The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርአት ማሻሻያን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ!
#ለመረጃ!
ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ "የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል።

የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF)፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።
*ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ስለ አዲሱ ፖሊሲ። ፕሮፌሰሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማክሮ እና ኢንተርንኛሽናል ኢኮኖሚክስ ተመራማሪ ናቸው።*

*"እኔ በአዲሱ ፖሊሲ ትግበራ በጣም አዝኛለሁ::*

*በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የዚን ፖሊሲ አደገኝነት ሳብራራ ነው የከረምኩት።* ⁉️

*ይህ ፖሊሲ አደገኛ ሚሆንበት የተለያዩ ምክኒያቶች አሉት፡* ⁉️

⁉️ *1* . አቅርቦትና ፍላጎትን ማዋሃድ አስቸጋሪ ነው። ቢያንስ ቀስ ብለው ቢሄዱበት የተሻለ ይሆን ነበር። በርግጠኝነት አይወሃድም የምናየው ነው ሚሆነው ግን ያ ሚሆንበት እድል በጣም አነስተኛ ነው። 14 ቢሊዮን እየገዛን 3.5 ቢሊዮን እየሸጥን አቅርቦትና ፍላጎትን ማመጣጠን አይሆንም። የብር ዋጋ እየረከሰ ይመጣና የዋጋ ንረት አዙሪት ውስጥ ነው ምንገባው። ሱዳንም ላይ ያየነው ነገር ነው ይሄ።

⁉️ *2.* የዋጋ ንረቱ በህዝቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በመንግስትም ላይ ነው ሚመጣው። ከ 30-40% ሚሆነው የመንግስት በጀት በራሱ የውጭ ምንዛሬን ሚፈልግ ነው። ስለዚህ በዚም ይባዛል ማለት ነው። ታክስ የመሰብሰብ አቅሙ፣ ጦርነቱ እንዲሁም ሌሎች ተግዳሮቶች አሉበት። ከጠቅላላው GDP 15% የነበረው ታክስ አሁን 6 እና 7% ነው ይሄ በሆነበት ከየት አምጥቶ ይሸፍነዋል? ብድር እንሰጣለን ሚሉትም ነጮቹ ሚሰጡን አማራጮች ታክስ ጨምሩ፣ ወጪ ቀንሱ ነው ሚሉት ያንን ደግሞ ሚሸከም ኢኮኖሚ የለንም። ይህ ሁሉ ደግሞ ከብሄራዊ ባንክ ወደ መበደር እንዲሁም ብር ወደማተም ነው ሚወስደን ይበልጥ ጣጣውን እየጨመረ ነው ሚሄደው።

⁉️ *3.* ሌላኛው ደግሞ ሰው ላይ ሚያመጣው ተጽኖ ነው። ሰዉ የዋጋ ንረትን መሸከም ማይችልበት ደረጃ ላይ ነው ያለው። 70% ሚሆነው ህዝብ የወር በአማካኝ ሚያገኘው ደሞዝ 5000ብር ነው። ይህን ሚሸከም አቅም ያለው ሰው የለም እያልኩ በየቦታው ስጮህ ነው የቆየውት። ምንም እንኳን ይህን ደሞዙን ብትጨምርለት ግሽበቱን በሚሄድበት ልክ መጨመር አይቻልም።

*መልካም ጎኖች አሉት ወይ?* ⁉️

‼️ብዙ ሚታየኝ መልካም ጎን አላየውም።

‼️ምናልባት ምናልባት በኮንትሮባንድ ሲወጣ የነበረው እቃ ወደ ዋናው ገበያ ሊመጣ ይችላል።

‼️IMF እንደሚለው ከውጭ ሚገቡ እቃዎች ይቀንሳሉ ሚለው አይሆንም።

‼️ ኤክስፖርትም በአንዴ መጨመር አንችልም።

‼️ከ 200 በላይ ድርጅቶች ጠይቀን ባደረግነው ጥናት አብዛኞቹ ችግራቸው የጸጥታ፣ የዶላር እጥረት እና የጉምሩክ ችግር ነው ይሄን ሳትፈታ የገንዘብ ፖሊሲ ብትቀይር ለውጥ አያመጣም።

‼️እንደ ኢኮኖሚስት እና ተመራማሪ ተስፋ ምትቆርጥበት ነገር ነው። ተመራምረህ ለፍተህ ይሄ ነው ሚመጣው ብለህ እንደ ነብይ ቀድመህ ተናግረህ ይሄ ሳይፈጸም ቀርቶ ሰዉ ሲሰቃይ ስታይ ኬንያ፣ ግብጽ ላይ ሄጄ አልመራመርምንዴ ምትልበት ነው። እንግዲ መጸለይ ነው። *ተስፋ ማደርገው እኔ ተሳስቼ ሰዉ እና ሃገሩ ደና እንዲሆን ነው።"*

ከሸገር FM::
Give & Take!

በኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ግብይት  በገበያ እንዲወሰን ተደረገ! የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር #ብድር አፀደቀ!
በዓለም ላይ የምንዛሬ ተመንን በገበያ ለማድረግ የወሰኑ ሀገራት ከውሳኔው በኋላ ኢኮኖሚያቸው የገጠመው.....!

ከውሳኔ ጀምሮ በኢትዮጵያ ገበያ ምን እየተከሰተ ነው!

ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ለመመለስ......

1. ዶላር 74 ብር ሆነ ማለት Devaluate ተደረገ ወይስ Floating ተደረገ?

2. የምንዛሬው ፖሊሲ መንግስት በእድል ኢኮኖሚስቶች ደግሞ በስጋት ለምን ይገልፁታል?

3. ከውሳኔው በኋላ ጥቁር ገበያ ለምን አልጠፋም?

4. ብሔራዊ ባንክ ከተለያየ ምንጭ አገኘሁት የሚለው 13ቢሊዮን ዶላር የእውነት ነው?

5. የIMF ብድር ድጋፍ ሊባል ይችላል?

6. የንግድ ባንኮች አሁንም ከብሔራዊ ባንክ ተመን እየጠበቁ ነው? (ሰኞ እለት ለምን ዘግይተው ምንዛሬ ተመኑ? ለምን ተመሳሳይ ተመን አደረጉ?

ይህንን ትንታኔ ለመመልከት https://youtu.be/3qzpOs5B6_c

ይህ ነው Floating Exchange Rate (ምንዛሬን በገበያ መወሰን) ማለት፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዶላር ያለው ፍላጎት ስለጨመረ (አልያም የዶላር አቅርቦት ስለቀነሰ) በአንድ ቀን ውስጥ የአሜሪካ ዶላር የመግዣ ዋጋውን ከ74.73ብር ወደ 77.12 በሰዓታት ወስጥ ደግሞ ከ77.12ብር ወደ 80.02 ብር አሳድጓል!
Channel photo updated
ይህ ነው Floating Exchange Rate (ምንዛሬን በገበያ መወሰን) ማለት፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዶላር ያለው ፍላጎት ስለጨመረ (አልያም የዶላር አቅርቦት ስለቀነሰ) በአንድ ቀን ውስጥ የአሜሪካ ዶላር የመግዣ ዋጋውን ከ74.73ብር ወደ 77.12 በሰዓታት ወስጥ ደግሞ ከ77.12ብር ወደ 80.02 ብር አሳድጓል!
ዋጋ ንረት ሲጨምር (የምንዛሬ ተመን በፍጥነት ሲለዋወጥ) "Shoe Leather Costs" እና "Menu Costs"

የአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ሰሞን ማለትም ከ1921-1923 በጀርመን ከፍተኛ የዋጋ ንረት በየቀኑ በመከሰቱ ሰዎች ግራ በመጋባት ገንዘባቸውን ይዘው ወደ ባንክ ይሄዱና የተሻለ በተባለው ምንዛሬ ለመለወጥ ይሞክሩ ነበር! እና በወቅቱ ወደ ባንክ በመመላለስ ብዛት ጫማቸው ስለሚጎዳ የቆዳ ጫማቸውን የጉዳት ዋጋ ያጠቃልሉ ነበር! ከዚያ ወዲህ በኢኮኖሚክስ ውስጥ ፈጣን የዋጋ ንረት መፈጠር ከሚፈጥረው ያልታሰበ የእግር መመላለስ በተነሳ "Shoe Leather Costs" የሚለው ቃል ታዋቂ ነው፡፡

በተመሳሳይ በፍጥነት የሚለዋወጥ ዋጋን ለመቋቋም ሰዎች ከባንክ ወደ ገበያ የሚኖራቸው ምልልስ ይጨምራል! በፍጥነት በሚለወጠው ዋጋ ለመሸመት ከባንክ ተጨማሪ ገንዘብ ለማውጣት የሚኖር መመላለስ ከፍተኛ በመሆኑ! ወደ ባንክ ካሽ ፍለጋ ከመመላለስ ከፍተኛ ካሽ በቤታቸው ይዘው ይጠባበቃሉ (ምልልሱ ትርፉ ጫማ መጨረስ ነው!)

ዋጋ ንረት በፍጥነት የሚለዋወጥ ሲሆን ሬስቶራንት ያላቸው ሰዎች የነበራቸውን የምግብ፤ የመጠጥ እና የአገልግሎት ዋጋ መለዋወጣቸው አይቀርም! በመጀመሪያ 100ብር የነበረ ምግብ በነጋታው 102ብር ቢሆን አዲስ ሜኑ ያትማሉ! በተካታታይ ከሆኑ በየቀኑ አዳዲስ ዋጋን አውጥተው ሜኑ መለወጣቸውን ይቀጥላል! በዚህ ወቅት ሜኑ ለማሳታም የሚያወጡት ወጪ "Menu Costs" የሚለው ቃል ታዋቂ ምሳሌ ነው፡፡ (እንዳንድ ሜኑ ላይ በፕላስተር የተለጠፈ አዲስ ዋጋና በነበረው ላይ ተደርቦ የተጻፈ የምትመለከቱት ሜኑ በተደጋጋሚ ወጪ በማውጣት ከማሳተም በሚል ነው!)፡፡

በዚህ ወቅት ኢትዮጲያ ውስጥ ከሸማች በላይ ቸርቻሪና አከፋፋይ የመሸጫ ዋጋ ለማውጣት መጨነቁ አይቀርም (በየትኛው የምንዛሬ ተመን ይወስናል?)
ዋጋ ንረት (Inflation) ዜሮ እንዳይሆን የሚፈልጉት መንግስት እና ብሄራዊ ባንክ ናቸው!

ለምሳሌ ያህል……

አምና 100ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ 110ብር ቢሸጥ (10% ዋጋ ንረት ይባላል)!

አምና 100ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ 90ብር ቢሸጥ (-10% ዋጋ ንረት ይባላል)!

አምና 100ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮም 100ብር ቢሸጥ (0% ዋጋ ንረት ይባላል)!

የሚከተለውን አመክንዮ ይመልከቱ...

https://youtu.be/g7qrIeD4jDk?si=DHFXNjA9by3cttxx
የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (World Bank) ድርጅቶች ልዩነት፤ አባላቶቻቸው፤ ከፍተኛ ባለድርሻዎቻቸው፤ ከፍተኛ ተበዳሪዎቻቸው፤.....

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የዓለም ባንክ (World Bank) ድርጅቶች አመሰራረት እና ልዩነት.....

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ከፍተኛ ባለድርሻዎች እና ከፍተኛ ተበዳሪዎች ዝርዝር.....

የዓለም ባንክ ከፍተኛ ባለድርሻዎች እና ከፍተኛ ተበዳሪዎች ዝርዝር.....

የዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ አባል ያልሆኑ 7ቱ ሀገራት ዝርዝር....

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ዝርዝር መረጃ https://youtu.be/nKVcsts-GpY ተመልከቱ!
IMF ኢትዮጵያ የምንዛሬ ተመኗን በገበያ በመወሰኗ (Floating Exchange Rate በመከተሏ) በምትኩ የሚያገኘው ምንድን ነው?

IMF ለኢትዮጵያ ባዘጋጀው የሪፎርም ሰነድ ላይ....

የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት በ2017 ወደ (30.1%) ያድጋል ከዚያ በ2018 (16.2%)፤ በ2019 (12.2%)፤ በ2020 (10.4%) እና በ2021 (9.6%) ይሆናል የሚል የትንበያ ቀመር አለው።

ይህ IMF የኢትዮጵያ መንግስት ካዘጋጀው የኢኮኖሚ ሪፎርም (የምንዛሬ ተመንን በገበያ መወሰንን ጨምሮ) ጋር የተያያዘ እና ለዚህ ፕሮግራም ከሰጠው እና ከሚሰጠው ድጋፍ እና ብድር ጋር የተያያዘ ነው....

ታዲያ IMF ሀገራት እንዲያድጉ ከፈለገ ለምን በሪፎርሞቹ (Privatization፤ Liberalization፤ Exchange rate reform፤ ወዘተ) ላይ ክርክር እና አመፅ ይነሳል?

ይህንን ትንታኔ ለመመልከት https://youtu.be/8bclfQ06UzI

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነገው ዕለት  የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው!

የውጪ ምንዛሬ (የአሜሪካ ዶላር) ለመግዛት ፍላጎትት ያላቸው ባንኮች እንዲያመለክቱ ጥሪ ቀርቧል (አንድ ባንክ ለጨረታ ከሚቀርበው ዶላር ውስጥ ከፍተኛ መግዛት የሚችለው 20% ነው)።
ጨረታው በሚቀጥለው ሳምንትም እንደሁኔታው ሊኖር ይችላል ይላል!

ጨረታው የባንኮች የምንዛሬ ተመን ፍጥነት እና መጠን ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል የብሄራዊ ባንክ መሳሪያ ነው!
አንዳንድ ኢኮኖሚስቶች የምንዛሬ ተመኑ በገበያ መወሰኑ የዘገየ እና #በረከት ይዞ የመጣ ነው ሲሉ ሌሎች የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ደግሞ ቅድመ ዝግጅት የሌለው እና #አደጋ ሊፈጥር ይችላል ይላሉ!

የመንግስት ኢኮኖሚስቶችን አመክንዮ ጨምሮ የሃገራችን ታዋቂ ኢኮኖሚስቶች (ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ) ፅሁፍ እና ኢንተርቪው ስመለከት የገባኝን ነገር ልንገራችሁ!https://youtu.be/Rm4ccpU1CXo