ኢትዮጵያ ዉስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃኪሞች እጂግ በሚዘገንን እና ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ማንነቱ እና አላማው በዉል በማይታወቅ ሁኔታ በጭቃኔ ይገደላሉ ማነዉ ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል ግን የለም ።
የተሰበረን ልብ የሚጠግኑ ፈዋሺ እጆች በጭካኔ ይገደላሉ በዚ ስድስት ወር ብቻ ከአስር በላይ ሃኪሞች ማንነቱ በልታወቀ መንገድ ተገድለዋል ኣንዳቸዉም ፍትህ ኣላገኙም ይሄ ደግሞ ሃዘናችንን ጥልቅ እና ብርቱ ያደርገዋል።
ለመሆኑ ከሄትኛዉም የፓለቲካ እንቅስቃሴ ነፃ የሆኑ በሰባዊነት ሂወትን የሚታደጉ ሃኪሞች ለምን በግፍ ይገደላሉ???
ለምንስ ማስቆም ገዳዮችን ለፍርድ ማቅረብ አልተቻለም??? እስከመቼ ነዉ ይህ አረመኔያዊ ተግባር ሚቀጥለዉ????😭😭😭😭😭
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

💔12😢2❤1🤯1
"ኢትዮጲያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ Intra-uterine transfussion" ተሰራ ብለው ከዚህ በፊት እንደማይሰራ አርገው የዘገቡ ሚዲያዎች ይሄን ገራሚ ምናልባትም በአይነቱ በሀገራችን የመጀመሪያ ስራ ሳይዘግቡት ቀሩ እያላችሁኝ ነው?
🔥12❤4
Dr. Melesse Gebeyehu
Advanced Head & Neck Oncologic Surgeon | President, African Head & Neck Society
Dr. Melesse is one of fewer than 20 fellowship-trained head & neck oncologic surgeons in Africa, serving a continent of over 1.4 billion people. He is a nationally and continentally recognized expert in complex head & neck cancer surgery & reconstruction.
Currently based in Addis, Ethiopia, Dr. Melesse continues to lead advanced care for patients with head & neck cancers while playing a pivotal role in specialist training, mentorship, & surgical capacity building.
He serves as the President of the African Head & Neck Society (AfHNS), providing leadership for one of the most critically under-resourced surgical subspecialties on the continent. His clinical expertise includes advanced oncologic resections, neck dissections, & reconstructive procedures, often managing cases that would otherwise require referral outside the country.
@debolteam

❤11🔥1
ለወንዶች 15 ወሳኝ ሕጎች!
1. በፍጹም አታላህ (ማግጣብህ) ወደተለየሃት ሴት አትመለስ።
2. አንዲት ሴት በፍጹም እንድትንቅህ (እንድታዋርድህ) አትፍቀድ።
3. ተቀምጠህ የእጅ ሰላምታ አትስጥ (አትጨብጥ)።
4. ሌሎችን ለማስደመም (ለማስመሰል) ብለህ በፍጹም አትጎዳ።
5. ያልገዛኸውን ነገር የመጨረሻውን ቁራሽ በፍጹም አትብላ።
6. ሁልጊዜ የተሻለ ለመሆን ትልቅ ምኞት (ተነሳሽነት) ይኑርህ።
7. ማንም ወንድ እንዲደፋፈርህ ወይም እንዲያዋርድህ በፍጹም አትፍቀድ።
8. ጥያቄ ስትጠየቅ (መልስ ከመስጠትህ በፊት) ከ1-3 ሰከንድ ቆም ብለህ አስብ።
9. ለፍቅር ግንኙነት አትለምን።
10. እጅ ስትጨብጥ አጨባበጥህ ጠንካራ (ጽኑ) ይሁን።
11. በሳምንት ቢያንስ 4 ጊዜ ስፖርት ስራ።
12. ዝግጅቱ ምንም ይሁን ምን በደንብ (ዘንጠህ) ልበስ።
13. ራስህን መከላከል ተማር።
14. ገንዘብ ለመስራት የተለያዩ መንገዶችን ፈልግ (ፍጠር)።
15. ሁልጊዜም ትልቁን ዓላማ (ዋናውን) አልም።
Bini

❤14👏7👌2💯2
Prof. Wendemagegn Enbiale is a renowned Ethiopian dermatologist and public health expert with over 20 years of experience in clinical service, teaching, research, and health leadership.
He holds an MD, MPH, and a PhD in Global Health & Dermatology, and is internationally recognized for his work on neglected tropical skin diseases.
He serves on major global & national platforms, including the WHO Strategic and Technical Advisory Group on Neglected Tropical Diseases (STAG-NTDs), and holds leadership roles within global health dermatology networks. His work spans academic medicine, operational research, policy advising, and community-based health interventions.
Beyond academia, Prof. Enbiale is a powerful symbol of humanitarian service. He is a blood donation ambassador and has personally donated blood 79 times, a contribution estimated to have helped save more than 200 lives. His commitment exemplifies the highest ideals of the medical profession, service, sacrifice, and leadership by example.

❤4👏2🔥1
የወሲብ ፊልሞችን የማየት ሱስ ተያይዞ ያለ ራስን በራስ የማርካት ችግር
የወሲብ ፊልም (ፖርኖግራፊ) የማየት ሱስ እና ቴሌቪዥን ተያያዥ ራስን በራስ የማርካት ችግር የዘመናችን ከፍተኛ የባህሪ ሱስ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ።
ይህ ችግር የአንድን ሰው ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ጤንነት በእጅጉ ሊጎዳ የሚችል የባህሪ ሱስ ነው። የሱስ ምልክቶች በዋነኝነት የሚታዩት ድርጊቱን መቆጣጠር ሲያቅት እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ እንቅፋት ሲፈጥር ነው።
ዋነኞቹ የዚህ ችግር ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ባህሪያዊ ምልክቶች (Behavioral Symptoms)
መቆጣጠር አለመቻል፦ ድርጊቱን ለማቆም ወይም ለመቀነስ ደጋግመው ሞክረው ሳይሳካሎት ሲቀር።
ጊዜ ማጥፋት፦ በፊልሞቹ ፍለጋ እና እይታ ላይ ረጅም ሰዓታት ማሳለፍ፣ ይህም ለስራ፣ ለትምህርት ወይም ለቤተሰብ ሊሰጥ የሚገባውን ጊዜ መውሰድ።
ምስጢራዊነት፦ ድርጊቱን ከሰው ለመደበቅ መሞከር፣ የታዩ ድረ-ገጾችን (Browser history) ደጋግሞ ማጥፋት እና ስለ ጉዳዩ ሲጠየቁ መዋሸት።
የማህበራዊ ግንኙነት መዳከም፦ ከጓደኞች እና ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ከማሳለፍ ይልቅ ፊልሞቹን ማየት መምረጥ።
2. ስነ-ልቦናዊ ምልክቶች (Psychological Symptoms)
የጥፋተኝነት ስሜት እና መሸማቀቅ፦ ፊልሙን ካዩ በኋላ ከፍተኛ የሆነ የጸጸት፣ የሀፍረት ወይም የዝቅተኝነት ስሜት መሰማት።
ትኩረት ማጣት (Brain Fog)፦ በሌሎች የሕይወት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ለማድረግ መቸገር እና አእምሮ ሁልጊዜ በወሲባዊ ምስሎች መጠመድ።
ለጥቃቅን ነገሮች መበሳጨት፦ ፊልሙን ለማየት በማይመችበት ጊዜ ወይም አንድ ሰው ሲያቋርጥዎት ከፍተኛ ንዴት እና ብስጭት መሰማት።
ጭንቀት እና ድብርት፦ ከሱስ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የባዶነት ስሜት እና ከፍተኛ የስነ-ልቦና መረበሽ።
3. አካላዊ እና ወሲባዊ ምልክቶች (Physical & Sexual Symptoms)
የወሲብ ፍላጎት መቀነስ፦ ከእውነተኛ የትዳር አጋር ጋር የሚደረግ ግንኙነት መደበኛ እና ሰልችቶት የሚሰማዎት ከሆነ።
ተጨማሪ ማነቃቂያ መፈለግ፦ በጊዜ ሂደት መደበኛው ፊልም እርካታ ስለማይሰጥ ይበልጥ ያልተለመዱ (Extreme) ምስሎችን ለማየት መፈለግ።
የአካል ህመም፦ ለረጅም ሰዓት ኮምፒውተር ወይም ስልክ ፊት በመቀመጥ የሚመጣ የአይን ድካም፣ የራስ ምታት እና የጀርባ ህመም።
መፍትሄውስ?
ከዚህ ሱስ ለመውጣት የመጀመሪያው እርምጃ ችግሩ መኖሩን ማመን ሲሆን የስነ-ልቦና ባለሙያዎችን በማነጋገር እርዳታ ማግኘት ወሳኝ እርምጃ ነው።

❤21🔥2
የልቅ ወሲብ ፊልሞች ሱስ
ፖርኖግራፊ የግሪክ ቃል ሲሆን ፖርኒ «Porni» በኢንግሊዘኛዉ ፕሮስቲቲዩት «Prostitute ወይንም ሴተኛ አዳሪ የሚል ፍቺ ሲኖረዉ ግራፌይን (Graphein) በእንገሊዘኛዉ (To write) ወይንም መፃፍ የሚል ፍቺ ይይዛል፡፡ በግርድፉ ስለ ሴተኛ አዳሪዎች የተጻፈና የተተረከ ወሲብ ቀስቃሽ ጽሁፍ ወይንም ምስል ማለት ነዉ፡፡ እኚሁ ወሲብ ቀስቃሸ ምስሎች በተለያዩ አረኪዎሎጂስቶች በሜሶፖታሚያ እና አከባቢዉ (ኢራን እና አከባቢዉ ማለት ነዉ) በሱሜሪያዉያን ዘመን እንዲሁም በ መካከለኛዉ አሶራዉያን ህዝቦች ቅሪተ ቅርሶች
እንደተገኘ ይነገራል፡፡ ይህንንም አረኪዮሎጂስቶች ቬኑስ ፊጉርስ ( Venus Figurines) ይሉታል ፡፡ እንዲሁም ይህዉ ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች በጥንት ግጻዉያን በዴር መዲና (Deir-el-Medina) (5500 ዓ.ዓለም ተቀርጾም እንደነበር አርኪዮሎጂስቶች ይናገራሉ፡፡ ህንዶች ካማ ሱትራ ሚለዉን ወሲብ ቀስቃሽ ምስል ህትመት ከ 4 ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለያዩ ቅርጻ ቅርጾች ላይ ከመቅረጽ አልፈዉ እንደ መጽፋፍ ጭምር በማዘጋጀት ስንፈተ ወሲብን ለማከም፣ የተዛባ የትዳር ህይወትን ለማስተካከል፣ የፍቅር አጋርን ለማማለል እና ለመምረጥ፣ ብሎም በወሲብ ዉስጥ ያለዉን ጥቅም ለማስተማር ይጠቀሙት እንደነበር ይናገራሉ፡፡
በፈረንሳይ የ ፖርኖግራፊ አብዮት በ600 በ ኢንላይትመንት ዘመን ( ከ748-49) የህትመት ሚዲያዉን መስፋፋት ተከትሎ እንደ ጀመረ ይነገራል፡፡ በዚሁ ሀገር ጆን ክሌላንድ የተባለ ደራሲ እና ጸሃፊ ፋኒ ሂል ( Funny Hill ) ተብሎ የተሰየመዉን ወሲብ ቀስቃሽ ልብወለድ በማቅረብ ይጠቀሳል፡፡
በኋላም ይህ ፉኒ ሂል የተሰኘ የፈረንሳይ ፖስት ካርድ ተብሎ ይሸጥ እንደነበር ይነገራል፡፡ በጃፓን በ6ኛዉ ክፈለ-ዘመን የወሲብ ቀስቃሽ ምስል ኢሮቲክ ዉደ ቡሎክ (Erotic wood block) ተብሎ እንደ ታተመ ተሪክ ያስረዳል፡፡ የፖርኖግራፊ ታሪካዊ አጀማመር በተያዩ ሀገራ ያለዉን እዉነታ እንገነዘባለን፡፡
ይህ የፖርኖግራፊ አብዮት በየሀገሩ እንዲህ እንዲህ እያለ እየተስፋፋ በ837እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር ንግስት ቪክቶርያ ወደ ስልጣን ሲመጡ በለንደን ከተማ ከ5ዐ በላይ የልቅ ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎች (ፖርኖግራፊ) ሱቆች እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በ9ኛዉ ክፍለዘመን የተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመላዉ አለም ሲተዋወቅ በዚያዉ የልቅ ወሲብ ፊልሞች አለማችንን ማጥለቅለቅ እንደጀመር በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ባጠቃላይ በእሩቅ ምስራቅ እና በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚገኙ ሜሶፖታማዉያን፣ ሱሜርያዉያን እና ግብጾች እና ህንዶችን ጨምሮ አረኪዮሎጂስቶች እንደሚናገሩት ይህን ወሲብ ቀስቃሽ ምስል እና እርቃን የሆኑ ፎቶዎች እና ስእሎችን በመጠቀም በስንፈተ ወሲብ የተጠቃን ግለሰብ የሚያክሙበት ጥበብ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
ይህን እርዳታ እና ህክምና የሚያደርጉበት ምክንያት በአከባቢዉ በርካታ ሰዎች የሚከተሉት እምነት ለተመስጦ ወይንም ለሜዲቴሽን ትልቅ ትርጉም እና ዋጋ ስለሚሰጡ፣ ስሜትን ማለትም ወሲባዊ ስሜትን መጫን እና ማጥፋት ለፈጣሪ እንደ መቀደስ ተደርጎ ስለሚወሰድና የእምነቱ ዋናዉና መሰረታዊ ቀነኖ በመሆኑ ከዚህም የተነሳ ቅድስናቸዉም ስለሚጨምር ፣ ነፍስ እና መንፈሳቸዉ ለፈጣሪ ስለምትለይ፣ በፈጣሪ ዘንድ ጽድቅም ተደርጎ ስለሚቆጠርላቸዉ ምናልባት ለወደፊት ትዳር መመስረት የሚፈልግ ሰዉ በ ስንፈተ ወሲብ የመጠቃት እድል ይኖረዋል ብለዉ በማመናቸዉ ይህን የፖርኖግራፊክ ቴራፒ (ህክምና)
አድርገዉ እንዳዘጋጁት ይናገራሉ፡፡
ከዚህ የተነሳ በወቅቱ የነበሩ የዚህ ስራ ባለሙያዎች እንዲህ አይነቱን ችግር ለመቅረፍ የሚሰጡት ህክምና እና እርዳታ የጎልማሶችን የዎሲብ ባህሪ ለማነቃቃት የተለያዩ ስእሎችን በመሳል በተለይም ወሲብ ቀስቃሽ ምስሎችን እንዲመለከቱ በማድረግ እርዳታ እና ህክምና መስጠት ከብዙ ሺ አመታት በፊት ጀምሮ የተለመደ እንደሆነ የፖርኖግራፊ ምስሎች ታካዊ አመጣጥ ያስረዳል።
ልቅ የወሲብ ፊልሞች (Pornography)- ተብሎ የሚጠራዉ ከድህረገጽ እና ከፊልም ኢንዱስተሪዉ ማደግ ጋር ተያይዞ አሁን መላዉን አለም እያወከ፣ እያሳመመ፣ አእምሮን እያበሰበሰ እና ትዉልድን እያጨነገፈ ያለ ገዳይ የ2ኛዉ ክፍለዘመን ድምጽ አልባ አዉዳሚ ጦርነት እና የጦር መሳርያ ነዉ፡፡ ፖርኖግራፊ የዚህ ትዉልድ ፈተና እና አጨንጋፊ ገዳይ መርዝ ነዉ፡፡
በአሜሪካን ሆሊዉድ፣ በህንድ በቦሊዉድ፣ በናይጄሪያ ናሊዉድ የፊልም ኢንዱስተሪያቸዉ ዉስጥ ከፍተኛ ክፍያ እየተከፈላቸዉ ይህንን አስጸያፊ ፊልም የሰሩ መልከ መለካ ሞዴል አርቲስቶች ብዙ ገንዘብ ቢያገኙም ስለተበላሸዉ ህይወታቸዉና ማንነታቸዉ የሰጡትን ምስክርነት የዚህን ገዳይ አደገኛ መርዛማ ፊልም መዘዝን መረዳት ይቻላል፡፡
ሰዎች በተለይም ወጣቶች ለምን በዚህ አደገኛ ፊልም ሱስ ይጠመዳሉ? ለምንስ ከገቡበት መላቀቅ ያቅታቸዋል? የሚያስከትለዉ ችግርስ ምንና ምንድነዉ? መዉጫ መንገዱ እና እርዳታ እንዴት ማግኘት ይቻላል የሚሉ ሃሳቦችን በዚህ ርእስ ስር እናያለን፡፡
ከላይ ለመመልከት እንደሞከርነዉ ፖርኖግራፊ ወሲብ ቀስቃሽ ፍልሞች ብቻ ማለት አይደለም፤ ወሲብን ሊቃሰቅሱ የሚችሉ እርቃን ፎቶ ግራፎች፣ ጽሁፎች፣ በድምጽ የሚተላለፉ ንግግሮች፣ ዳንሶች እና እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያካትታል፡፡
ይህን ትዉልድን በአደገኛ ሁኔታ እየፈጀ ያለዉ የፖርኖግራፊ ዳራ ይህ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ በዚያ ዘመን የተጀመረዉ ልቅ የወሲብ ቀስቃሽ ምስል አሁን አድጎ በማህበራዊ ድህረገጽ የእያንዳንዱን ሰዉ ጓዳ እያወከ፣ ትዉልድ እያበላሸ፣ ከትምህርት፣ ከስራ እና ከእድገት ሀገሪቷን ወደኋላ እያስቀረ፣ ከልጅ እሰከ አዋቂ የሚገኝን ትዉልድ አእምሮ እያበላሸ ይገኛል፡፡ ባጠቃላይ ፖርኖግራፊ የዚህ የ2ኛዉ ክፍለዘመን ትዉልድ አጨንጋፊ እና ገዳይ መርዝ ሆኗል፡፡
ስለ ፖርኖግራፊ አሁን ብዙ ማዉራት ሳይሆን ትዉልዳችንን እንዴት እንታደግ በሚል ብዙ መነጋገር እና እርምጃ መዉሰድ የሚገባን ሰዓት ላይ እንገኛለን፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ አሁን ለራሱ እና ለልጁ ብሎም ለትዉልድ ስነ አእምሮ እና መንፈሳዊ ጤና ይህንን አደገኛ ጦርነት ለመፋለም መነሳት ይገባዋል፡፡ ጌዜዉ ሳይረፍድ እና ሳይሄድብን በፖርኖግራፊ ላይ መዝመት ነው

❤26🔥3👏2👍1🤔1
'...አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ! በቀዝቃዛው ወራት በቤተልሔም በከብቶች በረት መወለድክን ባሰብን ጊዜ ከበረት ብዙም የማይለየው ህሊናችን ወዳንተ ሊገሰግስ ይበረታል!'
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!
❤26🔥3👍2👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
We can’t stay quiet seeing all the love our fearless leader, Mirafe, is getting! Not only did he make us proud, he also represented the rich history of Ethiopia and kept the vibe alive during iShowSpeed’s stream. Calm, eloquent, and clear, he communicated Ethiopia’s story with confidence and ease.
We’re incredibly proud of him. And if you thought he was impressive on the stream, just imagine what it’s like to work with him at ALX. #DoHardThings

❤4🔥3
🔴🔴 ዛሬ ብሞትስ በል!!! 🔴🔴
ዛሬ ብንሞትስ ብላችሁ አስቡ እስኪ
🔊 ለነገ ያሳደርናቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውን ይሞታሉ
🔊 ለነገ ያቆየናቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ
🔊 ዛሬ ሳናወጣው የደበቅነው ተሰጥኦአችን አብሮን ይቀበራል
🔊 ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ
🔊 ለሰዎች ያላሳየናቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል
🔊 ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ
🔊 ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት
ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት just do it now አይመስልህም ?

❤16👏4🔥2
የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የጉበት በሽታ ምንድን ነው ? ለግንዛቤ ያክል 👇👇
ጉበት በሆድ እቃችን ውስጥ ከሳንባችን ስር ከቀኝ ወደ ግራ አግድም የተቀመጠ አካል ሲሆን ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ፕሮቲኖችን ከማምረት ጀምሮ መርዛማ ነገሮችን በማጣራት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ምግቦች ብቻ ወደ ደም ስራችን እንዲደርሱ የሚያደርግ በጣም አስፈላጊ የሰውነት አካል ነው።
የጉበት በሽታ መንስኤዎች
የጉበት በሽታ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ቢሆንም እንደኛ ላሉ ታዳጊ ሀገራት የጉበት ቫይረሶች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።
ሄፓታይተስ B እና C ስር የሰደደ የጉበት በሽታ (Chronic liver disease )የሚያመጡ ሲሆን A እና E ደግሞ አጣዳፊ (Acute liver disease ) ያስከትላሉ።
1.የጉበት ቫይረሶች (A,B ,C , D ,E and G)
2.የተለያዩ መድሐኒቶች
3.ከመጠን በላይ የብረትና የመዳብ ክምችት ሲኖር (Hemochromatosis, Wilson disease )
4.የሰውነታችን የመቆጣት ችግርና የራሳችንን አካል በራሱ ሲያጠቃ (Autoimmune liver disease )
5.ከጉበት ወደ አንጀት የሚውስዱ ቱቦዎች በተለያየ ምክንያት ሲዘጉ
6.አልኮል አዘውትሮ እና ለረጅም ጊዜ መጠጣት
7.እና የመሳሰሉ ምክንያቶች
ሄፓታተስ ቢ ምንድን ነው(Hepatitis B infection )
ሄፓታይተስ ቢ ጉበትን የሚያጠቃ ቫይረስ ሲሆን ለጉበት በሽታ /Chronic liver disease/ መንስኤ የሆነና የማያቋርጥ ዓለም አቀፍ ችግር ነው።
ኢትዮጵያ በጣም ከተስፋፋባቸው ሀገራት ውስጥ ትመደባለች፡፡
በኢትጵያ የአንድ ሰው የዕድሜ ልክ ሄፓታይተስ ቢ መያዝ እስከ 80% ይደርሳል::
በሄፐታይተስ ቢ ከሚያዙ አዋቂዎች 90 % ሙሉ በሙሉ ይድናሉ::
በተወለዱበት ጊዜ ወይም ከአንድ አመት በፊት ከተያዙ ሕፃናት መካከል ደግሞ 90 % የሚሆኑት ሥር የሰደደ የጉበት በሽታ ይከሰትባቸዋል፡፡
ሄፓታይተስ ቢ እንዴት ይተላለፋል?
√በተበከለ ደም እና ሌሎች የሰውነት ፈሳሾች መጋለጥ
√በወሊድ ጊዜ ከእናት ወደ ልጅ
√በግብረ ሥጋ ግንኙነት
√ደህንነቱ ባልተጠበቀ መርፌ እና/ወይም ደም በመስጠት ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው ይተላለፋል።
በአጠቃላይ ሄፓታይተስ ቢ ከኤችአይቪ ከ 50-100 እጥፍ በበለጠ ይተላለፋል::
የሄፐታይተስ ቢ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ሀ) አጣዳፊ የሄፐታይተስ ቢ ኢንፌክሽን (Acute hepatitis B) ምልክቶች:
ድካም, ማቅለሽለሽ, ማስታወክ, የሆድ ህመም ፣ የቆዳ ,የሽንት እና የዓይን ቢጫ መሆን ናቸው።
ለ) ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ቢ(Cirrhosis) ያለባቸው ሰዎች ደግሞ
√የሆድ እብጠት, ያልተለመደ ደም መፍሰስ፣የኩላሊት ችግር(Hepatorenal syndrome )፣የሳንባ ህመም (Hepatopulmonary syndrome )፣ እና የአዕምሮ ሁኔታ መለወጥን(Hepatic Encephalopathy ) እና የመሳሰሉትን ያስከትላል፡፡
√የጉበት ሲርሆሲስ (Cirhossis) የጉበት ካንሰርን በማምጣት ለሞት ይዳርጋል ፡፡
√ሄፓታይተስ ቢ የሲርሆሲስ በሽታ በማይኖርበት ጊዜም እንኳ የጉበት ካንሰር (Hepato cellular carcinoma) ያስከትላል፣ ስለዚህ ቢያንስ በየ 6 ወሩ የህክምና ክትትል እና የአልትራሳውንድ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
የሄፓታይተስ ቢ መከላከያዎች ?
ሄፓታይተስ ቢን በክትባት መከላከል ይቻላል።
ክትባቶች መቼ ይሰጣሉ?
በብሔራዊ የክትባት መርሃ ግብር በተወለዱ፣ በ6 ፣ በ10 ፣ በ14 ሳምንታት ዕድሜ
ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ካለባት እናት የተወለደ ህፃን ክትባቱ በተቻለ ፍጥነት ከተወለደ በኋላ (በተወለደ በ24 ሰዓታት ውስጥ ማግኘት አለበት)፣ነገር ግን ክትባቱ በ24 ሰዓት ውስጥ መስጠት ካልተቻለ በተወለደ ሁለት ሳምንታት ውስጥ መስጠትም ውጤታማ ያደርገዋልና ክትባቱን መስጠት ያስፈልጋል ።
√የሄፐታይተስ ቢ ክትባቶች (ብዙ ጊዜ በ 0፣ በ1 እና 6 ወር ይሰጣሉ )
ክትባቱ ብዙ ጊዜ የሚሰጠው
-ለነፍሰጡር እናቶች
-የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ ታካሚዎች እና
-ለጤና ባለሙያዎች ወዘተ…።
ለሄፐታይተስ ቢ ሕክምናው ምንድነው?
* ቴኖፎቪር(TDF) እና የመሳሰሉ Anti viral Medication ሲሆኑ።
እነማን መድሀኒት መጀመር አለባቸው ስለሚለው
በ Guidelines በግልፅ ተቀምጧል።
√ሥር የሰደደ ሄፐታይተስ በአሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ አይድንም (no cure) ነገርግን በአብዛኛዎቹ ታካሚዎች የቫይረሱ መራባት መጠን መቀነስ እና የጉበት አሰራር መስተካከል በማምጣት የህመሙን ተፅዕኖ ይቀንሳል፡፡
ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ
በሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ መያዝን ተከትሎ ከ50 እስከ 85 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ሥር በሰደደ ሄፓታይተስ ይያዛሉ;: ይሁን እንጂ ሥር የሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ አብዛኛውን ጊዜ ቀስ በቀስ እያደገ የሚመጣ በመሆኑ በብዙ ታካሚዎች ግልጽ የሆነ የጉበት በሽታ ምልክት ላያመጣ ይችላል፡፡
ከ5 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት ሥር በሰደደ በሽታ የተያዙ ሰዎች ከ 20 እስከ 30 ዓመታት ባለው ጊዜ ውስጥ የሲርሆሲስ በሽታ ይያዛሉ፡፡
የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የመተላለፊያ መንገዶች
-የተበከሉ የሕክምና መርፌዎች ወይም መሣሪያዎች
-ከተዛማች ለጋሽ ደም መውሰድ
-በስራ ላይ የደም መጋለጥ (የመርፌ ጉዳት)
-በበሽታው ከተያዘች እናት መወለድ;
-የእንሽርት ውሀ ለረጅም ጊዜ መፍሰስ
-በበሽታው ከተያዙ አጋሮችጋር ልቅ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ
√በንቅሳት እና አካል መበሳት
√በሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የተበከሉ መሳሪያዎች መጠቀም ናቸው ።
የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህመም ምልክቶች
አብዛኛዎቹ በአጣዳፊም ሆነ ሥር በሰደደ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ የተጠቁ ታካሚዎች ምንም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል፡፡
የአጣዳፊ ሄፓታይተስ ሲ ምልክቶች
-ማቅለሽለሽ፣
-ሽንት መጥቆር፣
-የቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም፣
-መጠነኛ የሆነ ትኩሳት፣
-ብርድብርድ ማለት፣
-የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣
-ሰውነትን ማሳከክ፣
-የጡንቻ እና የመገጣጠሚያ ህመም፣
-የስሜት መረበሽ ሊኖራቸው ይችላል።
አጣዳፊ ሕመም አብዛኛውን ጊዜከ 2 እስከ 12 ሳምንታት ይቆያል፡፡
ሥር የሰደደ የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ኢንፌክሽን ምልክቶች?
√ድካም የተለመደ ምልክት ነው.
አንዳንዴ ማቅለሽለሽ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመም፣ክብደት መቀነስ
ምልክቶቹ እንደ ድብርት ካሉ ሌሎች በሽታዎች ጋር ስለሚመሳሰሉ ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ::
ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህክምናው
√ሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ከሰውነታችን በመድሀኒት መጥፋት የሚችል (curable) ህመም ሲሆን መድሀኒቶችን በአብዛኛው ለ12 ሳምንታት በመውሰድ መታከም ይቻላል፡፡
ለሄፐታይተስ ቢ እና ሲ ቫይረስ ምርመራ ቅድሚያ መመርመር የሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች፤
√የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ ልምምዶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ በሚሆኑባቸው ቦታዎች
√ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች
√ነፍሰጡር እናቶች
√ከሄፐታይተስ ቢ ወይም ከሄፐታይተስ ሲ ከተያዙ እናቶች የተወለዱ ልጆች
√ኤች.አይ.ቪ.በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች
√የጤና ባለሙያዎች
√ደም ወይም የደም ተዋጽኦ የተሰጣቸው ሰዎች
√የህግ ታራሚዎች
√ቤተሰብ ወይም የትዳር አጋር ህመሙ ካለባቸው
√በወሲብ ስራ የሚተዳደሩ ሰዎች
√በርካታ የወሲብ አጋሮች ያለው/ላት ወይም የአባላዘር በሽታ ያለበት/የታከመ ሰው
√የኩላሊት እጥበት ላይ ያሉ ታካሚዎች

❤8
የበሽታ መከላከያ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች?
የሄፐታይተስ ቢ ሆነ የሄፐታይተስ ሲ ቫይረስ ህክምና በኢትዮጵያ በተወሰኑ የመንግስት ሆስፒታሎች የሚሰጥ ሲሆን ምርመራውን አድርጎ ቫይረሱ የተገኘበት ሰው ወደ ሆስፒታሎች በመምጣት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላል።
መልካም ቀን ☕️
#share

❤9🔥2👏1