የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ከምሽት 1፡00 ጀመሮ ማየት ይቻላል።
የሀገረ አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የሚታይባቸውን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል።
አገልግሎቱ የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉም አሳውቋል።
ተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
አያይዞም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን ምአገልግሎቱ ያሳውቃል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

የትምህርት ሚኒስቴር በክረምት በጎፈቃድ መርሃ ግብር በ43.5 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነቡ ሦስት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን አስጀመረ።
------------------------- // ----------------------------
(ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም) ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የ2018 ዓ.ም ክረምት በጎ ፈቃድ በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን የሦስት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ያስጀመረ ሲሆን 4.3 ሚለየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍም አድርጓል።
በመርሃ ግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮ፤ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፣የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ እና የቡኖ በደሌ ዞን አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ ከ6ዓመት በፊት ያስጀመሩት ፕሮግራም ዛሬ ላይ ህብረተሰቡ ከቃል ወደ ተግባር ቀይሮታል ብለዋል።
ይህ መርሃ ግብር የህብረተሰባችንን የመደጋገፍ፣ የመተባበርና የመረዳዳት እሴት የበለጠ እንዲጎለብት አድርጎታል ያሉ ሲሆን፦
በዘንድሮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ሦስት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ማስጀመሩንና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Jz8dB46Hx/

የትውልድ ሥነ ምግባርና ግንባታና ሙስናን የመከላከል ተግባር ቀጣይነት ያለው የሥራ ባህል ለውጥ የሚፈልግ መሆኑ ተመላከተ
-------------------------------- // ---------------------------------
(ነሐሴ 22/2018ዓ.ም.) ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሥነ-ምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚዎች ከ2019-2021 የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የዕቅድ ውይይቱ ዓላማ በአገራዊ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታ፣ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል እንዲሁም የህግ ተጠያቂነትን የማስፈንን ሥራ ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በተጨማሪም የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን፣ ስትራቴጂን በጋራ ለመመልከትና በትምህርት ዘርፉ ሪፎርም አተገባበር ዙሪያ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ሚናቸውንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻልና ቀጣይ ተልዕኮዎችን ግልጽ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነፃነት ካሳሁን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የትውልድ ሥነ ምግባር ግንባታና ሙስናን የመከላከል ተግባር ቀጣይነት ያለው የሥራ ባህል ለውጥ ስራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም በተቋማት የሥነ ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራ የአንድ ቀን ስራ ባለመሆኑ የስነ ምግባር መከታተያ የሥራ ክፍሎች በእቅዳቸው የተቀመጡ ተግባራትን በተቀናጀ አመራር ፣በጋራ ኃላፊነት፣ በጠንካራ ክትትልና ተጠያቂነት ማስፈጸም እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1DQRsNVrEw/

ማስታወቂያ
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት በሚሰጥባቸው ነባርና አዲስ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለመቀበል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁና ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች በተመዘገባችሁበት ሊንክ መለያ ኮዳችሁን ( Reference Number) በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን።
በተጨማሪም ለፈተና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ፈተና የሚሰጠው በበየነ መረብ (online) ስለሆነ የሚቀርባችሁን የፈተና መስጫ ማዕከል በዛው ሊንክ በመግባት መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የሙከራ ፈተና እሮብ ነሃሴ 27/2018 የሚሰጥ ሲሆን ዋና ፈተናው ነሃሴ 28 የሚሰጥ መሆኑ አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን።