በትምህርትና ጤና ክላስተር ስር የሚገኙ ተቋማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባቀዱት የ90 ቀን የጋራ እቅድ ውጤታማ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።
(ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትምህርትና ጤና ክላስተር ከጥቅምት 1/2019 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2019 ዓ.ም በ90 ቀናት በጋራ ለማከናወን በተዘጋጀ የማስፈጸሚያ እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የክላስተሩ አስተባባሪ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ የትምህርትና የጤና ስራዎችን በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስታውሰው በክላስተሩ የሚገኙ ተቋማት የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል እንዲሁም የጤና አገልግሎት ሽፋንና ተደራሽነትን በማሳደግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ከተረጂነት እንዲላቀቁ ለማስቻል የ90 ቀን የጋራ እቅድ አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸውን አመላክተዋል።
ኃላፊው አያይዘውም አፈጻጸሙን በየ15 ቀኑ በመገምገም የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞች ለማስቀጠልና በሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ የዛሬው መርሀግብር መዘጋጀቱን ጠቁመው በክላስተሩ የሚገኙ ተቋማት ልዩ ትኩረት የሚሹና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራትን በመለየት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

❤13😁1
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ጤና ቢሮ ፣ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን እና ለነገዋ ሴቶች የተሀድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል አመራሮች የተገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ አፈጻጸሙን አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤11
❤14😁6👎2
❤32💔7👏3👎2🎉2👍1😢1