የቡኢ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በፍጥነት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ።
----------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም) የቡኢ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል በሚያስችል ሁኔታ በፍጥነትና በትኩረት እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት የተመራ ልዑክ የትምህርት ቤቱ የግንባታ ሥራ የደረሰበትን ወቅታዊ ደረጃ በቦታው በመገኘት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የሕንጻዎቹ የግንባታ ሂደት በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቱ በ2019 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ እንዲሆን ከሥራ ተቋራጩ ጋር በቀሪ ሥራዎችና በማጠናቀቂያ ሂደት ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል።
በተጨማሪም ከግንባታው ጎን ለጎን ትምህርት ቤቱን ለማስጀመር የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል ምልመላና ምደባ ጨምሮ ሁሉንም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከመስከረም 2019 ዓ.ም በፊት ለማጠናቀቅ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፣ የቡኢ ከተማ ከንቲባ፣ የሥራ ተቋራጩ ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል። ተሳታፊዎቹም ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅና ትምህርት ቤቱ በወቅቱ ተማሪዎችን እንዲቀበል የየድርሻቸውን ኃላፊነት በሙሉ እንደሚወጡ ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BkueAVRCc/

ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር በነባርና አዲስ ትምህርት በሚጀመርባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንና ርዕሳነ መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። በመሆኑም መፈርቱን የምታሟሉ በሙሉ በበየነ መረብ ባልችሁበት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገልጽን
በመምህርነት መመዝገብ ለምትፈልጉ በ https://sbs.moe.gov.et/career/teacher
በርዕሰ መመህርነት ለመመዝገብ የምትፈልጉ https://sbs.moe.gov.et/directors መጠቀም የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።

በኢትዮጵያ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፤
የትምህርት ሚኒስቴር ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርትን ለማጠናከርና ጥራቱን ለማሻሻል የተዘጋጀውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ለማስገባት ቴክኒካል ሥራዎች በጋራ እየተሰሩ ነው።
---------------------------- // ----------------
(ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም) በፕሮጀክቱ ትውውቅ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የመምህራንን ሙያዊ ብቃት ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት በተማሪዎች የወደፊት ትምህርታዊና ሙያዊ እድገት ላይ ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ተማሪዎች በመንግሥትም ሆነ በግል ትምህርት ቤቶች በእኩል ዕድል የቋንቋውን ክህሎት እንዲያገኙ ማድረግ ቀዳሚ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
በተጨማሪም፣ በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ፈጣን ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራንን አቅም የመገንባት፣ የማስተማር ብቃታቸውን የማጎልበትና ውጤታማነታቸውን የማረጋገጥ ሥራዎች በተጠናከረ ሁኔታ ማከናወን እንደሚገባ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች በበኩላቸው፣ ትምህርት ከማንኛውም ኢንቨስትመንት በላይ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ ቁልፍ ዘርፍ መሆኑን ገልጸው፣ የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን በቀጣይነት እንደሚደግፍ አስታውቀዋ። ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://www.facebook.com/share/p/1HUucXCCag/

በክረምት መርሃ ግብር ለመማር ለተመረጣችሁ መምህራን በሙሉ
ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተናበበ የሥልጠና ማዕቀፍ፣ ፕሮግራሙን ለመምራት የሚያስችሉ የትግበራ ሰነዶችንና የሰልጣኝ መምህራንን ምልመላ፣ መረጣ እና ምደባ ተከናውነዋል።
ስለሆነም ባለፉት አመታት በስልጠናው አሰጣጥ ጥራት ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመምህራን የክረምት የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በዚህ ክረምት ለማስጀመር ስምንት ዩኒቨርሲቲዎች ተለይተዋል። እነዚህም ባህር ዳር ፣ ሀዋሳ ፣ መቀሌ ፣ ጂማ ፣ ሃሮማያ ፣ ጎንደር ፣ አርባ ምንጭ እና ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ በ2018 ዓ.ም ክረምት 8273 መምህራንን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
በዚህ መሰረት የመግቢያ ምዘና ወስዳችሁ ያለፋችሁ እና በየዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ሰልጣኝ መምህራን ምዝገባው ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን በተጠቀሱት ቀናት በየተመደባችሁባቸው ዩኒቨርስቲዎች በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ለማዎቅ ይህንን https://shorturl.at/ZjN9e ማስፈንጠሪያ በመጫን ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የኢንተርፕረነርሽፕ ስራ ፈጠራ ስልጠናዎችን ማስፋፋት የትምህርት ጥራትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ፤
------------------------- // ------------------------
(ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት የኢንተርፕረነርሽፕ ስራ ፈጠራ ስልጠናን ማስፋፋት የትምህርት ጥራትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ ያስችላል።
የኢንተርፕረነርሽፕ የስራ ፈጠራ ምሩቃንን ስራ ፈላጊና ቅጥር ጠባቂ ሳይሆኑ የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩና ለሌሎችም የስራ እድል እንዲከፍቱ እድል እንደሚሰጥ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኢንተርፕርነርሽፕ የስራ ፈጠራ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሀሳቦችን በማዳበር ምሩቃን በየአካባቢያቸው ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የመፍቻ እድል አድርገው እንዲያዩና መፍትሄ እንዲያፈልቁ ማገዝ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል።
የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሰን ሑሴን በበኩላቸው ኢኒስቲትዩቱ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢንተርፕረነርሽፕ ስራ ፈጠራን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለማዝለቅና አደረጃጀትን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢንተርፕርነርሽፕ ስራ ፈጠራን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማዋሃዱ የሚካሄደው ተግባር ለማጠናከርም ተቋማቱ በላቀ ቅንጅትና ትብብር መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ሐሰን ተናግረዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://tw

በትግራይ ክልል በወረቀት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።
------------------------ // --------------------------
(ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም) የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላት ፈተናቸውን በወረቅት እየወሰዱ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ እየተሰጠ የሚገኘውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በመፈተኛ ማዕከላሉ ተገኝተው የተመለከቱት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) አሁን ላይ መንግሥት ያደረገውን ርብርብ ተከትሎ በትግራይ ብሄራዊ ክልል የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በየመፈተኛ ማዕከላቱ ተገኝተው ፈተናቸውን መውሰድ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በአክሱም፣ በመቀሌና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲዎች ከ15 ሺ በላይ ተማሪዎች በወረቀት የሚሰጠውን ፈተና በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በክልሉ በሚገኙ በአራቱም ዩኒቨርስቲዎች በበይነ መረብ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል።
በዛሬው እለትም በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች ተገኝተው አገር አቀፍ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፈተናውን ተረጋግተው እንዲወስዱና መልካም እድል እንዲገጥማቸውም ሚኒስተር ዴኤታው ተመኝተዋል።
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው የፈተናው መጀመር በክልሉ የሚገኙ ወጣቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቃና እና ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችል መሆኑን አንስተዋል።
ለፈተናው ስኬት አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ በማከናወን ተማሪዎቹ ያለምንም እንግልትና ስጋት ፈተናቸውን እንዲወስዱ የጸጥታና የፈተና አሰተባባሪዎች የተቀናጀ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝም አብራር