Addis Ababa Police Official
18.8K subscribers
9.64K photos
14 videos
1.12K links
Addis police
Download Telegram
ህገ ወጥ የተሽከርካሪ ጥቁር ሽፋን (Sticker) ፈቃድ ወረቀት በሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህገ ወጥ የይለፍ ወረቀት (Pass) በሚጠቀሙ፣ ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ውጪ የሆነ የጥቁር ስቲከር ፈቃድ ወረቀት እንዲሁም በልየ ልዩ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ውስጥ የተገኙ ሞተር ሳይክልና ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል፡፡

ዋና ጠቅላይ መምሪያው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ባደረገው ቁጥጥር አንድ ሺህ አንድ መቶ አስራ አንድ ተሽከርካሪዎች ላይ በደንቡ መሰረት ርምጃ መውሰዱን የትራፊክ ዋና መምሪያ ኃላፊው ኮማንደር አበራ ባይሳ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ጊዜው ያለፈበትና ፈቃድ ሰጪው አካል የማይታወቅ የስቲከር ፈቃድ ወረቀት የያዙ 899፣ 153 በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ውስጥ የተገኙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች እንዲሁም አፈር ጭነው መንገድ ያበላሹ 59 ተሽከርካሪዎች ላይ በትራፊክ ደንቡ መሰረት ህጋዊ ርምጃ ተወስዷልም ብለዋል፡፡

አሽከርካሪዎቹ የትራፊክ ቁጥጥርን መጣስ፣ በከተማ ክልል ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ያልታደሱ የጥቁር መስታወት ሽፋኖችን ፈቃድ ወረቀት መጠቀምና መሰል ጥፋቶችን በመፈፀማቸው የተወሰደ ርምጃ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

አሽከርካሪዎች በከተማዋ ያለው የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ ፍሰት ሠላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤10👍4👏1😁1
Strict enforcement is being carried out against drivers who use unauthorized permits for applying dark-tinted film (stickers) to their vehicle windows
***
Addis Ababa; 29, October 2026 G.C. (Addis Police): The Addis Ababa Police Headquarters is conducting strict enforcement against motorcycles and vehicles found using illegal passes, unauthorized "black sticker" permits (issued outside of the official licensing authority), or committing various other traffic regulation violations.

Commander Abera Baysa, Head of the Main Traffic Department, stated that the department took action against 1,111 vehicles in accordance with regulations during an inspection conducted over the span of just one week.

The official further stated that legal action, in accordance with traffic regulations, has been taken against 899 motorcycle riders found with expired sticker-based licenses issued by authorities of unknown Source, as well as 153 riders who committed various traffic violations, and 59 vehicles that damaged roads while transporting soil.

He further explained that the measures were taken because the drivers had committed various violations, such as disregarding traffic regulations, exceeding the permitted speed limit within the city, and using expired or unrenewed permits for tinted vehicle windows.

The Addis Ababa Police Headquarters, which urged drivers to play their part in ensuring road safety and smooth traffic flow in the city, has also announced that enforcement against traffic violators will continue to be intensified.
*
Reporter: D/Inspector Dawit Ergete
*
For police updates:
Facebook: https://www.facebook.com/Addisababapolice TikTok: https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial? Telegram: https://t.me/addispolice
YouTube: https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
Twitter: https://twitter.com/AddisPolice
Website: https://www.addispolice.gov.et/
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤8👍8👏1
የ7 ዓመቱ ታዳጊ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አለፈ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ወሰን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሠለሞን ሙሉ የ7 ዓመት ልጃቸው ህፃን አማኑኤል ሠለሞን በገዛ የጥበቃ ሠራተኛቸው ታግቶ መወሰዱን በመግለፅ አጋቹ የልጃቸውን በህይወት መገኘት የሚፈልጉ ከሆነ 4ሚሊየን ብር በአካውንት እንዲያስገቡ ይህን ካላደረጉም ህፃኑ በአጋቹ እጅ ሦስተኛው ሟች ሊሆን እንደሚችል እንደነገራቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥቆማቸውን ሰጥተዋል፡፡

የወንጀል ምርመራ ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ የክትትልና የምርመራ ቡድን በማቋቋም ስራውን ጀምሯል፤ በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በጥበቃ ሠራተኝነት የተቀጠረ ግሩም ወርቁ የተባለ ግለሰብ እንደሆነም የግል ተበዳይ ለምርመራ ቡድኑ መረጃውን ይሰጣሉ፡፡

ፖሊስ ባዋቀረው ሁለት የምርመራና የክትትል ቡድን አንዱን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሀን በኩል ሁለተኛውን ቡድን በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢረሱ በማድረግ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ/ም በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢረሱ ዞን አርጎባ ልዩ ወረዳ ጋቸኒ ከተማ በቁጥጥር ስር ሊያውለውም ችሏል፡፡

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላም በተደረገው ምርመራ ተከሳሽ በጥበቃ ሠራተኝነት ከተቀጠረበት ዕለት ጀምሮ ህፃን አማኑኤል ሰለሞንን የተለያዩ ጣፋጭ ነገሮችን እየገዛ እንዲለምደው ያደረገ ሲሆን ወንጀሉ በተፈፀመበት ቀንም ህጻኑን ሳር አጭደን እንመለሳለን በማለት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቀርሳ ቅዱስ ሚካኤል ጫካ ይዞት ሄዷል፡፡

ቦታው እጅግ በጣም አስቸጋሪና አድካሚ ሲሆን ህፃኑን ረጅም መንገድ በእግሩ ካስኬደው በኋላ አንድ ቦታ ላይ በማስቀመጥ በእጁ ገመድ አስይዞ ፎቶ በማንሳት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በገመዱ አንቆ በመግደል አስከሬኑን ደረቅ ፅድ ቅርንጫፍ አልብሶ ከአካባቢው ተሰውሯል፡፡ ተከሳሽ ህጻኑን ከገደለም በኋላም በህይወት ያለ በማስመሰልና ፎቶ ለቤተሰቦቹ በመላክ ገንዘብ ሲጠይቅ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል።

ተከሳሽ ሲጠየቅም ፎቶ ያነሳሁት ልጁን ይዤ በምንቀሳቀስበት ወቅት ልያዝ ስለምችል በህይወት ያለ በማስመሰል ገንዘብ ለመቀበል በማሰብ ነው ሲልም ቃሉን ሰጥቷል፡፡

የም/ዋና ጠቅላይ መምሪያው የምርመራና ቴክኒክ ቡድንም በተከሳሽ መሪነት እጅግ አስቸጋሪ ጫካ በነበረው የወንጀል ስፍራው ባደረገው የህጻን አማኑኤል አስከሬንን ፍለጋ ማግኘት የቻለው ነገር ቢኖር የተገደለበትን ገመድ፣ የህፃኑን ጃኬትና ቲ ሸርት እንዲሁም የተበጣጠሱ የሰውነት አካሉን ሲሆን በአውሬ ለመበላቱም ማሳያ በመሆኑ የተገኙትን አካሎች በማስመርመር ለቤተሰብ አስረክቧል፡፡ 

ተጨማሪ የምርመራ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ፖሊስም ከወንጀል ስፍራው አካባቢ የህፃኑ የራስ ቅል አለ የሚል መረጃ በመምጣቱ ተከሳሽን በመያዝ ወደ ስፍራው በማምራት ፍለጋ በሚያደርግበት ወቅት ራሱን መከላከል ባልቻለው ህጻን ግድያ ወንጀል ያልተፀፀተው ግለሰብ ከተጠያቂነት እና ከህግ ለማምለጥ ሲል በቦታው ላይ ከነበሩ የፖሊስ አባላት ጋር ግብግብ በመፍጠር ገደል ለገደል ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ በተተኮሰበት ጥይት የተመታ ሲሆን ህይወቱን ለማትረፍ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ማዳን አለመቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተከናወነው ተግባርም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደብረ ብርሀን እና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጋቸኒ ከተማ ፖሊስ ላደረገው ትብብር ምስጋናውን ያቀረበው ፖሊስ ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛም ይሁን ጥበቃ ሲቀጥር ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት ከመሆኑም ባሻገር ህፃናት ተገቢውን ክትትል የሚሹ በመሆኑ አይኑን ከልጆቹ መነጠል እንደማይኖርበትም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹
❤38😭27💔12👏10