በጅጅጋ ከተማ የህጻናት ነፃ ከአንገት በላይ የቀዶ ጥገና ሕክምና መስጠት ተጀመረ ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 10/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 9/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጅግ ጂጋ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማኅበራዊ አገልግሎቶች ዘርፍ ከሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና ከጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሸይኽ ሀሰን ያባሬ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በጅጅጋ ከተማ ለ100 ህፃናት ነፃ ከአንገት በላይ የቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
“ከአንገት በላይ ደህንነት ለሁለንተናዊ የህፃናት ጤናማ ሕይወት” በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው ይህ ነጻ የህክምና አገልግሎት ንቅናቄ ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማገዝ ማኅበራዊ ደህንነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ ያለው ስለመሆኑ ተመላክቷል።
ነጻ የህክምና ንቅናቄውን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ የህፃናትን ጤና መደገፍ የላቀ ሰብዓዊ እና ማኅበራዊ ተግባር ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በጤና ችግር ምክንያት ከመደበኛ ሕይወት ተነጥለው የሚችሉ ህፃናትን በመለየት ነጻ የሕክምና ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የጅጂጋ ዩኒቨርሲቲ ሸይኽ ሀሰን ያባሬ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አይድሩስ መሀመድ በበኩላቸው ሆስፒታሉ አስፈላጊውን የሕክምና ባለሙያና መሠረተ ልማት በማዘጋጀት አገልግሎቱን በጥራት ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሙሀመድ ዓሊ ዩሱፍ የተጀመረው ነጻ የህክምና አገልግሎት ህጻናቱ ተገቢ ሕክምና በነጻ እንዲያገኙ ከማድረጉም በላይ የቤተሰቦችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና በማቃለል የህፃናትን የወደፊት ተስፋ ያለመልማል ብለዋል።
ነጻ የህክምና አገልገሎቱ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቆይታውም 100 ህፃናት ነጻ የምርመራ፣ የቀዶ ህክምና፣ የክትትል እና የምክር እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ የሪፈራል አገልግሎቶች እንደሚያገኙ ተመላክቷል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
The Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council Ethiopian Hajj Mission Office wishes to select, through a competitive process, service providers for Ethiopian Hajj pilgrims in the Kingdom of Saudi Arabia for 1448/2027 Hajji season.
Accordingly, eligible service providers are invited to submit their applications via email to ethiohajj@gmail.com until Tuesday, September 22, 2026, at 4:00 PM in accordance to the attached terms and conditions.
Sep/21/2026