በሳለፍነው ዓመት መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት ስጥቶ መስራቱን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ ገልጹ።
--------------------------- // ---------------------------
(መስከረም 26/2018 ዓ.ም) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የ2018 ዓ.ም የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ባዳርጉት ንግግር ባለፈው ዓመት መንግስት ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት ስጥቶ መስራቱ ተናግረዋል።
በትውልዶች ውስጥ የሚስተዋለው የእሴት መሸርሸር ዋናውና መነሻው የትምህርት ጥራት ችግር እንደሆነ መንግስት እንደሚያመን አንስተው ይህንን ሳንካ ለመቅረፍ ባለፈው ዓመት በትምህርት ጥራት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ገልጸዋል።
በተለይም መንግስት አዲስ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ ማድረጉን፣ የ”ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ቃል ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ የትምህርት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስራ መስራቱን አብራርተዋል። ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/174cdgzumN/

ማስታወቂያ
የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ (NGAT) የፈተና ጊዜን ስለማሳወቅ
በ 2018 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ የተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ፤
ፈተናው የሚሰጠው ሰኞ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተመደባችሁበት የፈተና ማዕከል እንድትገኙ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፤
• ሁሉም ተፈታኞች በተመደቡበት የፈተና ማዕከል ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ እና በ https://ngat.ethernet.edu.et ፖርታል በኩል የተላከላቸውን Exam Entrance ቲኬት ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።

የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብን ስለማሳዎቅ
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን እናሳውቃለን።
1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።
2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ።

የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት የምትችሉ መሆኑነ እንገልጻለን።
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot

ልጆቻችንን በጥራት ካስተማርናቸው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመወዳደር ብቃትና ችሎታ አላቸው፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
የሆጤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ተመርቋል።
--------------------- // ----------------------
(መስከረም 28/2018 ዓ.ም) በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የሆጤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ የትምህርት ሚኒስቴርና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመርቋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአማራ ክልል በሰሜኑ ጦርነት የተጎዱ 45 ትምህርት ቤቶች ግንባታ መጠናቃቸውንና ሰባት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ እየተገነቡ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ወደፊት ይችን ሀገር የሚመሩ ልጆችን ለማፍራት በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የአንድ ሀገር እድገት የሚረጋገጠው በትምህርት ላይ በሚሰራ ስራ በመሆኑ የትምህርት ስብራቱን ለማስተካል የተለያዩ የለውጥ እርምጃዎች እየተተገበሩ መሆኑን አንስተዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/17URKmXJcE/

ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፤
---------------------------------------------------------
(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራንና ተመራማሪዎች የተካተቱበት የኢትዮጵያ ሴት ተመራማሪዎች ማህበር ምስረታ እውን ሆኗል።
በምስረታው ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ባስተላለፉት መልዕክት ሴት ተመራማሪዎች አቅማቸውን በማሳደግ ሴቶች በምርምርና ፈጠራ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሚናቸውን በሚገባው ልክ መወጣ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።፡
ማህበሩ ሴት ተመራማሪዎች አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨት መልካም አጋጣሚዎችን እንዲጠቀሙና ተተኪ ሴት አመራሮችን ለማፍራትና እርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበትና የሚረዳዱበትን እድል እንደሚፈጥር ክብርት ወ/ሮ ሁሪያ ገልጸዋል፡፡
ሴት ምሁራንና ተመራማሪዎች ያካበቱትን ልምድና እውቀት የህጻናት ትምህርትን ፣ ድህነትን ፣የሴቶች ተሳታፎና ተጠቃሚነትን የሚገድቡ ችግሮችን በጥናትና ምርምር ስራዎች በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣
https://www.facebook.com/share/p/1Bt1LWd7xP/

ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ዙሪያ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት ተፈራረመ ፤
-------------------------- // --------------------
(መስከረም 30/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ለ2018 ዓ.ም ሊተገበሩ በታቀዱ ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የአፈጻጸም ውል ስምምነት (Performance contract) የዩኒቨርሲቲዎቹ የቦርድ አመራሮች በተገኙበት አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዎች ቁልፍ የውጤት አመላካቾችን መሠረት በማድረግ ቆጥረው የወሰዱትን ተግባራት አፈጻጸም ጥራትና ተዓማኒት ባለው መረጃ አስደግፈው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበረ ያለው የመስክ ልየታ ፕሮግራም የአካባቢያቸውን ጸጋ እና በሂደት ያካበቱትን እምቅ አቅም አስተውለው በመለየት የየራሳቸው ተፈላጊነትና ተወዳዳሪነት እንዲኖሯቸው የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው ተቋማቱ በተማሪዎች ዘንድ ተመራጭ ለመሆኑ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Fc6nSzWLq/