Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
272 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
ቢሮው ዕውቅና ተበረከተለት።


​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በሩብ ዓመቱ በነበረው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም የባለጉዳይ መስተንግዶ ምልከታ ግኝቶችን በዛሬው ዕለት ከተቋም ኃላፊዎች ጋር ገምግሟል።


ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጀመረው ተቋማዊ አሰራርና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት የላቀ የሥራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት ዕውቅና ሰጥቷል።


ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባስመዘገበው ውጤት ዕውቅና ተበርክቶለታል።


ከዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ትምሕርት ቢሮ እና የከተማው ደምብ ማስከበር ባለስልጣን ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል።


ዕውቅናው ተቋማት መልካም ተሞክሮዎቻቸውን እንዲያጠናክሩና በቀጣይም የተገልጋይ እርካታን የሚያረጋግጥ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲያስፋፉ ዓቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑ በዚሁ መድረክ ተመላክቷል።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጥቅምት 12/2019
👍10❤6
በቅርቡ የከተማችን ምክር ቤት በከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት የሥልጣንና የተግባር ክፍፍልን ለመወሰን ባጸደቀው አዋጅ መሠረት፣ ቀደም ሲል በትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ይከናወኑ የነበሩ ተግባራት ለትራንስፖርት ቢሮ፣ ለመንገዶች ባለሥልጣንና ለትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ተከፋፍለው ተሰጥተዋል።

በዚሁ መሠረት፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ሥራዎች በትራንስፖርት ቢሮ ውስጥ እንደ አንድ ዘርፍ ሆነው በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ እየተመሩ የሚከናወኑ ሲሆን፣ በመንገዶች ባለሥልጣን በኩልም የመንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ፣ የትራፊክ ምልክቶችንና የፍጥነት መቀነሻዎችን ማስተዳደር፣ እንዲሁም የመንገድ አጠቃቀም ፈቃዶችን መስጠትን ጨምሮ ተያያዥ ሥራዎች እንዲከናወኑ ተደንግጓል።

የአዋጁ ዓላማ የትራፊክ ሥራዎችን ማቋረጥ ሳይሆን፣ በተለያዩ ተቋማት መካከል በግልጽ የተከፋፈሉ ኃላፊነቶችን በተቀናጀ መልኩ ማስፈጸም ነው።

ከአዋጁ ተግባራዊ አፈጻጸምና ከሥራ ርክክብ ሂደቱ ጋር በተያያዘ፣ ለጥቂት ቀናት የቁጥጥር ሥራዎች ላይ ክፍተቶች ተፈጥረዋል። በዚህም ምክንያት የፓርኪንግ ክፍያን አለመፈጸም፣ የፓርኪንግ አጠቃቀም ሥርዓትን መጣስ፣ እግረኞች መንገድ ሲሻገሩ ቅድሚያ አለመስጠት፣ በአንዳንድ የውስጥ መንገዶች የትራፊክ ሕግን የሚጥሱ ድርጊቶች መታየት፣ እንዲሁም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ከተፈቀደው ፍጥነትና የእንቅስቃሴ ሰዓት ውጪ መንቀሳቀስ ተስተውሏል።

እነዚህ ችግሮች በፍጥነት ሊታረሙ እንደሚገባ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የደረሱን አስተያየቶችም ያመለክታሉ።

በመሆኑም የሥራ ርክክብ ሂደቱ ተጠናቆ፣ የትራንስፖርት ቢሮ የቁጥጥር ሥራዎቹን በመደበኛው ሁኔታ ለማስቀጠል አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል። ከነገ ጀምሮ የትራንስፖርት ቢሮ ኦፊሰሮች መደበኛ የቁጥጥር ሥራቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን፣ ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር የሕግ ማስከበርና የመንገድ ደህንነት ሥራዎችን ያጠናክራሉ። በበጎ ፈቃድ የትራፊክ ሥራዎችን ሲያግዙ የነበሩ በጎ ፈቃደኞችም አገልግሎታቸውን ይቀጥላሉ።

የከተማ አስተዳደሩ ለሕብረተሰቡ ክብርና ጥቅም፣ ለፍትሐዊ አገልግሎትና ለመንገድ ደህንነት መጠበቅ ቅድሚያ ይሰጣል። በመሆኑም የትራፊክ ሕግን የሚጥስ ማንኛውም አሽከርካሪ፣ የቁጥጥር ሠራተኛ ወይም የሕግ አስከባሪ በሕጉ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል።

በመጨረሻም፣ የትራንስፖርት አገልግሎቱ በተቀናጀ መልኩ እየተሰጠ መሆኑን ለሕብረተሰቡ እያረጋገጥን፣ ሁሉም የትራፊክ ሕጎችን እንዲያከብርና ለደህንነቱ እንዲተባበር ጥሪ እናቀርባለን።
❤7👍4
70 ግራም ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ከዳቦ አምራች ማህበራት ጋር ስምምነት ተደረሰ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከአዲስ አበባና ዙሪያዋ የዳቦ አምራቾች ማህበር አመራሮችና አባላት ጋር በዳቦ አቅርቦት ዙሪያ ተወያይቷል።

በውይይት መድረኩ ከ70 ግራም የዳቦ አቅርቦት ጋር ተያይዞ ከክብደት፣ ከዋጋና ከጥራት አንፃር የተካሄደ የዳሰሳ ውጤት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በመድረኩ የዳቦ አምራቾች ማህበር አባላት ከስንዴ ዱቄት አቅርቦትና ከብልሹ አሠራር ጋር ተያይዞ እየገጠመን ነው ያሉትን ችግሮች ለአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አቅርበዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የከተማ አስተዳደሩ ለህብረተሰቡ ዳቦን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ ከማድረግ አንፃር ለዳቦ ፋብሪካዎች ለ10 ዓመት መሬት በነፃ ከመስጠት ጀምሮ፣ በሸገር ዳቦ አማካኝነት ድጎማ የማድረግና ሌሎች የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጦ በመስራቱ የዳቦን ገበያ ለረጅም ጊዜ አረጋግቶ ማቆየት መቻሉን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ አያይዘው በከተማችን የሚገኙ የዳቦ አምራቾች የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ 70 ግራም ዳቦ በብዛትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የድርሻቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ የከተማ አስተዳደሩ በመዲናዋ በቂ የስንዴ ዱቄት አቅርቦት እንዲኖር በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው የዳቦ አምራቾች ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ ሠራተኞች ሲያጋጥሙ በ8588 ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀው በጥቆማው መሠረት ፈጣንና ተገቢ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በመጨረሻም የዳቦ አምራች ማህበራት አመራሮችና አባላት የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ 70 ግራም ዳቦ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ይህንንም ለከተማ አስተዳዳሩ በአጭር ጊዜ ለማሳወቅ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
❤10👍7👎2
ቢሮው  ለ24 ማሕበራት የስራ ዕድል ቅደም - ተከተል ሰጠ።
 
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በዓዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም ሂደት ውስጥ የወጣቶችን የኦኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ እንዲሁም በዘርፉ ተወዳዳሪ ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎችን ለማብቃት ባለመ መልኩ የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሞችን ገቢራዊ ሲያደርግ ቆይቷል።

 
በዚህ መነሻነት በዛሬው ዕለትም ከስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የተላኩለትን 24 ማሕበራት የቢሮው አመራሮች ፣ የማሕበራቱ ተወካዮች እና የሚዲያ አካላት በተገኙበት የስራ ዕድል ቅደም -ተከተል አስይዟል።


በዚህም መሰረት ማሕበራቱ ቢሮው በሚያከናውናቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ እንደየ ቅደም-ተከተላቸው የስራ ስምሪት የሚሰጣቸው ሲሆን ማሕበራቱም የቢሮው መገለጫ በሆነው 7/24 የስራ መርህ ስራዎችን ሰርተው ለማስረከብ ከወዲሁ ዝግጁነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ኦረንቴሽን ተቀብለዋል።


የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም
❤20👍7