Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
ትምህርት ሚኒስትሩ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀመሩ
 
-------------------------- // -----------------------------

(ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ወጪ በድሬዳዋ ከተማ የሚገነባውን የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በይፋ አስጀምረዋል።

በዚሁ ጊዜ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት የተሻለ የትምህርት ጥራትና የላቀ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር በመላ ሀገሪቱ የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸውን የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ አካባቢዎች እየገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም፣ ዛሬ ግንባታው የተጀመረው ትምህርት ቤትም ከመላው ሀገሪቱ በብቃታቸው የተመረጡ ተማሪዎችን በመቀበል የሚያስተምር ሲሆን፣ ግንባታው በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን የማስፋፋት ሥራ በቀጣይነት እንደሚቀጥል ገልጸው፣ በባህርዳር፣ አርባምንጭ እና አሶሳ ተመሳሳይ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ለከተማዋ እድገትና ለትውልድ ግንባታ እያደረገ ላለው አስፈላጊ ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸው፣ የከተማ አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤  https://web.facebook.com/share/p/1PuiqKwBrR/
በትምህርት ዘርፉ ከተወሰዱ የሪፎርም ተግባራት ዋናውና ወሳኙ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነት ላይ እየተሰራ ያለው ሥራ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
 
---------------------- // ------------------------
 
(ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር በድሬዳዋ ከተማ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
 
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለሕፃናት የመማር መሠረትን የሚጥል በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራሽነቱን ለማስፋፋት ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ነው።
 
በተለይም በትምህርት ሪፎርሙ ማዕቀፍ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ፍትሃዊና ጥራት ያለው የመማር ዕድል ለመፍጠር የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታና ማስፋፊያ ሥራዎች ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ መሆን ጠቅሰዋል።
 
ክቡር ከንቲባ ከድር ጀዋር በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በከተማው ያለውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ፍላጎት ለማሟላትና የሕፃናትን የመማር ዕድል ለማስፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18Xc4aqgiL/
ሁሉም መሠረተ ልማት የተሟሉላቸው ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተገነቡ ይገኛሉ።
 
---------------------- // ---------------------
 
(ሰኔ 18/2018 ዓ.ም) በዚህ መሠረት፣ በዛሬው ዕለት በትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ወጪ የሚገነባው የድሬዳዋ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሥራ በይፋ ተጀምሯል።
 
የግንባታ ሥራውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጀዋር በጋራ አስጀምረውታል።
 
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ በሀገሪቱ የትምህርት ሪፎርም ጉዞ ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚኖረው ሲሆን እንደ ሀገር 50 ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
 
የድሬዳዋ ሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ሲጠናቀቅ ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎች፣ የሳይንስ ላቦራቶሪዎች፣ የኮምፒውተር ማዕከላት፣ የስፖርትና የመዝናኛ ጨምሮ የተሟላ የትምህርት አካባቢ የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል።
 
በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ በአካባቢው ያለውን የተማሪ ክፍል ጥምርታ ለማሻሻል፣ ለተማሪዎች የተሻለ የመማሪያ አካባቢ ለመፍጠር እና የትምህርት ጥራትን በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል እንደሚሆንም ገልፀዋል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18tBtY9TRj/
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ከአካባቢ ልማትና ጸጋ ጋር የተያያዘ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።
 
----------------------------- // -----------------------------
‎
‎(ሰኔ 19/2018 ዓ.ም) የቡሌሆራና ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲዎች በማዕድንና ነዳጅ ላይ አትኩሮ ከሚሰራው የኦስትሪያው ሊዮቤን ዩኒቨርስቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የዩኒቨርስቲዎች የተልዕኮና የትኩረት መስክ ልየታ ከአካባቢ የልማት ጸጋ ጋር የተያያዙ እንዲሆን እየተሰራ ነው።
‎
‎ የትኩረት መስክን ከተፈጥሮ ፀጋ ጋር ማያያዝ ሀብት፣ ጊዜና አቅምን በአግባቡ በመጠቀም ውጤታማ አንደሚያደርግም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
‎
‎የቡሌሆራና የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲዎች   የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነትም በመምህራን ልማትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የዩኒቨርስቲ ኢንዲስትሪ ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያስችል ተናግረዋል ።
‎
‎የቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ ከሊዮቤን ዩኒቨስቲ እና ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ስምምነት መፈራረሙን ጠቅሰው ይህም በማዕድን ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተሻለ ተፎካካሪ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል።
‎
‎የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርስቲም ከሊዮቤን ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ጋር የተፈራረመው ስምምነት ዩኒቨርስቲው በአገር ውስጥ ብዙም ባልዳበረው የነዳጅና ኤነርጂ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆን ያግዘዋል ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1E2Y46YHWQ/
የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አሳሰቡ።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 በበይነ መረብና በወረቀት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ተካሂዷል።

             -------------------------- // -----------------------

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፈተና ስርቆትን የሚጠየፍ ትውልድ በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡

በተለይም በፈተና ሂደት ወቅት ፈተና ለመስረቅም ይሁን ለማሰረቅ የሚሞክሩ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ለፈተናው ስኬታማነት ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ 


የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው የፈተናው አጠቃላይ ሂደት ደህንነቱ የተጠበቀ በሰላምና በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ በተባበረ አግባብና በተቀናጀ ሁኔታ መሰራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡


የዘንድሮ የ12ኛ ክል ብሄራዊ ፈተና ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል በአብዛኛው በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑና የፈተና ተቋማቱ በርከት ባለ ሁኔታ በክልል ደረጃ የተደራጁ መሆናቸው ልዩ እንደሚያርገውም ገልጸዋል፡፡


በመሆኑም የፈተናውን ደህንነቱን የማረጋገጥ ጉዳይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያፈልግ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ አየለች አስገንዝበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HCE2Y1BwH/
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።
**************

የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ዙሮች በስኬት እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

አገልግሎቱ እንዳመለከተው፣ ፈተናው በበይነ መረብ (ኦንላይን) መሰጠት የጀመረ ሲሆን፣ ተፈታኞች በስድስት ዙሮች ተከፋፍለው በተሳካ ሁኔታ ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ ብሏል።

ሆኖም የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፒውተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናውን በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14 ሺህ 755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ ይገኛል።

በሌላ በኩል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15 ሺህ 325 የክልሉ ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ተመላክቷል።

እነዚህ በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎች ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ መቐለ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት፣ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ገለጻ (ኦሬንቴሽን) በመከታተል ፈተናቸውን መውሰድ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጨምሮ ገልጿል።