጢር የፈጸመባት እናቱ እናታችን እመቤታችን ድንግል ማርያም ነች።
❤5
አስገራሚው የፕሮቴስታንት አይዶሎጂ 🙄

በኢየሱስ ያመነ ተአምር መስራት እንደሚችል ይናገሩና የእርሱ የኢየሱስ እናት ቅድስት ድንግል ማርያምና መላእክት ሁሉ እንዲሁም በክርስቶስ ቅዱሳን የተባሉ ግን ምንም ማድረግ አይችሉም ይላሉ።

እንዴት ? 😂
👍7
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው።

እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ያለውን ሁሉን ያውቃል ይህ አምላካዊ ባሕርይ ነው።

ኢየሱስም በሰው አካል የተገለጠ እግዚአብሔር ነውና ሁሉን አዋቂ ነው።

“ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።” — ዮሐንስ 2፥24-25
❤5👍2
የሰው ልጅ ማንነት በሞት የሚገታ አይደለም🚫💀። ሰው ካለመኖር ወደ መኖር የመጣ ፍጡር ነው✨። ሞት ደግሞ መንገድ ነው🛣️። ወደ ሌላ ዓለም ወይም Dimension የምንሄድበት መንገድ ( portal ) ነው🌀።

እኛ ሰዎች ካለ መኖር ወደ መኖር መጣን🌱። በሞት ደግሞ ወደ ሌላ መኖር እንሄዳለን🌌። ያ የምንሄድበት መኖር ወይ የደስታ መኖር ነው🎉 ወይ የሃዘን መኖር ነው😢። ዛሬ ላይ በምድር ሳለን የምንናረገው ነገር ነጋችንን ይወስናል⚖️🌅።

መልካም እንሁን🙏✨።
👏5🥰1
➾ ስለ እምነት ክርክር

እኛ ተከራከርን አልተከራከርን ለእግዚአብሔር የሚጨመር የሚቀነስ ክብር ወይም የእውነተኛዋን እምነት ምንነት የሚቀይር አይደለም።

የነቢያት ትንቢት፣ የሐዋርያት ትምህርት፣ የአበው ምስክርነት ስለ ጌታችን ኢየሱስ የማዳን ሥራና ሰው የመሆኑ ምሥጢር ነው (ተዋሕዶ)። ጥሪያቸውም በእግዚአብሔር ልጅ አምነን የዘላለም ህይወት እናገኝ ዘንድ ነው።

በከንቱ መበሻሸቅ የሚፈጠር እውነተኛ ነገር የለም። በእርግጥ ውይይት ማድረግ ጥሩ ነው። ውይይት ማድረግ ያለብንም ከልበ ሰፊ እወነትን ከሚፈልግ ሰው ጋር ቢሆን የተሻለ ነው።
❤4👏2👍1
ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ እንደሆነ እናምናለን። 🌼
❤6
ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት በኢየሱክ ክርስቶስ ያመኑ ታላቅ አባት ስለሆኑ እርሱ ጌታ በምድር በሥጋ ሳለ ያደርግ የነበረውን የተአምራት ሥራ በጌታ ፈቃድና ሃይል ሰርተዋል።

ጌታ ኢየሱስ በጻድቁ ጸሎትና ምልጃ ይምረን ዘንድ ጸልዩ።
👏2🥰1
"አርገ እግዚአብሔር በይባቤ
ወእግዚእነ በቃ ቀርን"

"አምላክ በእልልታ
እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ አረገ"
(መዝ፡46፥5)
❤7👍1👏1
እግዚአብሔር አምላክ በአቡነ አረጋዊ ጸሎትና ምልጃ ይማረን።

አቡነ አረጋዊ እንስሳትን መግራት የቻሉ ታላቅ አባት ሲሆኑ ይህም ዘንዶ የተባለውን ተሳቢ እንስሳ በመግራትና በማዘዝ ዳሞ የተባለውን ተራራ እንዲያሶጣቸው አድርገውታል።

መጽሐፍ ሲናገር

(ያዕ. 3)--7 የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤ 8፤ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።
❤5👍1
1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤
³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።
⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።
⁶ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤
⁷ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
⁸ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
⁹ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
¹⁰ ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
❤2
አዳም በተፈጠረ በ40 ቀኑ ሐሙስ ቀን ወደ ገነት ገባ። ክርስቶስ ከሞት በተነሳ በ40 ቀኑ ሐሙስ ቀን ወደ ሰማይ ዓረገ። 40 ቀን በቤተክርስቲያን ብዙ ምሥጢር አላት።
❤5🥰2