Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.64K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በፔንስዮኖችና የሌሊት ጭፈራ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ15ሺህ በላይ የሺሻ ዕቃዎች ተወገዱ፡፡ 
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የህብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ወራት ያህል በመኖሪያ ቤቶች፣ በፔንሲዮኖች፣ በሆቴሎችና በሌሊት ጭፈራ ቤቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ15ሺህ በላይ የሆኑ የሺሻ ዕቃዎች እና 333 ግራም ካናቢስ የተባለ አደንዣዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር በማዋል ማስወገዱን የዋና መምሪያው አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ከተማ አስታውቀው ወንጀሉን ከምንጩ ለማድረቅ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመሆን አንዳንድ ንግድ ቤቶችን ዘርፍ ከማስቀየር ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም የህብረተሰቡን ጤና የሚጎዱና የአካባቢውን ሠላም የሚረብሹ አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል መሠል እርምጃዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታዬ ሽፈራው በበኩላቸው የክፍለ ከተማውን ደህንነት ይበልጥ ለማረጋገጥ፣ ህብረተሰቡን የሠላሙ ባለቤት ከማድረግና አካባቢውን ከወንጀል ስጋት ነፃ ለማድረግ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ከፀጥታ አካላት ጋር በመተሳሰር አዋኪ ድርጊቶችን የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚንስቴር የቂርቆስ ክ/ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ አራጌ እንደተናገሩት በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ ላይ ሺሻን መጠቀም የጤንነትና የስነ ምግባር ደንብ መተላለፍ መሆኑ የተደነገገ ሲሆን ተጠያቂነትን እንደሚያስከትልም ገልፀዋል። በ2011 ዓ/ም በተሻሻለው በምግብና መድኃኒት አስተዳደር ስር ሆኖ በወጣው አዋጅ ሺሻን መጠቀምም ሆና ማስጠቀም በህግ እንደሚያስጠይቅ አስቀምጧል።

ጉዳዩ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ ሁሉም ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

አንዳንድ ያነጋገርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የትውልዱን ጊዜና ገንዘብ የሚያባክኑ ሱስ የሚያሲይዙ ጉዳዮችን ሁሉም ዜጋ ያገባኛል በሚል መንፈስ ልጆቹን ከመምከር ጀምሮ ለፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለበትም አሳስበዋል። 

የአካባቢውን ሠላም የሚያውኩና ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው የሚያስተጓጉል እንዲሁም  ወደ ሱስ የሚገፋፉ  ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ሁሉም ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤25👏4🔥1🤔1
በመንገድ ትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ ደርሷል
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሰው ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ስድስት ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት አካባቢ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መንግስቱ ታደሰ እንደገለፁት የጉዞ አቅጣጫውን ከመገናኛ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3A-70671 አ/አ የከተማ አውቶቡስ ከመንገድ በመውጣት ዕድሜያቸው በግምት 40 ዓመት የሚሆናቸውን ሴት በመግጨት የሞት እንዲሁም በሁለት እግረኞች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

በአደጋውም ከሞት፣ ቀላልና ከባድ አደጋዎቹ በተጨማሪ በቦታው ላይ ቆመው በነበሩ 11 ተሽከርካሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው የንብረት ጉዳት መድረሱንም መምሪያ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ድርብ ኃላፊነት አለባቸው ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ፣ ውድ በሆነው በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል በጥናት ላይ የተመሰረተ ህግን የማስከበር ተግባሩን እንደሚወጣም አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤16😱5😢2👏1