ET Netsa Apps™
23.8K subscribers
3.27K photos
476 videos
261 files
2.64K links
ET Netsa Apps™ is the premier choice and destination for anyone seeking knowledge and information about latest airdrops technology and online courses.
CA: EQAz_XrD0hA4cqlprWkpS7TIAhCG4CknAfob1VQm-2mBf5Vl

Buy ads: https://telega.io/c/ET_Apps
Download Telegram
🚨 Important Update for Ethiopian Traders 🚨

📢 Bybit has officially announced the removal of Ethiopian Birr (ETB) from its P2P Trading Platform starting July 21, 2025, at 10:00 AM UTC.

What You Need to Know: ✅ ETB trading pairs will be delisted from P2P. ✅ All ETB advertisements will be removed. ✅ Ongoing appeals/disputes will continue until fully resolved.

⚠️ Action Required: 👉 Please close your ETB orders and finalize any pending trades before the deadline. 👉 Contact Bybit Customer Support if you have any questions.

📆 Deadline: July 21, 2025

Let's stay informed and manage our trades wisely.

#CryptoNews #BybitUpdate #EthiopiaCrypto #ETB #P2PTrading
😢9❤7😁2
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
የክሪፕቶ ሀብትህ የሞት ሽረት ጉዳይ ሲሆን…

በክሪፕቶ አለም ውስጥ ከ"ራግፑል" (Rugpull) የባሰ ነገር መጥቷል።

ሰዎች እየታገቱ ነው። እየተሰቃዩ ነው። እየተገደሉ ነው።

አብዛኞቹም ልክ አሁን አብዛኛዎቹ ትሬደር ነኝ ባይ ኢንፍሉዌንሰሮች እየሰሩት ያለውን ስህተት ሰርተው ነው ለዚህ የበቁት።


በግሌ የክሪፕቶ ሀብትህን ኦንላይን በኩራት ማሳየት እንደመጨረሻ የሞኝነት ተግባር ቆጣሪ ነኝ። በዚህ የማታምን ከሆነ ምናልባት እንደገና ልታስብበት ይገባል።

ወንጀለኞች ነቅተዋል — በፊት ለዝናና ለእይታ የሚደረግ ፉከራ፣ አለፍ ሲልም ሌሎችን ለገበያቸው ለመሳብ ሲሉ በሌላቸው ነገር የሚጋጋጡበት የማርኬቲንግ ስትራቴጂ: አሁን ግን በጀርባቸው ላይ ቀይ የጥቃት ኢላማ እንደመሳል ሆኗል።

ለዲጂታል ሀብትህ የሚሰነዘሩ እውነተኛና አካላዊ ጥቃቶች አሁን የተለመዱ ሆነዋል።

🔖ጨዋታው ተቀይሯል
ጉዳዩ የምስጢር ቁልፎችን (seed phrases) ስለመጠበቅ ብቻ አይደለም። የክሪፕቶ መስራቾች እና ትሬደሮች የዋሌቶቻቸውን ቁጥጥር ለማስረከብ ሲሉ ብቻ ለእገታ፣ ለድብደባና ለከፋ ስቃይ እየተዳረጉ ነው። ይህ አልፎ አልፎ የሚከሰት ሳይሆን፣ አለም አቀፋዊ እና ወቅታዊ ክስተት ሆኗል።(አያይዤ የለጠፍኩትን ምስል ሹፉት)

🔖ከፓሪስ የተገኘ የማስጠንቀቂያ ታሪክ
ሶስት ጭምብል ያጠለቁ ወንጀለኞች የፔይሚየም (Paymium™) ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚን ልጅና የልጅ ልጅ ለማገት ሞክረው ነበር — ሊያውም በሀሰተኛ ሽጉጥና በአይን የሚያቃጥል ስፕሬይ ታግዘውና በጠራራ ፀሀይ። የአካባቢው ሰዎች በጊዜ ደርሰው ባይገላግሏቸው ኖሮ ታሪኩ ሌላ ነበር። ጥቃቱ እንዲሁ በዘፈቀደ የተፈጸመ አልነበረም፤ ፖሊስ እንዳረጋገጠው "አላማቸው የዋሌቱን ቁልፎች መውሰድ ነበር።"

🔖የሌጀር (Ledger) መስራች ዴቪድ ባላንድ የኖረው ቅዠት
ይህ በክሪፕቶ ዓለም ከሚታወቁ ግለሰቦችና ከፊት ከሚሰለፉት መካከል የሆነ ኢንተርፕረነር በፈረንጆቹ ጥር ወር ታግቶ ነበር። አጋቾቹ በቪዲዮ ካሜራ ፊት €10 ሚሊዮን ዶላር በUSDT እንዲከፍላቸው እየጠየቁ አንዷን ጣቱን ቆርጠውታል። ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ዋሌቱ ቢታገድም፣ እሱ ግን በህይወት ሊተርፍ ችሏል። ይህ ግን ነጠላ ክስተት አይደለም — እየተስፋፋ የመጣ የወንጀል ስልት አካል ነው።

🔖ከታይላንድ እስከ ካሊፎርኒያ — በየትኛውም ቦታ
🇹🇭 ታይላንድ፡ ቻይናዊ ባለሀብት ለ$500,000 ዶላር ክሪፕቶ እስኪበቃው መሠቃየቱን አይተናል።
🇨🇦 ቶሮንቶ፡ ጥንዶች የNFT ትርፋቸውን ኦንላይን ከለጠፉ በኋላ በጦር መሳሪያ በታገዘ መልኩ ተዘርፈዋል።
🇺🇸 ካሊፎርኒያ፡ አንድ ትሬደር ከኤርፖርት ጀምሮ ተከታትሎ $1.3 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፏል።
🇬🇧 ለንደን፡ በቢትኮይን ማይኒንግ ስራ ላይ በተሳተፈ ኢንቨስተር ቤት በሀይል ገብተው $800,000 ዶላር ሰርቀዋል።

ይህ ተራ ስርቆት አይደለም። የተደራጀ: አካላዊ እና አሰቃቂ የክሪፕቶ ወንጀል ነው።

🔖ማህበራዊ ሚዲያ — የወንጀለኞች ማደኛ መጫወቻ ሜዳ
አብዛኞቹ ተጠቂዎች አንድ የጋራ "ገዳይ" ስህተት ነበራቸው — የክሪፕቶ ሀብታቸውን ኦንላይን ያሳዩ ነበር።🙈😁 በፊት የጉራ ምንጭ የነበረው ነገር: አሁን ለወንጀለኞች ጥሪ ማድረጊያ መብራት ሆኗል።

"ጉዳዩ የዋሌት ብቻ አይደለም። የህይወት ጉዳይ ነው!"
— ቴይለር ሞናሃን、 የሜታማስክ (MetaMask) የደህንነት ሃላፊ



🔖የመረጃ መፍሰስ (Data Leaks) ስጋቱን አባብሶታል
ከሌጀር (Ledger) እስከ ኮይንቤዝ (Coinbase) እና ክሮል (Kroll) ያሉ ኩባንያዎች ላይ የደረሰው የመረጃ ፍሰትና ስርቆት: ለወንጀለኞች የተዘጋጀ የተጠቂዎች ዝርዝር ሰጥቷቸዋል።

ስምህን ያውቃሉ።
ያለህን የሀብት መጠን ያውቃሉ።
አድራሻህንም ያውቃሉ።


አሁን በተራ የኢሜል ማስመሰል (phishing) አያጠቁህም — በአካል ቤትህ ድረስ "ከች" ይሉልሀል።😀

ይኸው ነው . . . 🤷‍♂️🙇‍♂️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤18🕊1🏆1
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
እንዴት አደርክ ብሮስኪ: ዝምብለህ እመነኝና . . .

ያለህበት ከጠፋህ: ውስጥህ የሚወደውን ነገር ተምረህ በደንብ አዳብረው:
ተምሬያለው ብለህ የምታስብ ከሆነ ደግሞ ተግብረው:
ተግብረኸውም መልስ ካጣህ: ሳትታክት ደጋግመው።


በፋይናንሱም: በአስተሳሰቡም: በንቃተ-ህሊናውም . . . በሁሉም በምታስበው መስክ የስኬትህ ቁልፍ ያለው አንተ እራስሁ ውስጥ ነው . . . ፈልገው።✌️

ወጧ በቂቤ የሆነላትን ማክሰኚት በያላችሁበት 🙏

💚💛❤
❤15🔥9😁1
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
🔖Reminder 🕯

Never let negative thoughts consume you. They are not you. They only have power if you feed them.


ለታየው የሰው ልጅ ጭንቅላት የዚች ምድር ገዢ እና የፈጣሪ ባለአደራ ነው። ሀይልና ችሎታው: ሊነካ የሚችለው የማድረግ ብቃትና ችሮታው ከምናስበውም ከምናልመው በላይ ነው።

በአጭሩ . . . Rule it Or be Ruled.

💚💛❤
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8❤‍🔥1🔥1
Forwarded from ETN Learn™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
ለዛሬ ይዘነው የነበረው የክሪፕቶከረንሲ ትምህርት በተለያዩ የቴክኒካል ጉዳዮች ምክንያት ወደ4 ሰዓት የተላለፈ በመሆኑ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የቀጥታ መድረክ ስርጭታችን የምንጀምር ይሆናል።

በዛሬው ትምህርታችን የክሪፕቶከረንሲዎችን አገበያየት ከፎሬክስ ትሬዲንግ የሚለይባቸውን እና በጣም አብዛኛው የክሪፕቶ ትሬደር ቦታ የማይሰጣቸው ነገር ግን ከስነልቦናዊ ሁነት ቀጥሎ ከቴክኒካልም ሆነ ከፈንዳመንታል አናሊስስም ጭምር በላይ የክሪፕቶ ግብይቶቻንን ጥቅም በመስጠት እና እስትንፋስ በመሆን ስኬታማ ሊያደርግልን ስለሚችለው የኦንቼይን አናሊስስ የምንማማር ይሆናል። እንደተለመደው የመማማር ሂደታችን ለጀማሪያንም ምቹ ይሆን ዘንድ የመማማሪያ መዘውራችን የBabypips ዌብሳይት ላይ የተመሰረተ ይሆናል። የቀጥታ መድረኩ በ @cryptotalk_et ኦፊሴላዊ የቴሌግራም ገፅ በኩል የሚደረግ ይሆናል።

ETN-LEARN.
❤3
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
GM Gs...🙏

Invest in your mind, body, and soul.

Because when the system collapses and the noise fades, all distractions will be stripped away leaving you alone with yourself.

And most won’t be able to cope with what they find.

💚💛❤
❤9❤‍🔥1
በባይቢት የp2p ጉዳይ አሁን ከመሸ ከባይቢት የአፍሪካ ተወካይ የደረሰኝን መረጃ ለማካፈል ያህል:

Bybit™ የP2P ግብይት በአገሪቱ ህገወጥ እንደመሆኑ እና በቅርቡም የኢትዮጵያ መንግስት ከመሰል ጉዳዮች ጋር እያደረገ በነበረው እንቅስቃሴ ተባባሪ ለመሆን እንደሆነ ጠቁመውኛል። ተያይዞም ተጠቃሚዎች የኢትዮጵያ ብርን በመጠቀም በፕላትፎርሙ ላይ ከኢትዮጵያ ባንክ እና መሠል የፋይናንስ ተቋማት ጋር የተያያዘ አገልግሎት ማግኘት አይችሉ እንጂ ትሬድ ማድረግ መቀጠል እንደሚችሉ አያይዘው ገልፀዋል።

በስተመጨረሻም የጊዜ ሂደት እንጂ ይህ ጉዳይ በናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካም ከዚህ ቀደም የገጠማቸው የነበረና አገራቱ ነባራዊ ሁነቱን እና የኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎቻቸውን በማጤን አገሮቻቸው በማይጎዱበት መልኩ ህግ አውጥተው ያስቀጠሉት መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያም አሁን እያሳየች ካለው ክፍት የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር በአጭር ጊዜ ውስጥ በህግ ማእቀፍ ስር ሰዎች አገልግሎትን ማግኘት የሚቀጥሉበት መንገድ እንደሚኖር ተስፋቸው እንደሆነ ገልፆውልኛል።

🙏✌️

🏦😍
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤14👍6😢4
Forwarded from CryptoTalk-Ethiopia™🇪🇹 (Nathnael Biruk)
☀️እንዴት አደራችሁ ጋይስ፡

🔖ምናልባት ለቀጣዩ የቡል አካሄድ ከጠቀማችሁእስካሁን በነበሩት ታሪካዊ የቡል ማርኬቶች የነበረው የገበያ ባህሪ ይደገማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ይታወቃል። በዚህም የካፒታል ፍሰቱን ለመመልከት ያህል ፡

These is where money flows.


በመጀመሪያ ከ70ሺህ ዶላር ጀምሮ የነበረው ወደቢትኮይን ይደረግ የነበረው የካፒታል ፍሰት አለ፤ ከዛ ቢትኮይን ጤናማ የሆነ ኮሬክሽን ማድረግ ሲጀምር ካፒታል ወደ ዋና ዋና የሚባሉ አልትኮይኖች ይዞራል፤ ከዛ ከፍ ያለ ግምት ወደሚሰጣቸው የሜም ኮይኖች ናሬቲቩ ይቀየራል፤ ቢትኮይን ቀጣይ ረዘም ያለ ጉዞውን ይቀጥል ዘንድ ካፒታል ተመልሶ ወደቢትኮይን ይመለሳል። ምናልባትም ከዚያ በኋላ ከበድ ያለ bear market ይጠበቃል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤10
Forwarded from ኮርማ™ Signals. (Nathnael Biruk)
#Bitcoin💸 ከ #ጉግል: #ኢንስታግራም: #አማዞን: #ቪዛ: #ዎልማርት: #ኮካ-ኮላ: #ማክዶናልድስ: #ኔትፍሊክስ: #ዲዝኒ: #ሄርሜስ: #ቴስላ . . . ከእነዚህ ሁሉ ግዙፍ እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የበለጠ የገበያ ዋጋ ለመያዝ ከተመሠረተ 15 ዓመታትን: ዓለም በይፋና በዋና ዋና መገናኛ ብዙሀን ከተዋወቀው ደግሞ አራት እና አምስት አመታትን ብቻ አስቆጥሮ መሆኑን ስታስቡት ነገ ላይ ሊኖረው ስለሚችለው አቅም ካሁኑ መረዳት የሚያስችል በር ይከፍትልናል።

KORMA™
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥7❤1
Forwarded from ETN-DAILY™
🔖ታላቅ የፖሊሲ ለውጥ፡ የአሜሪካ ባንኮች አሁን ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶዎችን ለደንበኞች መያዝ ይችላሉ!

በፋይናንስ ዓለም ውስጥ ታሪክ ተሰርቷል!

የአሜሪካው ማዕከላዊ ባንክ (Federal Reserve) እና ሌሎች የገንዘብ ተቆጣጣሪ ተቋማት (OCC እና FDIC)፣ ባንኮች የደንበኞቻቸውን ቢትኮይን እና ሌሎች ዲጂታል ሀብቶችን እንዲይዙ የሚያስችል ታሪካዊ መመሪያ አውጥተዋል። ይህ ማለት ባህላዊው የባንክ ስርዓት ለክሪፕቶ በሩን በይፋ ከፍቷል ማለት ነው።

📌ውሳኔው ሁለት ዋና ዋና አማራጮችን ያቀርባል፦

✔️በአደራ ማስቀመጥ ብቻ (Non-fiduciary): በዚህ አማራጭ መሰረት ባንኮች ምንም አይነት የማስተዳደር ኃላፊነት ሳይወስዱ፣ ልክ እንደ ካዝና (vault) የእርስዎን ቢትኮይን ወይም ሌላ ክሪፕቶ በከፍተኛ ደህንነት ይጠብቁልዎታል። ዋናው ትኩረት ደህንነት ላይ ብቻ ነው።
✔️በሙሉ ኃላፊነት ማስተዳደር (Fiduciary): እዚህ ላይ ባንኩ ሙሉ የባለአደራነት ኃላፊነት ወስዶ፣ ልክ እንደማንኛውም ንብረት (ለምሳሌ ቤት ወይም አክሲዮን) የክሪፕቶ ሀብትዎን ያስተዳድርልዎታል። ይህ ለኢንቨስትመንት አማካሪነት፣ ለውርስ አፈጻጸም እና ለሌሎችም የንብረት አስተዳደር አገልግሎቶች በር ይከፍታል።

❓ይህ ውሳኔ ለእኛ በኢትዮጵያ ላለነው ምን ማለት ነው?
ይህ ዜና የአሜሪካን የባንክ ስርዓት ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራትም ትልቅ አንድምታ አለው።
⭐️እውቅና መስጠት፡ ክሪፕቶን እንደ እውነተኛ እና ህጋዊ የሀብት አይነት (asset class) እውቅና እንዲያገኝ ያደርጋል። ይህ ትልቁ እርምጃ ነው።
⭐️የወደፊት ተስፋ፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ ማዕከላዊ ባንኮች ወደፊት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ መንገድ ሊጠርግ ይችላል።
⭐️ደህንነትና አመኔታ፡ የባንኮች መግባት፣ ብዙ ሰዎች በክሪፕቶ ላይ ያላቸውን ስጋት በመቀነስ አመኔታን ይፈጥራል።

🔔በአጭሩ፣ ባህላዊውን የገንዘብ ስርዓት (TradFi) እና የክሪፕቶውን ዓለም (DeFi) የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ተሰርቷል። ይህ ለዓለም አቀፉ የክሪፕቶ ማህበረሰብ ታላቅ ድል ሲሆን፣ ወደፊት ምን ሊከተል እንደሚችል በጉጉት እንጠብቃለን!

#Bitcoin #Crypto #Ethiopia #Banking #FederalReserve #NBE #AmharicCrypto #ቢትኮይን #ክሪፕቶ #ኢትዮጵያ #ባንክ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤9🕊2🔥1
Off-Topic...

አሁን አሁን እዚች አገር ላይ መኖር በራሱ cvአችን ውስጥ መካተት ያለበት ጉዳይ ሆኖ መቷል። It's a skill bruh. ማለት በ2 እና 3ሺ ብር ደሞዝ የሚኖሩ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎችን ሳይ ችግራቸውን ማየት በራሱ ህመም ቢሆንም ከችግራቸው አልፎ የሚታየኝ ግን እንዴት እና እንዴት አርገው ወር ላይ እንደሚደርሱ ነው።

በያላችሁበት በርቱልኝ: አደራ ችግር በደጃፋችሁ እያለፈ እንኳን ቢሆን እስኪያለፍ ቢያለፋ እንጂ ማለፉ አይቀሬ ነውና በርቱልኝ።።

መልካም ቀን በያላችሁበት። 🙏✌️

💚💛❤
❤22🔥8👍3😁2
Forwarded from ኮርማ™ Signals. (Nathnael Biruk)
Those who entered #ETH on July 3 for a mid term position, you can take a portion of your partial profit since we are way much higher than we anticipated in the time frame that we get the profit. በተረፈ ለረጅም ጊዜ እቅድ የያዛችሁት ያው ሙሉ ታርጌታችን ገና ስለሆነ መያዝ የምትችሉ ይሆናል። Btw zoom in, watch the pips amount and take the lesson about patience. 🙏🏾✌🏾
🔥7🏆2❤1🕊1
Forwarded from ኮርማ™ Signals. (Nathnael Biruk)
FIAT VS BITCOIN

THE DIFFERENCE IS VISIBLE.
❤3🔥2
😍የዛሬ አመት 10 ሺህ ብር አውጥቶ የ$ETN ኮይኖችን የገዛ ግለሰብ ዛሬ ላይ በ300ሺህ ብር በመጠኑ ያገለገለ ባጃጅ መግዛት ይችል እንደነበር ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?!
ከአንድ አመት በኋላ የራይድ መኪና መግዣ ፈጣሪ ካለለትም ከዚያ በላይ ሊሆነው እንደሚችል እምነታችን ነው።😄

🏅ከመሬት የተነሳችው እና እዚሁ እናንተው ያዋለዳቹሀት #እቴኑ ዛሬ ላይ አንድ የአሜሪካን ሳንቲም ወይም ወደአንድ ብር ከሀምሳ ገደማ እየተሸጠች ትገኛለች። (30X since listing.)

🔖የፖስቱ ቁምነገር :
1. Limited supply always makes the product a KING in the market. (Like we have seen it above in both Bitcoin's and ETN's scenarios.
2. ብዙዎች ቢንቋትም ከየትኛውም የፈረንጆቹ ክሪፕቶ በላይ
$ETN ባሳለፈችው አንድ አመት ከታሰበላት መነሻ 30 እጥፍ አንፀባርቃለች። God willing it will Ccontinue shinning too.

ይኸው ነው።🙏✌️
💚💛❤

@Buy_ETN_bot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥7❤5
Forwarded from ኮርማ™ Signals. (Nathnael Biruk)
ቡልማርኬቱ የአልት ሲዝንን ከፊቱ አስቀድሞ እያኮበበ ይገኛል። ለመሆኑ በዚህ ከፍተኛ የእድገት ግስጋሴ ለመሳተፍ ራሳችሁን አዘጋጅታቹሀል?

የክሪፕቶ ማርኬት አጠቃላይ የገበያ ካፒታል መጠን ከምንጊዜውም ከፍተኛ ዋጋው በላይ በማስመዝገብ ከ4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በዛሬው ለት ገበያው ላይ ሲዘዋወር ለማስተዋል ተችሏል።

ከትላንት በስትያ ለማስታወስ እንደሞከርነው የቡልራኑ ለረጅም ጊዜ የሰዎችን ትእግስት ሲፈትን ከቆየ በኋላ እነሆ የመጨረሻ የሚባሉትን ምልክቶቹን እያሳየ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም መካከል አሁን በቅርብ ሰአታት ለመታዘብ የቻልነውን እና በአጠቃላይ የሳይክል አካሄዱ ከቢትኮይን የመጀመሪያ መተኮስ በኋላ ከፍ ያለ እንቅስቃሴ የሚያሳየው ኢትሪየም መሆኑን በገለፅነው መሰረት ኢቲሪየም ከ3600 ዶላር በላይ የገበያ ዋጋን በማስመዝገበ ጥንካሬውን ያዘለቀ ሲሆን ቢትኮይን በበኩሉ በተወሰነ ደረጃ ብዙም ባይባል ወደ 117500 አካባቢ ድረስ የወረደበትን ሁነት ለማየት ችለናል።

በዚህ ሁነት የቢትኮይን ዋጋ በጣም ቀስ እያለ እስከ 111ሺህ አጋማሽ የገበያ ዋጋ እርከን ድረስ ጤናማ ኮሬክሺን ሊያሳይ የሚችል ከሆነና እንደኢቲሪየም እና ሪፕል የመሳሰሉት ከቢትኮይን ቀጥሎ በጥንካሬያቸው የሚታወቁ አልት ኮይኖች የገንዘብ ፍሰታቸውን አስጠብቀው መቀጠል የሚችሉ ከሆነ የመጀመሪያው የአልት ሲዝን እንቅስቃሴ እንደተጀመረና ሁላችንም በተቻለ ለግብይት የሚሆኑንን የተወሰነ ካፒታል ብናዘጋጅ የሚል ምክርም ለመለገስ እንወዳለን። ምንም እንኳን ኮርሳቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎች ይህንን የኮርማ አናሊስስ በግርድፉ ያለአጋዥ መስማት ባይኖርባቸውም በተቻለ የራሳቸውን ሀላፊነት በመውሰድ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ከሚል እሳቤ ገበያው እያየነው ከሚያመልጠን ጠንካራ የሚባሉ የመግዛት እድሎችን ሳይ ከአሁን በኋላ በቋሚነት የግዢ ጥሪዎችን ከነአናሊስሳቸው የምናደርግላችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ለጊዜው ያለው አገልግሎታችን በተወሰነ መልኩ በነፃ በቴክኒካል አናላሲስ ቻናላችን በኩል የሚቀጥል ቢሆንም በዘላቂነት የተሟላውን አገልግሎት ለማግኘት ግን የባይቢት የፓርትነርሺፕ ሪፈራል ኮዳችንን በመጠቀም አዲስ አካውንት መክፈት እንደሚኖርባችሁ ለማስታወስ እንወዳለን።
የባይቢት የሪፈራል መመዝገቢያ ሊንክ ፡ https://partner.bybit.com/b/132421

Stay Tuned.
KORMA.
❤8
የዛሬው ምሽት የቀጥታ መድረክ ዝግጅታችን ለጀማሪ የፎሬክስ ትሬደሮች የተዘጋጀ ሲሆን በዋነኝነት በተለይ ኢትዮጵያውያን ትሬደሮች ባለማወቅም ይሁን በተለያዩ አዋቂ ነን ባይ ሜንቶሮች ቦታ ስለማይሰጣቸው እንደፓተርን ምስረታዎች፤ ትሬዲንግ ሳይኮሎጂ እና የመሳሰሉት ባይተዋር የትሬዲጉ አለም እሳቤዎች የምናነሳ ይሆናል። ምናልባት ፕሮግራሙ ለጀማሪዎች የተዘጋጀ ቢሆንም ለመማርም ሆነ ልምዳችሁን ለማካፈል ይረዳ ዘንድ ልምድ ያላችሁ ቤተሰቦችም በፕሮግራሙ ላይ ትገኙ ዘንድ ተጋብዛቹሀል።

We are live.
https://t.me/cryptotalk_et?livestream
❤2👍1🙏1