ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
Audio
የአሕቃፍ ምእራፍ ክፍል 03

" በዚያም እናንተን በእርሱ ባላስመቸንበት (ድሎት) በእርግጥ አስመቸናቸው ፡፡ ለእነርሱም መስሚያንና ማያዎችን ፣ ልቦችንም አደረግንላቸው ፡፡ ግን መስሚያቸውና ማያዎቻቸው ፣ ልቦቻቸውም ከእነሱ ምንም አልጠቀሟቸውም ፡፡ በአላህ አንቀጾች ይክዱ ነበሩና ፡፡ በእነርሱም ላይ ያ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት ወረደባቸው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
✅  ጠቃሚ እውቀት ማለት ! 

ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

" እውቀት ማለት የጠቀመ ነው እንጂ እውቀት ማለት የተሸመደደው አይደለም " ።

https://t.me/bahruteka
🟢እባብ ጭንቅላቱ ሲመታ ጅራቱ ይወራጫል:

"እንደሚታወቀው እባብ አደገኛ መርዝ ያለው ተናዳፊ ተሳቢ ነፍሳት ነው:: በመሆኑም ሰዎች እባብን መግደል የሚቻለው ጭንቅላቱ ሲመታ ብቻ መሆኑን ያውቃሉና በከፍተኛ ጥንቃቄ አናቱን ይመቱታል:: እባቡም በደመ-ነፍስ ጅራቱን በማወራጨት ለመናደፍ ሲጣጣር ገዳይ ግን ዝም ብሎ ይመለከተዋል (ጭንቅላት ተመቶ መትረፍ አይታሰብምና):: "

ንፁህ እና ሙሉ በሆነው ዲን (ኢስላም) ላይ አዳዲስ የቢድዓህ መርዝ የሚረጩ ፈታኞችን ለማስጠንቀቅ ሰለፊዮች ምላሽ ሲሰጡ የሚፈራገጡ ጅራቶች ብዙ ናቸው።  ጭንቅላታቸው ስለተመታ በደመነፍስ በየአካባቢው ሲፍጨረጨሩ ይታያል::

ይሁን እንጅ ጭንቅላቱ የተመታ እባብ አቅምም መርዝም ስለሌለው ቢዘገይም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ይሞታልና አትፍሩት።

ስለዚህ የሙብተዲዖች ዋና ዋናዎቹ ሲነኩ ተከታዮቹ መፈራገጣቸው የተለመደ ነው። አሻኢራ ፣ሱፊይ፣ ኢኽዋን ፣ሱሩሪይ ፣ነባሮቹ ሙመይዓዎች ፣አዲሶቹ ጠበቆቻቸው በየደረጃው ጭንቅላቶቹ ሲመቱ  ተከታይ ጅራቶቹ እየተወራጩ አብሮነታቸውን ይገልፃሉ።

👉ወሰን ተለፈባቸው ፣ ተቸኮለባቸው ፣ በሳሎች ናቸው ፣ በሪፍቅ አናግሯቸው፣ ላ የልዘሙኒ ፣ የኢኽዋን ፊርቃ የለም ፣ የሙመዓህ ፊርቃ የለም ፣ አልቀበልም ወዘተ እያሉ ወድቀው ሲፈራገጡና የእባቡን ጭንቅላት የመቱትን የሱና ኡለማዎች ሲሳደቡ አልሰማችሁም⁉️

ጉዳዩ አላህ ዐዘ ወጀል እንዳለው ነው

《…وَإِنَّ الظَّالِمِينَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۖ وَاللَّهُ وَلِيُّ الْمُتَّقِينَ (19)》سورة الجاثية

《በዳዮች እኮ ከፊሉ ለከፊሉ ወዳጆች (ረዳቶች) ናቸው።አላህም የሙተቆች (የጥንቁቆች) ረዳት ነው።》

ሙብተዲዖች ደግሞ ከበዳዮች ናቸው።

የሱና ሰው ቢሆኑ እንዴት ቢድዐህና ሙብተዲዖቹ ተነኩ ብለው ይቆጣሉ?! በፍፁም! 

قال رجل لأبي بكر بن عياش: يا أبا بكر من السُّنِّي؟ قال: «الذي إذا ذُكِرت الأهواء لم يتعصب لشيء منها»
أصول الاعتقاد | للالكائي صـ٣١
እውነተኛ ሱንይ ማለት እኮ ስሜቶች(ቢድዓዎች) ሲነኩ ለየትኛውም አይነታቸው የማይወግን (የማይቆረቆር) ነው።

👌መርዛማና ተናዳፊ እባብ ሲያጋጥም ተባብሮ መግደል እንጂ ጭራ ሆኖ መፈራገጥ አያዋጣም።

https://t.me/Abuhemewiya
የጁምዓ ኹጥባ
በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት
ወቅታዊ የሆነ ወሳኝ የጁምዓ ኹጥባ


🔑 ርዕስ :- ከ አህለል ቢድዓ መራቅ ና ማስጠንቀቅ

🎙 በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት ሓራ (حفظه الله)

📅ቀን :- መስከረም 8/ 2019

ቦታ:-  ሰሜን ወሎ - ሀራ - መስጂል ፉርቃን

ለሁሉም በማዳረስ ይህን ወሳኝ ምክር እንዲሰሙት እናድርግ


https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
👉 ለሙስሊሞች አቧራ እንዳልመዝን ነው !

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ልጁ የሚዛንን ሳህን በልብሱ ጫፍ ሲጠርግ ያየውና ልጄ ሆይ ለምድነው እደዚህ የምታደርገው ይለዋል ። ልጁም ለአባቱ እንዲህ ሲል መለሰ : –
" አባቴ ሆይ ይህን ያደረግሁት ለሙስሊሞች የመንገድ አቧራ እንዳልመዝንላቸው ነው " ፉደይልም እያለቀሰ ለልጁ እንዲህ አለው : – ይህ ተግባርህ እኔ ዘንድ ከሁለት ሐጅና ከሁለት ዑምራ ይበልጣል ።

ከቱራሱል ዐረብይ የተወሰደ ።

https://t.me/bahruteka
👉 የማይጠገን ስብራት ማለት !

يقول عبدالله بن سليمان – رحمه الله –

ليست المصيبة أن يصاب الإنسان بنفسه أو ماله أو ولده، وإنما المصيبة العظيمة والجبر الذي لا ينجبر ، أن يصاب الإنسان بدينه، فيحل الشك محل اليقين ، فيرى الباطل حقا، والحق باطلا، والمعروف منكرا والمنكر معروفا "

الدرر السنية ( 15/466)

ዐብዱላሂ ኢብኑ ሱለይማን የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" ሙሲባ ማለት አንድ ሰው በነፍሱ ወይም በገንዘቡ ወይም በልጁ የሚደርስበት ሙሲባ አይደለም ። ነገር ግን ትልቁ የማይጠገነው ሙሲባ ማለት አንድ ሰው በዲኑ ሙሲባ ሲደርስበት ነው ። ጥርጣሬ የእርግጠኝነት ቦታ ሲዪዝ ፣ ባጢል ሐቅ, ሐቅ ደግሞ ባጢል , የሚታወቅ ነገር የማይታወቅ,የማይታወቅ ነገር ደግሞ የሚታወቅ ( ሱናው ቢዳዓ, ቢዳዓው ሱና) ሲመስለው ነው " ።

https://t.me/bahruteka
💢💢💢አስደሳች ሰበር ዜና‼️‼️‼️

በታላቅ ጉጉት በሚጠበቀው አለም አቀፉ የዳእዋ ፕሮግራም ላይ የሚቀርቡ አሊሞች÷ መሻኢኾች÷ ኡስታዞችና ዳኢዎች ዝርዝር ይፋ ሆነ‼️

☄️ የዚህ ብርቅዬ ፕሮግራም÷ እንቁ ተሳታፊዎች ☄️

1.   የተከበሩ ሸይኽ ዶክተር ኻሊድ ቢን ሙሐመድ አል-ጉፈይሊ... ከሪያድ/ሳውዲ
2.   ሸይኽ ሐሰን ገላው ሐሰን .... ከባህር ዳር
3.   ሸይኽ አብዱልሀሚድ... ከስልጤ/ለተሞ
4.   ሸይኽ ዶክተር ሁሴን ሙሐመድ … ከአዲስ አበባ
5. ሸይኽ ጡሃ ኸድር.... ከአዲስ አበባ
6. ሸይኽ ሙሀመድ ጀማል.... ከኮምቦልቻ
7. ሸይኽ  አቡዘር ሐሰን... ከኮምቦልቻ
8.  ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት... ከሀራ
9. ሸይኽ ሁሴን ከረም... ከሀራ
  10. ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ.... ከባህር ዳር
11.   ሸይኽ መህቡብ... ከወራቤ
12. ሸይኽ  ሰይፋሏህ… ከምስራቅ ስልጤ
13. ሸይኽ ሙባረክ... ከወልቂጤ
14. ሸይኽ አህመድ... ወረታ/ከአዲስ አበባ
15. ሸይኽ ሙሀመድ ሲራጅ… ከሀሮ
16. ኡስታዝ ሙሀመድ ኢብራሂም... ከመዲና
17. ኡስታዝ ሰልማን... ከመዲና
18. ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን.... ከአዲስ አበባ
19. ኡስታዝ አብዱልቃድር ሐሰን...  ከአዳማ
20. ኡስታዝ  ሙሀመድ እባቡ... ከቻግኒ
21. ወንድም አቡ ሷሊህ አል ኡስይሚን ኢልያስ… ከኩዌት

☄️ የፕሮግራሙ መሪዎች ☄️

1.   ኡስታዝ ባህሩ ተካ.... ከአዲስ አበባ
2.   ኡስታዝ አብዱረህማን ሰኢድ....  ከመርሳ
3.   ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን... ከደሴ
4.   ኡስታዝ አቡቦክር ዩሱፍ … ከባህር ዳር
5.   ኡስታዝ ሬድዋን ዳውድ… ከባህር ዳር

[ሁሉንም አሏህ ይጠብቃቸው]

ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት:-
🔻ቀን - መስከረም 16
🔻ሰአት - ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ መገባደጃ

🔻የሚተላለፍባቸው ቻናሎች:-
Telegram
https://t.me/bilalmesji
Imo
https://s.imoim.net/RKt0rh?from=copy_link

💢💢💢ሰለፍይነት ያብባል
ተውሂድ ይነግሳል 💢💢💢
Forwarded from Abu abdirahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን» (أنا المكدي وابن المكدي وهكذا كان أبي وجدي إلى متى يا نفس)
🎙🎙🎙ታለቅ ብስራት ለሰለፊዮች በሙሉ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته


ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም
ለሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የመስጅድ ቦታ ግዢ ።

እነሆ የፊታችን ሀሙስ ረቢዓ ሳኒ /13/ 1448 ወይም መስከረም 14/2019 ከምሽቱ በእትዮ #3:00 ጀምሮ የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የመስጅድ ቦታ ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም በኢሞ# ሩም ተዘጋጅቷል። በዚህ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የደዕዋ ፕሮግራም በመሳተፍ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ የታሪክ ተካፋይ ይሁኑ እያልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

➡የእለቱ ተጋበዥ እንግዶቻችን
🎙️ታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ አብዱልሀሚድ አለተሚይ {ሀፊዘሁሏህ}
🎙️ ኡስታዝ ሙሀመድ ኪርማኒ{ሀፊዘሁሏህ}
🎙ኡስታዝ አቡመርዋን ከሳንኩራ{ሀፊዘሁሏህ}
🎙ኡስታዝ ሙህይዲን በድሩ {ሀፊዛሁሏህ}
🎙️ኡስታዝ አብዱሹኩር ካሚል ከፎንቆ {ሀፊዘሁሏህ}
🎙ኡስታዝ ሙሀመድ ወልቂጢይ


የፕሮግራሙ አስተባባሪ
➢ኡስታዝ ሙህይዲን ከሌራ እና ሌሎች ወንድሞችም ይኖራሉ

💺:- አዘጋጅ :-ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ።

ሆሳእናን ተባብረን ከኩፍር ጨለማ እንታደጋት


በሀዲያ ዞን ላይ አሻራ ማስቀመጥ እነደሌላው ቦታ አይደለም

🕒 የፕሮግራሙ ሰዓት፦
🇪🇹 *በኢትዮ* *3:00pm*
🇸🇦 *በሳዑዲ* *9:00pm*
🇰🇼 *ዱባይ* *10:00pm*


*የመገናኛ ልንክ
We're in room የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሙስሊም ተማሪዎች የገቢ ማሰባሰቢያ. Join us! https://s.imoim.net/4fG2Is?from=copy_link

*የወትሳፕ ልንክ👇🏻👇🏻
https://chat.whatsapp.com/FapnD7O97xlLbZXPQTLFWK

ቴሌግራም
https://t.me/HHSMSCJ
👉 ለተበዳይ ልብ እረፍት የሆነ አንቀፅ !

ከቁርኣን አንቀፆች ውስጥ በበዳይ ላይ ቀስት ለተበዳይ ቀልብ ደግሞ እረፍት የሆነች አንቀፅ አለች አሉ ኢማሙ ሻፍዕይ ።

የትኛዋ አንቀፅ ናት ተብለው ጢጠየቁ እንዲህ የምትለዋ አሉ : –
{ …وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا }
مريم (64)
«… ጌታህም ረሺ አይደለም " ፡፡

https://t.me/bahruteka
🔹 ሐሰኑል በስርይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

( በሰለፎች ዘመን) አንድ ሰው እሾክ ይወጋዋል ። እሱም እንዲህ ይል ነበር :–
" አንቺ እሾክ ሆይ የወጋሽኝ በወንጀሌ እንደሆነና ልቅና የተገባው አምላኬ እንዳልበደለኝ አውቃለሁ " ።

https://t.me/bahruteka
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል አስራ ሁለት

ሰይድ ቁጥብ የነብዩን ሶሓቦች የሚሳደብ ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ ማረጋገጥ !

ሁለተኛ : ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን ሲሳደብ !
ባሳለፍናቸው ክፍሎች ለማየት እንደሞከርነው የነብዩን ሶሓቦች መውደድ ኢማን ሲሆን እነርሱን መጥላት ደግሞ ኩፍርና ኒፋቅ ነው ። ይህ ማለት የሚወዳቸው ሙእሚን ነው ማለት ነው የሚጠላቸው ደግሞ ሙናፊቅ ! ምክንያቱ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ አደራና ኑዛዜ ነው ። ሶሓቦቼን በመጥፎ አታንሱ አትጥሏቸው ብለው አደራ ብለውናልና ። ከዚህም በላይ የወደዳቸው እኔን ለመውደዱ ነው የሚጠላቸውም እኔን ለመጥላቱ ነው ብለውናል ። እንደሚታወቀው ነብዩን መጥላት ኩፍር ነው ። ሶሓቦችን መጥላት ደግሞ ነብዩን መጥላት ነው ።
የነብዩን ሶሓቦች የምንወደው አላህ መርጦ የሳቸው ባልደረባ ስላደረጋቸውና ለእስልምና ህይወታቸውን ፣ ክብራቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ እውቀታቸውን ፣ ገንዘባቸውን ጭምር ቤዛ ስላደረጉ ነው ። ለነብዩ ሸሪዓ ብለው ተሰደዋል ፣ ተርበዋል ፣ ተጠምተዋል ፣ ተገርፈዋል ፣ በእሳት ተቃጥለዋል ፣ በመካ ሀሩር የነደደ ቋጥኝ በእነርሱ ደም እንዲቀዘቅዝ ተደርጓል ። ለዚህ ነው አላህ ያላቃቸው ያከበራቸውና ዝናቸው ከፍ እንዲል ያደረገው ። በዚህ አላበቃም አመኞችን በመልካም እንዲያነሱዋቸውና ፈለጋቸውን እንዲከተሉ አዟል ። ይህ ነው የመወደዳቸው ሚስጢር ። ለዚህ ነው ሙእሚን እንጂ አይወዳቸውም ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም የተባለው ።
እነዚህን የአላህ መልእክተኛ ባልደረቦችን ነው ሰይድ ቁጥብ የሚያዋርደውና የሚያንቋሽሸው ። በአላህ ይሁንብኝ የሙሐመድ ሓሚዲን ጥብቅና ባይኖርና ወጣቶች እሱን ሰምተው የሰይድ ቁጥብን ተግባር ቀለል አድርገው በማየት ልባቸው ይታመማል ሳያውቁት ኒፋቅ ሊገባባቸው ይችላል የሚለው ስጋት ባይኖር ኖሮ የሰይድ ቁጥብን ቅርሻት ባልፃፍኩኝ ነበር ። ነገር ግን የዚህ ሰው ማንነት ሙሐመድ ሓሚዲን ከሚለውና ከሚገልፀው በጣም የራቀ ይልቁንም ራሱ አምኖበት በተናገረው ንግግሩና ፅሑፉ የአላህ መልእክተኛን ሶሓቦች የሚያዋርድና የሺዓዎችን አንጀት የሚያርስ በሶሓቦች ክብር ተረማምዶ በራፊዳዎች ሜዳሊያ የተሸለመ ግለሰብ መሆኑ እንዲታወቅ ነው ። ለማንኛውም ማየት ማመን ነውና እስኪ በነብዩ ላይ ይወርድ የነበረውን ወሕይ ከሚፅፉት የነበረውን ፣ የመጀመሪያውን በባህር ላይ የተደረገውን ዘመቻ የመራውን ፣ የምእመናን አጎት የሆነውንና የአላህ መልእክተኛ ዱዓእ ያደረጉለትን ብርቅዬ ሶሓብይ ሙዓውያንና ጓደኛውን ታላቁን ሶሓብይ ዐምር ኢብኑ ዓስም ምን እንደሚላቸውና እንዴት እንደሚያዋርዳቸው እንመልከት : –

"إن معاوية وزميله عَمْراً لم يغلبا علياً لأنهما أعرف منه بدخائل النفوس، وأخبر منه بالتصرف النافع في الظرف المناسب . ولكن لأنهما طليقان في استخدام كل سلاح، وهو مقيد بأخلاقه في اختيار وسائل الصراع . وحين يركن معاوية وزميله إلى الكذب والغش والخديعة والنفاق والرشوة وشراء الذمم لا يملك عليٌ أن يتدلى إلى هذا الدرك الأسفل فلا عجب ينجحان ويفشل، وإنه لفشل أشرف من كل نجاح ".

كتب وشخصيات ص (242)

" ሙዓዊያና ጓደኛው ዓምር ዐልይን ያሸነፉት ከሱ የበለጠ በሰዎች ውስጥ ያለውን በማወቃቸው ወይም በክስተቶች ጠቃሚ የሆነውን መንገድ በመከተል ከሱ የበለጠ እውቀት ኖሯቸው አይደለም ። ነገር ግን እነርሱ ለማሸነፍ የሚያስችለውን የትኛውንም መንገድ በመከተል ልቅ ስለሆኑና እሱ ግን በፍልሚያ ጊዜ መጠቀም ያለበትን መንገድ እንዲመርጥ በባህሪው የተገደበ ስለነበረ ነው ። ሙዓዊያና ጓደኛው ወደ ውሸት ፣ ማታለል ፣ ክህደት ፣ ንፍቅናና ፣ ጉቦ በመስጠት የሰዎችን ጫንቃ ወደመግዛት በተዘነበሉ ጊዜ ዐልይ ወደዚህ ዝቅጠት መዝቀጥ አይችልም ነበርና እነርሱ በማሸነፋቸውና እሱ በመሸነፉ መገረም አያስፈልግም ። መሸነፉ ከየትኛውም ማሸነፍ በላይ ክብር ነበርና " ።
ተመልከቱ ሰይድ ቁጥብ ሙዓዊያንና ዐምር ኢብኑ ዓስን በውሸት ፣ በማታለል ፣ በክህደት ፣ በሙናፊቅነት ፣ ጉቦ ሰጥቶ ሰዎችን በመግዛት ያሸነፉ ብሎ እንዴት እንደሚወርፋቸው ‼ ሱብሓነላህ ! እንዴት ይሆን ነገ አላህ ፊት ከሙዓዊያና ኢብኑል ዓስ ጋር ከሳሽና ተከሳሽ ሆኖ የሚቀርበው ? ለዛው ጠበቃቸው የአላህ መልእክተኛ ሆነው እሱ ነብዩ ለምን ሶሓቦቼን ሰደብክብኝ ሲሉት መልስ ሊሰጥ ! ከዚህ በላይ የሚገርመው ደግሞ የሶሓቦች ጠበቃ የአላህ መልእክተኛ ሆነው የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ ደግሞ ሙሐመድ ሓሚዲን ሆኖ አላህ ፊት መገናኘታቸው ነው ።
አላህ ሆይ አንተ ጠብቀን !

አላህ ካለ ይቀጥላል ።
 
https://t.me/bahruteka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ወድ ወንድምና እህቶች ቴሌግራም የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ እያስከፈለ ይለቃል። በመሆኑም እኔ ያለጠፍኩት ማስታወቂያ እኔን አይወክልም።  ማስታወቂያውን ሪፖርት አድርጋችሁ ለማስጠፋት ከጎን ያለውን ሶስት ነጥብ ነክታችሁ ምጫዎች ሲመጡ spam ብላች ላኩ።

https://t.me/bahruteka
👉 የሙስሊሞችን ሐቅ ያለ ፈቃዳቸው መጠቀም !

قال الشافعي – رحمه الله – :

"من مر لرجل بزرع أو ثمر أو ماشية أو غير ذلك من ماله لم يكن له أخذ شيء منه إلا بإذنه ؛ لأن هذا مما لم يأت فيه كتاب ولا سنة ثابتة بإباحته، فهو ممنوع إلا بإذن مالكه"

"المجموع" (9/ 55).

ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

" በአንድ ሰው በአዝመራው ወይም በፍሬው ወይም በተንቀሳቃሽ ከብቶችም ይሁን በሌላም በግል ንብረት በኩል ያለፈ ሰው ከሱ ምንም ያለ ፈቃዱ መውሰድ አይፈቀድለትም ። ይህ ቁርኣንም ይሁን ሐዲስ የተፈቀደ በመሆኑ ያልመጣበት ነው ። በመሆኑም ያለ ባለቤቱ ፈቃድ የተከለከለ ነው " ።

የኢማሙ ሻፍዕይ ንግግር የአንድ ሙስሊም ገንዘብ ያለ ፍላጎቱ መውሰድ አይፈቀድም ከሚለው ከነብዩ ሐዲስ የተወሰደ ለመሆኑ ግልፅ ነው ። ገንዘብ ወይም ንብረት ማለት መጠቃቀሚያ ነው ። ማንኛውም አንድ ሰው በተፈቀደ መልኩ የግሉ አድርጎ የሚጠቀምበትን ነገር ያለሱ ፈቃድ የተለያዩ ዘዴዮችን ተጠቅሞ መጠቀም ክልክል መሆኑን ያመለክታል ። በመሆኑም የአንድ ሰው የግል ቻናልን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ ለሌላ አካል በመክፈል በእጃዙር መጠቀም በምንም መልኩ የሚፈቀድ አይደለም ።
በጣም የሚገርመው የማፌያ ቡድኖች የሚሰሩትን አይነት ተግባር በመስራት የሰዎችን የግል ቻናል ያለፈቃዳቸው የራሳቸውን የሚፈልጉትን አካል ቻናል ማስተዋወቂያነት እየተጠቀሙ ይህን እንደጀብድ በመቁጠር ችሎታችንን ተመልከቱ የሚሉ ጉደኞችን እያየን ነው ። አው ከሸሪዓ የራቃችሁ የማፌያ ቡድኖች መሆናችሁን አውቀናል ነው መልሳችን ።

https://t.me/bahruteka
👉 የሀራው ጉዳይ ጥንቃቄ ይፈልጋል !

ውድ የሱና ቤተሰቦቻችን በሙሉ ሁሉም እንደሚያውቀው በቅርቡ በሀራ ሰለፍይ ወንድሞቻችን መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል ። ከዛ በፊት በሀላባ ሰለፍዮች መካከልም የተፈጠረው አለመግባባት እልባት አላገኘም ። እንደዚህ አይነቶቹ አለመግባባቶች ሁሉንም ሰለፍዮች ያሳዘነ መሆኑ ግልፅ ነው ። የሶሞኑ የሀራው አለመግባባት ከመቀራረብ ይልቅ መራራቅ ፣ ከማጥበብ ይልቅ ወደመስፋት እየሄደ ነው ። ሀላባም ይሁን ሀራ ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች በሰለፍዮች መካከል መሆኑ ግልፅ ነው ። አይደለም የሚል ካለ ማንኛው ከሱና እንደወጣ በመረጃ ግልፅ ማድረግ ይኖርበታል ።
የሀራው አለመግባባት ደግሞ በመሻኢኾችና በተወሰኑ ተማሪዮቻቸው መካከል መሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ። በመሆኑም መሻኢኾቹም ሆኑ ተማሪዮቻቸው አላህን ፈርተው ከስሜት ርቀው ችግሩን በሰከነ መልኩ ለመፍታትና የሰለፍቶችን አንድነት ለመጠበቅ የሚችሉትን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ። አለመግባባቱ ከማንም በፊት ዳዕዋውን ይጎዳል ። ሁሉም ቆም ብሎ ቢያስተውል ለዚህ ዳዕዋ ሰለፎች የከፈሉትን መስዋእትነት አይቶ እኔ የሚለው ስሜት ራስን ከመውቀስ ጋር እንዲጠፋ ማድረግ በተቻለ ነበር ። አሁንም አረፈደም ። መሻኢኾች የተማሪዮቻቸውን ጥፋትና ስህተት ለማረም መንገዱን ከሰሎፎች ተሞክሮ መውሰድ የግድ ነው ። ይረዝምብኛል ባልል በጣም ብዙ ማሳያዎችን በጠቀስኩ ነበር ። ተማሪዮችም የመሻኢኾቻቸውን ስህተትና ጥፋት የሚሉትን በምን መልኩና እንዴት ማረም እንዳለባቸው ከሰለፎቻቸው በቂ ተምሳሌት አለላቸው ።
ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው የጋራ ነጥብ መከባበር ፣ መተዛዘን ፣ ስህተትን በስተትነቱ መስተካከል ያለበት መሆኑን ማመንና መንገዱን ወደ ቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ ላይ አድርጎ ተሞክሯቸውን መጠቀም ነው ። በመሆኑም ሁለቱም የሱና ወንድሟሟቾች አላህን ፈርተው ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ ምንም አይነት ነገሮችን የሚያባብሱ ነገሮችን ከመፃፍም ሆነ ከመናገር እንዲቆጠቡ በአላህ ስም እጠይቃለሁ ።
ሌላው በየቦታው የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ትፈታላችሁ ተብሎ ሀላፊነት የተጣለባችሁ የሀገራችን የሱና መሻኢኾች የሰለፍያን ዳዕዋ እንደ እሳት የሚበላውን የሰለፍዮችን አቅም የሚያዳክመውን ከአላህ እዝነት የሚያርቀውን አሳዛኝ አለመግባባት እንደሰደድ እሳት እየተዛመተ ሰለፍያን ከመብላቱ በፊት ቅድሜያ ሰጥታችሁ እንድትፈቱ ለዚህም የትኛውንም ዋጋ እንድትከፍሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ ።
በመጨረሻም በየትኛውም አካባቢ በሰለፍዮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶች በአላህ ፈቃድ በአጭር ጊዜ ተፈተው ሰለፍዮች ወደ አንድነታቸው እንደሚመለሱ በአላህ ተስፋ እንድናደርግ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ። ለዚህ አላማ የትኛውም ሰለፍይ የትም ሆኖ የሚችለውን እንዲያደርግ አደራ እያልኩ ከዚህ ሰአት ጀምሮ ከየትኛውም አለመግባባቱን ከሚያሰፉ ተግባሮች ተቆጥበን ወደ መግባባት የሚያደርሱ ሰበቦችን በማድረስ ተራ በተራ የሁሉም ሰለፍዮች የደስታ ብስራት የሚነገርባቸውን ቀናቶች እንጠብቅ እላለሁ ። አላህ ይረዳናል ሰለፍዮች አንድ ይሆናሉ ተውሒድና ሱና በሰለፍዮች ጥረትና በአላህ እገዛ የበላይ ይሆናሉ ።

https://t.me/bahruteka
ما-نصيحتكم-للدعاة-الذين-يستعملون-الذكاء-الاصطناعي-في-كتابة-الردود…
🟢አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው
� سؤال وجواب �

↞ ما نصيحتكم للدعاة الذين يستعملون الذكاء الاصطناعي في كتابة الردود والمقالات وينشرونها بأسمائهم؟

▫️إجابة الشيخ العلامة أ .د:
عبد الله بن عبد الرحيم البخاري
حفظه الله ونفع بعلمه

🎙مقتطف من الدرس التاسع من شرح «الأربعون في الأحكام»

•
https://t.me/dr_elbukhary/5261
•
الذكاء الاصطناعي
Artificial Intelligence
(AI)

አርቴፊሻሉን AI ተጠቅመው የራሳቸው ፅሁፍ አስመስለው የሚለቁ ዳዒይ ተብዬዎች
ረድ እና ሌላም ፅሁፍ ይፅፋሉ የሚገርመው
አርቴው ከተሳሳተ እነርሱም ከነ ስህተቱ በጭፍን ተቅሊድ ይለቁታል ወይም ፕሮፋይል ያደርጉታል። ያልሆነውን አስመስለው ያቀርቡታል። እነዚህን ዳዒይ ተብዬ አብረቅራቂዎችን ተጠንቀቁ። የዲን ሿሿ እንዳይሰሯችሁ።

አንዳንድ ዳቦ ቤቶች ደጅ ላይ የተለጠፈው ያማረ ዳቦ ቢጤ ነው።ፍቶውን የሚመስል ዳቦ ያመርታሉን!? ጠይቋቸው

https://t.me/FATTAWAS