Ministry of Education Ethiopia
169K subscribers
4.25K photos
40 videos
6 files
644 links
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Download Telegram
የተረጋጋ ሀገር እንዲኖር በትምህርት ዘርፉ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል እድል በመስጠት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መሄድ ያስፈልጋል፤ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

-------------------- // -----------------------

(የካቲት 22/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዳሰነች ወረዳ የተገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመረቁበት ወቅት በትምህርት አቅርቦት ረገድ በሁሉም አካባቢ ምንም ልዩነት ሊፈጠር አይገባም ብለዋል።

ይህንንም ለማረጋገጥም በትምህርት ዘርፉ የተለያዩ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝም አብራርተዋል ።

በተለይም ምቹ የመማሪያ ከባቢን በሁሉም አካባቢ ለመፍጠር “በትምህርት ለትውልድ” የትምህርት ቤቶችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ንቅናቄ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውንና የነባር ትምህርት ቤቶች ጥገና መደረጉን አንስተዋል።

አክለውም የትምህርት ስራ የሚለወጠው ከታች ጀምሮ ሲሰራ መሆኑን በማመን በከተማና በባለሀብቶች ብቻ ታጥሮ የቆየውን የቅድመ አንደኛ ትምህርት በመቀየር በሁሉም አካባቢ ያለ ልዩነት ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ጠቅሰዋል።

በዚህም ባለፉት ዓመታት ከ34 ሺ በላይ አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማና በገጠር ተገንብተው የአምስተና ስድስት ዓመት ህፃናት እየተማሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

ትምህርት ለሁሉ ነገር ወሳኝ በመሆኑ ልጆቻችንን በአግባቡ በማስተማር የአለምን ፈተና መቋቋም የሚችሉ ጠንካራ ሀገር ተረካቢዎችን ለመፍጠር መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/18FMt7JKvz/
ውሳኔዎችን ስናሳልፍና ጉዳዮችን ስናስፈጽም ከጥቅም ግጭት እና ሙስና ተግባር የጸዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤
--------------------- // ------------------------
(የካቲት 24/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከፌዴራል ስነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ዘርፍ-ተኮር ስልጠናዊ ውይይት አካሂዷል።

በስልጠናዊ ውይይቱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ስልጠናዊ ውይይቱ ከአመራሩ የዕለት ተዕለት ስራ ጋር ተያያዥነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው ውሳኔዎችን ስናሳልፍና ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ስናስፈጽም ከጥቅም ግጭትና ከሙስና ተግባር የጸዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

መንግስት ትውልድ መቅረጽ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም መሰረት የትምህርት ዘርፉ የትውልድን ሥነ-ምግባር ከመሰረቱ ለማነጽ የግብረገብ ትምህርትን በስርዓተ-ትምህርት አካቶ እየሰጠ መሆኑን አንስተዋል።

የስነ-ምግባር ችግሮችን እና የሙስና ተግባራትን ለመከላከልና ለመቅረፍ አሰራሮችን ማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ ለውጥ በሚያመጣ መንገድ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ውይይታዊ ስልጠናውም ለእነዚህ ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1BZBdjBbBr/
በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ የታዩ ለውጦችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እጅግ አበረታች መሆናቸው ተገለጸ።
------------------------------ // --------------------------

(የካቲት 26/2018 ዓ.ም) ከዛምቢያ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ እየወሰደቻቸው ባሉ የሪፎርም ተግባራት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ የተገበረቻቸውን የሪፎርም ተግባራ አስመልክቶ ለዛምቢያ የትምህርትና ስልጠና ልኡካን ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ገለፃውን ያደረጉት የትምህርት ፕሮግራሞና ጥራት መሻሻል መሪ ስራ አስፈጻሚ ዮሐንስ ወጋሶ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፉ የወሰደቻቸው የሪፎርም እርምጃዎችና የተመዘገቡ ስኬቶች የቀጣናው ሀገራት ትልቅ ልምድ የሚቀስሙባቸው መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ ያከናወነቻቸው የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የገለጹት መሪ ስራ አስፈጻሚው ጥራትን ከማሻሻል ባለፈ ሁሉም ዜጎች እኩል የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ለማድረግና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዛፉ አብርሃ በበኩላቸው የተደረጉ ለውጦችና የፓሊሲ ማሻሻያዎች በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ የነበሩ መዋቅራዊ ክፍተቶችን ለመሙላት ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1ArBckGwJQ/
የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቋንቋ ዲጂታይዝ አድርጎ ለትምህርት ግብዓት መጠቀም የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ።
---------------------- // ----------------------

(የካቲት 26/2018 ዓ.ም) የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነዱ በትምህርት ሚኒስቴር እና በባህልና ስፓርት ሚኒስቴር መካከል የተፈርሟል።

ስምምነቱ ሀገራችን ያሉ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቋንቋን ዲጂታይዝ በማድረግ ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ እና ለትምህርት ግብዓትነት እንዲውሉ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል ።

በተለይም የጽሕፈት ሥርዓት ያላቸውን ቋንቋዎች ዲጂታይዝ የማድረግ፣ የመሰነድና የቴክኖሎጂ ቋንቋ የማድረግ ሐሳብን መሰረት አድርጎ በሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ቋንቋዎቹን ለማጎልበትና ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ፍይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/@ministry-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብንና አገርን የመለወጥ ሚናቸውን በላቀ ቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስገነዘቡ።
‎ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የግማሽ ዓመት ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
‎
----------------- // ---------------------
‌‎(የካቲት 30/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መድረኩን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ተቋማት አገርን ለመታደግ ከአገር መከላከያ ያልተናነሰ ሚና ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰብንና አገርን የመለወጥ ኃላፊነታችሁን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
‎
‎ዩኒቨርስቲዎች ዕውቀትና እውነት ተዋህዶ የሚሰጥባቸው ቦታዎች በመሆናቸው ችግሮችን በጥናትና በውይይት በመፍታት ከመንግስትና ከህብረተሰቡ የሚጠብቅባቸውን አስተዋጽኦ መወጣት እንደሚጠባቸውም ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
‎
‎ከዓለም የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ እድገት አኳያም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሞራል መሠረታቸውን በማሳደግ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ጥቅም የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

ተለዋዋጭ በሆነው የዓለም ሁኔታ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሀገር እድገትና መረጋጋት ኃላፊነታቸው የላቀ መሆኑንም አንስተዋል።
‎
‎የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በበኩላቸው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የውጤት የአፈጻጸም አስተዳደር ስርዓት ወደ ተግባር እንዲገባ መደረጉን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1DzzFR8Hm8/
የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።
--------------------- // --------------------

(የካቲት 30 /2018 ዓ.ም) 11ኛው ሀገር አቀፍ የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን ''የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና አለው!'' በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት ሰመራ ከተማ ስኬታማ ስራዎችን በመጎብኘትና የፓናል ውይይት በማካሄድ ተከብሯል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር በአስቦዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ቤት ምገባ ለተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት አይተኬ ሚና ያለው በሆኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚበ ገልጸዋል።

መርሃ-ግብሩ በለውጡ መንግስት ትኩረት ተሰጥቶት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝና ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑንም አያይዘው አንስተዋል።

ለት/ቤት ምገባ ውጤታማነት የሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ የአጋር ድርጅቶችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበው ይህ መርሃ ግብር በተለይም አነስተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች እፎይታን የሰጠና በተማሪዎች የትምህርት አቀባበልና ጤንነት ላይ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1HuYqcWsau/