19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ‹‹ ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን ›› በሚል መሪ ቃል ተከበረ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጽያ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራርና አባላት፣ አባት አርበኞች የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት 19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በአድዋ ሙዚየም በድምቀት ተከብሯል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ባደረጉት ንግግር ሰንደቅ ዓላማችን አባቶቻችንና እናቶቻችን ለነፃነትና ለሉዓላዊነት የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚያስታውስ የታሪካችን ህያው ምስክር ነው ብለዋል።
የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት በመጠበቅ ለከተማችን ልማት በጋራ በመስራት ለሀገራችን ሠላምና ደህንነት እንዲሁም ሉዓላዊነት መጠበቅ ውድ ህይወታቸውን ለከፈሉና አሁንም በትጋት የሀገራቸውን ዳር ድንበር እያስከበሩ ላሉት ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ለመላው የፀጥታ አካላትና የሀገር አገልጋዮችን በክብር አመስግነዋል።
የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከበር ለሀገራችን ሠላምና ደህንነት መረጋገጥ በምንወስደው ቁርጠኝነትና በምንፈፅመው ተግባር ጭምር ነው ሲሉ አፈ ጉባኤዋ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በቦታው የተገኙ አባት አርበኞች ፖሊስና ሰንደቅ ዓላማ ያላቸው ቁርኝት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ሀገርን ከወንጀል ፈፃሚዎች በመጠበቅና ህግን በማስከበር ቀድሞ የሚገኝ፤ መስዋትነትን ጭምር በመክፈል ያረጋገጠ ተቋም መሆኑን ገልፀው የአባቶችን ፈለግ በመከተል ሀገርን ከማንኛውም ውስጣዊና ውጫዊ ጠላት ሊከላከል ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
*
ዘገባ፡- ምክትል ሳጅን ሳምሶን ሠለሞን
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤35👏7👍6👎6
በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በከተማችን አዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ወንጀል የመፈፀም፣ የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ የመንገድ ትራፊክ ህጎችን የመጣስ ( በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ.) በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉን ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቦ የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸው እና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይከል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል፡፡
*
ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ

❤88🫡35🙏18👍13👏8🥰4
ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪዎች ደረጄ አለማየሁ፣ አበበ ካሮ እና ብሩክ ሙላት ወንጀሉን የፈፀሙት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው አራት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት ነው።
ተጠርጣሪዎቹ በተቋሙ ውስጥ በሲስተም ዝርጋታ ሙያ ተቀጥረው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ጠቅላላ የዋጋ ግምታቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ሦስት ላፕቶፖች፣ ለኔትወርክ ዝርጋታ ከተሰጣቸው ንብረቶች ውስጥ አራት ዋይፋይ ራውተር በማውጣት ሸጠዋል፡፡
የንብረቶቹን መጥፋት መረጃ የደረሰው በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የ4ኪሎ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ጠንካራ ክትትል እና ምርመራ በማድረግ ተጠርጣሪዎችን እና ገዢውን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የ4ኪሎ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተቋማት ለስራ ማከናወኛ ለሰራተኞቻቸው የሚሰጧቸው ንብረቶች ላይ የቅርብ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንዳለባቸው ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀልን በመከላከል ረገድ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
*
ዘገባ፡- ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ፃዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹 v

❤18👍10👏1
በግድያ ወንጀል በተጠረጠረው ኢዮብ እንዳለ ላይ ምርመራው ቀጥሏል
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪ ኢዮብ እንዳለ ይባላል፤ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ ሠባት ልዩ ቦታው ብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ( ወመዘክር ) ቅጥር ግቢ ውስጥ ከምሽቱ 2፡10 ሠዓት አካባቢ ነው፡፡
ፖሊስ ከተከሳሽ ቃል መረዳት እንደቻለው በግድያ ወንጀሉ የተከሰሰው ወጣት ኢዮብ እንዳለ ከሟች ዮርዳኖስ አምበሉ ጋር ከአንድ ዓመት በላይ ትውውቅ እንዳላቸውና በፍቅር ግንኙነት እንደቆዩ የገለጸ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መግደል ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር ኃይሉ ኡምኔሳ አስታውቀዋል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ የባህሪዋ መለዋወጥና በስልክ የምናደርገውን የድምፅ ድውውሎሽ ወደ ፅሁፍ መልዕክት በመቀየሯ በሌላ ሰው እንድጠረጥራት አድርጎኛል ያለው ተከሳሽ ኢዮብ፤ ሌላም ጊዜ ወደምንሄድበት ብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት (ወመዘክር) ለመገናኘት ከቀኑ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ቄራ አካባቢ ተቀጣጥረን ነበር ብሏል፡፡
ቄራ አካባቢ በቀጠሮአችን ሰዓት ስላረፈደች የሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ በመግዛት ደብቆ ይዞ የጠበቃት ሲሆን ሟች ስትመጣም የራይድ ከፍላ ወደ ተባለው ወመዘክር ሄደዋል፡፡
ተከሳሽ ከዚህ ቀደም ከሟች ጋር ወደ ምንቀመጥበት ቦታ ላይ አረፍ ብለን ስናወራ ነበር ብሎ በመሀላችን በንግግር ያለ መግባባት በመፈጠሩ እና በሌላ ሰው ጥቃት ልታደርስብኝ ትችላለች በሚል ጥርጣሬ ለወንጀሉ ድርጊት በገዛሁት ቢላዋ አራት ቦታ ወግቻታለሁ ብሏል፡፡
የምርመራ መምሪያ ኃላፊው ኮማንደር ኃይሉ ሲያብራሩም ተከሳሹ ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ስልኩን በማጥፋት ከግቢው በወቅቱ በማምለጥ ወደ ሀዋሳ ጉዞ ለማድረግ ሞጆ ላይ ቆይቶ፤ ኋላም ስልኩን በመክፈት ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ተመልሷል ብለዋል፡፡
ፖሊስ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በቅንጅት ባከናወነው ቴክኖሎጂ መር የክትትል ስራም ተከሳሹ ከተደበቀበት አካባቢ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በዋና ጠቅላይ መምሪያው የክትትልና ኦፕሬሽን ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውልም ችሏል ብለዋል፡፡
ሟች በወቅቱ አደጋው እንደደረሰባት በግቢው የሚገኙት አራት የጥበቃ ባለሙያዎች በአካካቢው ወደሚገኘው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መውሰድ ሲገባቸው ይህን ኃላፊነት ባለመወጣታቸውና ግለሰቡ ወደ ግቢው ሲገባም ፍተሻ ባለ ማድረጋቸው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም አስታውቀዋል ኃላፊው፡፡
ፖሊስ በወቅቱ በግቢው ውስጥ የነበሩ ሠላሳ ስድስት ሰዎችን ጭምር አስሮ ምርመራ ያጣራ ከመሆኑም በላይ የተከሳሽ ወላጅ አባት ልጃቸውን ለማሸሽ ባደረጉት ሙከራም ምርመራ ሲጣራባቸው ቆይቶ በፍርድ ቤት ዋስ መለቀቃቸውን ኮማንደር ኃይሉ ተናግረዋል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የሚከሰቱ ያለ መግባባቶችን በንግግር መፍታት እንደሚገባ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል በሚፈፀምበት ወቅት እያዩ ያለ ማስቆም፣ ወንጀል የተፈፀመበትንና አደጋ የደረሰበትን ግለሰብ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ያለ ማድረግ ወይም ያለ መርዳት የወንጀል ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

❤43😭16👎1