የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture
2.78K subscribers
688 photos
11 videos
56 files
139 links
The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture
Telegram @yehas

#For Your Comment or Info Use
@arcnat
Download Telegram
"ቤት በመቀመጥ ሀላፊነታችንን እንወጣ
ስለምንወዳቸው ሰዎች ስንል ከቤት አንውጣ"
Natenael Firew:
ሰላም ሰላም….፣ሰላም ይብዛላችሁ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
እንደሚታወቀዉ አብዛኞቻችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በቤታችን ቁጭ ብለናል፡፡
🙈🙈🙈🙈🙈🙈
ይህ ለ አርክቴክቶችና ለአርክቴክቸር ተማሪዎች የማይገኝ የህወት ዘመን ዕድል ነዉ፡፡ 😁😁😁😁
አብዛኞቻችን ግን ይህን ወርቃማ ጊዜ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዶች ላይ የሚሰሩ ሜሞችን በመጎርጎር (scroll) በማድረግ ጊዜያችንን በከንቱ እያሳለፍን ነዉ፡፡ በፕሮጀክትና በስራ ምክንያት ራሳችንን ወደ ፍጹም አርክቴክትነት ማሳደግ ያገደንን ጊዜ አሁን ላይ ያለ ገደብ አግኝተነዋል…….ስለዚህ ምን በማድረግ ማሳለፍ እንችላለን፡፡🤔🤔🤔🤔

📕📙📕📔📓ጊዜ ከማጣትም ይሁን ከስንፍና ጋር ተያይዞ ትልቁ ጉድለታችን መጽሀፍትን አለማንበብ ነዉ፡፡ በድርሰት ዓለም ዉስጥ፤ኪነ-ህንጻ ታሪክን፣ ፍልስፍናን አንዲሁም የኑሮን ዘይቤ መናገር የሚችል የጥበብ ዘርፍ በመሆኑ የስነ-ጽሁፍ ጥበብ ዉስጥ ገብቶ በዉብ ገላጭ ቃላት እየተሽሞኖሞነ የሚቀርብ ወሳኝ አምድ ነዉ፡፡ ይህም ማለት በገጸ-ባህሪየቶች የህይወት ዉጣ ዉረድ ዉስጥ የሰዉ ልጅ ፍላጎት እና አስተሳሰብ በኪነ ህንጻዉ ተንጸባርቆ ስለምናገኘዉ የማሰናሰል አቅማችንን እናሳድጋለን ማለት ነዉ፡፡ በተጨማሪም የቴክኖሎጂ እንዲሁም የአርክቴክቱራል ሳይንስ መጽሀፍቶችን በጥቂቱ እንኩዋን ብንዳስስ ተጠቃሚ እንሆናለን፣ አመለካከታችንም ይሰፋል፡፡ የምንሰራዉ ንድፍም ከኢንተርኔት የተገለበጠ የ (composition of vertical and horizontal elements ) ከመሆን ድኖ ህይወት ያለዉ ማንነት ዉስጥ ሰርጾ የሚገባ ይሆናል……እናንብብ፡፡🤫🤫😠

💻🖥💻🖱💻የዘመናችንን ኪነ ህንጻ ለመከተል የዲጂታል ሶፈተዋሮች ድርሻ ይህ ነዉ ተብሎ አይገለጽም፡፡ በመሆኑም የ(online tutors) በማየት የ(modelling ,rendering and presentation skills) ማዳበር እንችላለን፡፡

🔖🔖🔖🖌✏️✏️
ብዙዎቻችን ከዲጂታል አለም ተጽእኖም ሊሆን ይችላል የምናስበዉን ንድፍ ወደ ስዕል ቀይሮ ሃሳቡን ከማብላላት ይልቅ ቶሎ ወደ ኮምፒየተር ቀይሮ በሶስት አዉታር (3d) ማየት ይቀለናል፡፡ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመን የተለያዩ ዘዴዎችን ከመጽሀፍት እንዲሁም (tutorials) በማየት አቅማችንን መገንባት እንችላለን፡፡
የተለያዩ የእጅ ስራዎችን መስራት እንችላለን፡፡

📱📲📱💻📱📱
አርክቴክቸራል የማህበራዊ የትስስር ገጾችን መጎብኘት (archdaily, deezen, interior design, pintrest,…)

🦠🦠🦠🦠🦠
ለአዳዲስ ሃሳቦች ራሳችንን ማዘጋጀት እና ማደራጀት አለብን

ለሌሎች ሀሳቦች ካሉንም ለሌሎች እናጋራ

ርቀታችንን እንጠብቅ
እጆቻችንን በደንብ እንታጠብ
በተቻለ መጠን ከቤት አንዉጣ
👉የቻናል ጥቆማ helpful channel 👌
.
▶️የ ኮንስትራክሽ፣ሲቪል፣ኣርክቴክቸር ተማሪ ኖት? ወይም በ ጠቅላላ የ ኮንስትራክሽን ስራ የተሰማሩ ባለሞያ ከሆኑም በእርግጥም ይህ ቻናል ለናንተ በጣም ይጠቅማል፡፡
.
📚በ አማርኛ እና ኢንግሊዘኛ የ ሌክቸር ትምርቶች፣መፅሃፍቶች፣ቪድዮዎች እንዲሁም ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን እውቀቶች ለማግኝት ከታች ባለው ሊንክ በ መጫን ይቀላቀሉን።
፡
👉👇👇👇👇👇👇
http://t.me/ETCONp
Forwarded from Comeshy art (Nati Comeshy)
ዘመነ አበጀ
#ይመለከተኛል
ይህን መግቢያ ቃል ስጠቀም የትኛውም የከተማዋ ነዋሪ በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ በከተማዋ ላይ የሚተገበሩ ማናቸውም # ፖሊሲዎች :
# እቅዶች : # አተገባበሮች በነዋሪው የአኗኗር ዘይቤ ፡ በሚከተለው
የባህልና የሀይማኖት ስርዓት ፡ በሚያራምደው አመለካከት ( social
philosophy ) መሠረት አድርጎ የማህበረሠቡን ፍላጎት ጠንቅቆ ባወቀና
በተረዳ መሪ አስፈፃሚነት ( አለቅነትን አያካትትም )እውነት ገብቷቸው
እውነትን በሚያስተጋቡና በሚመሠክሩ እንደራሴዎች አጋፋሪነት ፡
ማሕበረሠቡን ወርደው በመረመሩ ባጠኑ አዎቂዎችና የሙያ ባለቤቶች
እቅድ፡ከ ንድፍ፡ መመሪያ፡ መተግበሪያ ሰነድ አዘጋጅነት እዲሁም በሠፊው
ህዝብ ይሁንታ አገኝቶ የሚተገበሩ በመሆናቸው ከንቲባነት የአንድ ወገን
ሳይሆን የሁሉም ነዋሪ ግዴታ ነው ስለዚህ ሁሉንም ይመለከታል
እኔ ደግሞ የከተማዋ ነዋሪ ነኝ
እንደ ድርሻዬ ማወቅ ያለብኝን እጠይቃለው
በገባኝ መጠን በጎውን አወድሳለው
ባለኝ እውቀት ስህተት የመሠለኝን እነቅፋለው
እንጂ ዝም #አልልም
ሆኖም ሀገር አንድ ነገር ብቻ አላት " መነሻ የሆናት ታሪክ " መድረሻዋ ግን
እንደየዘመኑ የማህበረሠብ ፍላጎት ይወሠናል ስለዚህ ያደለው ተሻጋሪ እና
ተወራራሽ (ቅብብሎሽ ) ራዕይ ይኖረዋል ; ግብዙ ደግሞ ጥሩ መነሻ
ኖሮት ነገን ሳያስብ እንጭጭ ራዕይ ( short sighted) ኖሮት
ማህበረሠብን ሲጎትት ይውላል የተረገመው ደግሞ መነሻውንም ትቶ
(ረስቶ ) የግሉን ህልም ሲኖር የሚውል አለቃ (ግብዝነት የተጠናወተው )
ህልሙ ለራሱ እንጂ ለማህበረሠብ ግራ የሆነ ብቻውን አልሞ
ማሕበረሠቡን ያወረ ይሆናል፡፡
ታዲያ # አዲስአበባ ፡ # ኢትዮጲያዬ መድረሻቸው የቱ ይሆን በግብዝነት
ሳይሆን በገባችሁ ልክ ከላይ ከተጠቀሡት ከ3ቱ በአንዱ ይወከላሉና
ለእራሳችሁ ንገሩት እኔ ነግሬዋለው፡፡
እናም ሆነና ወደ መደምደሚያዬ ስመጣ የከተማዋ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ
ነው ( በሽታ ሲመጣ ለሁላችንም አንደነተነገረን ) ማናቸውም ግንባታዎች፡
ንድፎች፡ ረቂቆች፡ ማሻሽያዎች፡ህጎች ፡ ሀሳቦች እንኳን ሳይቀር (ከሥነ
ሕንፃ እና ከከተማ እቅድ ጋር ብቻ ነው ለጊዜው ያነሳሁት በሌሎች
ሙያዎች እናንተ ጨምሩበት ) እደየ ደረጃችን ማወቅ አለብን ስለሆነም
የበላይ አካላት( መሪዎች ወይም አለቆች ) ለምትመሩት ህዝብ ብቻችሁን
አትወቁለት ምከንያቱም ከእናንተ በላይ ብዙ የሚያውቁ እንዳሉ አትዘንጉት
ይሉቁንም ተነጋግሮ ተማክሮ መምራት ትክክልም ነው ፡፡ አዋቂዋች፡
ተመራማሪዎች የሕዝብ እንደራሴዎች እናንተም ለቆማችሁለት ሕዝብና
አላማ ብቻ ኑሩ ፡ ጠይቁ ፡ ሞግቱ ፡ ታገሉ፡ ለውጤት ትጉ ፡፡ ነዋሪዎችም
ከተማችንን እጠብቅ ስለ ከተማችን ይመለከተናል ወጤቱ የሁላችንም
ነውና ክንዋኔውም የሁላችንም ይሁን ፡፡
#አዲስአበባዬ የበቁት አበጁሽ
#አዲስአበባዬ ያወቁት አቆዩሽ
#አዲስአበባዬ አሁን ግን እንጃ ፈራን....
# አዲስአበባዬ ነገን እንዳትወቅሺኝ እኔ ስላንቺ ይህንን ተመኘሁልሽ አዋቂ፡
ሠሚ ፡ ይሉኝን የሚፈራ ፡ አብዝቶ የሚወድሽ፡ ሚሳሳልሽ ፡ ባንቺ የሚኮራ፡
ሙሽራ አድርጎ የሚያናኖርሽ መሪና ተመሪ ፡፡ አበቃሁ
ይህ #ይመለከተኛል
ኢትዮጵያ ትቅደም
መቼ ? ሁሌም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
https://www.press.et/Ama/?p=31137
የቅርስ ጥበቃ ተቋማት ቅርሶችን የመታደግ ጉልበት እንደሌላቸው ተገለጸ
Forwarded from Ketema Journal
Ketema is a bi-monthly architecture and construction journal focusing on the built environment and professionals involved with a mission of promoting modern-day architecture and it’s practitioners through publication.

Ketema aspires to create one of the most compelling architectural publications in the continent by influencing the built environment towards a designed future.

@ketema_journal
Claim your free copy @Ketema_Journal_Bot
Forwarded from YaMb3 STYLE 👉
#DigitalArt
#QuarantineCircle

Gift for Ur friends and loved ones
Order a gift...
Send Your pictures...
@Yambe7
Forwarded from YaMb3 STYLE 👉
#DigitalArt
#QuarantineCircle

Gift for Ur friends and loved ones
Order a gift...
Send Your pictures...
@Yambe7
ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ነበር መጽሀፉን ያነበብኩት፤
የማይታመን እዉነት፤ አንጀት የሚበላ አገላለጽ ነዉ፡፡
በእዉነት አዉሮፓዉን ስለኛ ሲጽፉ ለምን እንደምወደዉ እስካሁን አልገባኝም፡፡ ምናልባትም የዚህ እፉዬ ገላ ትዉልድ አንዱ ናሙና ሆኜ ይሆናል፡፡ ግን በቃ፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
መጽሀፍ ያረገዉ የግል ማስታወሻዉን ነዉ፡፡
💠💠💠በኢትዮጵያዊነት እምነት፤ጥንካሬ፤ወኔ፤ድፍረት፤ ልበ-ተራራነት ተማርኮ ከነሱ ጋር ያሳለፈዉን ጊዜ እንደ መመረጥ ቆጥሮት ለራሱ የኢትዮጵያዊነት አክሊል አጎናጸፈ፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆነ!!!!!!
😁😁😁😁😁😁😁
ኢትዮጵያዊ ለመሆን አልከበደዉም ፤ ነፍሱን ለመስጠት አላመነታም በቃ ከልቡ አንጀቱ ተላዉሶበታል፡፡ ሰሞኑን ትረካዉን እንደ አዲስ እየሰማሁት ነበር፡፡ እናም ትረካዉ መጽሀፉ ላይ ነፍስ ተዘርቶበት ሰማሁት፡፡
ከመጽኀፉ ቀልቤን ከገዙት ሁነቶች መካከል አንዱ ፋይዳዉ ጎልቶብኛል፡፡ እንደዉ አንዳንዴ ታሪክ አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች ሲተርኩ ከሰማችሁ በዚህኛዉ ክ/ዘመን እንትና እንትናን ገሎ ነገሰ፡፡ በዚህ ጊዜ ገናና ነበርን፡፡ በዚህ ጊዜ ተዋግተን እያሉ አዋቂነታቸዉን ሲያስመሰክሩ ፤ ገሚሱም እነ አከሌ በዚህ ክ/ዘመን ይሄን ህዝብ ወረዉ ይሄን ጨፍጭፈዉ እያሉ ምሁርነታቸዉን ያስተጋባሉ፡፡እዉነት ግን የታሪክ ፋይዳዉ ይህ ነዉ ;;;;;

ከዚህ መጽሀፍ ያገኘሁት ሁነት ግን ለአሁናችን ጥሩ መማሪያ ይመስለኛል፡፡ መፍትሄም ጭምር፡፡ ከታሪካችን መዝገብ መዘን ማዉጣት ካለብን እንዲህ ዐይነት ባህሎቻችንን፤ እዉቀቶቻችንን እና ልማዶችን አምጥተን አጎልብተን መጠቀም ነዉ፡፡ ወደ ድሮ እንመለስ ማለት ወደ ድሮ ክ/ዘመን መመለስ ሳይሆን በጎዉን ፍልስፍና ፤እዉቀት ባህልና ዘይቤ መዞ አዉጥቶ በጭፍን ክምንዳክርበት ፖለቲካ እና ባህል ጋር አሰባጥሮ ከሁሉም ጥሩ ጥሩዉን ቀስሞ ማጎልበት ነዉ፡፡
የተፈጸመዉ ሁነት በርግጥም መጽሀፉ ላይ የዋናዉ ታሪክ ክፍል ሆኖ በደንብ ባይተረክም ለኔ ግን ትልቅ ፋይዳ ነበራት፡፡ ሆኖም ራሳችሁ አንብባችሁ ድረሱበት፡፡ ተጋብዛችኃል!!!!

መጽሀፉ ወደ አማረኛ የተተረጎመዉ የሀበሻ ጀብዱ ነዉ፡፡
ቀኑ ሚያዚያ 27ም አይደል
መጽሀፉን ጋብዤ እንኩዋን ለድል በአላችን በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ነዉ፡፡
✍✍ናትናኤል ፍሬዉ