በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ።
በሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ በ2017 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች እውቅናና ሽልማት አበርክቷል።
-------------------- // ----------------------
(መስከረም 09/2018 ዓ.ም) በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት ትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሀረሪ ክልል በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተመዘገበው 22 በመቶ ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቁመው ክልሉ ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር በትምህርት ዘርፉ የሰራና የለፋ ብቻ ውጤት የሚያገኝበት ሥርዓት እየተዘረጋ መጥቷል ያሉት ሚኒስትሩ ዛሬ የተሸለማችሁ በአቋራጭ ሳይሆን በስራና በድካም ያገኛችሁት ውጤት በመሆኑ ልትኮሩ ይገባችኋል ብለዋል።
በቀጣዩ የ2018 የትምህርት ዘመንም የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና በክልሉ ሙሉ በመሉ ከወረቀት ነፃ በሆነ መልኩ በኦላይን ለመስጠት ከክልሉ አመራር ጋር መግባባት መደረሱንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
በመሆኑም በክልሉ አሁን በተገኘው ውጤት መዘናጋት ሳይኖር የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም ይሄ ትውልድ የሥራ ትውልድ፣ በራሱ የሚኮራ ትውልድ እንዲሆን እንደ ሀገር የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
በዕውቅናና ሽልማት መርሀ-ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ማስታወቂያ
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ፡-
1. የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫችሁ ውስጥ ማካተት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
2. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑ እናሳውቃለን።

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ያለፋችሁ እና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ መስከረም 16/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።

ለፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት መምህርነት የተመዘገባችሁ መምህራን እና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ፤
ለፈተና የተመረጣችሁ ዝርዝራችሁን በተጠቀሰው ሊንክ፤
ለመምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/career/check-status
ለር/መምህራን፤ https://sbs.moe.gov.et/directors/check-status
በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የፈተና ቀን ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል።
ትምህርት ሚኒስቴር

sbs.moe.gov.et
MoE | Ethiopia Boarding Schools Admission
Ethiopia Boarding Schools Admission System
በትምህርት ሪፎርሙ የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል የተወሰዱ እርምጃዎች እና ከታች ጀምሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ስራዎች
በሀገራችን የትምህርት ምዘናና ፈተና አስተዳደር ሥርዓቱን ለማስተካከል ከተወሰዱት እርምጃዎች አንዱ በትምህርት ፖሊሲው የተቀመጠውን አንድ ተማሪ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ወይም እርከን ለመሸጋገር ቢያን 50 ከመቶና በላይ አማካይ ውጤት ማስመስመዝገብ አለበት በሚል የተደነገገውን የማስጠበቅ ጉዳይ ነው። በዚህም በሪፎርሙ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችም ይሁኑ በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ሲያመጡ ወደ ሚቀጥለው ክፍል/እርከን እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ተማሪዎች 50 ከመቶ በታች አማካይ ውጤት አምጥተው ወደ ሚቀጥለው ክፍል እንዲዛወዱ ወይም በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ይደረግ እንደነበር የሚታወስ ነው። አሁን ባለው አሰራር ይህንን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በየትኛውም የክፍል ደረጃ 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያላመጣ ተማሪ ወደ ቀጣዩ ክፍል ወይም እርከን አይዛወርም።
በተጨማሪም በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች በነዚህ ፈተናዎች 50 በመቶና በላይ አማካይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል እንዲዛወሩ እየተደረገ ይገኛል። ይህም በየደረጃው የትምህርት ጥራቱ ያለበትን ደረጃ እየለኩ ለመሄድ ትልቅ አስተዋጻኦ ይኖረዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/17CF2bPKAt/

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የተዘመገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።
------------------------//------------------------------
(መስከረም 23/2018 ዓ.ም) በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ያመለከቱ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተናቸውን በኦላይን በ52 የመፈተኛ ማዕከላት እየወሰዱ ይገኛል።
ትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስና ቴክኖሎጂ የበቁ የነገ የዚች ሀገር መሪ መሆን የሚችሉ ዜጎችን ለማፍራት እያስገነባቸው ካሉ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስቱን በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ሥራ ለማስጀመር የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።
እነዚህ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም አካባበዎች የሚመጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው፣ አብሮ መኖርና ማደግን የሚለምዱባቸውና እየተቀየረ ያለውን የአለም ሁኔታ ሊሸከሙ የሚችሉ በሁሉም ዘርፍ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ተወዳዳሪ ልጆችን ማፍራት የሚያስችሉ ናቸው
ሙሉ ዜናውን ለማግኘት https://web.facebook.com/share/p/17BorJ7evN/
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et
ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/@MinistryofEducationEthiopia

ማስታወቂያ፤
ትምህርት ሚኒስቴር በፌደራል ደረጃ ለተቋቋሙ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዳይሬክተርነት ለመወዳደር የተመዘገባችሁና እና ለፈተና የተመረጣችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፤
ፈተና የሚሰጠው ሀሙስ መስከረም 29/2018 ዓ.ም ሲሆን በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በትምህርት ሚኒስቴር 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እያሳዎቅን ለፈተና ስትመጡ፤
ሙሉ የትምህርት ማስረጃ ኦርጂናል እና ኮፒ፣
ልዩ የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የአንድ አመት ልዩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ስራ ላይ ስልጠና ሰርትፍኬት፣
የሙያ ፍቃድ እና እድሳት ሰርትፍኬት፣
በትምህርት ቤት አመራርነት ተገቢነት ያለው የስራ ልምድ ማስረጃ የሚገልጽ ደብዳቤ መያዝ የሚያስፈልግ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።