ሀገራዊ ፋይዳን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በአንድ ያሳካው የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደር ፕሮጀክት!!!!
ከለውጡ አስቀድሞ በነበሩ ልምምዶች በልማት ከቀያቸው የሚነሱ ዜጎች ለቀጣይ እጣ ፈንታቸው ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት ዜጎች ለተለያዩ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች ሲጋለጡ ቆይተዋል።
ይህን መራር እውነት ከመሰረቱ ለመቀየርና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስትራቴጂ ነድፎ ስራዎችን በስፋት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልማት የሚነሱ ዜጎች መፃዒ ዕጣ ፈንታቸውን በሚያቀና መልኩ በለመዱት የሕይወትና የስራ መስመር ተሰማርተው እራሳቸውን ፣ ቤተሰባቸውን ብሎም ሀገራቸውን የሚደግፉባቸው የተቀናጁ ማዕከላትን እየገነባ ሲያቀርብ ቆይቷል።
በዛሬው ዕለት በክብርት ከንቲባ በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደርም የዚሁ ተግባር ማሳያ ነው።.............

❤5
..........ትልቅ ሀገራዊ ትልም ሰንቆ በመገንባት ላይ ለሚገኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎ (AI) ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት ቦታቸውን የለቀቁ አርሶ አደሮችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ታስቦ የተገነባው ፕሮጀክቱ ከመደመር ዕሳቤ የተቀዳው የአካታችነት እና የሁሉን አቀፍነት መርህ የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን ሀገራዊ ፋይዳንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በአንድ ያሳካም ጭምር ነው።
መንደሩ የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የወተት ላም ሼዶች ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ ፣ የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን ፣ ወፍጮዎች ፣ የስፖርት ሜዳዎች ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል እንዲሁም የስብሰባ አዳራሽ ተሟልተውለታል።
የከተማው የስራ ባህል መገለጫ በሆነው 7/24 መርህ በአጭር ጊዜ በተገነባው በዚህ ፕሮጀክት ላይ የቦሌ ክፍለከተማ ዲዛይንና ግንባታ ፅ/ቤት በባለቤትነት በማስተባበር ፣ መስኤፍ ጠ/ስ/ተቋራጭ በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኬኦን ኮንሰልቲንግ በአማካሪነት የተሳተፉበት ሲሆን ካለው ፋይዳ ባሻገር የአስተዳደሩ ፕሮጀክቶችን የመፈፀም ዓቅሙ የደረሰበት ከፍታም የታየበት ነው።
ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥቅምት 22/2019

❤9👍8
👍4
የኮንስትራክሽን ህግጋትን የተረዳና በዕውቀት የጎለበተ ስራ ተቋራጭና አማካሪ ማፍራት ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና እንዳለው ተመላከተ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያሰናዳውና የስራ ተቋራጮችን እና አማካሪዎችን ዓቅም ለማጎልበት ያለመ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ስልጠናው የዘርፉ ተዋንያን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲውን ተረድተውና የህግ ማዕቀፎቹን ተገንዝበው ስራዎቻቸውን በዕውቀትና በኃላፊነት እንዲሁም በተጠያቂነት ስሜት የመፈፀም ዓቅም ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።
እንደ አሰልጣኙ አቶ መላኩ ይኸይስ ማብራሪያ መሰል ስልጠናዎች ከብልሹ አሰራር አመለካከት የፀዳና ዕውቀትን ያስቀደመ ስራ -ተቋራጭና አማካሪን በማፍራት የኮንስትራክሽን ኢንዱስሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሻገር የማይተካ ሚና የሚጫወቱ ናቸው ብለዋል።
ለ2 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚሁ ስልጠና ላይ ከ200 በላይ አዳዲስና ነባር ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን በዘርፉ ብቃት ያላቸው ተዋንያንን ለማፍራትና ኢንዱስትሪውን ዕውቀት ባለው ባለሙያ ለመደገፍ አስቻይ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም

❤11👍8