Greetings Architects,
Our 21st architects ወርሃዊ session will be on Thursday, June 04.
We have prepared for you another exciting virtual session on the topic of 'Advancing Architecture with manufacturing technologies.'
We will share the link to the live stream on all our social media pages so you can all tune in.
If you haven't had the chance to follow last months session you can read the summary here:
https://drive.google.com/file/d/1AO8QQWkyPUHCsLJA-R_agqPL2U3C1IMn/view?usp=sharing.

ይህ የኔ፣ ያንተ፣ ያንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ ጣና ነው።
ጣና ታሟል! የሀገሬ ባለስልጣናት ችላ ብለውታል።
እባካችሁ እባካችሁ ጣናን አታጨልሙብን
ይህንን ፅሁፍ በየ "ግሩፑ" በየ "ቻናሉ" #ሼር በማድረግ ድምፃችንን ላልሰሙት በማሰማት ሀላፊነትህን ተወጣ።
@yismakeworku

"ሰሞንኛ የከተማ ነዋሪዎች ሥነ ልቦና" በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ላይ አተኩረን ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተገናኘ የሚስተዋሉ አንዳንድ ጉዳዮች ዙርያ ቆይታ ይኖረናል ።
በቀጥታ ስርጭት ወቅት ሃሳቦችችሁን እንድታካፍሉን እና ማክሰኞ ግንቦት 25 2012 ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 እንድትከታተሉ እና እንድትሳተፉ እንጋብዛለን ።
የከቤት እስክ ቤት አዘጋጆች ።
"Current Urban Dewllers Psychology" is the subject of this week program. By focusing on Addis Abeba we will reflect on some points related to the subject in the time of the Corona pandemic
We invite you to tune in and have your say on the live show from 8 to 9 pm on Tuesday June 2, 2020
The Kek team

፡፡፡፡፡፡፡፡፡ወንጌል እና ወንጀል፡፡፡፡፡
ሳንጠይቀው ሰጪ
ሳንለምነው ለጋሽ
ሰው የሆነው እግዜር
ሰው የሆነው ታጋሽ
ምድር ላይ እያለ
እንዲህ ነበር ያለ......
"ዳቦ ለጠየቀ ድንጋይ አይሰጥም
አሳ ለተራበ እባብ አይለገስም"
ብሎ እንዳልነገረን....
ቃሉ ቀድሞን ኖሮ ቀድመን እኛ አርጅተን
ማቴዎስን ክደን
ሰውነትን ንቀን
ዘረኝነት ሞልቶን
ቀለም አስመልኮን
እንኳን ዳቦና አሳ
ላንዱ የሚበዛ ካንዱ ተቀንሳ
ተርፎ ለሞላ አየር ለፈጣሪ ፀጋ
እኔ ስቤው ማይጎል ለማያልቅ አንተጋ
አየር ለጠየቀ
ትንፋሽ ለለመነ
ምፅዋቱ ሞት ሆነ
✍✍✍✍✍ኤርማ
ሳንጠይቀው ሰጪ
ሳንለምነው ለጋሽ
ሰው የሆነው እግዜር
ሰው የሆነው ታጋሽ
ምድር ላይ እያለ
እንዲህ ነበር ያለ......
"ዳቦ ለጠየቀ ድንጋይ አይሰጥም
አሳ ለተራበ እባብ አይለገስም"
ብሎ እንዳልነገረን....
ቃሉ ቀድሞን ኖሮ ቀድመን እኛ አርጅተን
ማቴዎስን ክደን
ሰውነትን ንቀን
ዘረኝነት ሞልቶን
ቀለም አስመልኮን
እንኳን ዳቦና አሳ
ላንዱ የሚበዛ ካንዱ ተቀንሳ
ተርፎ ለሞላ አየር ለፈጣሪ ፀጋ
እኔ ስቤው ማይጎል ለማያልቅ አንተጋ
አየር ለጠየቀ
ትንፋሽ ለለመነ
ምፅዋቱ ሞት ሆነ
✍✍✍✍✍ኤርማ
Forwarded from Deleted channel (Yohannes Mekonnen)
እየተቸን እናግዛለን።
እያገዝን እንተቻለን!
ከዚህ ቀደም "መስቀል አደባባይ ላይ ምን እየተሠራ ነው?" በሚል ርእስ ሰጋቶቼን እና ቅሬታዎቼን አጋርቼ ነበር። በቦታው ላይ ዋንኛ ባለድርሻ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ አስተዳደሩን "ምን እየተሠራ እንደሆነ ማብራሪያ መጠየቋ ይታወሳል።
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኒቱን መብት እና ጥቅም የሚጋፋ ፕሮጀክት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ለቤተክህነቱ በመግለጽ ዝርዝር ዲዛይኖቹን እንዲያስረዱ በባለቤት በኩል ለዲዛይን ክለሳ (Design Review) የተመደቡ አርኪቴክቶች በአካል ጠቅላይ ቤተክህነት በመቅረብ ለቤተክርስቲያኒቱ አባቶች እንዲያስረዱ፤ ከማድረጋቸውም በላይ ቤተክርስቲያኒቱ የዲዛይን እና የግንባታ ሂደቱን በጋራ የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንድትመድብ ተደርጓል። (ቤተክርስቲያኒቱ አስፈላጊ እንደሆነ ባመነችበት ጊዜ መግለጫ የምትሰጥበት ይመስለኛል)
ምንድነው የሚሠራው?
የፕሮጀክቱ ስያሜ እንደሚገልጸው "ከመስቀል አደባባይ፣ ላጋር መዘጋጃ ቤት" የሚያጠቃልል ምቹ የእግረኛ መንገድ ማስፋት፣ የቅርሶች ጥገና፣ የአጸዶች መትከል፣ የአረንጓዴ ሥፍራዎች ዝግጅት፣ የመኪና ማቆሚያ እና የመስቀል አደባባይን በተሻለ መልክ ማዘጋጀትን (Refurbishment) ያካትታል።
ዲዛይነሩ ማነው?
ፕሮጀክቱ የዲዛይን ግንባታ (Design Build) እንደመሆኑ የግንባታ ሥራውን የተረከበው የቻይናው ሥራ ተቋራጭ በሥሩ ሀገር በቀል የሆነ አማካሪ ቀጥሯል። የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ የዲዛይን ሥራውን እና የግንባታ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ በሥራ ተቋራጩ የተቀጠረው አማካሪ ቢሮ ላይ ላለመተው በራሱ የዲዛይን ክለሳ (Design Reviewer) አማካሪ በካቢኔው ይሁንታ ቀጥሯል።
በዲዛይኑ እነማን ተሳትፈዋል?
የመስክ ጉብኝት ባደረኩበት ወቅት ዋናው ተቆጣጣሪ አርኪቴክት (Chief Project Architect) እንዳብራሩልኝ የአርኪቴክቸር፣ የቅርስ ጥበቃ (Conservation)፣ የከተማ ዲዛይን (Urban design) ባለሙያዎች የሆኑ በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን አብረው እየሠሩ ይገኛሉ። (አንዳንዶቹ ዲዛይነሮች የእኔም መምህራን የነበሩ ፕሮፌሰሮች ናቸው።)
የመዋቅር ዲዛይኑን (Structural Design) የሚከታተለው አምስት ኪሎ የሚገኘው የምህንድስና ትምህርት ቤት መምህራን ቡድን መሆኑን አረጋግጫለሁ። ዲዛይኑ ከፍተኛ ጭነት እና ፍንዳታ እንዲቋቋም ታስቦበት መወጋጀቱን ታዝቤአለሁ።
የገጸምድር ዲዛይን (Landscape Design) የሚያጠኑ ባለሙያዎች በሥራ ተቋራጩ አማካሪ ሥር ተቀጥረው እየሠሩ ነው። በእኔ ምርመራ ዲዛይኑ የተሰጠበት አካሄድ የመርህ ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ ግን ሀገሪቱ አሉኝ በምትላቸው ምስጉን የዲዛይን እና የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጫለሁ።
የሚፈርሱ ቅርሶች አሉን ?
ከመዘጋጃ ቤቱ በላጋር እስከ መስቀል አደባባይ ያሉትን ቅርስ የሆኑ ሕንጻዎች (Heritage Buildings) እና ሐውልቶች (Monuments) አንድ በአንድ ለመጎብኘት እና በግንባታው የሚደርስባቸው ተጽእኖ ይኖር እንደሆን ለማጥናት እድል አግኝቻለሁ።
የፕሮጀክቱ አማካሪ አርኪቴክት በዝርዝር እንዳስረዱኝ እና በግሌ የዲዛይን ጥናቶቹን እንዳየኋቸው አንድም የሚነካም ሆነ የሚፈርስ ህንፃ እና ሃውልት የለም። በቅርስ ጥበቃ ኤክስፐርቶች ምክር የሚታደሱ እና ከቅርሶቹ ጋር ወደሚሄዱ አገልግሎቶች (Adaptive Reuse) የሚቀየሩ ግን ይኖራሉ።
የመስቀል ደመራ እጣ ?
የዲዛይኑም ሆነ የግንባታው ማዕከል በዩኔስኮ የተመዘገበው የደመራው እና የመስቀል በዓል አከባበር እንደመሆኑ ይህንኑ መንፈሳዊ እሴት ይበልጥ ለማድመቅ እና ምቹ ለማድረግ ብዙ እንደተሠራ ታዝቤአለሁ።
ለምሳሌ ደመራው የሚተከልበት ቦታ እንደ መንፈሳዊ ትውፊቱ ከታች ጀምሮ የመጣ ድንግል መሬት ላይ እንዲተከል የተሠራ ሲሆን በገጸ ምድሩ ላይ የተለየ ማድመቂያ ዲዛይን (Surface Aarticulation) ተዘጅቶለታል።
(ጥንት ንግሥት ዕሌኒ እንደተከለችው ሁሉ ደመራው ከሥሩ በሚገኙ በምድር ቤቶቹ ምክንያት በመጣ ተንሳፋፊ ኮንክሪት ላይ ሳይሆን ተለይቶ በተዘጋጀ መሬት ላይ እንዲተከል ዲዛይኑ ተዘጋጅቷል)
ግንባታው መቼ ይጠናቀቃል?
የፕሮጀክት ቢሮው ባለሙያዎች እንዳስረዱኝ ለመጪው አዲስ ዓመት የሚደርሰው የደመራው መትከያ እና አካባቢው መቀመጫ ደረጃዎች ይሆናሉ። ቀሪው የመኪና ማቆሚያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች እስከ ገና (ታህሳስ ወር መጨረሻ) ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል።
ማጠቃለያ
ከዚህ ቀደም እንዳነሳሁት በዚህ ፕሮጀክት ላይ የነበሩኝ የመርህ (የቅደም ተከተል፣ የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ውድድር ወዘተ) ቅሬታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሥራውን ግን በምንችለው ሁሉ እንደ ዜጋ ማገዝ አለብን ብዬ አምናለሁ። በግሌ በዲዛይኑ ውስጥ ቢካተቱ፣ ትኩረት ቢያገኙ የምላቸውን የባለሙያ ሃሳቦች ለማካፈል እድል አግኝቻለሁ። ለዚህም ነው "እየተቸን እናግዛለን፤ እያገዝን እንተቻለን!" የምለው።
በሀገራችን "አኩራፊ እረኛ ቁርሱ እራት ሆኖ ይጠብቀዋል (ያውም ቀዝቅዞ) እንደሚባለው የሀገርን መልክ እና የዜጎች ሕይወት በእጅጉ የሚቀይሩ እና ተጽእኖ የሚያሳርፉ ፕሮጀክቶችን በአካሄድ ቅሬታ መንግሥትን አኩሩፎ ከዳር ቆሞ በደረቁ ከመተቸት በሀሳብ እየተከራከርን በሥራ ደግሞ እየተጋገዝን መጓዝ አለብን እላለሁ።
መንግሥትም የአካሄድ ችግሮቹን ለማረም የዜጎችን ሙያዊ ትችት ለመቀበል በወቃሽነት ብቻ ሳይሆን በገንቢ ሱታፌ (Constructive engagement) በቀናነት ሊያየው ይገባል እላለሁ።
እያገዝን እንተቻለን!
``````````````````````

````````````````````````````