Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
645 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ፣ኢንጂነሪንግ፣አርትና ሂሳብ (STEAM) ማዕከል ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፣
------------------------- // --------------------------
(ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም) የSTEAM ማዕከላት ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣ የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር አስተዋጽኦው የጎላ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የሂሳብ፣ሳይንስና ሥነ-ጥበብ ማበልጸጊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ታደሰ ተሬሳ ገልጸዋል።

በዚህም የሀገር አቀፍ የSTEAM ስልጠና ማቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው ሰነዱ ወተግባራዊ መሆን ሲጀምር ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት መሻሻል፣የቴክኖሎጂና ፈጠራ ክህሎት መዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

የሳይንስ፣አርትና ሂሳብ ትምህርቶች በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተግባር ተደግፈው ለተማሪዎች እንዲሰጡ የመምህራን ኮሌጆችን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ የአጠቃላይ ትምህርት እርከን ላይ የሚያስተምሩ መምህራንን በSTEAM የሥልጠና ማዕቀፍ መሰረት ማብቃት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ ታደሰ አክለውም በቀጣይ ለማዕቀፉ ተግባራዊነት የሚያግዙ ሌሎች የማስፈጸሚያ ሰነዶች እንደሚዘጋጁም ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/17hQt2QuS1/
ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራትን እንደሚያሻሽል ተገለጸ፤

---------------------------- // -------------------------

(ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም) በአዲሱ የትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ዲጂታል ሥርዓት አጠቃቀም ላይ ለወረዳ የትምህርት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ባለሙያዎች እና ለ2ኛ ደረጃ የኣይሲቲ ትምህርት መምህራን በሀገር አቀፍ ደረጃ በዘጠኝ የሥልጠና ማዕከላት ላይ የአሰልጣኞች ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

የትምህርት መረጃ አመራርና ኣይሲቲ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስብ ለማ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የውስጥ አቅም የበለጸገው ኦንላይን የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የዘርፉን የመረጃ ወቅታዊነትና ጥራት የሚያሻሽል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከትምህርት ተቋማት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ላይ የሚስተዋሉ የወቅታዊነት፣ጥራትና ተዓማኒነት ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችል እና የትምህርት መረጃ ሥርዓቱን የሚያዘምን ዲጂታል ሥርዓት ማበልጸግ መ/ቤቱ እየተገበራቸው ካሉ የሪፎርም አጃንዳዎች ማካከል አንዱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አቶ ሰብስብ አክለውም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2018 ዓ.ም የትምህርት መረጃዎችን በዚህ ኦንላይን የመረጃ ሥርዓት ብቻ እንዲያስገቡ አቅጣጫ ተሰጥቶ ወደ ተግባር የተገባ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በፌዴራል የሚሰጠው የትምህርት ቤቶች የቁሳቁስና የድጎማ በጀትም የሚለቀቀው ወደ ሥርዓቱ በሚገባው የተማሪዎች መረጃ መሰረት ብቻ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BDttc22Db/
ማስታወቂያ

ለትምህርት ማህበረሰቡና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ በረቂቅ መመሪያዎችና ደንብ ላይ አስተያየት እንድትሰጡ ስለመጠየቅ፤

የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ3 የተለያዩ ጉዳዮች ማለትም፤
1. የርቀት ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/oat5fXajoS5Fiwgj8
2. መደበኛ ያልሆነ የጎልማሶች የሙያ ክህሎት ማበልጸጊያ ስልጠና የአተገባበር ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/JFWANT1kUpYZmiLe8
3. የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች የሽግግር ረቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/3WpLE88aXBTFGZG67
4. የማታ ትምህርት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ረለቂቅ መመሪያ፤ ሊንክ- https://forms.gle/ghKnfuhwx1u6eSJc7

በመሆኑም ሰነዶቹን በማንበብ አስተያየት እንድትሰጡ እየጠየቅን፤
 ለመጀመር ከእያንዳንዱ ረቂው መመሪያ ፊት ለፊት ያሉትን ሊንኮች መጫን፤
 በመቀጠል ማስፈንጠሪያ የሚለውን በመጫን ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፣
 ሰነዱን ካነበባችሁ በኋላ የተጠየቁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን ሞልታችሁ (submit) የሚለውን በመጫን መረጃውን መላክ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር
ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በነዚህ ውስን ክፍት ቦታዎች ተማዝግባችሁ ለመማርና የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች https://sbs.moe.gov.et/apply በመግባት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
7ተኛው ዙር የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች ግምገማና የደረጃ ዕውቅና አሠጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።
---------------------------- // ---------------------------

(ጥር 08/2018 ዓ.ም) የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ያደረጉት ውይይት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታተሙ የምርምር ውጤቶች ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የጠበቁና ተዓማኒነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት ቁልፍ መልክት የሀገር ውስጥ የምርምር ጆርናሎች የግምገማና የእውቅና አሠጣጥ ሂደቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላቸው አሠራሮች ጋር የተጣጣሙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

የስራ ሀላፊው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባደረጉት ገለጻ የሀገር ውስጥ ጆርናሎች በሳይንሳዊው ማህበረሰብ ዘንድ ታይታን እንዲያተርፉ በትኩረትና በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

መሠል ተግባራት የሀገሪቱን የምርምር ባህል ከማሳደጋቸውም በላይ፣ ምሁራን በሥራዎቻቸው የሚገባቸውን ዕውቅና እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታና መደላድል የሚፈጥር መሆኑ በውይይት መድረኩ ላይ ተመላክቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤
https://www.facebook.com/share/p/17yt2DeGgZ/
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በተገነባ የት/ቤት ምርቃት ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት
------------------------- // -------------------------

በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል።

ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን ያገለግላል።

ግቢው ማደሪያ ክፍሎችን፣ መማሪያ ክፍሎችን፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች ያሉት የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ ነው።

ይኽ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ፣ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው።