Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.64K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
በተለምዶ ‹‹ትፍታ›› የተባለውን የማታለል ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ አንተነህ ጌታቸዉ የተባለዉ ተጠርጣሪ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመዉ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ሻላ መናፈሻ የተባለ አካባቢ ነው፡፡

የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ኤፍሬም ዓለሙ ሲገልፁ ተጠርጣሪ አንተነህ ጌታቸው ከአንድ ጀርመናዊው ግለሰብ ላይ ምራቅ ከተፋ በኋላ ይቅርታ በማለት ልብሱን በመጥረግ ከኪሱ ውስጥ ግምቱ 140ሺህ ብር የሚያወጣ አይፎን 13 pro max ስልክ ይዞ ተሰውሯዋል፡፡

የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸውን ድርጊት በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ለአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ በማመልከታቸው ተገቢው ክትትል ሲደረግ ነበር ያሉት ኮማንደር ኤፍሬም ተጠርጣሪውን ከሚጠቀምበት የሠሌዳ ቁጥር B61211 አ/አ ቶዮታ ኤክስኪዩቲቭ ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር  ስር ማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ የማስፋት ተግባር እንደሚቀጥል ያስታወቁት ኮማንደር ኤፍሬም በግለሰቡና በተሽከርካሪው ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ በመምጣት ጥቆማ መስጠት የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል። 
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
👍18❤16👏5