A.A HOUSING DEVELOPMENT & ADMINISTRATION BUREAU
33.9K subscribers
17.7K photos
151 videos
52 files
876 links
Download Telegram
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ባለፈው ክረምት የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ የተከላቸዉን ችግኞች የመንከባከብ እና የማፅደቅ ሥራ ያለማቋረጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀ።

በኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ የችግኝ ተከላ መረሃግብርን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ግዙፍ ህዝባዊ ንቅናቄ ነው። ሀገሪቱ ከተራቆቱ መሬቶች መልሶ ማገገም ባለፈ፣ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋኗን ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማሳደግ ችላለች። ይህ መርሃግብር ለአየር ንብረት ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ እና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የላቀ አስተዋፆም አለው።

በመሆኑም መትከል ብቻውን በቂ ስላልሆነ፣ ችግኞች ራሳቸውን ችለው እስኪያድጉ ድረስ በቅርብ መከታተልና መንከባከብ ዘላቂ አረንጓዴ ልማትን ያረጋግጣል ያሉት የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ ቢሮው ባለፈው የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ የተከላቸዉን ችግኞች የመንከባከብ እና የማፅደቅ ሥራ ያለማቋረጥ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፁዋል።

በችግኝ እንክብካቤ መረሃግብሩ ላይ የተሳተፉት የቢሮው ሰራተኞች ችግኝ መንከባከብ፣ ችግኞቹ የተተከሉበትን ዋና አላማ ማሳካት ነው ያሉ ሲሆን እሱም የጥላ አገልግሎት ከመስጠት አንስቶ የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል እንደዚሁም የምግብ ዋስትናን እስከማረጋገጥ የሚደርስ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።

ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ
ኮሙኒኬሽን  ዳይሬክቶሬት
      
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aahdab