የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture
2.78K subscribers
688 photos
11 videos
56 files
139 links
The present Ethiopia is the remain of the greater Ethiopia

Follow us on facebook
#http://facebook.com/yehabesha students of architecture
Telegram @yehas

#For Your Comment or Info Use
@arcnat
Download Telegram
Good evening Everyone
For the last three days you are participating on the amazing architectural online compitition.
Which is focuses on konso vernacular architecture.
Thank you for your participation.

This is the first: and we will continue.
🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌
we have winner.....the prize to the first ethio-architect presents online challenge goes to Nahom, 2nd year, EiABC, Congratulations.👏👏👏
የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture pinned «Good evening Everyone For the last three days you are participating on the amazing architectural online compitition. Which is focuses on konso vernacular architecture. Thank you for your participation. This is the first: and we will continue. 🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌🙌…»
👆👆👆👆👆👆
What do you remember😐?
Water Tower Architecture in Darfur, Sudan by H3AR

Inspired by the shape of the African Baobab tree, Polish Architectural Design H3AR firm has come up with this interesting Water Tower Design for South Sudan. According to them "...it was the inspiration of the water tower skyscraper which are also comprises a treatment plant, hospital, school and a food storage center to trigger economical development while bridging the cultural differences of the three different religions and languages in the turbulent African nation..."

http://africanarchitecture.blogspot.com/2014/09/inspired-by-shape-of-african-baobab.html
ሠላም እንደምን ከርማችኃል ሠሞነኛውን የሜክሲኮ ህንፃ ትችት ስከታተል ነበር እናም እኔ ስለ ስነ-ህንፃ እና ሀገር ቁርኝት የማምንበትን ላጋራችሁ ምክንያቱም ስለ አንድ ወይም ሁለት ህንፃ ህፀፅ ማውጣት እውቀትም መፍትሄም ስለማይሆን እንደ ስነ - ህንፃ ባለሙያነታችን ቀጥሎ የተፃፈውን በተለየ አቅጣጫ እንድታዩት እፈልጋለው ፡፡ እስቲ ከጥያቄ ልጀምር ሀገር ምንድነው? እንዴትስ ይገነባል ? ገንቢዎቿስ እነማን ናቸው ? ለማን ይገነባሉ? ለምን ይገነባሉ? ይህ ጥያቄ በቀጥታ የስነ - ህንፃን ትርጓሜ ይሠጠናል ታድያ እኛ ባለሙያዎች ምን ያህል ትርጉሙ ገብቶናል ብለን እራሳችንን ጠይቀናል? እንጃ እኔ ግን ትልቁ እንደ ሀገር ውሉ የጠፋብን እዚህ ጋር ይመስለኛል ከልብ አድምጡኝ ከላይ የለጠፍኩኣቸውን አባባሎች በተርታ እዪኣቸው እና አእምሮአችሁ ውስጥ ምን አቃጨለ 3 ነገር ህዝብ ፡ ሀገር ፡ እና እቅድ ታዲያ እንደኛ ሙያ እነኚህን 3ቱ ምን ይገምዳቸዋል ? ንድፍ ተሳሳትኩ ? እናስ የእነዚህ ጉንጉን የእኛ የእራሳችንን ፍፁም መልክ ይሠጠናል መለያችንም ይሆናል ፡፡ ታዲያ ሁላችንም እንደ ሀገር እንደ ህዝብ አንድ አገራዊ መለያ ሊኖረን አይገባም ትላላችሁ እስቲ የ በስነ - ህንፃ ጣራ የነኩት አገራት እኮ ሥያሜን እንኳ በሀገር አስደርገዋል ይህ ግን የሆነው በቅዠት ሳይሆን የ100 እና 200 አመት ራዕይ ይዘው ስለተነሡ ነው ስለዚህ እንደ ሀገር እንደ ዜጋ ትልቅ ህልም ይኑረን ህዝባችንን እንወቅ ምን እንደሚያስፈልገው እንረዳ ያኔ ምን እንደምንሠጠው አይጠፋንም ስለዚህ ዛሬ የምንናደድባቸው ንድፎች እና የተገነቡት ህንፃዎች ሁሉ ከእኛ ራዕይ ማጣት የመነጩ እንደሆኑ እንረዳለን ማለት ነው ፡፡ ስለዚህ እንደ መፍትሄ መጀመሪያ መሆን የምንፈልገውን ሳይሆን መሆን ያለብን ምንድነው ብለን መጠየቅ ምሣሌ ከእናንተ ውስጥ ህግ አውጪ መሆን አለብኝ ብሎ ያሠበ አለ? ( በስነ - ህንፃ ማለቴ ነው ) ነው ሠው ባወጣውና በተጨማለቀው መዝለቅን የወደደ ማን ነው ከተማው ይህን መምሠል አለባት ብሎ የሂስ መድረክ አዘጋጅና ሞጋች እሆናለው ብሎ ያሠበ አረ ማነው ህዝቤን ሀገሬንና ህሊናዬን ነው የማስቀድመው መለዮዪን አልቀይርም እንደውም የአባቶቼን ለልጄ ድልድይ ሆኜ ማሳየት ያለብኝ ብሎ የወሠነ ማነው ኢትዮጵያን 100 አመት ምን እንደምትመስል ቀድሞ የነደፈ ማነው? ማነው? እኔ ፡ አንቺ ፡ አንተ ፡ አኛ ፡እኮ ማን ይህንን ጥያቄ የመለስን ጊዜ ዛሬ የተወያያችሁበትየሜክሲኮ ህንፃ ችግሩ የት ጋር መፍትሄውም ምን እንደሆነ ቁልጭ ብሎ ይታያችኃል እንደ ማጠቃለያ የኝ ሙያ ውስንነት የለውም ስለዚህም በማንኛውም ሁኔታ የሀገርን መልክ የእናንተን እገዛ የሚሻውን ማህበረሠብ ፍላጎት እንዲሁም አእምሮኣችሁ ውስጥ ያለውን ራዕይ አየሸመናችሁ ቆንጆ ጥበብ እንስራ እኔ ተማሪ ሆኜ ነው የጀመርኩት አልከሠርኩም እናንተም ካመናችሁበት በጊዜ ጀምሩት የአያቶቻችን ላይ የእኛን ጨምረን ለልጆቻችን እስተላልፍ አለበለዚያ አያቶቻችንን እና ልጆቻችንን ማቆራረጣችን ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ትቅደም
መቼ? ሁሌም
የሀ-በሻ ኪነ-ህንጻ ፡ Yeha-Besha Architecture pinned «ሠላም እንደምን ከርማችኃል ሠሞነኛውን የሜክሲኮ ህንፃ ትችት ስከታተል ነበር እናም እኔ ስለ ስነ-ህንፃ እና ሀገር ቁርኝት የማምንበትን ላጋራችሁ ምክንያቱም ስለ አንድ ወይም ሁለት ህንፃ ህፀፅ ማውጣት እውቀትም መፍትሄም ስለማይሆን እንደ ስነ - ህንፃ ባለሙያነታችን ቀጥሎ የተፃፈውን በተለየ አቅጣጫ እንድታዩት እፈልጋለው ፡፡ እስቲ ከጥያቄ ልጀምር ሀገር ምንድነው? እንዴትስ ይገነባል ? ገንቢዎቿስ እነማን…»
ኢትዮጵያዊነት ስቃይና መከራ ነዉ
ኢትዮጵያዊነት ኪራትና ክብርም ነዉ
ኢትዮጵያዊነት ጭቆናና ጥቃትም ነዉ
ኢትዮጵያዊነት አሻፈረኝና እምቢባይነትም ነዉ (ፕሮፌሰር መስፍን)

የካም ጸዳል ጀግኖች እናት
እምቅድመ ዓለም ፍኖት እሳት
የዘላለም ችቦ ብርሀን የማትሻር ህይዉነት
ረዕይ ናት ኢትዮጵያዊነት (ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን)

የእሳት ልጅ አመድ ሆነን አንዲት ውድ ሕይወታቸውን ሰውተው ሰው ላደረጉን አያት ቅድማያቶቻችን ፣ ሕይወት ለግሰው ያቆሟትን አገር እንዳሻሽ ብለን ትተናታል። በሕይወት ዘመናችን ተከፍሎ የማያልቅ እዳ አለብን። ሁሉ ቢቀር በየመክሊታችን ንቁ ባለሙያዎች ለተተኪው ትውልድም ሊያልፍ የሚችል አንዳንድ ነገር ሰርተን እንለፍ!
ቢሆንም ዘላለም እንዳለው ዛሬም ነፃ ሰዎች ነን፡፡ በባርነት ጭነት ቅስማችን ያልተሰበረ: በጭቆና ቀንበር ልባችን ያልተሸበረ፤ ጎንበስ ማለት የሚያንገሸግሸን: ቀና ብለን ኖረን ቀና እንዳልን ማለፍ የሚናፍቀን፤ የነጮችን ጥቃት ለመቋቋም ቆዳችን የሚሳሳብን፤ አልደፈር ባይ የጥቁር አፈር ትንታጎች ነን፡፡
በትውልዱ ሊጠየቅ የሚገባውን ጥያቄ ወንድወሰን ውቤ እንዲህ ሸጋ አድርጎ ገልፆታል። “ያጣሁት ጀግንነት እንዴት የጀግንነት እርሾ ከውስጤ ጠፋ? ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ የአልገዛም ባይነት ሥሪት ነው። የኢትዮጵያዊያን እምቢተኝነት የነጭ ዘርን ወታደራዊና ሥነ-ልቡናዊ ልዕልናን ዓድዋ ላይ እስኪሰባብር ድረስ አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን በምድራቸው ላይ ለሠለጠኑት ባዕዳን ሎሌ ሆነውና በፍረሃት ቆፈን ተይዘው ኖሩ። ዓድዋ መጣና የጥቁር ሕዝብ እምቢታ በራሷ ኃይል እንደምታደርግ አረጋገጠላቸው። በልባቸው ውስጥም “ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን የፈጸሙትን ጀግነነንነት እንደግመዋለን!” የሚል የጀግንነት ወሳኝ ብርታት አደረ። እናም ቅኝ ገዥውን በሽምቅ ውጊያ ይተገትጉት ጀመር። ታዲያ ለአፍሪካ የተረፈ ጀግንነት ከበቀለባት ምድር በቅዬ እንዴት ጀግንነት አነሰኝ? ኢትዮጵያዊነቴን ማን ቀማኝ? የት ጣልኩት”
መልካም የደብረታቦር/ቡሄ በዓል ይሁንላችሁ!
........................................................................
"የወፍ ደግ የወፍ ደግ የዘራሽው ይደግ
የወፍ ፋፋ የወፍ ፋፋ ሰላም ፍቅር አይጥፋ"
........................................................................
BEHAGERLIJ . 2012
Architects Making Headlines!
Check these links for more.

“የሀገራችን ባለሙያዎች መከበር አለባቸው” አርክቴክት ዘለቀ በላይ
https://www.press.et/Ama/?p=37444

‹‹ሕንፃዎችን ለመቶ ዓመት እንጂ ለአስርና ሃያ ዓመት ብለህ አትገነባም››- አርክቴክት ራሔል ሻውል
https://www.press.et/Ama/?p=37041

«ኢትዮጵያ የጥንታዊ ኪነ ሕንፃ ሀገር ነች» አርክቴክት ፋሲል ጊዮርጊስ (ተባባሪ ፕሮፌሰር)
https://www.press.et/Ama/?p=36568

አዲስ አበባ ከጎጆ ቤት እስከ ዘመናዊ ሕንጻ
https://www.press.et/Ama/?p=33550

ሕጉ ቢቀመጥም የአፈጻጸም ችግር አለ – አርክቴክት አርኪዮሎጂስት ታደሰ ግርማይ
https://www.press.et/Ama/?p=31254

የማስተር ፕላኑ ልዩ ጎኖች
https://www.press.et/Ama/?p=30787
የከተማዋ መለጠጥ ያስከተለው ቀውስ
https://www.press.et/Ama/?p=30317

የከተሞች መስፋፋትና መለጠጥ እስከየት?
https://www.press.et/Ama/?p=29929