A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
33.9K subscribers
17.7K photos
151 videos
52 files
876 links
Download Telegram
የሰው ተኮር ልማት በተግባር የተረጋገጠበት የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደር!

ዛሬ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደርን ለአካባቢው የልማት ተነሺዎች አስረክበናል።

የከተማ ልማት ዋነኛ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠር ነው።

በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው። ሆኖም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል መሬቱን ለእርሻ፣ ለግጦሽና ለመኖሪያነት ሲጠቀሙ የነበሩ አርሶ አደሮችን ሕይወት የሚነካ በመሆኑ፣ የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል።

በዚህም መሠረት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የልማት ከእርሻና መኖሪያ ቦታቸዉ ተነሺ ለሆኑ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ አርሶ አደሮች የተቀናጀ መኖሪያ መንደር ገንብተን፣ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉ አቅርቦቶችንም አካተናል። ይህም የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር ጠብቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ሁኔታ የሚያሸጋግር ሰው ተኮር የልማት አሠራር ነው።

ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ መንደሩ የሚከተሉትን አቅርቦቶች ይዟል፦

* የወተት ላሞችን የሚይዙ የከብት ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ።
* የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች።
* የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል።
* የስብሰባ አዳራሽ።

እነዚህ አቅርቦቶች ነዋሪዎቹ የተሻለ መኖሪያ እንዲኖራቸው፣ የወተት ልማትና ሌሎች የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ፣ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዲጠብቁ እና ልጆቻቸው ምቹ አካባቢ እንዲያገኙ የተዘጋጁ ናቸው።

ልማት ማለት ሰውን ከነበረበት ቦታ ማንሳት ብቻ ሳይሆን የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታው ለታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንደሚውል ስናስረዳቸው፣ ዩንቨርቲዉ ለልጆቻቸው የመማር ዕድልና ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሚፈጥር በመገንዘብ በፈቃደኝነት ትብብራቸውን አድርገዋል። ለዚህ ከልብ እናመሰግናለን፤ ትልቅ ክብርም ይገባቸዋል።

ይህ ተግባር በመደመርና በትብብር ስንሰራ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ ማድረግና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው።

የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደር ይህንኑ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫችንን በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ ነው። የምንገነባት አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿን ክብር፣ መብትና ጥቅም የምታስጠብቅ፣ ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን።

የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችና በስራዉ ሂደት አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁለ ከለብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የህብረተሰቡን የቤት ችግር ለመቅረፍ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ነው

አዲሰ አበባ ከተማ የብልጽግና ተምሳሌትነቷን እያረጋገጠች፤የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እውን እያደረገች፤የከተሜነት ጉዞዋን እያፋጠነች የምትገኘው ከተማችን፤ በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በ24/7 የስራ ባህልን በመተግበር፤ ለዜጎች የቤት ልማት አቅርቦትን ለማሳደግ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ላይ የአቅርቦት እና የአሰራር ለዉጥ በማድረግና የተለያዩ ሞዳሊቲዎችን በመቅረጽ ፤በመንግስት እና በግል አጋርነት፤በበጎ-ፈቃድ፤በግል ባለሀብቶች (በሪልስቴት፣ በግልእና በማህበር አልሚዎች ከቤት ግንባታ ወደ ቤት አቅርቦት መሸጋገር የቻለችው ከተማችን አዲሰ አበባ፤ ለነዋሪዎች የቤት አቅርቦትን በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ  ቀዳሚ  ግብ  አድርጋ በመስራት ላይ የምትገን ከተማ ናት፡፡

ከተማዋ ቤቶችን አልምታ ከማቅረብ በሻገር የተገነቡ ቤቶች የህብረተሰቡን ማህበራዊ መሰተጋብር እና አብሮነትን በሚያጠናክሩ አሰራር የተቃኙ በመሆናችው ፣ የጋራ መገልገያዎች ፤የስፖርት ማዘውትሪያ ስፍራዎችን፣ የህፃናት መጫወጫ፣ አከባቢውን ጽዱ እና ወብ በማድረግ የተቀናጀ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትና የጋራ አስተዳዳር እንዲኖራችው ተደርገው በጥንቃቄና በጥራት የተገነቡ በመሆናቸው ለነዎሪዎች ምቹ መሆን ችላለች፡፡

በተለይም ለልማት ተነሺዎች፣ ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ ፣ለአካል ጉዳተኞች ፣ ለአገር ባለውለታዎች ቅድሚያ በመስጠት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ከማድረግ  በተጨማሪ ሁሉንም አይነት የቤት አማራጮች በሽያጭ፣ በኪራይ፣ በቁጠባ (በረጅም ጊዜ ክፍያ) እና መክፈል ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያማከለ አካታች የአሰራር ስረዓት በመዘርጋት በመተግብር ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ከተማዋ የምታከናወነው  ሰው ተኮር ተግባር በዓለም መድረክ ሰሟ ከፍ ብሎ እንዲነሳ ብሎም እውቅናና እና ምስጋን እንዲቸራት አድርጓል፡፡