Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.64K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
በመንገድ ትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ ደርሷል
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የመንገድ ትራፊክ አደጋው የደረሰው ጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ስድስት ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት አካባቢ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መንግስቱ ታደሰ እንደገለፁት የጉዞ አቅጣጫውን ከመገናኛ ወደ አፍንጮ በር ያደረገው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3A-70671 አ/አ የከተማ አውቶቡስ ከመንገድ በመውጣት ዕድሜያቸው በግምት 40 ዓመት የሚሆናቸውን ሴት በመግጨት የሞት እንዲሁም በሁለት እግረኞች ላይ ከባድና ቀላል አደጋ ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

በአደጋውም ከሞት፣ ቀላልና ከባድ አደጋዎቹ በተጨማሪ በቦታው ላይ ቆመው በነበሩ 11 ተሽከርካሪዎች ላይ የተለያየ መጠን ያለው የንብረት ጉዳት መድረሱንም መምሪያ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ድርብ ኃላፊነት አለባቸው ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ፣ ውድ በሆነው በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል በጥናት ላይ የተመሰረተ ህግን የማስከበር ተግባሩን እንደሚወጣም አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤16😱5😢2👏1
" ፖሊስ የህፃናትን ሠላምና ደህንነት ጠባቂ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም " ተማሪዎች
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የዜጎችን ሠላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅ፣ የከተማውን ፀጥታ ይበልጥ ለማረጋገጥና ያለ ምንም አድልኦ ፍትህን ለማስፈን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ፖሊስ ፍትህና እኩልነትን ለማስፈንና የዜጎችን ደህንነትን መጠበቅ ቀዳሚው ተግባር ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ህብረተሰቡ " ህፃናትንና ታዳጊዎችን ፖሊስ እጠራብሻለሁ/ እጠራብሀለሁ " በማለት የሚያስፈራሩበት መንገድ በህፃናትና ታዳጊዎች አዕምሮ ውስጥ ፍራቻን የሚያስከትል ሆኖ ይታያል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ ዋና መምሪያ የፖሊስ ሠራዊት ስዕብና ግንባታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ወንደሠን ደረጄ በሄሌኒክ ግሪክ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት ፖሊስ ከህዝብ የተገኘና የህዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚተጋ በመሆኑ ወላጆችና ትምህርት ቤቶች ለህፃናትና ታዳጊዎች የስነ ምግባር ትምህርት በመስጠት ትኩረት አድርገው መስራት እንዳለባቸው አስታውሰው፤ ህፃናትንና ታዳጊዎች ፖሊስን አስፈሪ አድርገው እንዲመለከቱ መደረጉን ለማስወገድ ሊተጉ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የሰከላ ኤቨንት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ የሆነው አርቲስት ዋሲሁን አራጌ እና የፊልም ባለሙያዋ አርቲስት ኤልሳቤጥ ጌታቸው በበኩላቸው ህፃናት የፖሊስን ሙያና ስነ ምግባር እንዲሁም ወንጀልን ለመከላከልና ፍትህን ለማስፈን እያደረገ ያለውን ስራ በተገቢው መልኩ በመረዳት ፖሊስን እንደ ወዳጅ አድርገው እንዲገነዘቡ የቤተሰብ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው የሄሌኒክ ግሪክ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በበኩላቸው ፖሊስ ከራሱ ጥቅም ይልቅ ለህብረተሰቡ ደህንነት የቆመ አካል መሆኑን ጠቅሰው የፖሊስን ሙያ እንደሚወዱና ተማሪዎች በስነ ምግባር የታነጹ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል ።
*
ዘገባ፡- ዋና ሳጅን ደጀኔ ኡልፋታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤11👍5👏1
"የድል ሠራዊት"
***
ኢትዮጵያን በአሸናፊነት ላጸና፣ የአያት ቅደመ አያቶቻችንን የጀግንነት ታሪክ እየደገመ ለሚገኘው፣ ዘመኑ የሚመጥነውን ወታደራዊ ቁመና ለያዘውና ዛሬም ለኢትዮጵያ ዳር ድንበር እየተዋደቀ ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት 119ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ።
* የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ *
❤29👍11👏2
👍4❤2
በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር እስኪጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡

ከተማችን የምታስተናግደው የሩጫ ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ፤ የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራው ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ሩጫው ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ፡-
• ከቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ
• በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
• ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
• ከጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
• ከትምባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
• ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
• ከቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
• ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
• ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል
• ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ መስመር ግራና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤38🙏7👏4