Civil Engineering
1.37K subscribers
1.26K photos
20 videos
962 files
673 links
*ለሲቪል ; ለአርክቴክቶች÷ለኮንስትራክሽን ÷ ለሀይድሮሊክ መሀንዲሶች እና ተማሪዎች የተዘጋጀ ትምህርታዊ ቻናል ፡፡

@engineer03


http://www.Indiabix.com በዚህ ደግሞ ማንኛውንም ጥያቄና መልስ ታገኛላችሁ!

╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲╭
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕
Download Telegram
👉Today Tip
.
➡ በ አንድ ሜትር ካሬ ምን ያህል ብሎኬት እንጠቀማለን??
⏩የብሎኬት👇
▶ ስፋት =0.4ሜ
▶ቁመት =0.2ሜ
=1/(0.4*0.2)
=12.5
=~13
🚩ስለዚህ በ አንድ ሜትር ካሬ 13 ፍሬ ብሎኬት እንጠቀማለን ማለት ነው።

@engineer03
💬Cantilever retaining walls can safely be used for a height not more than________
Anonymous Quiz
43%
A.3 m
14%
B.4 m
16%
C.5 m
17%
D.6 m
10%
E.8 m
👉የጠቅላላ ሁኔታ ኮንስተራክሽን ውል (General Condition of contract)
.
▶🚧የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ አንድ ህንፃ ተቌራጭ ስራውን ለማከናወን ወደ ኮንስትራክሽን ሳይት የሚያስገባቸው የህንፃ
ግብዓቶች ከኮንስትራክሽን ሳይት የማስወጣት መብቱ ምን ያህል
ነው ድረስ ነው?

▶አማካሪ/መሐንዲሱ/ ስራው አልቌል ብሎ እስካልተስማማ
ድረስ እቃ ወይም ሰራተኛ ለማመላለስ ከሚወጣ መኪና በስተቀር ማንኛውም ለፕሮጀክቱ የተመደበ የህንፃ ግብዓት ከኮንስትራክሽን ሳይት እንዳይወጣ በደብዳቤ መከልከል ይቻላል።
.
83. 🚧Ownership of plant and material
83.1 All equipment, temporary works, plant and materials provided by the Contractor shall,
when brought on the Site, be deemed to be exclusively intended for the execution of the works and the Contractor shall not remove the same or any part thereof, except for the purpose of moving it from
one part of the site to another, without the consent of the Engineer. Such consent shall, however, not be required for vehicles engaged in transporting any staff, labor, equipment, temporary works, plant or
materials to or from the Site.
@engineer03
🚧መያዥያ ገንዘብ (Retention money) vs
ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)???

1,ቅደመ ክፍያ (ADVANCE PAYMENT)
.
➡በልዩ ሁኔታ ለፕሮጀክቱ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል ቅድሚያ ክፍያ/advance payment/ የሚፈቅድ ከሆነ ስራ ተቌራጩ ስራውን ለማሰጀመር ማሽነሪ እና የግንባታ ግብአት ለማስገባት በሚጠየቅ ግዜ የሚከፈል ክፍያ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል
1) ቅድመ ክፍያው ስራ ተቋራጩን የሰራ ውሉን ተፈፃሚ የሚያደርግበትን የጠቅላላ ግምት ነው።
2)በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀው የኮንትራት ውል(Special condition of contract) የቅድሚያ ክፍያውን መጠን መግለፅ ሲኖርበት ነገር ግን ከጠቅላላ ፕሮጀክት ወጪ ሰላሳ (30%)ፐርሰንት መብለጥ የለበትም።
3) ውል ተፈፅሞ ፕሮጀክት ሳይት ርክክብ ሳይደረግ ቅድሚያ ክፍያ አይሰጠውም።
4) ስራ ተቋራጩ ለሚወስደው ክፍያ ዋስትና ቦንድ ሊያቀርብ ይገባል።

2,መያዥያ ገንዘብ (Retention money)
.
👉ስራ ተቋራጩ የተሰጠውን ስራውን ጨርሶ የስህተት ማስተካከያ ግዜ ድረስ/defect liability period / ሀላፊነት
ለመወጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን ከእያንዳንዱ የክፍያ ቅፅ የሚያዝ
ገንዘብ ነው።
▶ከክፍያ ቅፅ ምን ያህል ሊቆረጥበት እንደሚገባ ለፕሮጀክቱ በልዪ ሁኔታ የተዘጋጀው ውል/special condition of contract/በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል።
▶ሆኖም ከ አስር ፐርሰንት (10%) የበለጠ መሆን አይችልም።
▶በሀገራችን አብዛኛውን ግዜ አምስት ፐርሰንት(5%) ብቻ የተለመደ ነው።
ስራው እንደተጠናቀቀ ግማሹ ከመጨረሻ ክፍያ ጋር ቀሪው ደግሞ ከርክክብ በኋላ ስራው ላይ ስህተት ቢፈጠር በውሉ ላይ የማስተካከያ ቀነ ገደብ ሲጠናቀቅ ከመጨረሻ ርክክብ ጋር በ
አርባ አምስት (45) ቀናት ውስጥ ይለቀቅለታል።
.
🚩ለሁሉም እንዲዳረስ ፖስቶቹን SHARE አድርጉልን።
@engineer03
💬On sag (or valley) curves the available sight distance is determined based on :__________
Anonymous Quiz
11%
B.height of obstacle
47%
C.height of driver eye
11%
D.night-time driving conditions
Wish you have a nice night
@engineer03
@engineer03
@engineer03
🚧ስለሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) እና የጥገና/የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)

========== ===========
#የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (Retention Money/Bond) የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ የሚባለው በኮንስትራክሽን ውል አስተዳደር ወቅት ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ፈጽሞ ክፍያ በሚጠይቅበት ወቅት የፕሮጀክቱ ባለቤት ከግንባታው አማካሪ መሀንዲስ ጋር በመሆን ስለሥራው ጥራት ደረጃ በሚል ሊይዘው የሚችለው ዋስትና ነው፡፡
የሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ዓላማ የግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ሲባል ሥራ ተቋራጮች ለአሰሪዎች የሚገቡት ዋስትና ነው፡፡የግዥ መመሪያውም በአንቀጽ 28.5(ለ) ላይ በግልጽ እንደሚደነግገው በእያንዳንዱ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ 5(አምስት) ፐርሰንት የክፍያው ገንዘብ የሚያዝ ይሆናል፡፡
በዋናነት ከተያዘው ገንዘብ ውስጥ 50(ሃምሳ) ፐርሰንት የሚሆነው ገንዘብ ሥራው እንደ ተጠናቀቀ እና ጊዚያዊ የርክክብ ምስክር ወረቀት (provisional acceptance certificate) ከተሰጠ በኋላ ለሥራ ተቋራጩ ይመለስለታል፡፡ የቀረው ገንዘብ ደግሞ እስከ አንድ አመት ድረስ ዋቢ ሆኖ ይቆያል፡፡ ነገር ግን የተቀረው የመያዣ ገንዘብን አስቀድሞ ሥራ ተቋራጩ ለአንድ አመት የሚጸና ዋስትና ማቅረብ ከቻለ የተያዘበትን ቀሪ ገንዘብ ማስለቀቅ ይችላል፡፡
በተመሳሳይ መልኩም የሲቪል ሥራዎችን በተመለከተም እኤአ በ1994 ዓ.ም የወጣው የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ወጥ ውልም ስለ የዋና ገንዘብ መያዣ ዋስትና በአንቀጽ 59(5) እና 60 ላይ ተቀራራቢ ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል፡፡
BUT,,,,የሪቴንሽን ገንዘብ (retention) የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናቆ የጊዜያዊ እና የመጨረሻ ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ የተያዘው 5(አምስት) ፐርሰንት ገንዘብ አብዛኛውን ጊዜ ተመላሽ አይሆንም፡፡ በዚህ ሳቢያም ሥራ ተቋራጮች ለሌላ ወጪ የሚዳረጉበት ሁኔታ አለ፡፡////The law stipulates that the retention bond shall be paid to contractor after provisional acceptance or final acceptance but its applicability is denied by government side most of the time. So, dear contractors, please ask before you bankrupt///

#የጥገና ወይም የብልሽት አላፊነት መያዣ (Maintenance or Defect Liability Bond)
የጥገና ዋስትና የተበላሹ የግንባታ ግብዓቶችንና የሥራ አሰራር ግድፈቶችን ለመከላከል በሚል ሥራ ተቋራጩ ለፕሮጀክት ባለቤቱ የሚገባው ዋስትና ነው፡፡ በተለይም ከላይ ስለ ሪቴንሽን ገንዘብ/መያዣ (retention) ቆይታ እንደተመለከተው ለአንድ ዓመት ጊዜ የሚያዝበት ምክንያት ከጥራት ጉድለት ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመጠገን ነው፡፡ በሚለቀቅበትም ጊዜ ያለ ቅድመ ሁኔታ ዋስትና ሥራ ተቋራጩ እንዲያቀርብ የሚደረግበት ምክንያት በህንጻው ግንባታ ላይ የሚታዩ ግድፈቶችን ለመጠገን በሚል ነው፡፡
የጥገና እና ብልሽት አላፊነት መያዣ በዋናነት የዋና ገንዘብ መያዣ ቆይታ እንዳበቃ የሚጀምር ነው፡፡ በርግጥ ሥራ ተቋራጩ ለባለቤቱ ለተወሰኑ ዓመታት ዋቢ ይሆናል፡፡ለምሳሌ፡- በሲቪል የግንባታ ሥራዎች በተለይም በፍ/ህ/ቁ 3039 እንዲህ የሚል ይነበባል፡-“ሥራ ተቋራጩ ሥራውን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ ስለመልካም አሰራር፣ ስለ ሥራው እና ስለጠንካራነቱ ለ10 (አስር) አመት መድን (guarantee/ warranty) ነው፡፡ በዚህም ጊዜ ውስጥ በሥራው ጉድለት ወይም በተሰራበት መሬት ዓይነት ምክንያት በተሰራው ሥራ ላይ ለሚደርሰው መጥፋት ወይም መበላሸት አላፊ ነው፡፡”
በተመሳሳይ መልኩ የመንግስት የግንባታ ውሎችንም በተመለከተ የፍትሐብሔር ሕጉ ከአንቀጽ 3277-3282 ላይ የ10 (አስር) አመት የብልሽት መድን ጊዜ ያስቀምጣል፡፡
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በቅጽ 18 በሰ/መ/ቁ 101378 በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር መካከል በነበረው ክርክር የጥገና ዋስትና (maintenance bond) ሊኖር እንደሚችል ካተተ በኋላ አንድ ሥራ ተቋራጭ በሠራው ህንጻ ላይ የተከሠተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በሌለበት ሁኔታ ወደፊት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሊኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከልከል አግባብነት የሌለው መሆኑን እሰገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡

@engineer03
@engineer03
ወደ ጥያቄና መልስ ቻናል ይግቡ
🔑ለሁሉም ምሃንዲስ የሚጠቅም
🔆ለተማሪዎችም ሼር ያድርጉሏቸው
👇Click on the link 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFgM2PoIcCzAqQUoJw
https://t.me/joinchat/AAAAAFgM2PoIcCzAqQUoJw
https://t.me/joinchat/AAAAAFgM2PoIcCzAqQUoJw
📌Difference between working stress approach and limit state approach

🔸Working Stress Approach

➡️The service loads are used in the whole design and the strength of material is not utilized in the full extent.

➡️In this method of design, stresses acting on structural members are calculated based on elastic method and they are designed not to exceed certain allowable values.

➡️In fact, the whole structure during the life span may only experience loading stresses far below the ultimate state and that is the reason why this method is called working stress approach.

➡️Under such scenario, the most economical design can hardly be obtained by using working stress approach which is now commonly used in the design of temporary works.


🔸Limit State Approach

▶️For each material and load, a partial safety factor is assigned individually depending on the material properties and load properties.

▶️Therefore, each element of load and material properties is accurately assessed resulting in a more refined and accurate analysis of the structure.

▶️In this connection, the material strength can be utilized to its maximum value during its life span and loads can be assessed with reasonable probability of occurrence.

▶️Limit state approach is commonly used for the majority of reinforced concrete design because it ensures the utilization of material strength with the lowest construction cost input.

#ConstructionNotes

#Structure

@engineer03
Purpose of stirrup

1. It increases the compressive strength of the column (column is compressive member)

2. It can improve the ductility of column

3. Stirrups prevent the buckling of amin reinforcement bar

4. At the time of concreting it prevents the movement of main reinforcement

5. Improve dowel action of column reinforcement

6. In beams stirrups used for lump sum same purpose as in column

7. To provide lateral confinement of longitudinal bars

8. It provide resistance against shear and torsion

9. To hold longitudinal bars during construction

10. It confine the concrete in the core , thus improving ductility and strength

11. It prevents premature buckling of individual bars

👉🏿SHARE IT WITH YOUR FRIENDS

@engineer03
❤1
Say something engineer's about it.
👉@engineersWorks
➡Hydraulics and water supply Lecture @engineer03
.
👉ለዛሬ ደግሞ የ ላየኛው የምድር ውሃ (surface water) ለማጣራት የምንጠቀማቸው ዘዴዎች አዘጋጅተናል 👇
.
⓵ስክሪኒንግ (screening) - ይህ የመጀመረርያው የማጣራት
ደረጃ ሲሆን በዚህ የማጣራት ዘዴ ውስጥ በውሃው ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፍ አካላትን ለምሳሌ የዛፍ ጉቶ ፣ግንድ፣ ቅጠል እና ልዩ ልዩ የፕላስቲክ ተንሳፋፊ ቁሳቁሶች ወደ ዋናው የማጣሪያ ገንዳ እና ስርዓት
እንዳይገቡ ያግዳል ።
.
⓶ማርጋት (Coagulation )፦ በዚህ የማጣራት ደረጃ ላይ
ለአይን እይታ ያነሱ ጥቃቅን
አካላትን (Particle size 10^-7cm የሚሆኑ) በማርጋት እና
የኬሚካል ቻርጃቸውን ኒውትራላይዝ የሚያረግ ኬሚካል በመጨመር እርስ በእርሳቸው
እንዲሳሳቡ ማድረግ ነው ።
ለዚህ የአልሙኒየም ፖሊመሮች (Alum) እና አይረን (Fe+3)
አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
እንደ የቁልቋል ተክል ያሉ የተፈጥሮ አርጊዎች (coagulants) መጠቀምም ይቻላል
.
⓷ጉግለት (Flocculation)፦ ይህ እርከን ፤ ማርጋት
(coagulation ) ወቅት የረጉ ጥቃቅን አካላትን እርስ በእርሳቸው ቦንድ እስኪፈጥሩ እና እርስ በእርሳቸው ተጣብቀው እስኪጓግሉ ውሃው በተለያየ ፍጥነት የሚማሰልበት ነው።
ይህ ዘዴ ሜካኒካል ወይም ማኑዋል በሆነ መልኩ ይተገበራል።
.
⓸መዝቀጥ/ማዝቀጥ (sedimentation) ፦ በፍሎኩሌሽን ወቅት የጓጎለው ጥቃቅን አካላት በዚህን የማጣራት ደረጃ እንዲዘቅጡ ይደረጋል ። ይህ ዘዴ የሚተገበረው የሚጣራው የውሃን ፍጥነት በመቀነስ ግራቪቲን ተጠቅሞ እንዲዘቅጥ ማድረግ ነው።
በግራቪቲ ለማዝቀጥ የሚከብዱ እጅግ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን በፍሎኩሌሽን ወቅት ስንጠቀማቸው የነበሩ ኬሚካሎችን በመጠቀም እንዲዘቅጡ ይደረጋል።
.
⓹ ማጥራት (filtration ) ፦ በዚህ የማጥራት ደረጃ ከማዝቀጥ
ደረጃ ያለፉ ጥቃቅን ቆሻሻዎችን እጅግ ጥቃቅን ቀዳዳዎች ባሉት አካል (medium ) እንዲያልፍ በማድረግ የድፍረስነቱን መጠን እጅግ መቀነስ ነው።
.
⓺ማከም (Disinfection) ፦ ከላይ በተጠቀሱ የማጣሪያ ሂደቶች የተጣራው ውሃ
(በዋነኛነት ከተለያዩ ህይወት ከሌላቸው ጥቃቅን ቆሻሻዎች)
ለህብረተሰቡ ለአገልግሎት
ከመድረሱ በፊት በዚህ ሂደት (ዲስኢንፌክሽን) ማለፍ አለበት ።
ምክንያቱም ውሃው ለአገልግሎት የሚቀርበው ከተለያዩ በአይን ከማይታዩ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ነፃ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው ። ዲስኢንፌክሽን ውሃውን በማፍላት ፣ ሚካኒካል
በሆነ መልኩ ፣ ለጨረር በማጋለጥ (radiation ) እንደሁም በኬሚካል ሊከናወን ይችላል።
በሃገራችን በዋነኛነት
ሃሎጅኖችን (ብሮሚን ክሎሪን እና አይኦዲን ) በመጠቀም
ኬሚካል በመጠቀም ውሃን እናክማለን ።
፟
➡ከዚህ ሁሉ የማጣራት ሂደት በኋላ የተጣራው ውሃ ይጠራቀምና
ለተጠቃሚዎች ይዳረሳል።
.
▶ስለ surface waterን የማጣራት ሂደቶች ጥቂት የሆነ ገለፃን እንዳደረግንላችሁ ተስፋ
እናደርጋለን ። ርእሱ ሰፊ እንደመሆኑ ዳግመኛ በጥልቀት ለመዳሰስ ቃል እንገባለን✌
.
👇👇👇👇👇
Join for more updates via the link below;
t.me/engineer03
👆👆👆👆👆
⚡ አሁኑኑ Join በማረግ እና ለጓደኛዎ እና ለሚያቁት ሁሉ ሼር ያድርጉ።
#በኮንስትራክሽን_ውል_ጉዳይ_የክፍያ_ምስክር_ወረቀት(#PAYMENT_CERTIFICATE )
============== ============= ==================== ===================


የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ በአሰሪው በሚመደብ አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና በተቋራጩ ተረጋግጦና ተማምነውበት የሚፈረም ሲሆን ለተቋራጩ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠንም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡


(የክፍያ ምስክር ወረቀት ጋር ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪ አባሪ ተደርጐ ይያያዛል፡፡)
ቴክ ኦፍ ሽት የአሰሪው አማካሪ/ተቆጣጣሪ መሀንዲስ እና የተቋራጩ መሀንዲስ በግንባታ ቦታ በአካል የሳይት ቪዚት በማካሄድ የተሰራውን ስራ መጠን እና አይነት ከለቀሙ በኋላ በቢል ኦፍ ኳንቲቲ ከተመለከተው የእያንዳንዱ ስራ አይተም ዩኒት ሬት/ነጠላ ዋጋ አንጻር በዝርዝር በተናጠል በዋጋ የሚያስቀምጡበት የተሰራውን ስራ መጠን እና የገንዘብ መጠን ገላጭ ዝርዝር ሰነድ ነው፡፡
ግራንድ ሳመሪ ደግሞ በዋናነት የግንባታወችን ዝርዝር/ብሎክ በማስቀመጥ የውሉን ዋጋ፣አስቀድሞ የተከናወነ ስራ መጠን፣አሁን የተከናወነ ስራ መጠን እና አጠቃላይ በተቋራጩ የተሰራውን የግንባታ ስራ መጠን ይጠቅሳል፡፡


የክፍያ ሰርተፍኬት በአብዛኛው በአንድ ገጽ ተጠቃሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በይዘት ደረጃ ግን ብዙ መረጃወችን አምቆ የያዘ ሰነድ ነው፡፡
የክፍያ ሰርተፍኬት በተለይ ክፍያው የመጀመሪያ ዙር፣ሁለተኛ ዙር እያለ በሚታወቅበት መንገድ የሚዘጋጅ ሲሆን የመጨረሻ ዙር ክፍያ የሚባልም አለው፡፡
የመጀመሪያ ዙር ክፍያ የሚፈጸመው በአብዛኛው ከቅድሚያ ክፍያ በኋላ ሲሆን ክፍያውም ለተሰራ ስራ የሚፈጸም ነው፡፡


የመጨረሻ ዙር ክፍያ ደግሞ ግንባታው ተጠናቆ ጊዜአዊ ርክክብ/provisional acceptance/ ከተከናወነ በኋላ በህግ ከተቀመጡ ተቀናሾች በስተቀር ቀሪውን የስራ ክፍያ ጠቅልሎ አካቶ ወዲያውኑ በግንባታ ውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚፈጸም ክፍያ ነው፡፡
የክፍያ ሰርተፍኬት የፕሮጀክቱን ስም፣ቦታ፣አሰሪውን፣ተቋራጩን፣አማካሪውን ይጠቅሳል፡፡ ዋናውን የውል ገንዘብ መጠን፣ተቀጽላ ስራዎችን፣ቫሬሽንን እና የተከናወነውን የስራ መጠን ያመለክታል፡፡ውሉ የተደረገበትን ጊዜ እና ኮመንስመንት ዴት ይጠቁማል፡፡በተጨማሪም የቅድሚያ ክፍያ መጠን እና አድቫንስ ሪፔይ ያመለክታል፡፡በዚህም አስቀድሞ የነበሩ የክፍያ ቁጥሮችን ጭምር ይጠቁማል፡፡ እንደዚሁም የሪቴንሽን መጠን እና የቅጣት መረጃንም የሚሰጥ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን ሁሉ መረጃ በያዘ የክፍያ ሰርተፍኬት ላይ አሰሪው/ተቆጣጣሪው/አማካሪው እና ተቋራጩ የሚፈራረሙበት ይሆናል፡፡


ስለዚህ የክፍያ ሰርተፍኬት ጸደቀ ማለት በሰርተፍኬቱ ላይ የተመለከተው ስራ ስለመሰራቱ እና ዋጋውንም ጭምር አሰሪውና ተቋራጩ አምነውበታል ማለት ነው፡፡


((((እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የአሰሪው ዋና ግዴታ ለተቋራጩ በወቅቱ ክፍያ መፈጸም ነው፡፡))))

የፌዴራል ፕሮክዩርመንት ዳይሬክቲቭ ክሎስ 28.5 ላይ ስለኮንስትራክሽን ስራዎች ክፍያ እንዴት መፈጸም እንደሚገባው ይዘረዝራል፡፡


በዚህ ረገድ በተለይ ክሎስ 28.5(a) ላይ የተቀመጠው እንደሚያስገነዝበው በኮንስትራክሽን ስራዎች ጉዳይ ክፍያ የሚፈጸመው በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠና የጸደቀ የክፍያ ምስክር ወረቀት/payment certificate/ እንዲቀርብ በማድረግ መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
እንግዲህ የክፍያ ጥያቄ የሚያቀርብ በመጀመሪያ ተቋራጩ እንደመሆኑ አማካሪው/ተቆጣጣሪው መሀንዲስ የሳይት ቪዚት በማካሄድ የክፍያ ጥያቄውን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ የክፍያ ሰርተፍኬቱን፣ቴክ ኦፍ ሽት እና ግራንድ ሳመሪውን ጨምሮ የሚያጸድቅና አረጋግጦ የሚፈርምበት እና በማህተምም የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡


አማካሪው/ተቆጣጣሪው በተቋራጩ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት በ7(ሰባት) ቀናት ውስጥ የማረጋገጡን ስራ ማጠናቀቅ እንደሚገባው በዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(d) ላይ በአስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡


እንደዚሁም አሰሪው ደግሞ በአማካሪው/ተቆጣጣሪው የተረጋገጠ የክፍያ ሰርተፍኬት በደረሰው በ14(አስራ አራት) ቀናት ውስጥ ለተቋራጩ ክፍያውን መፈጸም እንደሚገባው በአስገዳጅ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡


እንግዲህ ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በእጁ ይዞ እያለ እና አሰሪውም ደርሶት እያለ ሳይከፍለው ያዘገየበት እንደሆነ በግንባታ ውሉ እና የውል አካል በሚያደርጉት ጀኔራል ኮንዲሽን በተመለከተው አግባብ ተቋራጩ ኪሳራ ከአሰሪው ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል ዳይሬክቲቩ ክሎስ 28.5(g) በግልጽ እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይደነግጋል፡፡


ፒፒኤ 2011 ክሎስ 59 እንደዚሁ የኮንስትራክሽን ጉዳይ የስራ ክፍያ የሚፈጸመው በክፍያ ሰርተፍኬት አማካይነት ስለመሆኑ ይገልጻል፡፡


በአጠቃላይ ከላይ የተመለከተው የክፍያ ሰርተፍኬት ባህሪ እና የህጉ ድንጋጌ የሚያስገነዝበው ተቋራጩ የክፍያ ሰርተፍኬት በአማካሪው/ተቆጣጣሪው እስከጸደቀለት ድረስ ያለምንም ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ክፍያ ሊፈጸምለት እንደሚገባ ነው፡፡


ጉባዔ አሰፋ (ጠበቃና የህግ አማካሪ,
https://t.me/engineer03
#የቅድሚያ_ክፍያ (#ADVANCE_PAYMENT)


በዚህ ፅሁፍ ቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው? አላማውስ? አቅራቢውና ተጠቃሚውስ ማን ነው? ያለባቸው ግዴታስ ምን ይመስላል? የሚሉትን ነጥቦች እንዳስሳለን፡፡


የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና በኮንስትራክሽን ዉሎች ከሚዘወተሩ የዋስትና አይነቶች አንዱና የተለመደዉ ነው፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ የቅድሚያ ክፍያ ምንድ ነው እሚለውን እንይ፡፡ በመንግስት ግዢ አዋጁ አንቀፅ 48 ላይ በመንግስት ገዥ አፈፃፀም ጊዚ አቅራቢዎች ከክፍያው ጋር እኩል የሆነ ዋስትና ሲያቅርቡ የቅድሚያ ክፍያ እንደሚስጥ ይገልፃል፡፡


ይህ የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ከጠቅላላው የውሉ ዋጋ ሰላሳ ፐርሰንት (30%) መበለጥ እንደለለበትና ሊከፈል የሚችለው የገንዘብ መጠንም በጨረታ መመሪያው ላይ መገለፅ እንደሚገባው የመንግስት ግዢ መመሪያ አንቀፅ 16.26.1 ያስገድዳል፡፡


ተዋዋይ ተቋራጮችም ይህንን የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ከማመለከቻ ጋር የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታዎች ያልተገደበ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሐገር ውስጥ ተቋራጮች ሲሆኑ በሁኔታዎች የተገደበ ዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የሚያቀርቡትም ዋስትና ከሚጠይቁት የቅድሚያ ክፍያ ገንዘብ ጋር እኩል መሆን አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በዋስትናው ምትክ ከመሰረታቸውና ከሚከታተላቸው ባለሰልጣን መስሪያ ቤት የሚያቀርቡት ደብዳቤ እንደ ዋስትና ተቀባይነት ይኖረዋል ሲል የመመሪያው አንቀፅ 16.20.5(ሐ) ይደነግጋል፡፡


ከዚህም በፊት ግን ተቋራጩ በግዢ ስነ-ስርዓቱ ያሸነፈውን ዉል መፈረምና የውል ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ዋስትና ያቀረበ መሆን አለበት (አዋጅ ቁ.649/2001፣ አንቀፅ 48/2/)፡፡


በአዋጁ አንቀፅ 78(3) መሰረት የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ አዋጁንና መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው መደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ [The Public Procurement Agency Standard Bidding Document: General Condition of Contracts: PPA-2011] ክሎስ 60(1) ላይ የቅድሚያ ክፍያው ለተቋራጩ መከፈል ያለበት ተቋራጩ ስራውን ለመጀመር የሚያወጣውን ወጪ ለመሸፈን እነዲረዳው ታስቦ ሲሆን ይህም የሚከፈለው ተቋራጩ ለግንባታ ስራው የሚያገለግሉ ማሽኖችን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን መግዛቱን ወይም ማዘዙን የሚያሳይ መረጃ ሲያቀርብ መሆኑን ያስቀምጣል፡፡ በስራው ጊዜያትም ገንዘቡን እነዚህን ዕቃዎችና ማሽኖችን ለመግዛትና ወደ ግንባታ ቦታው ለማንቀሳቀስ/ለማዘዋወር የተጠቀመበት መሆኑን የሚያሳይ ፋክቱር/Invoices ለኢንጂነሩ በማቅረብ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡


ከዚህ ጋር ተያይዞ በተጨባጭ የሚስተዋለው ችግር ቡዙ ጊዜ ተቋራጮች የቅድሚያ ክፍያውን ለታለመለት አላማ አያውሉም የሚል ሲሆን ይህም ችግር በተለይ በግንባታው ዘርፍ በተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ይህም ትልቁ ችግር መነሻው እነዚህ ተቋማት ምንም የሚያቅርቡት ዋስትና ሳይኖር ባቋቋማቸው መስሪያ ቤት ደብዳቤ ላይ ብቻ ተማምኖ ክፍያው ስለሚሰጣቸው ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ወይም በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ የኢንሹራንስ ዋስትና ያቀረቡ ተቋራጮችን አሰሪው/ተዋዋዩ የመንግስት አካል አስፈላጊ ሲሆን፡ የቅድሚያ ክፍያው ገቢ የሚደረግበትና ከውሉ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች ብቻ በመንግስትና በኢንተረፕራይዙ ወይም በኮንትራክተሩ ተወካዮች በጋራ ፊርማ ወጪ የሚደረግ የተለየ የባንክ አካውንት እንዲከፈት ሊያዝ ይችላል፤ ገንዘቡም ለታሰበለት አላማ ብቻ እንዲውል የተለየ ስምምነት መፈራረም አለበት፡፡


ስለዚህ የቅድሚያ ክፍያ ማለት ተቋራጩ ለስራው ማስጀመሪያ የሚሆኑትን የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች መግዢያነት የሚውል በአሰሪው የመንግስት መስሪያ ቤት በቅድሚያ የሚከፈለው ገንዘብ ነው፡፡ ይህም ምንም ስራ ሳይሰራ የሚከፈል ገንዘብ ስለሆነ ለተቋራጩ ዕዳ ወይም ብድር ነው፡፡ ስለሆነም ተቋራጩ ብድሩን እንዲምልስ ይገደዳል ማለት ነው፡፡


በመሆኑም ተቋራጩ ይህንን ብድር እንዴት ይመልሳል የሚለው አንዳንድ ጊዜ በግንባታ ውሎች ላይ አለመግባባት ያስነሳል፡፡ በግዢ መመሪያው አንቀፅ 16.26.9 ላይ እንደተገለፀው ለተቋራጮችና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተከፈለ የቅድሚያ ክፍያ በውሉ አፈፃፀም የተለያዩ ደረጃዎች ላይ በክፍያ ሰርተፍኬት ፀድቀው ከሚከፈሏቸው እያንዳንዱ ክፍያዎች ላይ እየተቀነሰ ሙሉ የቅድሚያ ክፍያው እስኪመልስ ድረስ የመንግስት መስሪያ ቤቱ ያስቅራል፡፡ ይህም ማለት ተቋራጩ የወሰደውን የቅድሚያ ክፍያ ሙሉውን ከአንድ ወይም ከሁለት ክፍያዎች ላይ የመክፈል ግዴታ የለበትም፡ አሰሪ መስሪያ ቤቱም ሙሉ ክፍያውን አንዴ ቀንሶ ማስቀረት አይችልም ማለት ነው፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አንዳድ ጊዜ ሙሉ ቅድሚያ ከፍያውን በአንዴ ቀንሰው በማስቀረት ከተቋራጮች ጋ እሰጣገባ ሲገጥሙ ይስተዋላል፡፡ ይህ ከህጉ አግባብ ውጭ ነው፡፡


የቅድሚያ ክፍያ ገንዘቡ ሙሉውን ሳይመለስ በተለያዩ ምክንያቶች ውሉ ቢቋረጥ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ የከፈለውን ገንዘብ ማስመለስ እንዲያስችለው ተቋራጩ የሚያቀርበው ዋስትና ክፍያው እስኪጠናቀቅ ድረስ አስገዳጅነት እንደሚኖውም መመሪያው ይገልፃል፡፡ ውሉ ቢቋረጥ እንኳን ያልተከፈለውን የቅድሚያ ክፍያ ዋስትናው ወዲያውኑ ካለምንመ መቃወሚያ እንዲከፍል ይገደዳል ይላል የመደበኛ የውል ሠነድ ጠቅላላ ሁኔታ ክሎስ 60.7፡፡


https://t.me/engineer03
Forwarded from Exam for Civil engineer's
💬The force in BF of the truss shown in given figure, is

A. 4t tension

B. 4t compression

C. 4.5t tension

D. 4.5t compression

E. zero.

For your answer and comments send here @engineersworks

Add your engineer's family
💬The cost of the earthwork in excavation for the surface drain of cross-section shown in the given figure for a total length of 5 metres @ Rs. 450% cum, is___________

A.Rs. 400

B.Rs. 425

C.Rs. 450

D.Rs. 500


For your solution, use @engineersworks
Civil Engineering
💬The cost of the earthwork in excavation for the surface drain of cross-section shown in the given figure for a total length of 5 metres @ Rs. 450% cum, is___________ A.Rs. 400 B.Rs. 425 C.Rs. 450 D.Rs. 500 For your solution, use @engineersworks
📝Solution

The length of drain = 5m.

Width of drain as per figure = 0.5m.
Depth of drain as per figure = 0.4m.

Total qty = 5 * 0.5 * 0.4 = 1 cum.

As per the question, cum excavation rate is 450%.

So the total cost required for excavation of drain is = 1 * 450 = Rs.450.

Therefore, the answer is "C."