7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር " የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ማሳደግ ፤ ደህንነቱ ለተጠበቀ ዲጂታል ፖሊስ እና ህዝባዊ አገልግሎት " በሚል መሪ ቃል ተከበረ።
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ 7ኛው የሳይበር ደህንነት ወር በተለያዩ ተቋማት እንደ ተቋሞቻቸው ተጨባጭ ሁኔታ በተለያዩ መርሀ ግብሮች እየታሰበ ይገኛል።
ወሩን ምክንያት በማድረግም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና ከኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ጋር በመተባበር ለፖሊስ አመራርና አባላትና እንዲሁም ሲቪል ሠራተኞች በሳይበር ደህንነትና ዲጂታል ፖሊስ አገልግሎት ላይ ስልጠና ሠጥቷል።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሠጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሎጀስቲክ መምሪያ ኃላፊና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ተወካይ ም/ኮሚሽነር ሠዒድ አህመድ፣ የኢትዮጵያ ሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሀኑ በየነ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኦዲትና ግምገማ ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላሁን እጅጉ እንዲሁም የዋና ጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሎጀስቲክ መምሪያ ኃላፊና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ተወካይ ም/ኮሚሽነር ሠዒድ አህመድ እንደገለፁት 7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን ስናከብር ፖሊስ ህግ አስከባሪ እንደ መሆኑ መጠን ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፖሊስ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ የሚፈጸሙ የሳይበር ወንጀሎችን በመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎትን በማጠናከር ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኦዲትና ግምገማ ዳይሬክተር ዶ/ር ጥላሁን እጅጉ በበኩላቸው የሳይበር ወርን በተመለከተ በተለያዩ የፋይናንስና የትምህርት ተቋማት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እየተሰጡ መቆየታቸውን ገልፀው፤ ከፖሊስ ጋር ስልጠናው መሰጠቱ ልዩ የሚያደርገው በተለያየ መንገድ የሳይበር ወንጀል ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፖሊስ ምርመራ እያጣራ ለፍትህ የሚያቀርብ በመሆኑ ስልጠናው ለፖሊስ አመራር እና አባላት በመሰጠቱ የተሻለ የሳይበር ደህንነትና ዲጂታል ፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት ሚናው የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።
ስልጠናውን ሲያስተባብሩ የነበሩት የዋና ጠቅላይ መምሪያው ሲቪል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቤዛዊት ግርማ እና ከሎሬት የማማከርና ስልጠና ተቋም የመጡት ዶ/ር ኢንጂነር አዲስዓለም ገንታ ስልጠናውን ለመስጠት ለተገኙ ምሁራንና ተሳታፊዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በስልጠናው አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምሁራን የምስጋና ምስክር ወረቀት የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያና ጥገና ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሚሊዮን አደፍርስ ተቋሙ በቀጣይ ያለውን የቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል መሰል ስልጠናዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
አንዳንድ ያነጋገርናቸው የስልጠናው ተሳታፊ የፖሊስ አመራሮች እና አባላት እንደገለፁት ስልጠናው ወቅቱን የዋጀና የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት መወጣት እንዲችሉ ተጨማሪ እውቀት እና ግንዛቤ የፈጠረላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ም/ሳጅን ፍፁም በቀለ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
🇪🇹 🏵💐🏵 🇪🇹

❤16🙏3👍2👏1