የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
22.3K subscribers
1.46K photos
275 videos
84 files
1.73K links
﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student |

ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦

https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1
Download Telegram
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
አንዳንድ ጉዞዎች ከእይታ ባለፈ ነፍስን ያነጋግራሉ፤ ታሪክን ህያው አድርገው ልብን በጥልቅ ስሜት ይነካሉ። ወንድማችን ጀማሉዲን ወደ ቦስኒያ ካደረገው ጉዞ በኋላ በእንግሊዝኛ ያካፈለን ይህ ማስታወሻ፣ የአንድን ህዝብ ፅናት፣ እምነት እና ስነ-ልቦና ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

​እጅግ ስሜትን በሚሰረስር እና በርካታ ቁምነገሮችን ባዘለ መልኩ ወንድሜ ጀማል ኡዲን የገጠመውን ገጠመኝ እና አስተንትኖ እነሆ ከዚህ በታች በመጠኑ አቅርቤላችኋለው። አንብቡት፣ ነፍስን ያድሳል!

​"ከቦስኒያ ስመለስ ልቤ በእጅጉ ተነክቷል። በአንድ በኩል አይንን በሚማርክ የተፈጥሮ ውበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላም ገና ባላባራ እና ትውልድ በተሻገረ ጥልቅ ሀዘንና ስነ-ልቦናዊ ስብራት የተገነባችን ምድር በአዲስ እይታ እንድመለከት አድርጎኛል።

​አላህ (ሱ.ወ) ይህችን ምድር በተፈጥሮም ሆነ በመንፈሳዊ ግርማ ሞገስ አድሎታል። ለምለም አረንጓዴ ተራሮች፣ ንጹህ ወንዞች እና እንደ ምሰሶ ቆመው የሚታዩ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሚናራዎች... እነዚህ ሁሉ እስልምናን እና ሙስሊሞችን ከአውሮፓ እምብርት ላይ ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የተቃጣባቸውን ጭካኔ የተሞላበት ዘመቻ በፅናት የተቋቋመና የተረፈ ህዝብ ህያው ምስክሮች ናቸው።

​ፀጉረ-ወርቅ እና ሰማያዊ አይን ያላቸውን ኢማሞች፣ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎችን እና ሂጃብ የለበሱ እህቶችን እዛው ማግኘት አንድ ትልቅ እውነታን ያስታውሰናል። ምንም እንኳን አውሮፓዊ እና ስላቪክ (Slavic) ማንነት ቢኖራቸውም፣ እነዚህ ሰዎች በቅርቡ የሰለሙ ህዝቦች አይደሉም። ከገዛ ወገኖቻቸው እንደ ከሀዲ እና እምነት አፍራሽ ቢቆጠሩም፣ አላህን በጌትነቱ፣ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) በመልዕክተኛነታቸው በሙሉ ልብ የተቀበሉ የ15ኛ እና የ16ኛ ትውልድ ሙስሊሞች ናቸው።

​ዛሬ በጋዛ እና በሶሪያ የምናየውን አሳዛኝ እና ዘግናኝ እልቂት የሚያስታውስ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው እንኳን ወደ ኋላ አላሉም። ከሶሻሊዝም ስርዓት አስገዳጅ ሴኩላሪዝም በኋላም፣ ፊታቸውን በቀጥታ ወደ አላህ ነው የመለሱት። የዘር ማጥፋት ሰለባ የነበሩ ህዝቦች በመሆናቸው፣ ለጋዛ ያላቸውን ጥልቅ ስሜት እና አጋርነት በግልጽ ማየት ይቻላል። በተደጋጋሚ የቦስኒያን ባንዲራ እና የ'ስሬብሬኒካ' አበባን ከፍልስጤም ባንዲራ ጎን በክብር ተውለብልበው አይቻለሁ።

​ብዙዎቹ የቦስኒያ ሙስሊሞች ሰፊው የሙስሊሙ ኡማ እንደረሳቸው ይሰማቸዋል። ነገር ግን በራሳቸው የሚተማመኑ እና ለራሳቸው ትልቅ ክብር ያላቸው በመሆናቸው፣ ለይስሙላ የሚደረግ እርዳታን ወይም ባዶ ርህራሄን አይፈልጉም። እነሱ የሚፈልጉት እውነተኛ ወንድማማችነትን እና ትስስርን ነው።

ብዙ ጊዜ እድለኝነትን የምንለካው በቁሳቁስ ምቾት ነው። ነገር ግን መከራን መቋቋም፣ ገንዘብ ሊገዛው የማይችለውን መንፈሳዊ ጥንካሬን እና ተወኩልን ያጎናጽፋል።

​ዛሬም ድረስ በዘመናችን እንዳሉት 'አስሀቡል ኡኽዱድ'፣ ከባድ ግፍ እና ሰቆቃ ሲደርስባቸው ፅናታቸውን ላላጡ ወንድም እና እህቶቻችን በቻልነውና አቅማችን በፈቀደው ልክ ከጎናቸው እንቁምላቸው።

አላህ ​የቦስኒያን ህዝብ በረካ ያድርገው፤ አሁንም ድረስ ከእስልምና ጠላቶች ከሚሰነዘርባቸው ተከታታይ ዛቻ እና አደጋም ይጠብቃቸው። አሚን!

| ፌስቡክ | ዋትስአፕ |
👍48❤16😢2
ለሚቀጥለው ወር በተዘጋጀው የኡምራ ፓኬጅ በሸይኽ አብዱልዋሲዕ አህመድ መሪነትና በጋዜጠኛ አብዱረሕማን አሚን አስተባባሪበት በአላህ ፍቃድ አብረን እንጓዛለን።

በነዚህ ቀናት ኡምራ ለማድረግ የነያችሁ ጉዟችሁን ከከውከብ ትራቭል ጋር ማድረግ ትችላላችሁ።

የጉዟችን ዝርዝር መረጃዎች፦
• የጉዞ ጊዜ፡ ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 03
• የቆይታ ጊዜ፡ 7 ቀናት በመካ እና 3 ቀናት በመዲና

በከውከብ ትራቭል ልዩ የጉዞ ጥቅል ውስጥ የተካተቱት፦
• የአየር ትኬት
• የዑምራ ቪዛ
• ምቹ የውስጥ ትራንስፖርት
• ደረጃውን የጠበቀ የሆቴል ማረፊያ
• የሁለቱንም ከተሞች ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት

ለበለጠ መረጃ እና ምዝገባ፦
📞 09 46 28 55 55
📞 09 11 27 40 33

📍 አድራሻ፡ ጀሞ 1፣ ሳባ ሕንፃ

ከውከብ ትራቭል - ታማኝ የጉዞ አጋርዎ!
❤19
የዘመኑ ምርጥ የዲፕሎማሲ ቀልድ! 🤣

​የእስራኤሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳዓር ሰሞኑን ቀልድ አምሮታል መሰል ለሚዲያ ቀርቦ እንዲህ ይላል፦

​"ሰዎች እስራኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተገልላለች ይላሉ... ይሄ እኮ ፈጽሞ የማይረባ ውሸት ነው! ብዙ ሀገራት ወደ እኛ እየመጡ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንደሚፈልጉ እየነገሩን ነው። ለማስረጃ ያህል... ልብ በሉ... በዚህ ሳምንት የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እኛ ጋር መጥቶ ነበር!"

​እውነትም ታላቅ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ድል! 👏😂

​አይ የዓለም ልዕለ ኃያልነት! የዓለም መንግሥታት ሁሉ በተግባራቸው አፍረውና ህዝባቸውን ሰግተው ጀርባቸውን ቢሰጡም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶች ውግዘት ቢያዘንቡም፣ አውሮፓውያን ቢሸሹም... ዋናው ነገር ኮንጎ ከእስራኤል ጎን ናት!

​ከ190 በላይ የዓለም ሀገራት ቢያገሉን ምን ይገርማል? ኮንጎ መጥታ ከጎበኘችንማ እንዴት "ተገልለናል" እንላለን?

​የእስራኤል መንግሥት የደረሰበትን የዲፕሎማሲ ኪሳራና የብቸኝነት ጥግ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ፖለቲካዊ ኮሜዲ ከየትም አይገኝም!

​እስኪ ኮንጎን አምጡልን! 🇨🇩🤝🇮🇱 😅

ቪዲዮው ፌስቡክ ኮሜንት ላይ አለ።
❤62👍19😱6🙉4🙊2
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
በቁም እስር ላይ ያሉን የሰው ልጆች በአውሬዎች አስከብቦ ማስፈራራትና ማሰቃየት... ይህ በዚህ ዘመን የምንሰማው ሳይሆን በጨለማው ዘመን የነበሩ ጨካኝ ነገሥታት እንኳ ለማድረግ የሚከብዳቸው ተግባር ነው። ነገር ግን፣ ይሄ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በእስራኤል ምድር ሊተገበር የታሰበ እውነታ ነበር።

​የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር የሆነው ኢታማር ቤን-ግቪር፣ ፍልስጤማውያን የፖለቲካ እስረኞች በሚገኙበት የኬትዚኦት እስር ቤት ዙሪያ፣ "አዞዎችን" በማስቀመጥ እስረኞቹን በከፍተኛ ፍርሃትና ሥነ-ልቦናዊ ስቃይ ውስጥ ለማኖር አውዛጋቢ እቅድ አውጥቶ ነበር።

ታዲያ እቅዱ ለምን ተገታ?

​የእስራኤል ፍርድ ቤት እቅዱን በጊዜያዊነት ያገደው ግን፣ የታሳሪዎቹ መብት ተገፎ፣ የሰው ልጅ በአውሬ ሊበላ ይችላል በሚል ስጋት ወይንም "ሰብዓዊ መብት" ተሟጋቾች በፈጠሩት ጫና አይደለም።

​ይልቁንም፣ 'ሌት ዘ ኤኒማልስ ሊቭ' የተሰኘ የእንስሳት መብት ተሟጋች ቡድን ያቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ነው። ፍርድ ቤቱ እግዱን የጣለው፦ "ይህ አሰራር በአዞዎቹ (በእንስሳቱ) ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል" በሚል ስጋት ነው።

ልብ የሚሰብረው እውነታ እዚህ ላይ ነው!

​ዓለም ለሰዎች ሰብዓዊ መብት መቆሙ ቀርቶ፣ ለእስራኤል ፍርድ ቤትም ሆነ ለመብት ተሟጋቾች፣ ከፍልስጤማውያን እስረኞች ሕይወትና ሥነ-ልቦናዊ ደህንነት ይልቅ፣ የአዞዎቹ ደህንነት በለጠባቸው!

​ሰውየው በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰው ልጆችን ከቀን በቀን በአዞዎች አፍ ፊት ለማኖር ሲያቅድ፣ የዓለም ፍርድ ቤቶች የሚያስቡት ስለ እንስሳቱ እንጂ ስለ ፍልስጤማውያኑ አይደለም። ይህ በእውነት የእስራኤላውያንን ጭካኔ ብቻ ሳይሆን፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለፍልስጤማውያን ያለውን ግድየለሽነትና ደብል ስታንዳርድ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ይህ ግፍ ግን እንዲህ አይቀጥልም፣ በአላህ ፍቃድ ፍልስጤማውያን ይህንን ሰው* በ*ላ ስርኣት ገርስሰው በነጻነት የሚኖሩበት ቀን ሩቅ አይደለም!

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
😢84❤31👍2🔥2
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት የተመዘገበው የአብዱልረህማን አል-ሰይድ አስደናቂ ድል፣ በዲሞክራቶችም ሆነ በሪፐብሊካኖች ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ከመፍጠሩም በላይ፣ የአሜሪካን የፖለቲካ ታሪክ አቅጣጫ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረ ይገኛል።

​በአሜሪካ የጽዮናውያን ዋነኛ የፖለቲካ ደጋፊ እና ሎቢስት የሆነው "አይፓክ" እና አጋሮቹ፣ የአብዱልረህማንን ተቀናቃኝ ለማሳለፍ ብቻ 65 ሚሊዮን ዶላር አፍስሰው ነበር።

​ይህን ያህል የገንዘብ ጎርፍ ለምን አስፈለገ? ከተባለ መልሱ ግልጽ ነው፤ የአሜሪካን ግብር ከፋይ ገንዘብ፣ የጦር መሳሪያ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የ"ድምጽን በድምጽ የመሻር" መብት በመጠቀም በፍልስጤም ህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያለውን የዘር ማጥፋት ያለከልካይ ለማስቀጠል ስለፈለጉ ነው።

​በደንብ አስቡት፣ አይፓክ በአንድ የሴኔት ወንበር ምርጫ ላይ የራሱን ተላላኪ ዕጩ ለማሳለፍ ብቻ 65 ሚሊዮን ዶላር አፈሰሰ። በመጨረሻ ግን... በሕዝብ ድምጽ ተሸነፈ!

​ይህ የምርጫ ውጤት ከአንድ ግለሰብ ማሸነፍ ባለፈ እጅግ ትልቅ ትርጉም አለው። ላለፉት ዓመታት የተፈጸመውን ጭ*ፍጨ*ፋ በቅርበት የተከታተለው ተራው አሜሪካዊ መራጭ፤ የሀገሩ ፖለቲካ በገንዘብ በሚገዙ የውጭ ሎቢስቶች ሳይሆን፣ በሕዝቡ ፍላጎት፣ እሴትና ህሊና እንዲመራ ያለውን ጽኑ አቋም አሳይቷል።

ቀድሞ በጽዮናውያን ሎቢ (አይፓክ) መደገፍ ለአንድ ፖለቲከኛ ትልቅ የድል ካርድ ተደርጎ ይወሰድ ነበር። ዛሬ ግን በአብዛኛው የአሜሪካ ክፍል የነሱ ድጋፍ ማግኘት እንደ ትልቅ የፖለቲካ ኪሳራና ውርደት መቆጠር ጀምሯል። የትኛውም የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ የሎቢስቶች ጥረት ከተራው ዜጋ ድምጽ ሊበልጥ አይችልም። የሕዝብ ገንዘብም ንጹሃንን ለመጨፍጨፍ መዋል የለበትም።

​የአሜሪካ ሕዝብ ግብሩ እና ሀብቱ የውጭ ሀገር ጦርነቶችንና ጭፍጨፋዎችን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ሳይሆን፣ ለፍትህ እና ለራሱ ሕዝብ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንዲውል አጥብቆ እየጠየቀ መሆኑን የሚቺጋኑ ድል በግልጽ አሳይቷል። ገንዘብ የሕዝብን ድምጽ መግዛት ያቃተው ታሪካዊ አጋጣሚ!

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
1❤86👍24🔥4
ክርስትናን በርግጥ የመሰረተው ማነው?

​ዛሬ በስፋት የሚታወቀው የክርስትና ሃይማኖት ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት በቀጥታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሰረተ ሳይሆን፣ በጠርሴሱ ጳውሎስ የተቀረጸ መሆኑን የሚከራከሩ የታሪክና የነገረ-መለኮት ምሁራን አሉ። ጳውሎስ በሥጋ አይቶትም ሆነ አግኝቶት የማያውቀውን የኢየሱስን ታሪካዊ ህይወት ወስዶ፣ ኢየሱስም ሆነ የመጀመሪያዎቹ ደቀመዛሙርት ወደማያውቁት አዲስ የድነት ርዕዮተ-ዓለም ቀይሮታል። ከእርሱ በፊት ከነበሩት የኢየሱስ የቅርብ ተከታዮች ትምህርት የተለየ እና የሙሴን ህግጋት የሚሽር አዲስ ወንጌል ይዞ ብቅ ማለቱ፣ ከመጀመሪያዋ የኢየሩሳሌም አማኝ አባላት እና ከኢየሱስ ተከታዮች ጋር ከፍተኛ የሥነ-መለኮትና የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ከትቶት ነበር።

​ይህንን ሃሳብ ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሃያም ማኮቢ በመጽሐፋቸው በሰፊው ዳስሰውታል። ማኮቢ እንዳብራሩት፣ የጳውሎስ ትምህርት ከንጹሑ የኢየሱስ አስተምህሮ የተገኘ ሳይሆን፣ በዘመኑ ከነበሩት የግሪክ ጣዖት አምልኮዎች የተቀዳና የኢየሱስን ትክክለኛ መሲህነት ያዛባ አዲስ ሃይማኖት ነው። በመሆኑም ዛሬ የምናየው ክርስትና የኢየሱስን ቀጥተኛ አስተምህሮ ሳይሆን፣ ጳውሎስ የራሱን ራእዮች እና አመለካከቶች ተጠቅሞ የፈጠረውን እምነት መሆኑን መገንዘብ እንችላለን።

• Hyam Maccoby, The Mythmaker: Paul and The Invention of Christianity, Chapter 1: The Problem of Paul.

.
.

⛳️ በዚህ ጉዳይ እንቀጥላለን!

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
1👍82❤18👏12
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
በአሜሪካ ሚቺጋን ግዛት የሪፐብሊካን ፓርቲ የፕራይመሪ ምርጫ ላይ የተከሰተው ታሪክ፣ ማንነቱን ለሚክድና ሃይማኖቱን ለዱንያ ጥቅም ለሚሸጥ ሁሉ ትልቅ ማስተማሪያ ነው።

​አሚር ሀሰን የተባለው ግለሰብ፣ ቀድሞ ሙስሊም የነበረና በኋላ ግን ሃይማኖቱን ቀይሮ ክርስቲያን መሆኑን ያወጀ ሰው ነው። ይህ ሰው በጽንፈኛ ፖለቲከኞች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ሲል፣ እጅግ አክራሪ፣ ፀረ-ሙስሊምና ፀረ-ስደተኛ አቋሞችን ማንጸባረቅ ጀመረ።

በዚህ የክህደት መንገዱም ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ከኮንግረስ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን እና ከሴናተር ቲም ስኮት ሳይቀር ሙሉ ድጋፍን (Endorsement) አገኘ። በገንዘብም በኩል ከፍተኛ ዶላር በማሰባሰብ፣ "አሁንማ ማንም አያቆመኝም" ብሎ የተመካበት ጊዜ ነበር።

​ነገር ግን የአላህ (ሱ.ወ) ጥበብና ፍትህ አስገራሚ ነው። የቱንም ያህል ማንነትህን ብትክድና ሙስሊሞችን ብትጠላም፣ ፀረ-ሙስሊም የሆኑ ዘረኞች መቼም ቢሆን በሙሉ ልብ አይቀበሉህም። አሚር ክርስቲያን ነኝ ብሎ ቢምልም፣ ዘረኞቹ መራጮች ስሙ "አረብኛ/ሙስሊም" ስለሚመስል ብቻ አላመኑትም፤ ድምፃቸውንም ነፈጉት። ከዚህም በላይ አላህ ይህንን ግለሰብ ያዋረደውና መሳለቂያ ያደረገው በጠንካራ ተፎካካሪ እጅ አይደለም!

​አሚር የተሸነፈው ቶም ስሚዝ ለተባለ ግለሰብ ሲሆን፣ ይህ አሸናፊ ሰው፦

⛳️ ​በፌስቡክ ገጹ 95 ብቻ ተከታዮች ፎሎወሮች ያሉት፣

⛳️ ​ለምርጫው ከ2,000 ዶላር በታች ያወጣ፣

⛳️ ​እና ከሁሉ በላይ ደግሞ "ከምርጫው ራሴን አግልያለሁ" ብሎ ላሳወቀና "ለሌላ እጩ ድምፃችሁን ስጡ" በማለት ቅስቀሳውን ላቆመ ሰው ነበር!

​ከምርጫው ራሱን ባገለለና ምንም ዓይነት የፖለቲካ ክብደት በሌለው ሰው መሸነፍ፣ ተራ ሽንፈት ሳይሆን ታሪክ የማይረሳው መለኮታዊ ውርደት ነው። እምነትን ሸጦ ክብርን ከሰው ልጆች መፈለግ መጨረሻው ኪሳራ ነው። ታላቁ ጌታችን አላህ በቅዱስ ቁርኣን ላይ፣ እውነተኛ ክብር ከማን ዘንድ እንደሚገኝ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል፡-

“እነዚያ ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ እነሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን ልቅናውም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው፡፡”
— አን-ኒሳዕ (4:139)

​የሰዎችን ውዴታ ለማግኘት ሲባል የአላህን መንገድ መተው የሚያስከትለውን አሳፋሪ ውድቀት፣ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በሚከተለው ሐዲሳቸው እንደሚከተለው ገልጸውታል፡-

​"አላህን በማስቆጣት የሰዎችን ውዴታ የፈለገ ሰው፣ አላህም በእርሱ ላይ ይቆጣል፤ ሰዎችንም በእርሱ ላይ ያስቆጣበታል።" (ሱነን አል-ቲርሚዚ 2414)

​ሃይማኖቱን ሸጦ ዱንያን ለማግኘት የሞከረ፣ አላህ በዱንያም እንዲህ መሳለቂያ ያደርገዋል፤ የአኼራውም ዕጣ ፈንታ የከፋ ይሆናል። አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን፤ ማንነታችንንና እምነታችንን ጠብቀን፣ ለፈጣሪያችን ብቻ አድረን በክብር የምንኖር ያድርገን!

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
👍117❤47🙊1
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ስሜታዊ ፍጡር ነው። በዘመናዊው የሥነ-ልቦና እና የፊዚዮሎጂ ሳይንስ እንደተረጋገጠው፣ በአካል መነካካት በሰውነታችን ውስጥ እንደ "ኦክሲቶሲን" እና "ዶፓሚን" ያሉ የቅርበት እና የስሜት መነሳሳትን የሚፈጥሩ ሆርሞኖች እንዲመረቱ ያደርጋል። ንክኪ በሁለት ሰዎች መካከል ያለውን ሥነ-ልቦናዊ የርቀት ግድግዳ የማፍረስ ከፍተኛ ኃይል አለው።

​እስልምና ይህንን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ (ፍትወተ-ሥጋ) በሚገባ ያውቃል። በመሆኑም ሎጂኩ እጅግ ግልጽ ነው፦ "አንድን አደጋ ለመከላከል፣ ወደ አደጋው የሚያደርሱትን መንገዶች በሙሉ መዝጋት ያስፈልጋል።" አንድ ሰው በሚያዳልጥ ጭቃ ላይ እየተንሸራተተ "አልወድቅም" ብሎ ማሰብ እንደማይችለው ሁሉ፣ የሰውን ልጅ ከተፈጥሯዊ ስሜቱ ጋር እያጋጩ "በንጹህ ልብ ከተደረገ ችግር የለውም" ማለት ምክንያታዊነት የጎደለው የዋህነት ነው። ለዚህም ነው እስልምና መጨባበጥን እንደ አንድ የዝሙት መግቢያ በመቁጠር አስቀድሞ በር የሚዘጋው።

መጽሀፍ ቅዱስ በማቴዎስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 5፣ ቁጥር 28 ፦ "ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል"። ይላል። ​እዚህ ላይ አንድ መሠረታዊ ጥያቄ እናንሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ "ማየት" ብቻውን የልብን ንጽህና አጉድፎ ወደ "ልብ ዝሙት" ያደርሳል ብሎ ካመነ፣ ከእይታ በበለጠ እጅግ ጠንካራ ስሜትን የሚቀሰቅሰው "አካላዊ ንክኪ (መጨባበጥ)" እንዴት "በንጹህ ልብ" በሚል ሰበብ ችላ ሊባል ይችላል? እይታ ኃጢአት ከሆነ፣ መነካካት በሎጂክ ደረጃ የከፋ ነው።

አላህ የሰው ልጅን የፈጠረ ጌታ እንደመሆኑ፣ ለሰው ልጅ የቱ እንደሚበጀው አስቀድሞ በማወቅ መከላከያ አጥርን አበጅቶለታል። እስልምና እጅግ ተግባራዊ (Practical) የሆነ ዲን ነው። በሽታው ከመጣ በኋላ መድኃኒት ከመፈለግ፣ በሽታው የሚመጣበትን መንገድ አስቀድሞ ማድረቅን የሚመርጥ መለኮታዊ ሀይማኖት ነው።

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
👍101❤19👏8🔥5
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
ክርስቲያን ወገኖች "ጅን"ን በተመለከተ ባለው የእስልምና አስተምህሮት ዙሪያ የሚሳለቁት፣ ቃሉን ከራሳቸው የ"ጋኔን" (እርኩስ መንፈስ) ትርጓሜ ጋር በማምታታት ነው። በክርስትና አስተምህሮ ጋኔን ማለት ወደ ንስሐ የማይመለስና የወደቀ እርኩስ መንፈስ ነው። "ታዲያ ከእርኩስ መንፈስ ጋር እንዴት ወንድማማችነት ይፈጠራል?" ብለው መገረማቸው የዚሁ የተሳሳተ መነጽር ውጤት ነው።

​እውነታው ግን እጅግ የተለየ ነው። በእስልምና ጅን ማለት ልክ እንደ ሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ የተሰጠው፣ የሚያስብ እና የራሱ ምርጫ ያለው ፍጡር ነው። በመሆኑም ከነሱ ውስጥ አላህን የሚያመልኩ ደጋጎች እንዳሉ ሁሉ፣ የሚያምፁ እርኩሳንም (ሰይጣናት) አሉ። እስልምና በእምነት "ወንድሞቻችን" የሚለው እነዚያን ፈጣሪያቸውን አውቀው በጎ መንገድን የመረጡትን አማኝ ጅኖችን እንጂ፣ አጥፊዎቹን አጋንንት አይደለም። ወንድማማችነት የሚገነባው በአምልኮ አንድነት እንጂ፣ በፍጡርነት የዘር ሐረግ አይደለም።

​ይህንን ሀሳብ የሚያጣጥሉ ወገኖች፣ ራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ቢመዝኑት ተመሳሳይ ሎጂክ ያገኛሉ። በራእይ ዮሐንስ ምዕራፍ 22 ቁጥር 9 ላይ፣ ዮሐንስ ላናገረው መልአክ ሊሰግድለት ሲል፣ መልአኩ እንዲህ ብሎ ገሰጸው፦ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር... አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ።"

​እዚህ ላይ መሠረታዊ ጥያቄ እናንሳ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በአይን የማይታይ መንፈሳዊ ፍጡር የሆነውን "መልአክ" የሰው ልጆች "ወንድምና አብሮ ባሪያ" መሆኑን ካረጋገጠ፣ እስልምና ነጻ ፍቃድ ኖሯቸው አላህን የሚያመልኩ መንፈሳዊ ፍጡራንን (አማኝ ጅኖችን) "የእምነት ወንድሞቻችን ናቸው" ሲል ለምን እንግዳ ይሆንባቸዋል? ትምህርቱ እጅግ ግልጽ ነው፤ በፈጣሪ ፊት የየትኛውም ፍጡር ክብርና ዝምድና የሚለካው፣ ለጌታው ባለው ፍጹም ታዛዥነት እንጂ በተፈጠረበት አካል አይደለም! ተውሒድ (አምላክን በብቸኝነት ማምለክ) በሰዎችና በጅኖች መካከል ያለውን ልዩነት አፍርሶ የሚያስተሳስር ታላቅ የወንድማማችነት ዘለበት ነው!

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
1👍69❤23
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
አላህ የፍጥረታትን መጨረሻ አስቀድሞ ያውቃል። ይህ መለኮታዊ ዕውቀቱ ፍጹም መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን "አስቀድሞ አወቀ" ማለት "አስገድዶ አሠራ" ማለት አይደለም። ለምሳሌ፣ አንድ ብቁ መምህር የትኛው ተማሪው እንደሚያልፍና የትኛው በስንፍናው ምክንያት እንደሚወድቅ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፤ ወረቀት ላይም ሊጽፈው ይችላል። ተማሪው ሲወድቅ ግን የወደቀው መምህሩ አስቀድሞ ስላወቀና ስለጻፈው ሳይሆን፣ የራሱ ምርጫና ስንፍና ስላመጣበት ነው። አላህም ሰዎች በነጻ ምርጫቸው ምን እንደሚሠሩ አስቀድሞ ያውቃል፤ አዋቂነቱ ግን የሰዎችን ነጻ ምርጫ አይነጥቅም።

አስተያየት ሰጪው ያነሳው ጥያቄ አዲስ አይደለም፤ ከ1400 ዓመታት በፊት ታላላቆቹ ሰሐባዎች ልክ እንደዚሁ ነብዩን (ﷺ) ጠይቀዋቸው ነበር። "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! መጨረሻችን አስቀድሞ የታወቀ ከሆነ፣ ለምን ሥራን ትተን በውሳኔያችን ላይ ብቻ አንደገፍም?" አሏቸው። የነብዩ (ﷺ) ምላሽ እጅግ ድንቅ እና ሎጂካዊ ነበር፦ "ሥሩ! (መልካም ተግባርን ፈጽሙ)፤ ሁሉም ሰው ለተፈጠረለት (ለተዘጋጀለት) ነገር ይገራል (ይመቻችለታል)።" [1]

​ይህ ማለት፣ አንተ የጀነት ሰዎች ከሚሠሩት መልካም ተግባር ጋር ራስህን ካገኘኸው፣ አላህ ለጀነት እያገራህ መሆኑን ታውቃለህ ማለት ነው። የገሀነም ሰዎች መጨረሻቸው የማይታወቀው እኮ፣ በምርጫቸው የገሀነምን ተግባር (ክህደትንና አመጽን) ስለፈጸሙ ነው። ስለዚህ አንድ ሙስሊም "ለገሀነም አለመወሰኔን በምን አወቅኩ?" ብሎ ተስፋ አይቆርጥም፤ ይልቁንም በአላህ እዝነት ተስፋ እያደረገ ወደ ጀነት የሚያደርሰውን ተግባር ይፈጽማል።

​ይህ አስተያየት ሰጪ የራሱን መጽሐፍ ቅዱስ በቅጡ ቢያነብ ኖሮ፣ ይህንን የ"ቀደር" ጽንሰ-ሀሳብ ነቅፎ ባልተሳለቀ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጳውሎስ፣ እግዚአብሔር አንዳንዶችን አስቀድሞ ለጥፋት እንዳዘጋጃቸው በግልጽ ጽፏል።

​ወደ ሮሜ ሰዎች በተጻፈው መልእክት ላይ እንዲህ ይላል፦ "ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?... እግዚአብሔር ቁጣውን ሊያሳይ ኃይሉንም ሊገልጥ ወዶ፥ ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎች በብዙ ትዕግሥት ከቻለ... እንግዲህ ምን እንላለን?" [2]

​እንግዲህ አስተውሉ! መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ፈጣሪ "ለጥፋት (ለገሀነም) የተዘጋጁ የቁጣ ዕቃዎች (ሰዎች)" እንዳሉ እየተናገረ፣ ተቺው ግን ሶሒሕ ሙስሊምን ጠቅሶ እስልምናን ይተቻል። ታዲያ በእሱ ሎጂክ መሠረት አጸፋዊ ጥያቄ እናንሳለት፦ "መጽሐፍ ቅዱስህ ለጥፋት የተዘጋጁ ዕቃዎች አሉ ካለ፣ አንተ ራስህ ለጥፋት ከተዘጋጁት የቁጣ ዕቃዎች መካከል አለመሆንህን በምን አወቅክ?"

ማጠቃለያ

የአላህን ዘላለማዊ ዕውቀትና የሰውን ልጅ ነጻ ምርጫ ማመዛዘን የጠለቀ ዲናዊ እውቀትን ይጠይቃል። እስልምና የሰው ልጅ በተስፋና በፍርሃት መካከል ሆኖ የጌታውን እዝነት እንዲሻ ሲያስተምር፣ ተቺዎች ግን የራሳቸውን መጽሐፍ ድንጋጌ ዘንግተው እንዲህ በከንቱ ትችት ይወድቃሉ።

​የግርጌ ማስታወሻዎች፦

[1] ሶሒሕ አል-ቡኻሪ፣ ሐዲስ ቁጥር 6605፤ እንዲሁም ሶሒሕ ሙስሊም 2647

[2] መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወደ ሮሜ ሰዎች፣ ምዕራፍ 9፣ ከቁጥር 21-22

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
👍55❤23👏3🤷3
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
Photo
እፎይ የተሰኘው የካራ እምነት ተከታይ በሰሒሕ ሙስሊም ላይ የሰፈረውን ይህንን ሐዲስ አንስቶ ያቀረበው ትችት፣ የአላህን መሐሪነትና የሰውን ተፈጥሮ በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው። ሐዲሱ እኮ ሰዎችን ለኃጢአት የሚያነሳሳ ሳይሆን፣ በተቃራኒው ተስፋ መቁረጥን የሚያክም ታላቅ ነብያዊ መድኃኒት ነው። የሰው ልጅ እንደ መላእክት ኃጢአት የማይሠራ ፍጹም ፍጡር ሆኖ አልተፈጠረም፤ ስህተት ሰርቶ መመለስ የሚችል ነጻ ፍቃድ የተሰጠው ፍጡር ነው። አላህ እጅግ መሐሪ በመሆኑ፣ ይህ መለኮታዊ ባሕሪው ይቅርታ ጠያቂዎችን በምህረት የሚመለከትበት ማንነቱ ነው። ሰዎች ፈጽሞ የማይሳሳቱ ቢሆኑ ኖሮ፣ የመላእክትን ባህሪ ይላበሱ ነበር እንጂ የሰው ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ በተግባር ባልታየ ነበር። ስለዚህ ሐዲሱ "ኃጢአት ሥሩ" እያለ ሳይሆን፣ "ብትሳሳቱም የአላህ እዝነት ከኃጢአታችሁ ይሰፋልና በተስፋ ወደ እርሱ ተመለሱ" የሚል የጠለቀ የውዴታና የተስፋ ቋንቋ ነው። [1]

​ይህ ግለሰብ ይህንን መለኮታዊ የእዝነት ቋንቋ ከማጣጣሉ በፊት፣ እስኪ የራሱን መጽሐፍ ቅዱስ ቢያስተውለው ኖሮ ልክ እንደ ሐዲሱ ዓይነት ተመሳሳይ ትምህርት ባገኘበት ነበር። ኢየሱስ በሉቃስ ወንጌል ላይ፦ "ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል" በማለት ያስተምራል። [2] ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ "ከጻድቃን ይልቅ በኃጢአተኛው ንስሐ በሰማይ ትልቅ ደስታ ይሆናል" ሲል፣ አምላክ ሰዎች ጻድቅ ከመሆን ይልቅ ኃጢአት እንዲሠሩ ይፈልጋል ማለት ነውን? ብለን ብንጠይቀው አይደለም እንደሚል ግልጽ ነው፤ የንስሐን እና የምህረትን ታላቅነት ማሳየቱ እንደሆነ ማብራራቱ አይቀርም።

​ታዲያ ለራሱ መጽሐፍ ሲሆን "የፈጣሪ ጸጋ መገለጫ ነው" ብሎ የሚያስተምረውን ሎጂክ፣ በእስልምና አስተምህሮ ላይ ሲያገኘው ለምን ጠማማ ትርጉም ይሰጠዋል? ይህ ጥላቻ የፈጠረው ግልጽ የሚዛን መሳት ነው። እስልምና የሰው ልጅን ደካማ ተፈጥሮ በሚገባ ስለሚያውቅ፣ ኃጢአት ቢሠራ እንኳ በጸጸት ርቆ እንዳይቀር የይቅርታን በር ወለል አድርጎ ይከፍትለታል። ይህንን ታላቅ የአላህ እዝነት በማጣመም ከሚሳለቅ፣ "ኃጢአት ሰርተን ንስሐ ከገባን፣ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን በላይ በሰማይ ትልቅ ደስታ እንፈጥራለን" የሚለውን የራሱን መጽሐፍ ቅዱስ ቃል እኩል ቢተቸው ኖሮ ቢያንስ ለሎጂኩ ታማኝ መሆኑን ባሳየ ነበር።

​የግርጌ ማስታወሻዎች፦

[1] ሰሒሕ ሙስሊም፣ ሐዲስ ቁጥር 2749።

[2] መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሉቃስ ወንጌል፣ ምዕራፍ 15፣ ቁጥር 7

ፌስቡክ | ዋትስአፕ
❤96👍44🔥3🤩3🥰1