ሃይማኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
1.5K subscribers
1.09K photos
20 videos
13 files
247 links
Download Telegram
“ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤”
— ሉቃስ 22፥31

የወደቀው መልአክ ሰይጣን እግዚአብሔርን ለአላማው መለመን ከቻለ፤ ቅዱሳን መልአክት ስለኛ ሰዎች መዳን፣ ደስታና ሰላም መነኛ ይለምኑ ይሆን?!

ሩፋኤል - እግዚአብሔር ፈዋሼ ነው።
❤9
በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከመጽሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ሌላ የተጻፉ ቅዱሳት መጽሐፍት አሉ። እነዚህ መጽሐፍት ሐሳባቸው ፍጹም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተስማሚ ናቸው።

እነዚህ መጽሐፍት

ገድላት ፣ ድርሳናት ፣ የጸሎት መጽሐፍት እንዲሁም የምርምር (ስነ-ተፈጥሮ) መጽሐፍት ናቸው።
❤2👏1
🌼 እንኳን አደረሳችሁ 🌼

አዲሱ ዓመት

🌼 ህጻናት የሚያድጉበት
🌼 ተማሪዎች የሚመረቁበት
🌼 የታመሙት የሚድኑበት
🌼 የታሰሩበት የሚፈቱበት
🌼 የተሰደዱ የሚመለሱበት
🌼 ንስሐ የምንገባበት
🌼 ያላገባ የሚያገባበት
🌼 ሐገራችን ሰላም የሚሆንበት
🌼 በስራ የምንባረክበት

🌼🌼🌼🌼 ዓመት ይሁንልን 🌼🌼🌼🌼

@WwEotc
❤4🔥1
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና፦
²⁰ ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ አላቸው።

ይህ የጌታ መልአክ የተባለው ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ራጉኤል ነው። ቅዱስ ራጉኤል በብርሐናት ላይ የተሾመ መልአክ ነው። የስሙ ትርጉምም የብርሃን አለቃ ማለትን ነው።
🔥2
St. cyprian

+ " No human being can take God as his Father unless he takes the Church as his mother. "
❤1
“ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።”  — ሐዋርያት 5፥15

መጽሐፍ ቅዱስ የሐዋርያው ጴጥሮስ ጥላውን ይፈውስ እንደነበረ ይነግረናል። ይህም አዳኝ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በቅዱሳን ላይና በእነርሱ በሆነው ላይ ሁሉ እንዳለ ማሳያ ነው።

ጥላ የሚባለው በብርሐን መሰናክል የማፈጠር የአንድ አካል ጥቁር ምስል ነው። ያ ይፈውስ የነበረውም የጴጥሮስ ጥላም ይሄው አይነት ነው። ይህን ጥላ ነጮች Shadow Art ይሉታል። እኛ በምድር የተሳለ ጥቁር ስእል ማለት እንችላለን።

“ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።”— ሐዋርያት 5፥16

ተወዳጆች ሆይ የሰውነን ቅርስን ብቻ የሚያሳየው የጴጥሮስ  ጥላ እንዲህ በእግዚአብሔር ሐይል ተአምር ሲሰራ ካያችሁ፤ በወግና በስርአት በቅዱስ ትውፊት እንዲሁም ሐዋርያው የህይወት ታሪክ ላይ ተመርኩዞ የሚሳሉ ስእሎች ምነኛ ተአምር ይሰሩ ይሆን?!

ይህን አንድ ምሳሌ ሁሉም ቅዱሳት ስእላትም የእግዚአብሔር እያደረባቸው እንደሚፈውሱ ማሳያ ነው።

ይቆየን።
👍3❤2
" ወቅድመ ሥዕላ ስግዱ ወኢሰገደሰ ላቲ ይደምሰስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝክረ ስሙ ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን ፥

በሥዕሏም ፊት ሰገዱ ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክት ይደረግ ይሁን ይበሉ፡፡"
❤4
የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ከቁስጥንጥንያ ተነሥታ ከጌታችን መድኃኒችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ የጌታችን መስቀል ተአምራትን እንዳያደርግ አይሁድ በምቀኝነት ቀብረውት ነበርና የተቀበረበትን ቦታ የሚያሳያት አጥታ በመፈለግ ብዙ ጊዜ አሳለፈች፡፡ በኋላ ግን አንድ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊ አካባቢውን ነግሯት ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ ብትማፀን የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ መንበረ ጸባዖት ደርሶ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ አመለከታት፡፡ እርሷም በምልክቱ መሠረት ብታስቆፍር የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል አገኘች፤ ከእርሱ መስቀል ጋር ሁለት ወንበዴዎች የተሰቀሉበትን መስቀል አብራ አግኝታው ስለነበር የጌታችን መስቀል ለይታ ያወቀችበት መንገድ ግን ድውያንን በመፈወሱ፣ አንካሳ በማበርታቱ፣ ጎባጣን በማቅናቱ የዕውራንንም ዐይን በማብራቱ ነው፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው፡፡
እርስዋም መስከረም ፲፯ ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች፤ የደመራ ሥርዓት ከዚህ ሲያያዝ የመጣ ነው፤ የበረከት በዓል ያድርግልን፤አሜን፡፡
👏2❤1
ቅዱሳት ስእላትን መቃወም መቼ ተጀመረ?

ይህ ስእል ሉቃስ የሳለው ሥዕል ሲሆን በዘጠነኛው መ.ክ.ዘ. ላይ ኒቅያ (ታናሽ እስያ) በአንድ ባልቴት ቤት ውስጥ ነበረች፡፡ በዚያን ወቅት ከ829-842 ዓ.ም. በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር፡፡

ይህች ሴትም በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡ የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ፤ ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጒንጯ ላይ ወጋት፡፡

ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ፤ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡

ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሲሸሹ የእመቤታችን ሥዕልን የወጋው ወታደር ግን በተፈጸመው ድንቅ ተአምር የቅዱሳት ሥዕላት መጥፋት አለባቸው ከሚለው ክህደት ተጸጽቶ ንስሐ ገብቶ ወደ ገዳም ገባ፡፡
🥰7❤2🔥2
ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን፡፡

(ቅዳሴ ያዕቆብ ዘስሩግ)
👏3❤2
St. Theophan the Recluse

+
"The goal of human freedom is not in freedom itself, nor it is in man, but in God. By giving man freedom, God has yielded to mam a piece of His Divine authority, but with the intention that man himself would voluntarily bring it as a sacrifice to God, a most perfect offering. "
❤2
" ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤ ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና።"(የዮሐንስ ወንጌል 5:19) '' ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤" ማለቱ አንድም ከአብ ተለይቼ ብቻዬን እንድም የአምላክነት ስራ አልሠራም ሲል ነው። የአምላክነቱ ስራዎች የአብም የወልድም የመንፈስ ቅዱስም ሥራዎች ናቸውና። " የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም #ሦስት ናቸውና፤ #ሦስቱም #በአንድ #ይስማማሉ ።"(1ኛ ዮሐ 5:8)
🤩4
በከፍታም ብሆን በዝቅታ
ደስተኛ ነኝ ሁል ጊዜ በጌታ ❤

@WwEotc
👏2❤1
የእመቤታችን ክብር ከሰማያትና በሰማያት ውስጥ ካሉ ሁሉ የበለጠ የከበረ ነው። እርሷን የሚመስል ፍጡር አንድም እንኳስ የለም። እርሷ የእግዚአብሔር ወልድ እናት ነች። እርሷ የመጀመሪያዋ ክርስቲያን ነች።

@WwEotc
❤7
🌼 ዳንኤል 3:18 🌼

ለእግዚአብሔር መታመን ያለብን እርሱንም ማመስገን ያለብን ስላደረገልን ብቻ አይደለም። እግዚአብሔር ቢያደርግልንም ይመስገን ፤ ባያደርግልንም ይመስገን።

በትንቢተ ዳንኤል ላይ ያለውም ይህ ነው
። ሶስቱ ወጣቶች ወደ እሳቱ ሊጣሉ ባሉ ጊዜ እግዚአብሔር ባያድነን እንኳ ለእርሱ ታምነን እንሞታለን ነው ያሉት። ግን እግዚአብሔር ከእሳቱ አዳናቸው።

ዳንኤል 3:18 ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል ...
ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ ባያድነንም እንኳ፤ አማልክትህን እንደማናገለግል፣ ላቆምኸውም የወርቅ ምስል እንደማንሰግድ ዕወቅ።”
🥰2❤1
ስለ ተወገዘው መጽሐፍ አንዳንድ እውነታዎች

በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ያለውና በምእመናን እጅ የሚገኘው ''ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ'' አልተወገዘም❗️

በቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት የተላለፈበት መጽሐፍ ገና ለኅትመት ያልበቃ፣ በምእመናንም እጅ ያልደረሰ ነው።

ያ የተወገዘው መጽሐፍ፡
👉 ታትሞ ለምእመናን ያልተሰራጨ በስምም <<ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ>> ሳይሆን <<ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ>> የሚል ሲሆን

👉 በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ላይ ያልዋለ፣

👉 በገዳማት ውስጥ አንዳንድ ግለሰቦች ይዘውት በማኅበር ሲያነቡት የተገኘና ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚሉ ግለሰቦች በደብረ ሊባኖስ የነበራቸው እንቅስቃሴ የታወቀበት ምክንያት ሆኗል

የመጽሐፉ ምንጭ ሲጣራ፡

👉 ግለሰቦች በግዕዝ ከብራና ላይ አገኘነው በሚል በ A4 ወረቀት ለቅጅ ያዘጋጁትና ገዳም ውስጥ ይዘውት የቆዩ

👉 በነጻ ሊያሳትሙት ፈልገው ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልግ ደገኛ የዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ አባት ትክክለኛ ነው በሚል አንድ ጥራዝ በቢጫ ወረቀት አትመው የሰጧቸው በዃላም ያገዱት፤ በኋላም በግለሰቦች ኮፒ ተደርጎ ሦስት ገዳማት ላይ የደረሰ

በመጨረሻም ከ4 ዓመት በፊት በመምህራን ተደርሶበት እንዳይታተም የተደረገ ነው፡፡
....

አስቀድሜ እንዳልኩት የተወገዘው መጽሐፍ ስም "ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ" ሳይሆን "ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" የሚል ሲሆን፣ በገበያ ላይ በኅትመትም ሆነ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ አታገኙትም። ይልቁንም በቢጫ ወረቀት የግለሰብ እጅ ላይ የሚገኘውን፣ “ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን” የሚሉ ግለሰቦች ስካን አድርገው እርስ በእርስ የሚቀባበሉት ነው።

ይህን መጽሐፍ በስቴንስል ማባዣ (ማተሚያ) አንዱ ጥራዝ ከታተመ በዃላ Copy አደርገው በእጃቸው ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች፣ ከአጋግ ወደ ደብረ ሊባኖስ በመምጣት ራሳቸውን “ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን” በሚል ስም ዳግም ለማሳተም እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር። ነገር ግን በመምህራን ጥረት ተደርሶባቸው እንቅስቃሴው ለጊዜው ቆሟል። መጽሐፉ ከኅትመቱ በፊት ነው የተወገዘው። የደብረ ሊባኖሱም ሊቅ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የወሰዱት ከመታተሙና ከመሰራጨቱ በፊት እንዲታገድ ነበር። ደብረ ሊባኖስ እና ኢቲሳ አካባቢ ለማሳተም ይንቀሳቀሱ ስለነበር ነው ቀድሞ እርምጃ የተወሰደበት።

የመጀመሪያውን ጥራዝ በየዋህነት በስቴንስል ያተሙት አባት ስማቸው ያልተጠቀሰው፣ ግለሰቦቹ ኮፒ አድርገው ከወሰዱት በኋላ ሲመረመር ስህተት ስለተገኘበት ለማስተካከል እየሞከሩ ስለነበር እንዲሁም በስርዋጽ የገባ መጽሐፍ መሆኑ ዘግይቶ ስለታወቀ ነው።

ኦርቶዶክሳውያን ወገኖች፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆችንና ገድል አስጣይ ቲክቶከሮችን ሰምታችሁ አትወዛገቡ። በእጃችሁ ላይ ያለው መጽሐፍ የታገደው አይደለም። ገበያም ላይ የተወገዘውን አታገኙትም። ስለዚህ በፍጹም መወዛገብ አይገባም። ዝርዝርና የተሟላ መረጃ መስጠት ይገባ ነበር።

anyways ስለ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት መምህር ዳንኤል ሰይፍ ሚካኤል መግለጫ በዝርዝር ይሰጡበታል።
..
✍️
Maryamawit Henok Lemessa
❤3👏3
ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ አምላክ ነው።

እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ያለውን ሁሉን ያውቃል ይህ አምላካዊ ባሕርይ ነው።

ኢየሱስም በሰው አካል የተገለጠ እግዚአብሔር ነውና ሁሉን አዋቂ ነው።

“ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።” — ዮሐንስ 2፥24-25
❤4🥰4
በቅጡ 5 ደቂቃ ቆሞ መጸለይ የማይችል ሁሉ ነው ኮ አቡነ ተክለሃይማኖት እንዴት በአንድ እግራቸው ቆመው ጸለዩ ብሎ የሚጠይቀው?

መጽሐፍ ግን '' ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል ማር 9:23'' ይላል።

የጻድቁ በረከት ይደርብን።
❤4