የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዛቸውንና አስተዳደራቸውን በማሻሻል ትክክለኛ መረጃ የመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
------------------------- // ------------------------
(ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ሥርዓት ለማሻሻል በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ ባሉ የሪፎርም ሥራዎች ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መደረክ አካሂዷል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት የመንግስትም ይሁን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ አያያዛቸውንና አስተዳደራቸውን በማሻሻል ትክክለኛ፣ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት የመስጠት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አያይዘውም ይህ መድረክ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በትምህርት ዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ተግባራትን እንዲያውቁ በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ አያያዝ፣ አስተዳደደርና ግልጽነት ላይ ተመጣጣኝ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በማጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/1C2hzs9JhD/

ሥራ ፈጣሪነትንና ፈጠራን በማስተማርና በማበረታታት ምሩቃንን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ማሸጋገር እንደሚገባቸው ተመላከተ
--------------------------- // ---------------------
(ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲዎች የተማሪዎችን ሀሳብና ፈጠራ በመደገፍ ምሩቃን ከስራ ፈላጊነት ወደ ስራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ዩኒቨርስቲዎች በአብዛኛው በማስተማር ስራ ላይ እንደሚያተኩሩ ያነሱት ሚኒስትር ዳኤታው ነገር ግን የሥራ ፈጠራ ሀሳቦችን ማመንጨትና ወደ ተግባር በመቀየር የማህበረሰቡን ህይወት መለወጥና ኢኮኖሚውን ማሳደግ እንደሚ ጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ይህ ከኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነትም የተማሪዎችና የመምህራን የፈጠራ ሀሳቦችን በመደገፍ ክፍተቶች ለመሙላትና የንግድ ፈጠራ ስራዎችን ለማበረታታት እንደሚያስችል ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሐሰን ሁሴን (ዶ/ር) ስምምነቱ የፈጠራና ኢኖቬሽን ስራዎችን በማበረታታት ችግሮችን ወደ እድል ለመቀየር እንደሚያስችል ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ይንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፤ https://www.facebook.com/share/p/16bk8n2iMU/

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አደረጉ።
------------------------- // -----------------------------
(ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ ህይወት ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ቢሰራም ከትምህርት ጥራት አንፃር የትምህርት ሥርዓቱ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይቷል ብለዋል።
በተጨማሪም ትምህርትና ፖለቲካ በመደበላለቃቸው የትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ፍላጎት ማስጠበቂያ ተደርገው መቆየታቸውንም ሌላው ችግር መሆኑን አንስተዋል።
አሁን አለም እየሄደች ባለችበት መንገድ ተቋቁመን አብረን ለመቀጠልና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በዚህ መንገድ መቀጠል ስለማይቻል ችግሩን ለመፍታት በትምህርት ዘርፉ በርካታ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው እየተተገበሩ እንደሚገኝም አብራርተዋል ። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17vatEPgCE/

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ሥራ የማስጀመር ሥነ ሥርዓት ተካሄደ።
------------------------ // ------------------------------
(ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት፣ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) እና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አስጀምረዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህር ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ለወደፊት ለሀገሪቱ ጠንካራ መሪ ለማውጣት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማቋቋም ከመላ ሀገሪቱ ተማሪዎችን በመቀበል ዛሬ ትምህርት የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሂደናል ብለዋል።
ትልቅ ስልጣኔ የነበራትና ትልቅ ሀገር መሆን የሚገባት ሀገር የምትበላውን የምትለምን ሀገር ሆና ወደ ኋላ ቀርታለች ያሉት ሚኒስትሩ።
ባለፉት የለውጥ አመታት በትንሹ በትልቁ ከመባላት ወጥተን እንዴት ሀገራችንን መለወጥ እንችላለን የሚለውን በማሰብ በትምህርት ሥርዓቱ ጠንካራ ተወዳዳሪና ብቃት ያላቸው ልጆችን ለማፍራት የሚያስችሉ ሥራወች እየተሰሩ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1AAzXZc75i/

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመለከቱ።
------------------- // ---------------------
(ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት የወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የደረሰበት ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
አመራሮቹ የትምህርት ቤቱን የመማሪያ ክፍል፣ የተማሪዎች ዶርም፣ የመመገቢያ አዳራሽ ፣ የአስተዳደር ህንፃና ሌሎች ግንባታዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በምልከታቸውም ግንባታው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን የተመለከቱ ሲሆን ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ ተማሪዎችን ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ የማዛወር ሥራ ይሰራል ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ እስኪደርስ ድረስ ተማሪዎች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ካምፓስ በመቀበል በዛሬው እለት የመማር ማስተማር ሥራ ማስጀመሩ ይታወሳል።