የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ-ገዝ አድርጎ መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
------------------------- // ---------------------
(ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም) ምክክሩ በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ተመላክቷል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ዘርፉ በመከናወን ላይ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባው አብራርተዋል።
የተቋማት ስኬትም ይሁን ውድቀት በዩኒቨርሲቲው አመራርና ማህበረሰብ ላይ የሚወድቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በቁርጠኝነት በማስፈጸም ዩኒቨርሲቲዎች ብቃት ያለው ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ማፍራት የሚያስችሉ ተቋማት እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም አክለው ገልጸዋል።
በዚህም ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረውን የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የማድረግ ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶችን በሚገባ በመለየት በመጪው አመት ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገጥማቸውን ጫና በመቋቋም ለእውነትና እውቀት የቆሙና የማይገፋ ጠንካራ ተቋም ሆነው ለመውጣት አስፈላጊውን ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Bod1xW7x1/

በኢትዮጵያና ህንድ መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ትብብር እየተጠናከረ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ አስታወቁ።
የሦስተኛ ዲግሪ ነጻ የትምህርት እድል ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።
------------------------- // --------------------------
(ታህሳስ 11/2018 ዓ.ም) የከፍተኛ የትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ መርሃ ግብሩን ሲከፍቱ እንደገለጹት በሁለቱ አገራት መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለው ወዳጅነትና ትብብር እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ነው።
ይፋ የሆነው የድህረ ምረቃ ትምህርትና ምርምር መርሃ ግብርም የድህረ ምረቃ ትምህርት አቅም በመገንባት በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ትልቅ ሽግግር ለማድረግ እንደሚያግዝ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
ከህንድ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰጠው የትምህርት እድል፣ የምርምር፣ ቴክኖሎጅና ፈጠራን በማሳደግ ብቁ የሰው ሀይል በጥራት ማቅረብ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) በበኩላቸው የመርሃ ግብሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኢንጂነሪንግና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን የሦስተኛ ዲግሪ እጥረት እንደሚያቃልል ተናግረዋል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/16THBQaqkd/

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው የሚገኙ ሀገር በቀል እውቀቶችን በምርምር በማደራጃትና በመሰነድ ለሀገር ልማት ማዋልና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡
------------------------------------ // ----------------------------
(ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ሀገር በቀል እውቀቶች በሳይንሳዊ አሰራር ተደግፈው እንዲሰባሰቡ፣ እንዲደራጁና እንዲሰነዱ የሚያደረግ ሀገራዊ ፕሮጀክትን በእኩል የግንዛቤ ደረጃ ለመተገበር ትኩረት ስጥቶ እየሰራ ይገኛል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከራ ጡሹኔ በዚሁ ጉዳይ ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው የሚገኙ ሀገር በቀል እውቀቶችን በምርምር ደግፈው በማደራጃትና በመሰነድ ለሀገር ልማት ማዋልና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ሀገራችን በዘመናት ሂደት ያካበተቻቸው በርካታ ሀገር በቀል እውቀቶች ቢኖሯትም፣ እስካሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደራጀ መልኩ ተሰንደው ባለመያዛቸው በሚፈለገው መጠን ጥቅም ላይ አለመዋለቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴታው አሁን ላይ ሀገር በቀል እውቀቶችን በምርምር ደግፎ ለሁለንተናዊ ልማት ለማዋልና ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://www.facebook.com/share/p/19rbEhbEjY/

የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ አዲስ ከተመደቡት የጣሊያን አምባሳደር ጋር ተወያዩ
---------------------- // -----------------------
(ታህሳስ 16 ቀን /2016 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ አዲስ የተመደቡትን የጣሊያን አምባሳደር H.E. Sem Fabrizi በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን ለረጅም ጊዜ የቆየ ትብብር ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰው በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይህ ግንኙነታቸው የበለጠ እየዳበረ መምጣቱን ተናግረዋል።
በትምህርት ዘርፉ ኢትዮጵያ እየተገበረቻቸው ያሉ ዋና ዋና የሪፎርም ተግባራትን ለአምባሳደሩ ያብራሩት ክቡር ሚኒስትሩ ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል የትምህርት ሥርዓት ለመዘርጋት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ገልጸውላቸዋል።
በኢትዮጵያ አዲሱ የጣሊያን አምባሳደር H.E. Sem Fabrizi በበኩላቸው ጣሊያን በትምህርት ዘርፉ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ስትሰራ መቆየቷን ጠቅሰው ይህንን ትብብር በማሻሻል ወደ ላቀ ደርጃ ማድረስ እንደሚፈልጉ ለክቡር ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1Ee8AFZSE3/