ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
👉 የፅናት መሰረቱ !

يقول ابن رجب الحنبلي – رحمه الله –

" أصل الاستقامة استقامة القلب على التوحيد "

جامع العلوم والحكم ص (193)

ኢብኑ ረጀብ አል ሐንበልይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" የፅናት መሰረቱ የልብ በተውሒድ ላይ መፅናት ነው " ።

http://t.me/bahruteka
በልብህ ውል ያላለ ነገር መሰጠት ትፈልጋለህ?
◈

📝 قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله:
✅ "وإذا اجتهد واستعان بالله تعالى ولازم الاستغفار والاجتهاد؛ فلا بد أن يؤتيه الله من فضله ما لم يخطر ببال."

✅ ​“አንድ ሰው ጥረት ካደረገ፣ በአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ከተታመነ (እርዳታን ከጠየቀ)፣ እንዲሁም እስቲግፋርን (ምህረት መጠየቅን) እና ጥረቱን አጥብቆ ከተያያዘው፤ አላህ ከችሮታው በሃሳቡ እንኳ ውል ብሎ የማያውቀውን (መልካም ነገር) መስጠቱ አይቀሬ ነው።”

📚 مجموع الفتاوى | ٣٩٠/١١
https://t.me/AbuImranAselefy
🔹ከዋና ቸናሌ እግርጌ ከስርስር ከሚለቀቁ የቢዝነሰኞች የዱኒያ ጥማተኞች ከቁማርተኞች በአጠቃላይ በፍቃዴ ስላለሆኑ ማስታወቂያዎች ሁሉ የጠራሁኝ ነኝ በነጋራችን ላይ በተለይ ሰለፊዮች እንዳትሸወዱ አጣሩ እኔ አሊም ነኝ እኔ ሙፍቲ ነኝ እኔ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ አዎ እንደዛ ነው ማለት አይደለም በተለይ የኦንላይን ዘራፊዎች በዝተዋል አሏህ ይጠብቀን ለዲናችን ምንጭ አለው ለምንጩም የሚያስተላልፈው ባለቤት አለው እና ባለቤቱ ማን እንደሆነ አጣሩ ።

join #telegram ቻናል
https://t.me/abuabdurahmen
👉 የዒባዳ መለኪያው ብዛት ሳይን ሱና ነው !

يقول الشيخ الألباني – رحمه الله –

" العبرة ليست بكثرة العبادة وإنما بكونها على السنة بعيدة عن البدعة "

سلسلة الصحيحة (5/1314)

ሸይኽ አልባኒ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ :–

" ዒባዳ ግምት የሚሰጠው በብዛቱ ሳይሆን ከቢዳዓ ርቆ ሱና ላይ በመሆኑ ነው " ።

http://t.me/bahruteka
🔷 በሁሉም ሙስሊም ላይ ሱናን መከተል ዋጂብ ነው !

يقول الشيخ ابن باز – رحمه الله تعالى –

" فالواجب على جميع المسلمين اتباع السنة والاستقامة عليها، والتواصي بها والحذر من البدع كلها "
نور على الدرب (11/328)

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ – ራሕመቱላሂ ዓለይሂ – እንዲህ ይላሉ : –

" ሱናን መከተልና በዛ ላይ መፅናት እንዲሁም በሱና ላይ አደራ መባባል ከሁሉም የቢዳዓ አይነት መጠንቀቅ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ንው " ።

http://t.me/bahruteka
👉 ከዱንያ ሰዎች ጋር አትቀማመጥ ዲንህንም ቀልብህንም ያበላሹብሀል !

‏ يقول سفيان الثوري – رحمه الله – في وصيته :

" ليكن جليسك مَن يُزَهِّدُكَ في الدنيا ، وَيُرَغِّبُكَ في الآخرة ، وإياك ومجالسة أهل الدنيا الذين يخوضون في حديث الدنيا ؛ فإنهم يفسدون عليك دينك وقلبك ، وأكثر ذكر الموت ، وأكثر الاستغفار مما قد سلف من ذنوبك ، وسل الله السلامة لما بقي من ‏عمرك "

حلية الأولياء ٨٢ / ٧

ሱፍያን አስ ሰውሪ ኑዛዜ ሲያደርግ እንዲህ ይላል :–

" የምተቀማመጠው ሰው በዱኒያ ጉዳይ ላይ እንድትብቃቃ ከማያስፈልግህ ነገር ችላ እንድትልና በአኼራ ላይ ጉጉት እንዲኖርህ የሚያደርግህ ይሁን ። እነዚያን በተገናኙ ቁጥር ስለ ዱንያ ከሚያወሩ ሰዎች ጋር ከመቀማመጥ ተጠንቀቅ ! እነዚህ ሰዎች ዱንያህንም ቀልብህን ያበላሹብሀል ። ሞትን ማሰብን አብዛ, ካለፈው ወንጀልህ ምህረትን ጠይቅ, ለቀሪው እድሜህም
የአላህን ጥበቃ ለምነው" ።

http://t.me/bahruteka
👉 ሙስተጃብ የሆነ ዱዓእ ቢኖረኝ ለመሪ አደርገው ነበር !

يقول الفضيل بن عياض – رحمه الله –

" لو أن لي دعوة مستجابة ما صيرتها إلا في الإمام ، قيل له : وكيف ذلك يا أبا علي؟ قال : متى ما صيرتها في نفسي لم تجزني، ومتى ما صيرتها في الإمام فصلاح الإمام صلاح العباد والبلاد ".
حلية الأولياى (8/91)

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" (አላህ ዘንድ)ተቀባይነት ያለው ዱዓእ ቢኖረኝ ኖሮ ለመሪ እንጂ አላደርገውም ነበር ። አንተ የዐልይ አባት ሆይ ይሄ እንዴት ነው ተብሎ ተጠየቀ, እሱም : ለራሴ ባደርገው ከኔ አያልፍም ። ለመሪ ባደርገው ግን የመሪው መስተካከል የህዝብና የሀገር መስተካከል ነው " ።

http://t.me/bahruteka
👉 ከሶደቃ ጥቅሞች !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" للصدقة تأثير عجيب في دفع البلاء ودفع العين ودفع شر الحاسد "

بدائع الفوائد 2/234

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" ለሶደቃ በላእን ፣ የሰው ዓይነን ፣ የምቀኛን ተንኮል በመከላከል አስገራሚ ተፅኖ አለው " !።

http://t.me/bahruteka
Forwarded from 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍ (أبو حموية)
🟢የሸይኽ ረቢዕ ምክር ለሰለፊዮች

✏️የሸይኹልኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ፤ የኢብኑልቀይም እና የነጅድ የተውሂድ ዑለማዎችን ኪታቦች ትኩረት አድርጉ ፤ በደንብ ተገንዘቧቸው ፤ ተመሩባቸውም።

✏️የልመና እጃችሁ እንደ ኢሃይ አቱራስ ወዳሉ ማህበራት (ጀምዒያዎች) እንዳትዘረጉ።

✏️ትንሽም ቢሆን አላህ በሰጣችሁ ሀብት ተብቃቁ።

✏️ዳዕዋ ሰለፊያ የቆመችው ሰለፊዮች ዘንድ ባለች ትንሽ ሀብት እና በብዙ ችግር ነው። ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ አይደለም የቆመችው።አስተውሉ ‼️

✏️ሀብት መሰብሰብ (በተለይ ከሂዝቢዮች) ዳዕዋን ያወድማል።

✏️የሂዝቢያ ድርጅቶችን ተጠንቀቁ ገንዘብ እየሰጡ እንዳያዳክሟችሁ።አላህ በሰጣችሁ ተብቃቁ።

✏️ሀራምና አጠራጣሪ ሀብትን በመጠንቀቅ እና በዙህድ የሰለፎችን መንገድ ተከተሉ።

✏️ደዕዋን በትክክለኛው የሰለፎች መንገድ አሰራጩ (አድርሱ)።

✏️ኢሃይ አቱራስ ኢስላማዊ ማህበር በዓለም ላይ ሰለፊዮችን ለመበታተን እየለፉ ነው። የዐብዱረህማን ኢብኑ ዐብዱልኻሊቅን መንሃጅ እያስፋፉ ነው። በጣም ተጠንቀቁ‼️

✏️ሽፋን ሊሆንላቸው የሱነህ ዑለማዎችን ኪታቦች ገዝተው ሊያድሉ ይችላሉ።

ማስታወሻ
የኢህያእ አቱራስ ኢስላማዊ ማህበርም ሆነ የዐብዱረህማን ኢብኑ ዐብዱልኻሊቅን አይነት መንሃጅ የሚከተሉ ሁሉ ማስጠንቀቂው ይመለከታቸዋልና ተጠንቀቋቸው‼️

https://t.me/Abuhemewiya
👉 የእቁብ ሰብሳቢዮች ግድፈቶች !

እቁብ ማለት በአንድ ወይም በተወሰኑ ሰዎች አማካይነት የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እየተሰሰበሰበ ለሰብሳቢው /ዎች የተወሰነና የእቁብ ከፋዮቹ የተስማሙበት የገንዘብ መጠን እንደ ደሞዝ እየተከፈ በአማና አስቀምጠው ሀላፊ ሆነው ሰብስበው በየተራ ለእቁብተኛው በእጣ ወይም ያለ እጣ እንዲሰጥ የሚደረግበት አሰራር ነው ። የዚህ አይነቱ አሰራር ከሸሪዓዊ ህግጋቶች በማይጋጭ መልኩ ከተሰራ በመልካም ከመተባበር ውስጥ ሊመደብ ይችላል ።
የዘመናችን የሸሪዓ እውቀት ባልተቤቶች የዚህ አይነቱን አሰራር በመልካም መተባበርና መልካም ብድር ውስጥ ይገባል ይላሉ ።
ይህ አሰራር ብዙዎችን የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያደርግ ሲሆን አብዛኞች በራሳቸው ለእቁብ በሚሰጡት ትኩረት ልክ አጠራቅመው መፈፀም የማይችሉዋቸውን ተግባራት በእቁብ አማካይነት ይፈፅማሉ ። ለምሳሌ የተለያዩ የስራ አይነቶችን መጀመር ፣ ትዳር መያዝ ፣ ቤት መግዛት ፣ መኪና መግዛትና የቤት ቁሳቁሶችን እንደሟሟላት የተወሰኑ ሰዎች በዚሁ መንገድ በማጠራቀም ሐጅና ዑምራ እንደማድረግ ያሉ ተግባራትን በእቁብ በመታገዝ ያከናውናሉ ።
ይሁን እንጂ ለእንደነዚህ አይነት መልካም ተግባራት አጋዥ የሆነው እቁብ ከ90% በላይ የሚሆነው በሰብሳቢዮቹ አማካይነት የሸሪዓ ጥሰት ያስተናግዳሉ ። የእቁብ ሰብሳቢዮችም ሆነ ከፋዮቹ አብዛኞቹ ከሸሪዓ እውቀት ጋር ግንኙነት የሌላቸው በመሆኑ ተግባሩን አሉታዊ ገፅታ ያላብሱታል ።
በሰብሳቢዮች ከሚሰሩ የሸሪዓ ጥሰቶች ውስጥ የተወሰኑትን እንይ : –
አንደኛ – ለአራትና ለአምስት ወር ያለ እጣ ዝም ብለው በመሰብሰብ አማና በተቀመጠባቸው የሰዎች ገንዘብ ያለ ፈቃዳቸው በመነገድ ከየትኛውም ነጋዴ በላይ ይበለፅጉበታል ። ወይም ለሌላ በትርፍ በማበደር ሐራም የሆነ ያልተገባ ጥቅም ያገኙበታል ። አደራ በተቀመጠ የሰዎች ገንዘብ ያለ ሰዎቹ ፈቃድ መነገድ ከባድ ሐራም የሆነ ተግባር ሲሆን ለሌሎች አበድሮ ትርፍ መቀበል ወለድ ነው ።
ሁለተኛ – ሰብሳቢዮቹ እቁብ ከፋዮችን በማሳመን አንድ እጣ ወጥቶ ለእቁብተኛ እንዲሰጥና አንድ ደግሞ ሽያጭ እንዲኖር በማድረግ የተቸገረ ሰው እቁቡን ያለ እጣ ወስዶ ለእቁብተኛው ከተወሰነው ክፍያ ውጪ በግዢ መልክ እንዲከፍል ያደርጋሉ ። ይህም የገዛው ሰው ከተወሰነው የእቁብ ክፍያ ውጪ ስለሚከፍል ወለድ ውስጥ ይገባል ።
ሶስተኛ – በቀኑ ያልከፈሉ ሰዎችን ቅጣት እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን ይህም ሪባ አንነሲኣ ( በጊዜ ምክንያት) የሚመጣ ወለድ ውስጥ ይገባል ።
እነዚህ ተግባራት ከሸሪዓ ያፈነገጡና የአብዛኛው እቁብ ሰብሳቢ አላማ ሰዎችን መጥቀም ሳይሆን ያለ አግባብ በሰዎች ለመጠቀም ያለመ መሆኑን ያሳያል ። ከዚህ በላይ እቁቡ ከወለድ ጋር የተነካካ በማድረግ ብዙዎች በማያውቁት መንገድ በገንዘባቸው ከአላህ ጋር ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል ። በመሆኑም እቁብ ሰብሳቢዮች አላህን እንዲፈሩና የተሰጣቸውን ገንዘብ አማናውን ጠብቀው ለከፋዮቹ በስምምነታቸው መሰረት በእጣ ወይም በየተራ በማስረከብ በሚከፈላቸው ደሞች እንዲብቃቁ አደራ ለማለት እወዳለሁ ።
ማስታወሻ : –
ለሰብሳቢዮቹ የሚከፈለው እቁብተኞቹ የተስማሙበትና መጠኑን ያወቁት ገንዘብ በየተኛውም መመዘኛ ወለድ ውስጥ የማይገባ ሲሆን ትርፍ ከሚያስገኝ ብድርም ጋር ግንኙነት የለውም ።

http://t.me/bahruteka
✅ የሰለፍያን መዝሀብ ላለመቀበል ምንም መረጃ የለም !

يقول شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله –

" واعلم أن ليس في العقل الصريح ولا في النقل الصحيح ما يوجب مخالفة الطريقة السلفية أصلا "
الفتاوى الحموية ص (276)

ሸይኹል ኢስላም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" እወቅ በትክክለኛ ግልፅ የሆነ ዐቅልም ይሁን ትክክለኛ ሶሒሕ በሆነ የቁርኣንና ሐዲስ የሰለፍያን መንገድ ለመቃረን የሚያስችል መረጃ የለም " ።

http://t.me/bahruteka
🔷 አንድ ሰው ዐቂዳው ሰለፍይ ሆኖ ስነምግባሩ ሰለፍይ ላይሆን ይችላል !

يقول الشيخ الألباني – رحمه الله –

" قد يكون الشخص سلفيا في عقيدته ، ولكنه ليس سلفيا في تربيته وسلوكه "

سلسلة الهدى والنور ص (781)

ሸይኽ አልባንይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

" አንድ ሰው ዐቂዳው ሰለፍይ ሆኖ ነገር ግን አስተዳደጉና ግብረገብነቱ ሰለፍይ ላሆን ይችላል "።

http://t.me/bahruteka
👉 ስጁድ የወረድክበት መሬት የሞትክ ቀን ያለቅሳል !

يقول عطاء الخراساني – رحمه الله –

ما من عبد يسجد لله سجدة في بقعة من بقاع الأرض إلا شهدت له يوم القيامة، وبكت عليه يوم يموت " .
حلية الأولياء ص (5/197)

አጧእ አልኹራሳንይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" ከምድር በየትኛውም ቦታ ለአላህ አንድ ስጁድ የሚያደርግ የለም የቂያማ ቀን የሚመሰክርለትና የሞተ ቀን የሚያለቅስለት ቢሆን እንጂ "

http://t.me/bahruteka
🔷 የነብያቶችን መቀማመጥ ማየት የፈለገ የዑለሞችን መቀማመጥ ይመልከት !

يقول سهل بن عبد الله التستري – رحمه الله –

" من أراد إلى مجالس الأنبياء فلينظر إلى مجالس العلماء " .

مفتاح دار السعادة ص (1/118)

ሰህል ኢብኑ ዐብዲላሂ አትቱስትርይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" የነብያቶችን መቀማመጥ ማየት የፈለገ ( የሱና) የዑለሞችን መቀማመጥ ይመልከት" !።

http://t.me/bahruteka
አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ!

ይህ የሌራ ኢማሙ አሕመድ ጀመዓ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
በዚህም መሰረት መስጂዱ ላይ በሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል ለተሚይ የሚሰጡ ዱሩሶች በዚህ ቻናል ላይቭ (ቀጥታ) የሚተላለፍ ይሆናል።

የቻናሉ ሊንክ ፦
t.me/Imamu_Ahmed1448

🗓 ጁማደል ኡላ 1/5/1448
👉 በኢኽላስ የሚሰራ ሰው ምሳሌ !

قال ابن مسعود – رضي الله عنه –

" المخلص لربه كالماشي على الرمل، لا تسمع خطواته ولكن ترى آثاره "

جامع العلوم والحكم ص (302)

ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ – ረዲየላሁ ዐንሁ – እንዲህ ይላል : –

" ለጌታው በኢኽላስ የሚሰራ ሰው ምሳሌ በአሸዋ ላይ እንደ ሚሄድ ሰው ነው ። (የኮቴው) ድምፅ አትሰማም ( ነገር ግን) ፋናውን ታያለህ "!

http://t.me/bahruteka