ሀሰተኛ ሰነድና የገንዘብ ኖት እያዘጋጀ ሲሸጥ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ግርማ ሙሴ የተባለው ተጠርጣሪ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለተጠቃሚ ግለሰቦች ለመሸጥ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር የዋለው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 እፎይታ አካባቢ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም ነው።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ም/መምሪያ ተወካይ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሚሊዮን የምሩ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ግለሰብ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደሚያዘጋጅ በምርመራ ጥናት መደረጉን ገልፀዋል፡፡
የመምሪያው የክትትልና ኦፕሬሽን አባላትም ግለሰቡ ያዘጋጀውን ሀሰተኛ ሰነድ ይዞ ለተጠቃሚዎች ለመስጠት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር በማዋል በፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በመኖሪያ ቤቱ በተደረገ ብርበራ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ሀሰተኛ ሰነዶች የተለያዩ መታወቂያዎች፣ መንጃ ፈቃድ፣ ክብና የራስጌ ማህተም፣ ቲተሮች እንዲሁም ለወንጀል ተግባሩ የሚጠቀምበት ሁለት ከለር ፕሪንተር አንድ ላፕቶፕና የተለያዩ ፍላሾች በተጨማሪም በብርና በዶላር መጠን የተዘጋጁ ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶች፣ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከመሰል 11 ጥይት ጋር የተገኘ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጠርጣሪው ላይ ተገቢውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ ለማቅረብ ጉዳዩ በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትም ሆነ መገልገል የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን በተለይ ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም በመንግስትና በግል ተቋማት ተቀጥሮ ለመስራት መሞከር በራሱ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት በዚህ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችም ሆኑ የሚያሰሩ አካላት በአቋራጭ ለመክበር ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊታቀቡ ይገባል ያሉት ኢንስፔክተር ሚሊዮን የምሩ ተቋማትም በሀሰተኛ ሰነድ የሚቀጠሩ አካላትን የመለየት ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ በመልዕክታቸው አሳስበዋል።
*
ዘገባ፦ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ
ፎቶ፦ረ/ኢንስፔክተር ሀቢብ ሻሚል
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤28👍7👏1😁1