Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
21.5K subscribers
15.3K photos
270 videos
95 files
777 links
Government Organization
Download Telegram
ኑ እንጠብቃችኋለን !

ከቀጨኔ–ጊዮን–ባምቢስ እስከ ሰላም መንገድ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ በምሽት በብርሃንና በውበት ይበልጥ ይደምቃል።
ወዳጆቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ይዛችሁ ኑ፤ ከዕለት ድካም እረፍት ውሰዱ፣ በፅዱና በውብ አካባቢው ንፁህ አየር ተቀበሉ፣ መንፈሳችሁንም አድሱ!

አዲስ አበባ ውበቷን ለማየት ብቻ ሳይሆን፣ ለመኖርና ለመደሰትም ጎራ በሉ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
❤11👍9👎1
ዓለም ከስሟ ባሻገር እንቁ ታሪኳን በሙሉ ጠንቅቆ ያላወቀላት ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ታሪኳን በራሷ ድምፅና በራሷ ብዕር ለዓለም ታስተዋውቃለች። ይፋዊው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድረ-ገጽ ዛሬ ይፋ ሆኗል!

ቡናን ከጫካዎቿ አፍልቃ ለዓለም ስጦታ ያበረከተች፣ የቡና ትውልድ ሀገር ኢትዮጵያ። የሰው ዘር የመጀመሪያ እርምጃውን የጀመረባትና አየሯን እስትንፋስ አድርጎ የተነፈሰባት ኢትዮጵያ። በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በሕዝቦቿ እጆች ዳግም እየለመለመች ያለች ምድር፤ ኢትዮጵያ። ወንዞቿን፣ ነፋሷንና ፀሐይዋን ወደ ኃይል ቀይራ ከራሷም አልፋ ለጎረቤቶቿ ብርሃን የሆነች ኢትዮጵያ። ከተሞቿ በአዲስ ውበት እያበቡ በልባቸውም የአፍሪካን አዲሷን አበባ ታቅፈው የያዙ ኢትዮጵያ። አፍሪካውያን የጥቁር ሕዝቦችን ዘመን ተሻጋሪ ኩራትና ወኔ በፓን-አፍሪካዊ አንድነት ድምፅ ለመግለጽ የሚተሙባት ኢትዮጵያ። ጥንታዊ ሥልጣኔዋን ዛሬም በድንጋዮቿ፣ በፊደሎቿ፣ በዜማዎቿና በፕሮጀክቶቿ ሕያው አድርጋ የምታኖር ኢትዮጵያ። ሯጮቿም የድል መንፈሷን ከትውልድ ትውልድ እያስተላለፉ፣ በዓለም የድል መድረኮች የምታበራ ኢትዮጵያ!

ወደ ኮፕ32 በሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ ይህ ድረ-ገጽ ከታሪካችን እስከ ዛሬ እርምጃችን፣ ከሥልጣኔያችን እስከ የወደፊት ርዕያችን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሀብትና ተስፋ ለዓለም የምናቀርብበት መድረክ ነው። ምድረ ቀደምትነቷን ይወቁ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ይመስክሩ!

🔗 ማስፈንጠርያ: https://ethiopia.gov.et/

ምድረ ቀደምት፤ ኢትዮጵያ 🇪🇹
❤6👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 3ኛውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ለመታደም ሞስኮ፣ ሩሲያ ገብተዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed has arrived in Moscow, Russia, to attend the 3rd Russia-Africa Summit.

#PMOEthiopia
❤4👏2
የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይል እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም እያላበሳት ነው።

ከዚህ ቀደም ከሩሲያ መንግስት ጋር በደረስነው ስምምነት መሰረት፣ ዛሬ የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች (Su-35 4++ Generation) ተረክበናል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ አራት የኤስ-400 (S-400) የአየር መከላከያ ስርዓት ባትሪዎችን ትረከባለች።

ወዳጄ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከስምምነታችን አንድ ዓመት አስቀድሞ እነዚህን የጦር አውሮፕላኖች እንድንረከብ ስላሳዩት ትጋት ላመሰግናቸው እወዳለሁ። እነዚህን የጦር ጄቶች በመታጠቅ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ሆናለች።

ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን፣ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም ይሆነናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
❤5👏2
ዛሬ የመደመር መጽሐፍ ወደ ሩሲያኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። በተዘጋጀው የመጽሐፉ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ በአካል ተገኝቼ በመካፈሌም ታላቅ ደስታና ኩራት ተሰምቶኛል።

ይህ ታሪካዊ ስኬት የመደመር ፍልስፍና ከኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ተነስቶ ዛሬ ላይ ድንበር በመሻገር ወደ መላው ዓለም እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ህያው ማረጋገጫ ነው። ከዚህ በፊት መጽሐፉ ከአገር ውስጥ ቋንቋዎች በተጨማሪ በእንግሊዝኛ፣ በቻይንኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለብዙኃን አንባቢያን መድረሱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሀሳብ ድንበር ተሻግሮ በሰፊው የሩሲያኛ ተናጋሪ ደጃፍ መድረሱ የፍልስፍናውን ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነትና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ይበልጥ ያጎለብተዋል።

ይህ እርምጃ የመደመርን ፍልስፍና፣ እሴቶችና ሀሳቦች ከኢትዮጵያ አልፈው ለሌሎች ሕዝቦች የሚደርሱበትን አዲስ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተው የራሷ የበሰለ ሀሳብ እንዳላት በተግባር የሚያሳይ ነው። ሩሲያ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የሥነ ጽሑፍና የዕውቀት መማሪያ ምድር ሆና እንዳገለገለች ሁሉ፣ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሀሳብ በሩሲያኛ ቋንቋ ለሩሲያ አንባቢያን መድረሱ የዕውቀት ልውውጡን ሙሉ ያደርገዋል።
ለዚህ ስኬት መሳካትና ለመጽሐፉ ዝግጅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የሩሲያ ቱዴይ (RT) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና አመራሮች ያደረጉትን ጥረትና ትጋት በከፍተኛ ደረጃ አደንቃለሁ።

ይህ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የበለጸጉ አገር በቀል እውቀቶች፣ ባህሎችና ፍልስፍናዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ይበልጥ ለማስተዋወቅና በሕዝቦች መካከል ጠንካራ የባህልና የሃሳብ ድልድይ ለመገንባት የሚኖረው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
❤18😁3👏2🤣1