ብቃት ተኮር ትምህርትን /competency-based learning) ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
------------------- // -----------------
(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) የብቃት ተኮር ትምህርትን ወደ ተግባር ለማስገባት ከጃፓን ዮቶሃማ ዩኒቨርስቲ የመጡ ፕሮፌሰሮች በሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ አጋርተዋል።
የሂሳብ፣ የሳይንስና ስነ ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ ተገኝተው በሥርዓተ ትምህርቱ መሠረት ብቃት ተኮር ትምህርትን (competency-based learning) ወደ ተግባር ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ይህንንም እውን ለማድረግ ከጃፓን ዓለም ከቀፍ ትብብር ድርጅት/ JICA / ጋር በመተባበር ከዮቶሃማ ዩኒቨርስቲ በመጡ የሙያው ፕሮፌሰሮች ከ5 ክልሎችና ከፌዴራል STEAM ዴስክ ለተውጣጡ 15 ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው የተሰጠውን ስልጠና ለማስፋትም የስልጠና ሞጁሎች ተዘጋጅተው በተመረጡ የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ስልጠና መሰጠቱንም የዴስክ ኃላፊው አቶ ታደሰ አብራርተዋል።
የጃፓን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር/JICA/ የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ተወካይ ሚስተር ያኩሺ ሂሮዩኪ በበኩላቸው ጃይካ በኢትዮጵያ ትምህርት ዘርፍ በተለይም በሂሳብ እና የሳይንስ ትምህርት የተማሪዎች ውጤት መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/14VqGkTKzCz/

የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
--------------------- // ---------------------
(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ትምህርት ሚኒስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ያስገነባው የአማሮ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት ተመርቋል።
ትምህርት ቤቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ተገኝተው መርቀውታል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ባስተላለፉት መልዕክት ይህ ዛሬ የተመረቀው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደ ሀገር ትምህርትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የምናደርገው ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል።
ከለውጡ ወዲህ እንደ በፊቱ የመሠረት ድጋይ አስቀምጦ መሄድ ቀርቷል ያሉ ሲሆን በትምህርት ሴክተሩ ፕሮጀክት ጀምሮ በአጠረ ጊዜ መጨረስ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰዋል።
የትምህርት ሴክተሩ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት ውስጥ ወድቆ በመቆየቱ ከዚህ ለማላቀቅ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት እየተተገበሩ መሆኑንና በተለይም ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ መስራትና መተማመን የሚችል ትውልድ ለመፍጠር እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Di1oWZQG5/

ኢትዮጵያ የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ።
----------------------------- // ----------------------
(የካቲት 20/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 130ኛውን የአድዋ ድል በዓልን '' አድዋ 130፣ ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል አገራዊ መሪ ቃል አክብረዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አድዋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ህያው ተምሳሌት በመሆኑ አባቶቻችንና እናቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነትና ላጎናጸፉን ድል ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
ትምህርት ለምናደርገው የእድገትና የብልጽግና ጉዞ ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ጅምር ስራዎቻችንን አልቆ በመፈጸም እንደሚገባ ክብርት ሚኒስትር ደኤታ አስገንዝበዋል።
አገራችን ለዜጎቿ የተመቸችና የልማት ተምሳሌት ወደምትሆንበት ደረጃ ለመውሰድ የትምህርት ዘርፉ ተዋናዮች የበኩላቸውን ድርሻ በላቀ የአገር ፍቅርና ስሜት መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም ክብርት ወ/ሮ አየለች አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17wXtv3gJt/

የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ በዓለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በተመለከተ መረጃ ለማግኘት https://rb.gy/lspeey
በትምህርት ዘርፉ ሁሉም ዜጎች እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ገለፁ።
--------------------- // -----------------------
(የካቲት 21/2018 ዓ.ም) በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ አሞራቴ ከተማ የተገነባው የአሞራቴ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፤ ተጨማሪ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት እቅድ ተይዟል።
በትምህርት ሚኒስቴርና በሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት የተገነባውን ትምህርት ቤት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ መርቀውታል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ዘርፉ ሁሉም ዜጎች አኩል የትምህርት እድል እንዲያገኙ ለማስቻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህ ዛሬ በዳሰነች የተመረቀው አዳሪ ትምህርት ቤት አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ የራሱን ሥራ ሲሰራ ልጆቹ ተረጋግተው የሚማሩበትን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል።
እነሱን ሳናስተምር ይች ሀገር ለሁላችንም እኩል ነች ማለት ከባድ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የዚህ ትምህርት ቤት መገንባት ትልቅ ደስታን እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CHREwWwgs/

የተረጋጋ ሀገር እንዲኖር በትምህርት ዘርፉ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ያስፈልጋል፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
-------------------- // -----------------------
(የካቲት 22/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዳሰነች ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመረቁበት ወቅት በትምህርት አቅርቦት ረገድ በሁሉም አካባቢ ምንም ልዩነት ሊፈጠር አይገባም ብለዋል።
ይህንንም ለማረጋገጥም በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝም አብራርተዋል ።
በተለይም ምቹ የመማሪያ ከባቢን በሁሉም አካባቢ ለመፍጠር “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንና የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገና መደረጉን አንስተዋል።
አክለውም የትምህርት ስራ የሚለወጠው ከታች ጀምሮ ሲሰራ መሆኑን በማመን በከተማና በባለሀብቶች ብቻ ታጥሮ የቆየውን የቅድመ አንደኛ ትምህርት በመቀየር በሁሉም አካባቢ ያለ ልዩነት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ጠቅሰዋል።
በዚህም ባለፉት ዓመታት ከ34 ሺ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማና በገጠር ተገንብተው የአምስተና ስድስት ዓመት ህፃናት እየተማሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ትምህርት ለሁሉ ነገር ወሳኝ በመሆኑ ልጆቻችንን በአግባቡ በማስተማር የአለምን ፈተና መቋቋም የሚችሉ ጠንካራ ሀገር ተረካቢዎችን ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/18FMt7JKvz/