🍇🍇🍇 እመቤታችን ሆይ አቤቱ መልካሙ የወይን ጠጅ እኮ የለንም። የወይን ጨጅ ይሰጠን ዘንድ ወደ ልጅሽ አሳስቢልን። 🍇🍇🍇
" የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም አለችው።"(ዮሐ 2:3)
🍇 ለሠርግ የተጠራው ሕዝብ በሠርግ ቤት ተገኝቶ የወይን ጠጅ ሲያልቅ ባለሠርጉ እጅግ በጣም ያፍራል: በሰዎች ዘንድም ይዋረዳል። እመቤታችን ሰዎችን ከውርደት ለማዳን ለችግሩ መፍትሔ ማምጣት ወደ ሚችለው ልጇ አመለከተች። በዮሴፍ ቤት የተለያዩ ተአምራትን ሲያደርግ ታየዋለችና በሠርግ ቤትም የወይን ጠጅ እንዲያበረከት ጠየቀችው። በሠርጉ ቤት የወይን ጠጁን ማለቅ የባለ ሠርጎችንም መጨነቅ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቃል። ስንኳ የጋኖች ሆድ የያዘውን የወይን ጠጅ የሰዎች ልብ የያዘውን አሳብ ያውቅ ነበርና። ድንግል ማርያም ''የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም'' ብላ እስክትጠይቀው ድረስ ዝም ማለቱ:- ማመልከት' መለመን' መጠየቅ' ማማለድ የድንግል ማርያም የሥራ ድርሻ መሆኑ እንዲታወቅ ነው። የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንይ:- አክአብና ኤልዛቤል ጣዖት እያመለኩ እግዚአብሔርን በዘነጉ ጊዜ ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በምድር ላይ ዝናብ እንዳይዘንብ ጸልዮ ሶስት አመት ከስድስት ወር በምድር ላይ ዝናም ዝናብ አልዘነበም ነበር/ 1ነገ 17:1 - ያዕ 5:18/። በምድር ላይ ረሃብ ቢጸናም እግዚአብሔር ያለ ኤልያስ ጸሎት ዝናብ አላዘነበም። ኤልያስ ዝናብ ይዘንብ ዘንድ ሁለተኛ ጸለ። እግዚአብሔርም በኤሌያስ ጸሎት ዝናብ አዘነበ።/ 1ነገ 18:14-46 ያዕ 5:18/ ይስሐቅ ወደ እግዚአብሔር ሳይጸልይ ሚስቱ ርብቃ አልጸነሰችም ነበር። ወደ እግዚአብሔር ከጸለየ በኃላ ግን ሚስቱ ርብቃ ጸነሰች /ዘፍ 25:21/። የሳሙኤል እናት ሐና ከመጸለይዋ በፊት ልጅ አልወለደችም ነበር። ወደ እግዚአብሔር ከጸለየች በኃላ ግን ታላቁን ነቢይ ሳሙኤልን ወለደች /1ኛ ሳሙ 1:9-20/።
🍇 ይህም የሚሆነው መለመን' መጸለይ የፍጡር ድርሻ ጸሎትን መቀበልና ምላሽ መስጠት የፈጣሪ ድርሻ' መመኘት መሻት/መፈለግ/ የፍጡር' መስጠት የፈጣሪ' ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት የፍጡር ድርሻ' ማድረግ መፈጸም የፈጣሪ ' ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት የፍጡር ድርሻ' ማድረግ መፈጸም የፈጣሪ ድርሻ መሆኑ እንዲታወቅ ነው።
🍇 የእመቤታችንም ድርሻ ይሁንላቸው ይደረግላቸው ይሰጣቸው ማለት ነውና ''የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም ።" ብላ እስክትጠይቀው ድረስ ታገሠ። ይህም ጥያቄ እመቤታችን ለምትጠይቃቸው ጥያቄዎች መጀመሪያ ነው። የጽድቅ ሥራ መሥራት ስለአቃታቸው ሰዎች ንጽሕናቸውን' ቅድስናቸውን ስለአጡ ሰዎች' ሥነምግባር ሥለሌላቸው ሰዎች' አሥራት ጸሎት መጾም መስጠት ስላቃታቸውውና ራሳቸውን መግዛት ስለተሳናቸው ሰዎች :- ጽድቅ እኮ የላቸውም' ንጽሕና ቅድስና እኮ የላቸውም' ሥነምግባር እኮ የላቸው' ኃጢአትን የማሸነፍ ችሎታ እኮ የላቸው / ሥርየተ ኃጢአት ይደርግላቸው / ብላ ስለምታቀርበው ምልጃ መጀመሪያ ነው።
ይቀየን።

👍3❤1
የቅዱሳን ምልጃ _" አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፤ ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ፤ እንደ ባሪያዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና " ( ኢዮ 42;8 )
👍1
ለእግዚአብሔር መላእክት ስግደት አይገባም ብለው ፕሮቴስታንት ወገኖች የሚያነሱሰ ጥቅስ ይህ ነው ግን እውን እነርሱ እንደሚሉት ነው እውን ለመላእክት ስግደት አይገባም ?
" ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና አለኝ።" (ራእ 19:10)
የመልአኩን ንግግር ካለመረዳት እንጂ ለመላእክት መስገድ ከሃይማኖት ውጭ ሆኖ ዮሐንስ ባለማወቅ የሰገደለት ሆኖ አይደለም። ይህንንማ እንዳንል የሰጋጁ የዮሐንስ ማንነት ያግደናል። ዮሐንስ ማለት ድንግላዊና የጌታ ሐዋርያ ከመሆኑም በላይ ጌታ የሚወደው በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ፤ ወንግጌልን መልዕክታትን የጻፈ ፥ እንዲሁም የዓለምን ፍጻሜ በራእይ ያየ ታላቅ አባት ነው።
ይህን ያህል የጌታ ባለሟል የሆነ ቅዱስን ሰው ለትንሿ ለነገር ለመላእክት መስገድ ተገቢ አለመሆን አጥቶት በስህተት ሰገደ ማለት የጻፋቸው ወንጌሎችም መልእክታትም ስሕተት አላቸው ማለት ነው።
ዮሐንስ ለመልአኩ የአክብሮት ስግደት ያቀረበው ለመላእክት መስገድ ተገቢ መሆኑን ስላወቀ ነው። መልአኩም ደግሞ #አትስገድልኝ ማለቱ የዮሐንስን ክብርና ማዕረግ መግለጡ ነው። ዮሐንስም በክብሩ ከመልአኩ እኩል ሆኖ ነበርና፥ እንድም በስልጣን በልጦት ነበር #ካህን ነውና ስልጣነ ክህነትህ ከእኔ ስልጣን ትበልጣለች ሲለው ነው..ስለ ስልጣነ ክህነት ታላቅነት " የትዳር ጉዳይ ይቅርና በመላእክት እንኳ እንድንፈርድ አታውቁምን?" (1ኛ ቆሮ 6:3) ተብሎ ተጽፏልና።
ስግደት ደግሞ የበላይና የበታች መግለጫ ስለሆነ አንተ'ኮ በክብር ከእኔ እኩል ነህ። ስለዚህ ለእኔ ልትሰግድ አይገባም ቢለውም ዮሐንስ ግን ከመስጊድ ወደ ኋላ አላለም ትሁት ነውና። ይህን ማረጋገጥ ከፈለግን ራእይ 22:8-9 እንመልከት.. '' ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።'' (ራእ 22:8-9)
እንግዲህ ዮሐንስ ተሳስቶ ሰገደ ቢባል እንኳ ሁለት ጊዜ ይሳሳታል? የመጀመሪያው አንሶ? እንግዲህ አባባሉ የትሕትና አባባል መሆኑ ግልጽ ነው።
'' መላእክትም ከሰይጣናት የሚለያቸው አንዱ ይህ ነው። ሰይጣናት የማይገባቸውን ክብር ሁሉ በትዕቢት ይቀበላሉ ፤ መላእክት ግን የሚገባቸው እንኳን ቢሆን ስለ ትህትና ይተዋሉ። ክብርን ሁሉ ለጌታቸው ይሰጣሉ። '' ቅዱስ እንድርያስ ዘቂሳርያ
አንድም '' እንዳታደርገው ተጠንቀቅ '' ማለቱ የመልአኩን ሁኔታ የማሳየት ነው። ይህም የዮሐንስን ትህትና እና የመልአኩን ህግ አክባሪነት ያሳያል። ይህም አንተ ካህን ሆነ ሳለ በክብር እየበለጥከኝ እንዴት ትሰግድልኛለህ? ይልቅስ አብረን ለእግዚአብሔር መስገድ እንችላለን ሲል ነው።''
ይቆየን 🍋

👍4❤1🔥1🥰1
በቅጡ 5 ደቂቃ ቆሞ መጸለይ የማይችል ሁሉ ነው ኮ አቡነ ተክለሃይማኖት እንዴት በአንድ እግራቸው ቆመው ጸለዩ ብሎ የሚጠይቀው?
መጽሐፍ ግን '' ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል ማር 9:23'' ይላል።
የጻድቁ በረከት ይደርብን።

❤12
ቅዱሳን ሰዎችና መላእክት ያድናሉ ስንል እግዚአብሔር አያድንም እያልን አይደለም። ይልቅስ የእነርሱ ማዳን የእግዚአብሔር ማዳን ነው፤ የእነርሱ ሞገሳቸው ሃይላቸው ክብራቸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ታላቅ ስም ነው እያልን ነው።
ክብር ለቅዱሳን 🌼
@WwEotc
ክብር ለቅዱሳን 🌼
@WwEotc
❤3👍1
[ ትምህርተ ተዋህዶ!]
• ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው፡፡ በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ ፥ በስጋ የማርያም ልጅ እንደ ሆነ እናምናለን፡፡ ሰው ባልሆነ አካል የሰውነትን ስራ አይሰራም ሥጋን ከርሷ ከእመቤታችን የነሳ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ሞት የሚሥማማት ስለሆነች ሞት የሚሥማማውን ሥጋ ተዋህዶአልና፡፡ ስለዚህም የተቀበለው ልቅሶ ፣ ሕማም ፣ ሞት ከድንግል የነሣው የሥጋ ገንዘብ ነው፡፡ አዘነ አለቀሠ ሲል ብትሠማ ያዘነ ያለቀሠ አምላክ ቃል እንደሆነ አታሥብ ይህ ሁሉ ሥጋ በመሆኑ ነው እንጂ፡፡
• ይህ ወልድ ለአንዱ የምንሰግድለት ለአንዱ የማንሠግድለት ባህርይ የምንል አይደለም፡፡ ሠው የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ባህርይ አንድ ሥለሆነ ሥጋው ጋር አዋህደን አንዲት ሥግደት እንሠግድለታለን እንጂ፡፡
• ከድንግል በነሣው ሥጋ ሞተ በማለት ፋንታ እግዚአብሔር አምላካችን ሥጋ በሌለው ባህርይ ታመመ ሞተ ይሉት ዘንድ አይገባም፡፡
• ክርስቶሥ ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን እናምናለን! ሥለሆነም ፍጡር ነው የሚሉትንና ዛሬም በአብ ቀኝ ተቀምጦ ለእኛ ያማልዳል የሚሉትን እንቃወማለን! እናወግዛለን!
• ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱሥ አንድነት ሣይለይ በምልአት ሣለ ሥጋ መሆኑ እንደምን ነው? ቢሉ የዓይን ብርሃን ከአይን ብሌን ሣይለይ ከብርሃነ ፀሀይ ጋር ተዋህዶ ምሉዕ እንደሆነ ጌታም በመልአተ ባሕርዩ ሣለ በመኀፀነ ድንግል አድሮ ከመቅጽበት ዓይን ሠው ሆነ፡፡ የማይለይ የማይነገር የማይመረመር ተዋህዶ ሆነ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለመሥቀሉ ክቡር!!!

👍8❤3👏2
ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ይማልዳል?
ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰማዕትነት ከመቀበሉ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ኢየሱስ ክርስቶስን በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየው - '' እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ፡ አለ።''
- ሐዋ 7:56 ይህ ማለት ክርስቶስ ወደ ሰማይ በክብር ከሄደ በኋላ ነው።
ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ ስለሚወግሩት ሰዎች ሲጸልይ እንዲህ አለ '' እስጢፋኖስም፦ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል፡ ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም፦ ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው፡ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ።'' ( ሐዋ 7:59-60 )
አሁን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚማልድ ቢሆን ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሚወግሩት ሰዎች አየሱስን በምድር በሥጋ ሳለ ያደርግ በነበረው ጸሎት አስምራቸው ባለው ነበረ። ነገር ግን አገልግሎቱን በምድር አንድን መስዋዕት አቅርቦ ጨርሶ ስለሄደና አሁን ስለማይለምን '' ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው፡ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።'' ማራቸው እንጂ አስምራቸው አላለም።

🥰6👍1
‹‹እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ይዋሐድ ዘንድ ምን አተጋው፤ በጨርቅ ይጠቀለል ዘንድ በበረት ይጣል ዘንድ ከድንግል ጡትን ይጠባ ዘንድ በዮርዳኖስ ይጠመቅ ዘንድ ምን አተጋው…፤ በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ ለእኛ ብሎ አይደለምን፤›› (ሃይማኖተ አበው ፲፮፥፪)
👍7
አቤቱ ተወዳጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፦
የምንኮራበት ክብራችን ፡ የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ፡ ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን፡ እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤
ጌታችን ሆይ ፦ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ፡ ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን ፤
ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን ፡ የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ ፡ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡
(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ)

👍2❤1
'' እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።'' - ዮሐ 14:28
+ አብ በአምላክነቱ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም/አያንስም፤ ወልድም በአምላክነቱ ከአብና ከመንፈስ ቅዱሥ አይበልጥም/አያንስም፤ መንፈስ ቅዱሥም በአምላክነቱ ከአብና ከወልድ አይበልጥም/አያንስም፡፡(1ኛ ዮሐ 5:8)
+ ጌታችን "ከእኔ አብ ይበልጣልና" ማለቱ አብ ዝቅተኛ ክብር ባለውና ደካማ በሆነው ሥጋ አለመገለጡን ለማሳወቅ ነው፡፡ አብ እንደ ወልድ በአይሁድ ዱላ አልተደበደበም ፣ አልተተፋበትም፣ በመሥቀል አልተቸነከረም በአጠቃላይ ወልድ የተቀበለውን መከራ አልተቀበለም ፡፡ ስለሆነም "ከእኔ አብ ይበልጣልና" አለ፡፡ አንድም አይሁድ እንደ እኔ ሊይዙት አይችሉም ሲል ነው፡፡
+ ወልድ ግን ቀዳማዊ፣ሰማያዊ አምላክ ቢሆንም ሥጋ በመልበሡ ትሑት ተባለ " እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና"(ማቴ 11:29) እንዲል፡፡
@" እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል። "(ት.ዘካ9:9)/(ማቴ 21:4-5) ተብሎም በትንቢት ተነግሮለታል፡፡የሠው ልጅ መከራ በፍቃዱ ተቀበለ፡፡
ሰው በሚቆምበት በጲላጦስ አደባባይ ተከሶ ቆመ፤ ሞትም ተፈረደበት፡፡ ይህን ሁሉ መከራ ስለሚሸከም አብ ይበልጠኛል ይላል፡፡ አብ ይበልጠኛል ማለቱ ከአብ ተለይቶ ሰው መሆኑን ለመግለጥ ነው እንጂ በአምላክነቱማ "እኔና አብ አንድ ነን"(ዮሐ 19:30) ብሏል፡፡
+ አባቶች እንዲህ ይላሉ:-" ዝኒ በእንተ አስተርእዮቱ ሥግወ ወተመክሮቱ ሕማማተ ወሞተ( አብ ይበልጠኛ ማለቱ:- በሥጋ ስለተገለጠና በሕማምና በሞት ስለ ተፈተነ ነው" ብለው ይተርጉሙታል፡፡ቅዱሥ ዳዊትም ሥለ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ብሏል:-"4፤ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?
5፤ ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።(መዝ 8:4-5)…ይህ የትንቢት ቃል ለኢየሱስ ክርሥቶሥ መነገሩን ቅ/ጳውሎስ በመልእክቱ ተርጉሞታል፡፡@" ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።"(ዕብ 2:9)
ከመላአክት አነሠ የተባለው ሞትን ስለ ቀመሠ ነው፡፡ መላአክት ሞትን አልቀመሡምና፡፡ ጌታ ግን መላአክት ያልቀመሡትን ሞት ሥለቀመሠ ከመለአክት አነሠ ተባለ፡፡ጌታ በመከራዉ፣ በሞቱ ከመላአክት አነሠ እንደተባለ ሁሉ " ከእኔ አብ ይበልጣልና" ማለቱ ሞትን ሥለ ሚቀምሥ ነው እንጂ በአምላክነቱ አይደለም፡፡
+ ቅዱስ ጳውሎሥም ይህን የተናገረው በጥንቃቄ ነው፡፡"ከመላእክት ያነሠውን ኢየሱስን አላለም፣ ከመለአክት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን አለ እንጂ፡፡" ከመላእክት አነሠ የተባለው በመከራው ውሥጥ ሣለ በሚሞትበት ጊዜ ነው፡፡ ሞትን ድል ካደረገ በኃላ ከመላእክት ያንሣል አይባልም፡፡ ለዚህ ነው "የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።"ያለው፡፡
ዮሐንስ አፈወርቅም " ወዝኒ ይደሉ ለትስብዕተ ክርስቶስ ለባሕታቱ ዘነሥአ እምኔነ" ትርጉም "ይኸም ከእኛ ለነሣው ለክርስቶስ ሰውነት /ሥጋ/ ብቻ ይገባል፡፡" ይላል፡፡ ከመላእክት አሳነስኸው የተባለው ሰው ሥለሆነ፣ ሥጋ ሥለ ለበሠ ነው ማለቱ ነው፡፡፪ተኛም " ከመላእክት አሣነሠው ማለት ለማን ይገባል? ሥለጠፋን ሥለ እኛ ሥስት መአልትና ሥስት ለሊት በከርሠ መቃብር ላደረው ለጌታችን ብቻ ነው እንጂ" ይላል፡፡
ይቆየን፡፡

❤4👍1👏1
ታላቋ ድንልግ ማርያም ሆይ፤ የሰው ልጅ በመርገመ ሥጋና ነፍስ በተያዘበት ዘመን ሁሉ እግዚአብሔር አብ ምድሪቱን ሁሉ አሻተተ እንዳንቺ ያለ በሁሉ ንጽሕት አላገኘም። እንደ ልጁንም ዓለም ያድን ዘንድ ወደ አንቺ ላከው።
@WwEotc
@WwEotc
🔥2🤩1
እመቤታችን ሞት የተፈረደበትን የአዳምን ሥጋ ይዛለችን? ለዛም ነው የሞተችው?
ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በኋላ ሞት ለክርስቲያኖች - ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ሽግግር ማረግያ መንገድ እንጂ የእርግማን ውጤት አይደለም።
"ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ?" (1 ቆሮ 15፡55)
ክርስቲያኖች የምንሞተው በሞት ድል ስለተነሳን ሳይሆን ወደ ዘላለማዊ እረፍት ወይም ሕይወት ለመግባት ነው።
የእመቤታችን ሞት ከዚህ አንጻር እንጂ ይታያል እንጂ ሞት የተፈረደበትን ሥጋ ስለያዘች ሞተች ቢሉ ትልቅ ስሕተት ነው።
እንደዛ ቢሆንማ ኢየሱስ የሞተው በፈቃዱ ሳይሆን ሞት የተፈረደበትን ሥጋ ስለያዘ ነው ወደሚል ክህደት እንገባለን።
'' እኔ ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም።'' (ዮሐ 10:18) እንዳለ።
የጌታ ኢየሱስ ስጋ ከማርያም ስለሆነ እርሷ አዳም የበደለውን ሥጋ ይዛለች ካልን እርሱም ይዛል ስለምንል እንጠንቀቅ።
የእርሷ ሥጋ አዳም ከመበደሉ በፊት የነበረው ንጹሑ ሥጋ ነው። ከሐጢአት የተጠበቀ የነጻ ነው። '' የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ ገሞራንም በመሰልን ነበር።'' ( ኢሳ 1:9) እንዲል።
ይቆየን።

👍6
'' ወንድሜ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።'' መኃልይ (Song of Solomon)
5:10
ወንድሜ የተባለው የክብር ጌታና አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእመቤታችን በነሳው ሥጋና ደም ወንድማችን ሆኗልና።
'' ለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።'' (ዕብ 2:17)
'' ነጭና ቀይ ነው'' ማለት ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ማለት ነው። ነጭ :- መለኮት መሆኑን ፤ ቀይ :- ሥጋ ወይም ሰው መሆኑን ያሳያል።
ወልድ ዋሕድ!

👏5
" የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።
"(የማቴዎስ ወንጌል 1:25)
👉 እርሷ እመቤታችን በትንቢት የተነገረላት እግዚአብሔርን የምትወልደው መሆኗን እስክትወልደው ድረስ ቅዱስ ዮሴፍ አላወቃትም ✅ አልተረዳም ፤ የአምላክን ሰው መሆን ምሥጢሩን አልተረዳም ✅
+ እግዚአብሔርን በሥጋ በወለደችው ጊዜ - መላእክት ሲያመሰግኑት ባየ ጊዜ፣ ኃያላን ነገሥታት ወድቀው ሲሰገዱለት ባየ ጊዜ እርሷ በትንቢት የተነገረላት ፣ በመዝሙር የተዘመረላት ቅድስት ድንግል ማርያም መሆኗን ተረዳ አወቀ። ያኔ አወቃት!
👉 ዛሬስ እንደ ቅዱስ ዮሴፍ ምሥጢርን ሳንመረምር እመቤታችን ያላወቅናት ስንቶቻችን ነን?
'' ስለዚህም ማርያም ሆይ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን! ''

❤5👍1👏1
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት ሃያ አምስት በዚህች ቀን 4ተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን።

❤4
“የበኲር ልጅዋን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም” ሲል ምን ማለቱ ነው?
“እስከ” የሚለውን ቃል አገባብ በተለያየ ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት እንደገባ በሚከተሉት ምሳሌዎችን እንመልከት፡፡
➾ “ የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከ ሞተችበት ቀን ድረስ ልጅ አልወለችም” 2ሳሙ.6፡23፡፡ አባባሉ ከሞተች በኋላ ልጅ ወለደች የሚል ይመስላል፡፡ ዳሩ ግን ሰው ከሞተ በኋላ ልጅ ሊወልድ ስለማይችል ትክክለኛው ትርጉም ሳትወልድ መሞትዋንና ልጅም እንደሌላት ለመግለጽ የተጠቀሰ መሆኑን ይገልጻል።
➾ “ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ” ሮሜ.5፡7፡፡ የሞት ንግሥና ከሙሴ በኋላ አለመቅረቱን የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ አነጋገሩ መቀጠሉን የሚገልጽ ክርስቶስ ሞትን በሞቱ እስኪሽር ድረስ።
➾ “እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማቴ.28፡20፡፡ ከዓለም ፍጻሜ በኋላ ከእናንተ እለያለሁ ማለቱ አይደለም፡፡ ከላይ በተገለጸው መሠረት “እስከ” የሚለው ቃል ፍጻሜ ላለው ነገር እንደሚገባ ሁሉ ፍጻሜ ለሌለው ነገርም ይገባል፡፡ ስለሆነም ወንጌላዊው ማቴዎስ “እስከትወልድ ድረስ አላወቃትም” በማለት ዮሴፍ ጌታን ከወለደች በኋላ በሴትና በወንድ ግብር ፍጹም አላወቃትም ማለቱ ነው፡፡ ዘላለማዊ ድንግል ነች እያለን ነው።

Telegram
ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
https://telegram.me/wwEotc
@ask_here_bot
@ask_here_bot
❤3👍3👏2

👍3❤1👏1