Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
270 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
አዲስ አበባ፦ የዘላቂ ከተማ ልማት ማሳያ!

አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማትን ማግኘቷ በከተማዋ እየተመዘገበ ያለውን የልማት ለውጥ፣ ዘላቂነትና ሰው ተኮር የከተማ ግንባታ አቅጣጫ ዓለም አቀፍ እውቅና ያስገኘ ታላቅ ኩራት ነው።

ይህ እውቅና የስኬት መገለጫ ብቻ ሳይሆን ወደፊት ለሚጠብቀን ተጨማሪ ኃላፊነትም ጭምር ነው። ከተማን ማልማት የነዋሪዎችን ኑሮ ማሻሻል፣ ታሪክና ቅርስን መጠበቅ፣ አረንጓዴ ስፍራዎችንና ለሁሉም ተደራሽ የሆኑ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን መፍጠር እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ምቹ ከተሞችን መገንባት ነውና ሁሉን አቀፍ ስራዎቻችን በአለምአቀፉ ማህበረሰብ አይን እውቅና ሲያገኝ፥ ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል።

የአዲስ አበባ ስኬት በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች ሁሉ የዘላቂ ልማት ማሳያ እንዲሆኑ የሚያነሳሳ አቅም አለው።

የዛሬ እውቅናችን ለቀጣይ ስራችን አቅም የሚሆን ነው፤ ታሪካችንን ጠብቀን፣ ለወደፊቱ ትውልድ የምትሆን ዘላቂ፣ ሰው ተኮርና ምቹ ከተማን በጋራ እንገንባ።
❤16👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መዲናችን አዲስ አበባ ከአለም ከተሞች ተወዳድራ አሸናፊ የሆነችበት UN-Habitat በቻይና የተዘጋጀዉ የ2026 እ.ኤ.አ ”የሸንሃይ አዋርድ" የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
❤8👍4
የሰው ተኮር ልማት በተግባር የተረጋገጠበት የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደር!

ዛሬ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደርን ለአካባቢው የልማት ተነሺዎች አስረክበናል።

የከተማ ልማት ዋነኛ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠር ነው።

በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው። ሆኖም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል መሬቱን ለእርሻ፣ ለግጦሽና ለመኖሪያነት ሲጠቀሙ የነበሩ አርሶ አደሮችን ሕይወት የሚነካ በመሆኑ፣ የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል።

በዚህም መሠረት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የልማት ከእርሻና መኖሪያ ቦታቸዉ ተነሺ ለሆኑ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ አርሶ አደሮች የተቀናጀ መኖሪያ መንደር ገንብተን፣ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉ አቅርቦቶችንም አካተናል። ይህም የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር ጠብቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ሁኔታ የሚያሸጋግር ሰው ተኮር የልማት አሠራር ነው።

ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ መንደሩ የሚከተሉትን አቅርቦቶች ይዟል፦

* የወተት ላሞችን የሚይዙ የከብት ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ።
* የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች።
* የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል።
* የስብሰባ አዳራሽ።

እነዚህ አቅርቦቶች ነዋሪዎቹ የተሻለ መኖሪያ እንዲኖራቸው፣ የወተት ልማትና ሌሎች የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ፣ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዲጠብቁ እና ልጆቻቸው ምቹ አካባቢ እንዲያገኙ የተዘጋጁ ናቸው።

ልማት ማለት ሰውን ከነበረበት ቦታ ማንሳት ብቻ ሳይሆን የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው።

የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታው ለታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንደሚውል ስናስረዳቸው፣ ዩንቨርቲዉ ለልጆቻቸው የመማር ዕድልና ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሚፈጥር በመገንዘብ በፈቃደኝነት ትብብራቸውን አድርገዋል። ለዚህ ከልብ እናመሰግናለን፤ ትልቅ ክብርም ይገባቸዋል።

ይህ ተግባር በመደመርና በትብብር ስንሰራ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ ማድረግና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው።

የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደር ይህንኑ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫችንን በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ ነው። የምንገነባት አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿን ክብር፣ መብትና ጥቅም የምታስጠብቅ፣ ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን።

የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችና በስራዉ ሂደት አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ ሁለ ከለብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
❤9👏4