The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
#Treasury_Bill (የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ)

መንግስታት በሁለት ምክንያት የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ያቀርባሉ…

የመጀመሪያዊ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመስራት የካፒታል ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት (መንግስት ገቢ ከመሰብሰቡ በፊት ፕሮጀክቶቹ በፋይናንስ እጥረት እንዳይቆሙ ከገበያው በወለድ በመበደር ለማከናወን በማሰብ) ሲሆን…..

በሁለተኝነት በገበያው ያለውን የገንዘብ አቅርቦት እና ፍላጎት ለማመጣጠን ሲል (የገንዘብ አቅርቦትን ለመጨመር ባሰብ ጊዜ ከገበያው ሰነድ በመሸጥ መበደሩን ሲያቆም የገንዘብ አቅርቦት እንዲቀንስ ከገበያው በሰነድ በመበደር ገንዘቡን በዘዴ ይሰበስባል "ሰነድ በሰዎች እጅ ገንዘብ በማዕከላዊ ባንክ እጅ ይገባል ማለት ነው" ነው፡፡

መንግስታት የግምጃ ቤት ሰነድ በቀጥታ በራሳቸው ቻናል ለሽያጭ በጨረታም ሆነ ያለጨረታ ሊያቀርቡም ሆኑ በሁለተኛ ገበያ/በካፒታል ገበያ በኩል ለሽያጭ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ መንግስት ለሸጠው ሰነድ መተማመኛ የሚሆን ሰርተፍኬት ለሰነድ ገዢ (ግለሰብ ወይም ድርጅት) ይሰጣል፡፡

የግምጃ ቤት ሰነድ ለአጭር ጊዚያት ማለትም (ከ28 ቀን እስከ 365 ቀናት የቆይታ ጊዜ ሊኖራቸው ሲችል እንደቆይታ ጊዚያቸው የወለድ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል) የሰነዱ የክፍያ ወቅት (Maturity) ሲደርስ መንግስት ወለዱን በማሰብ ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል፡፡

የግምጃ ቤት ሰነድ ወለድ አስተሳሰቡ ሁለት አይነት ዘዴ ሊኖረው ይችላል (ወለድ ማስቀመጥ (ለምሳሌ ለተገዛው ሰነድ መጠን 3 ከመቶ ወለድ ማሰብ እንደማለት) አልያም የመሸጫ እና የመክፈያ መጠን ማስቀመጥ (ለምሳሌ የ100 ብር ሰነድን በ95 ብር እንደመሸጥ አይነት (በ95 የገዛ ሰው 100 ብር ተደርጎ ይከፈለዋል እንደማለት ነው)፡፡

ሃሳቡን በቀላሉ እድትረዱት የኢትዮጲያ ልማት ባንክ የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ቦንድ ለህዝብ አቅርቦ ሰዎች በቻሉት መጠን በሙሉ ገዝተዋል ከአምስት ዓመታት (Maturity) በኋላ ወለድ በማሰብ ክፍያ ሲፈጽም የምትመለከቱት የእዳ ሰነድን ይወክላል (የህዳሴው ግድብ የግምጃ ቤት ሰነድ ሳይሆን እንደቆይታው በኖት እና በቦንድ ውስጥ ሊጠቃለል ይችላል (በኢትዮጲያ ሁኔታ አሁን ላይ የግምጃ ቤት ሰነድ ለልማት ድርጅቶች (የፋይናንስ ተቋማትም ይጋበዛሉ!) በሽያጭ የሚቀርብ ሲሆን ወደፊት የስቶክ ገበያው ሲከፈት ለጠቅላላ ገበያው ሊለቀቀቅ ይችላል፡፡

የግምጃ ቤት ሰነድ ከሌሎች የመንግስት የእዳ ሰነዶች አይነት የአጭር ጊዜ እዳ ነው፡፡ ሌሎቹ Treasury Note ከ1- 10 ዓመት ቆይታ ያለው ብድር ሲሆን Treasury Bond እስከ 30 ዓመት ሊቆይ የሚችል እዳ የሚይዙ ናቸው፡፡

የግምጃ ቤት ሰንድ ሻጩ መንግስት በመሆኑ ላይከፈል ይችላል/ Default የሚል ስጋት የሌለበት ነው፡፡ አንድ ሰነድ የገዛ ሰው የመክፈያው ወቅት እስኪደርስ ወለድም ሆነ የከፈለውን ገንዘብ ባያገኝም ለሌላ ሰው (በካፒታል ገበያ በኩል የመሸጥ እድል ግን ይኖረዋል)፡፡

የግምጃ ቤት ሰነድ በባህሪው ዝቅተኛ እና ቋሚ ወለድ የሚታሰብበት (አንዴ ለሽያጭ ከቀረበ በኋላ ዋጋ ንረትን ከግምት በመክተት የማይለዋወጥ) በመሆኑ ስጋት የሚፈጥር ሲሆን የመንግስት መተማመኛ ያለው እና በካፒታል ገበያ በኩል በቀላሉ ለሌላ ሰው መሸጥ የሚችል መሆኑ እንደ እድል ያስቆጥረዋል፡፡
#ጥሩ_ዜና፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለግብርናው ዘርፍ የብድር ወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ። “የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የሆነ ያልታረሰ የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል (DBE)።”
👍1
ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግም ሆነ የበጀት ጉድለትን ለመሙላት ለዘመናት የቆየ የውጪ ሀገራት እና ተቋማት እዳ አለባት።

ከውጪ እዳ ማቅለያ ስልት መካከል ዝቅተኛ ወለድ ያላቸው ብድሮች መውሰድ እና ከአበዳሪ ሀገራት እና ተቋማት ጋር ድርድር በማድረግ የእዳ ስረዛ እና የእዳ መክፈያ ጊዜን ማስረዘም አሉበት።

በዛሬ ዜና ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ከኢትዮጵያ የግማሽ እዳ ባለቤት ከሆነችው ቻይና እና ከዋናዎቹ የበለፀጉ አበዳሪ ሀገራት እና ተቋማት ጋር በነበራት ድርድር የመክፈያ ጊዚያቸው ከተቃረበ እዳዎች መካከል 1.5 ቢሊየን ዶላር ወደፊት ከ2027-2029 ባለው ጊዜ እንድትከፍል እፎይታ ተሰጥቷታል።

የእዳ ክፍያ ተራዘመ ማለት ለእዳ ክፍያ የተዘጋጀን የውጪ ምንዛሬ ለአንገብጋቢ ጉዳይ ለመጠቀም እድል ይሰጣል።
በቢዝነስ ፕላን ጥናት ለተከታታይ ዓመታት "የተጣራ ትርፍ" Income Statement አሰራር!

አንድ ቢዝነስ ለማቋቋም እና ለተከታታይ 10 ዓመታት ሊኖሩት የሚችሉት ወጪዎች (Operational Cost) እና ገቢዎችን (Revenue) በመሰብሰብ እንዴት ከተቀናናሾች (Depreciation, bank interest, tax, etc) በኋላ የተጣራ ትርፉን በExcel በቀላሉ ማስላት እንደሚቻል የሚከተለውን https://youtu.be/6hjm1kdKVbI ጥሩ ምሳሌ ተመልከቱ።

IMF የ2023 የመጨረሻ የኢኮኖሚ ሪፖርት (World Economic Outlook) በዓለም ዙሪያ ያለው ልዩነት (Navigating Global Divergences) በሚል አውጥቷል።

የአፍሪካ GDP 2.86 ትሪሊየን ዶላር፤ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 1.4 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን፤  አማካይ የአህጉሪቱ የእዳ መጠን ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት አንፃር 65.2 ከመቶ ደርሷል፤.......

በ2023 ከፍተኛ የGDP እድገት ያስመዘገቡ የአፍሪካ ሀገራት ሞዛምቢክ (7%)፤ ኮንጎ (6.7%)፤ ኮትዲቫር (6.2%)፤ ርዋንዳ (6.2%)፤ ኢትዮጵያ (6.1%)፤.........

በሪፖርቱ የዓለም ኢኮኖሚ እና የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሪፖርት እና ትንበያ ቀርቧል። ጠቅላላ ሰነዱን (182 ገፅ) ማንበብ ለምትፈልጉ እና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በንፅፅር መመልከት ለምትፈልጉ https://t.me/WaseAlpha ቴሌግራም ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
"በአቋራጭ ለመክበር አትሞክር!" የሚል የውጤታማነት መርህ ምክር ለኢኮኖሚስቶች ቢቀርብ፣ በኢኮኖሚክስ ውስጥ የአመክንዮ እንጂ የሞራል ጉዳይ የመጀመሪያ ረድፍ ባለመሆኑ እንዴት የሚረዱት ይመስላችኋል?
የኢትዮጵያ የውጪ እዳ ዝርዝር (የ2023 የዓለም ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት)!

ኢትዮጵያ ከነጠላ ሀገራት ከወሰደችው የውጪ እዳ ውስጥ የቻይና ድርሻ 20ከመቶ መድረሱ ምን ያሳያል?

የኢትዮጵያ የውጪ እዳ ከኤርትራ እና ከኬንያ የውጪ እዳ አንፃር ብናስተያየው ምን አይነት ልዩ ባህሪ አለው....

https://youtu.be/GzPPiV3IBTw

ሪፖርቱን ማንበብ ለምትፈልጉ https://t.me/WaseAlpha ከቴሌግራም ላይ መውሰድ ይችላሉ (የ183 ሀገራት እዳ ዝርዝር ተቀምጧል)።
International Debt Report 2023.pdf
4.2 MB
የዓለም ሀገራት የውጪ እዳ ዝርዝር ሪፖርት (World Bank, 2013)
የኢትዮጵያ የውጪ እዳ ዝርዝር (የ2023 የዓለም ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት)!

ኢትዮጵያ ከነጠላ ሀገራት ከወሰደችው የውጪ እዳ ውስጥ የቻይና ድርሻ 20ከመቶ መድረሱ ምን ያሳያል?

የኢትዮጵያ የውጪ እዳ ከኤርትራ እና ከኬንያ የውጪ እዳ አንፃር ብናስተያየው ምን አይነት ልዩ ባህሪ አለው....

https://youtu.be/GzPPiV3IBTw

ሪፖርቱን ማንበብ ለምትፈልጉ https://t.me/WaseAlpha ከቴሌግራም ላይ መውሰድ ይችላሉ (የ183 ሀገራት እዳ ዝርዝር ተቀምጧል)።
ኢትዮጲያ ገንዘቧን የት ነው የምታሳትመው?  በሀገር ውስጥ ብር ቢታተም ምን አይነት እድል እና ስጋት ሊኖረው ይችላል?

ሀገራት ብራቸውን ለምን በብዛት አያትሙም? ሀገራት የራሳቸውን ገንዘብ የማተም መብት አላቸው? ሀገራት ለምን ገንዘባቸውን በሌሎች ሀገራት እዲታተም ያዛሉ? ይህንን ሰፋ ያለ ትንታኔ እስከመጨረሻ ተከታተሉት፡፡ https://youtu.be/AjAMg_NgH70
በባንክ እና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን የምንዛሬ ተመን ልዩነት እንዴት ማቀራረብ ይቻላል?

ምንዛሬን ከማቀራረቢያ ስልቶች መካከል...

1. በማዕከላዊ ባንክ ውስጥ የውጪ ምንዛሬ ክምችትን ማሳደግ፤

2. የምንዛሬ ተመንን በውሳኔ ማዳከም (Devaluation)፤

3. የጥቁር ምንዛሬ ገበያን በቁጥጥር ለማስቆም መሞከር፤

4. ቅይጥ የምንዛሬ ተመን ስልትን (Dual Exchange Rate)፤

5. ምንዛሬ ገበያን በገበያ እንዲወሰን መፍቀድ (Floating Exchange Rate)፤

ከነዚህ በጥቁር የምንዛሬ ገበያ እና በማዕከላዊ ባንክ የምንዛሬ ተመን መካከል ያለን ልዩነት ለማቀራረብ ውጤታማ የሚሆነው የትኛው ነው?

የምንዛሬ ተመን ውሳኔ ከኢኮኖሚያዊ መነሻ ምክንያት በዘለለ የፖለቲካ እና የዓለም አቀፍ ግንኘነት ግፊት የበረታበት ነው። ታዲያ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንኮ ቀላሉ እና ከባዱ ስልት የትኛው ሊሆን ይችላል? የሚከተለውን https://youtu.be/kuSZgLpXeGg ትንታኔ ብትመለከቱ ምላሽ ይኖረዋል።

ከ5 ሺህ 500 በላይ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ያቀፈው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ‘ የኢትዮጵያ ብሪክስ ቡድንን መቀላቀል ጥቅም እና ስጋት ’ን የፈተሸ የባለሙያዎች ዳሰሳ አድርጎ ነበር  (በዳሰሳው 233 የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል)" የግኝቱ ዋነኛ ነጥቦች.....

* 49% የሚሆኑ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን የተቀላቀለችው በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች ተገፍታ ነው ብለዋል።

* 47% የሚሆኑት አዳጊ ኢኮኖሚ ስላላት ነው ብለዋል።

* 45.5% የጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶችን አንስተዋል።

* 41% እና 39% እንደቅደም ተከተላቸው ከምዕራባውያን ጋር የግንኙነት መሻከር እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በገፊ ምክንያትነት ጠቅሰዋል።

- ከተሳታፊ ባለሙያዎች ውስጥ ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ያሉት 51% ሲሆኑ 25% የሚሆኑት በተቃራኒው እንደሚሆን ገምተዋል።

Source፦ #ቲክቫህኢትዮጵያ

ከዚህ ቀደም በThe Ethiopian Economist View  "ኢትዮጲያ BRICSን መቀላቀሏ ሊኖረው የሚችለው ጥቅም እና ጉዳት ምንድን ነው?" ላይ የቀረበ ትንታኔን ለመመልከት.....

በመጀመሪያ አባል በመኮኑ ማታሰብ ያለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ተግባራዊ ስጋቶች ከአሜሪካ እና ከምዕራቡ ዓለም በምላሽ መልክ መምጣቱን ማሰብ፤ ስለ አዲስ ህብረቶች ሁኔታ መዘጋጀት እና BRICSን የመቀላቀል ጥቅሞች እና BRICS በመቀላቀል የሚመጡ አደጋዎችን ማመዛዘን ይገባል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን ትንታኔ ይመልከቱ https://youtu.be/k_gJB3G2vM8
የፈረንጆች ዓመት መጠናቀቂያ ወር (December) ላይ ብዙ ተቋማት ዓመታዊ ትርፋቸውን እና የአክሲዮን ትርፍ ክፍፍል መጠናቸውን ያቀርባሉ! የሪፖርት ቁጥር የቢዝነስ ስትራቴጂ አንድ አካል የመሆን እድል ስላለው ቁጥሮችን (ትርፍ እና የትርፍ ክፍፍል) በጥንቃቄ መመርመር ይገባል።

በቀጣይ ነባር አክሲዮኖች ለመሸጥ ጥሪ ስለሚያደርጉ ተቋማትም ሆነ አዳዲስ የአክሲዮን መመስረቻ አክሲዮኖች ለመሸጥ ከሚያስቡ ለመግዛት ለሚያስቡ.....

አዲስ አክሲዮን በመግዛት እና ነባር አክሲዮን በመግዛት መካከል ያለው ልዩነት፤ እድል እና ስጋት! አክሲዮኖችን መግዛት ኢንቨስትመንት መሆን የሚችለው የተጠና እና ምክንያታዊ ሲሆን ነው። የአክሲዮን ትርፋማነት እንዴት ይለካል?

ስለዚህ አዲስ የሚመሰረት አክሲዮን ለመግዛት እና ስራ ከጀመሩ ተቋማት ነባር አክሲዮን ለመግዛት ከመወሰን በፊት ከግምት መከተት ያለባቸው ጠቃሚ ሃሳቦችን https://youtu.be/x0niSsaddBc  ይመልከቱ።
ኢኮኖሚክስ ከ A እስከ Z ውስጥ ሲገለጽ!

የኢኮኖሚክስ ትምህርት በጣም ጥልቅ እና ከሁሉም የትምህርት ዘርፎች ጋር ጠንካራ ግንኙኘት ያለው ነው፡፡ ስለዚህ በዓለም ላይ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ከተጀመረ ጀምሮ ኢኮኖሚክስ ዘርፍ ውስጥ በዋናነት የሚጠቀሱ ቃላትን ከነትርጓሚያቸው በቅደም ተከተል ከA እስከ Z ውስጥ ያሉ መሰረታዊ የኢኮኖሚክስ ቃላቶችን ይወቋቸው፡፡

ከመጀመሪያው Absolute Advantage (A) እስከ መጨረሻው Zero-Sum Game (Z) ዘ ኢኮኖሚስት ላይ ብትፈልጉ ከነትርጉማቸው በጣም ብዙዎቹን የምታገኗቸው ምርጥ ቃላቶች ሲሆኑ ዋና ዋና የሚባሉት በመምረጥ ከዚህ
https://youtu.be/OuzPMyrLd4k ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡

ኢትዮጵያ የውጪ ብድር ዕዳ መክፈል ያለመቻል አመክንዮ እና ስጋት ምንድን ነው? የተሰጣት የብድር መክፈል ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ቀጣይ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም አቀፉ የዕዳ ጫና ዝርዝር በሚያወጣው ፊች የተሰጣት ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም ሀገራት የውጪ ዕዳ የመክፈል አቅም ደረጃ (ከAAA እስከ D) እንዴት ይመደባሉ?

የኢትዮጵያ መንግስት የውጪ ዕዳ ባለመክፈል የሚፈጠርን ጫና ለመቋቋም ምን አይነት ተገማች እርምጃዎች ሊወስድ ይችላል?

በጥልቀት ያለውን ትንታኔ እና መረጃ ከሚከተለው https://youtu.be/OsbhuVpYosw ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ።

የዓለም ሀገራት የዕዳ ክፍያ ሁኔታ ደረጃን እና በየደረጃው ያለውን ትርጓሜ መመልከት ለመትፈልጉ https://t.me/WaseAlpha ላይ pdf አስቀምጫለሁ።