Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ ተጠየቀ ።
------------------ // ------------------

(የካቲት 06/2018 ዓ.ም) በቅርቡ አዲስ የተመደቡ የቦርድ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ተረድተው ወደ ተግባር እንዲገቡ የሚያስችል የሥራ ትውውቅና መመሪያ ተሰጥቷል።

በመድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርስቲ አመራሮች የተጣለባቸውን አገራዊ አደራ ለመወጣት የተመደቡበት ተቋም ተልዕኮና የሥራ ድርሻ በውል መረዳት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም አመራሩ የተሰጠውን የሥራ ኃላፊነት በጥልቀት አውቆና ተረድቶ መስራቱ ለተቋሙ ስኬት መሰረታዊ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀትና የምርምር ማዕከል በመሆናቸው አመራሩ ግልጽ ራዕይ ይዞ መንቀሳቀሱ የተቋማዊ ለውጥ (Reform) ስራዎችን በብቃት ለመምራትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርምና መደበኛ ስራዎችን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል።

አዳዲሶቹ አመራሮች የተሰጣቸውን መመሪያ መሰረት በማድረግ ወደ ስራ ሲሰማሩ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ ካለው ሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ ጋር በማጣጣም መከወን እንደሚገባቸውም አቅጣጫ ተቀምጧል።
በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ለአይነ ስውራን የተዘጋጁ የ2ኛ ደረጃ የብሬል መጽሐፍት እየተጓጓዙ ነው።
------------------------ // --------------------------
‎
‎(የካቲት 09/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በመጀመሪያው ዙር ለስርጭት የተዘጋጁ የብሬል መጽሀፍቱን የስርጭት ሂደት ተመልክተዋል።
‎
‎ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ የመጽሐፍቱን ስርጭት ሂደት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ጥራት፣አግባብነት ፣ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋጥ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል ብለዋል።
‎
‎ከሪፎርም ስራዎች መካከልም የተሻሻለውን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መነሻ በማድረግ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ ተግባራዊ መደረጉን ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል።
‎
‎ተግባራዊ በተደረገው ሥርዓተ ትምህርት መሠረትም ተማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉባቸውን የመማሪያና የማስተማሪያ መጽሀፍት አንድ ለአንድ ለማድረስ ሲሰራ መቆየቱንም ክብርት ወ/ሮ አየለች ተናግረዋል።
‎
‎ሁሉም ዜጎች የመማርና የመማሪያ ግብዓቶችን ማግኘት መብት እንዳላቸው ያስገነዘቡት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ዜጎች በሁሉም ረገድ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1LN6njN6Dp/
ሴቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርትና ምርምር በመሳብ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ቅንጅትና ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተመላከተ።

-------------------- // ----------------------
‎
‎(የካቲት 09/2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሴት ተመራማሪዎች ቀን በአዲስ አበባ ተከብሯል። በበዓሉ ላይ ተገኝተው መለዕክት ያስለላለፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የሴት ተመራማሪዎች ቁጥር እድገት እያስመዘገበ መምጣቱን ጠቅሰው ሴቶችን በማብቃትና ወደ አመራር እንዲመጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‌‎የሴቶች በሳይንስ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎና የአመራርነት ሚና እንዲጎለብት በቅንጅት የተጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
‎
‎የሴት ተመራማሪዎች ማህበር መፈጠር ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ክብርት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል።

‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው አንድ ተቋም ብቻውን የሴቶችን የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ አይችልም ብለዋል።
‎
‎ሴቶች በሳይንስ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ውስጥ ያላቸው ተሳትፎና አመራር እንዲጎለብት የሁሉም ተሳትፎና ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BdiAm2D7P/
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ።

-------------------------- // ---------------------------

(የካቲት 10/2018 ዓ.ም) የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዬት ደምሴ ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደተናገሩት በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የትምህርት ቢሮው የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ ከትምህርት ሚኒስቴር በወረደው ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ንቅናቄ መሰረት የማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorials) እየሰጠ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ለዚህም ስራ ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን አስታውቀዋል።

ይህ በጀት ከመንግስት ፣ ከልማት ማህበራት እና ከባለሀብቶች የተሰባሰበ ሲሆን የተመረጡ መምህራን እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተውጣጡ መምህራን በማጠናከሪያ ትምህርቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉን አንስተዋል።


በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ወደ 20 በመቶ ለማድረስ ግብ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮ ሃላፊው ጠቁመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በትምህርት አመራሩ ላይ መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን አዳዲስ መመሪያዎችና ደንቦች ተዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባታቸውን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/179VmHHrT7/
የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ፕሮግራምና ስርዓተ-ትምህርት ከኢንዱስትሪው ጋር የተቆራኘ ተግባር ተኮር ዕውቀትና ክህሎት ያለው ባለሙያ ማፍራት በሚያስችል መልኩ እተቃኘ መሆኑ ተገለጸ።

------------------------- // --------------------------

‎(የካቲት 10/2018 ዓ.ም) በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ከኢንዱስትሪው ጋር የተቆራኘ መካከለኛ ባለሙያ እንዲያፈሩ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርስቲዎች ተግባር ተኮር ዕውቀትና ክህሎት ያለው መካከለኛ ባለሙያ እንዲያፈሩ መደረጉ ለአገር እድገት ትልቅ እድል እንደሚፈጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል።
‎
‎በትምህርት ዘርፉ የሪፎርም ዩኒቨርስቲዎቹ በተልዕኮና ትኩረት መስካቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ መደረጉንና ልዩ ልዩ ሰነዶች፣ ፍኖተ ካርታዎችና የትግበራ እቅዶች መዘጋጀታቸውን የገለጹት ዶ/ር ኤባ ዩኒቨርስቲዎቹ በትኩረት መስኮቻቸው ላይ የበለጠ አትኩረው እንዲሰሩ የትኩረትና ተልዕኮ መስክ ማስፈጸሚያ የስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ማዕቀፍ እንዲዘጋጅ መደረጉን ተናግረዋል።
‎
‎በዚህም በተዘጋጀው የስርዓተ ትምህርትና ፕሮግራሞች ማዕቀፍ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰብስቦ የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
‎
‎የምርምር (research) እና አጠቃላይ (Comprehensive) ዩኒቨርስቲዎች ፕሮግራምና ስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍም በባለድርሻ አካላት ግብዓት ተሰጥቶበት ለውሳኔ ዝግጁ መሆኑን ዶ/ር ኤባ ጨምረው ተናግረዋል።
የ2018 ዓም የ12ኛ ክፍል አገር ከቀፍ ፈተና በክልሉ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ እንደሚሰጥ የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ።
------------------------- // ----------------------------

‎(የካቲት 11/2018 ዓ.ም) የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ እንደገለጹት የ2018 ዓም የ12ኛ ክፍል አገረ አቀፍ ፈተና ከ2ሺ 400 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናው በበይነ መረብ ይሰጣል።
‎
‎በክልሉ በወረቀት የሚሰጥ የ12ኛ ክፍል ፈተና የለም ያሉት ኃላፊው በክልሉ በገጠርና በከተማ የሚገኙ 18 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ፈተናውን በኦንላይን እንደሚያስፈትኑ ተናግረዋል።
‎
‎ተማሪዎች ከወዲሁ የበይነ-መረብ ፈተናውን እንዲለማመዱ የቴሌግራም ቻናል ተከፍቶላቸው በየቡድናቸው ጥያቄዎች እየተላኩላቸው በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
‎
‎በክልሉ ባለፈው ዓመት በወረቀት ከተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ይልቅ በበይነ መረብ በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ማምጣታቸውንና ይህም የተማሪዎችን የማለፍ ምጣኔ ከፍ እንዳደረገው አቶ ጌቱ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1AzpUcRN6A/
እንደ ሀገር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽ ባልሆነባቸው ወረዳዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የትምህርት ቤት ግንባታ ለማካሄድ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል።

-------------------------- // --------------------------

(የካቲት 16/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለሟሟላትና ለማሻሻል በቀረጸው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።

በተለይም ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ትኩረት በመስጠት እና በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ነጻና የግዴታ ትምህርት እንዲሆን በማመላከት ከ34000 በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛል።

ባለፉት ዓመታት እነዚህ ትምህርት ቤቶች ቢገነቡም የነበረውን ክፍተት በሚፈለገው ልክ መሙላት ባለመቻሉ በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፤ ይንንም ለመቅረፍና ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

በዚህም ‎ትምህርት ቤቶቹን ለመገንባት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽ ያልሆነባቸው አካባቢዎችና የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ወረዳዎች ልየታ መደረጉም ተገልጿል።

በነዚህ በተለዩ ወረዳዎች ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ትምህርት ሚኒስቴር በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጋፍ ስርዓት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ግንባታውን ለማከናወን አቅዶ እየሰራ መሆኑም ተመላክቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/18GP5FGeFV/