Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ትምህርት የአገር አድገትም ሆነ ውድቀት ነጸብራቅ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።


---------------------------- // --------------------------

‎
‎ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም) የትምህርቱ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተተኞች በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና በቀጣይ ዓመት እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል።

‎
‎የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ትምህርት የአገር አድገትም ሆነ ውድቀት ነጸብራቅ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል።

‎
‎ባለፉት 5 ዓመታት ለትምህርት ጥራት መሠረት የሚጥሉ ቁልፍና አበይት ተግባራት መከናወናቸውንም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

‎
‎ከተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች መካከልም የሥርዓተ ትምህርት ለውጥና የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ማሻሻል በተለይም ደረጃቸውን የጠበቁ የቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታና እድሳት ሥራ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

‎
‎በተለይም የወደፊቱ መሪዎችና ሳይንቲስቶች የሚፈሩባቸው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ክልሎች የመገንባትና የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ አመላክተዋል።

‎
‎የሁለተኛ ደረጃ መጻህፍትን 1ለ1 ከማዳረስ በተጨማሪም ክልሎችን በመደገፍ የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም የመማሪያ መጽሀፍ በማሳተም ድጋፍ እየተደረገ መሆኑም ጨመረው ገልጸዋል።

‎
‎በትምህርት ቤት ምገባ ባለፉተ አምስት ዓመታት በተሰራው ሥራ የተማሪዎች ምገባ አቅም 8.9 ሚሊዮን ማድረስ መቻሉን ገልጸው በቀጣይም ትኩረት ሊሰራ የሚገባ መሆኑን ተመላክቷል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/shar
ባለፉት ዓመታት በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የትምህርት ተገቢነት፣ ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል ፦ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

-------------------------------- // ----------------------------


(ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ በ2018 የትምህርት ዘመን የእቅድ አፈጻጸምና በ2019 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።


‎መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ትምህርት የሀገራትን እድገትና ብልጽግና የሚወስን መሣሪያ መሆኑን አስገንዝበዋል።

‎
‎ባለፉት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራት፣ ፍትሐዊነትንና ተገቢነት ለማረጋገጥ በርካታ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን ክብርት ወ/ሮ አየለች አብራርተዋል።

‎
‎በአዲሱ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መነሻ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ እና የትምህርትና ሥልጠና ብቃት ማእቀፍ ሥርዓት ተዘርግቶ እንዲተገበር መደረጉን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/14neyAsGhbE/
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናወኑ።

--------------------------- // -----------------------------

‎
‎(ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት እያካሄዱ ከሚገኘው የምክክር መድረክ ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ለአካባቢ ጥበቃና ዘላቂ ልማት ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል።

‎
‎መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ COP 32 ልዩ ተልዕኮ ለትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በቢሾፍቱ የፍጥነት መንገድ በተሰጠው 6.2 ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ ተከላው ተከናውኗል።
‎
‎የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ለ8ኛ ዙር በምታካሂደው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ የትምህርት ዘርፉም የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

‎
‎ልዩ ተልዕኮ በተሰጠው የCOP 32 የአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀምበር እንደ ሀገር ለሚካሄደው መርሃ ግብር ችግኝ የማዘጋጀት፣ ጉድጓድ የመቆፈር እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰዋል።

‎
‎እንዲሁም ለተከላ የተዘጋጁት ችግኞች ለአካባቢ ጥበቃ ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ በተጨማሪ፣ የፍራፍሬና ሌሎች ተጠቃሚ ችግኞችን በማካተት ለአርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1AfcDPFCoD/
እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት መላክ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።
 
-------------------------- // ------------------------
 

(ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም) የ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ የትምህርት ንቅናቄ ሰነድ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎበታል።


በመድረኩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለች እሸቴ እንደገለጹት፣ በአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ መሠረት ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ማድረግ የመንግሥትና የማኅበረሰቡ የጋራ ኃላፊነት ነው።


በመሆኑም ሕብረተሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እንዲሁም በተለያዩ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ የነበሩ ተማሪዎች እንደገና ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል።


በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ሁሉም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናትን እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችን በሙሉ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ በማድረግ ረገድ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/19JdkqUhkP/