2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች የመንግስት ኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፤ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን አነጋግረዋል፡፡
………………………………….. // …………………………….
(መስከረም 04/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በ2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቁባቸው ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ እንደገለጹት ጦርነትና ግጭት ሸሽተው ከትግራይ የወጡ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከቻሉ ከትግራይ ወጥተው አሊያም ባሉበት በኦንላይ ለመማር የሚችሉበት ቦታ ላይ እንደሚመዘገቡና ትምህርትታቸውን መማር እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡
ተማሪዎቹን ምዝገባ ለማካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር በበይነ መረብ የምዝገባ ስርዓት ማዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ ሁሉም በትግራይ ክልል ባሉ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የኦንላይን መተግበሪያ ፕላት ፎርም በመሙላት እንዲመዘገቡ አሳውቀዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BgiGPjwXJ/

የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም መስክ የወደፊቱ አገር መሪዎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ ።
------------------------ // -------------------------
(መስከረም 05/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ ከተመደቡ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም በኩል የወደፊቱ የአገር መሪ የሚሆኑ ዜጎች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ይሆናሉ ብለዋል።
ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ፣ በሳይንስ፣ በፖለቲካ ፣በፍልስፍና በሌሎችም የሚገነቡ አገር ወዳድ ዜጎች መፍለቂያዎች እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
አያይዘውም ለሁሉም እኩል የሚያስቡና ሁሉንም እኩል መምራትና ማገልገል የሚችሉና አገርን ከቅርቃርና ከችግር ማውጣት የሚችሉ ዜጎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።
ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የሚማሩባቸውና ከሁሉም ቦታ የተውጣጡ መምህራንና በችሎታ ተመርጠው የሚያስተምሩባቸው ተቋማት መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Efqvo52qb/

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!
ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።
ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።
ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።
በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያና ስሎቫኪያ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ
---------------------- // -------------------------
(መስከረም 06/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር በኢትዮጵያ ራስቲስላቭ ክሪዛንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት መካከል በትምህርቱ ዘርፍ ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ከስሎቫኪያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው፣ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ስላሉ የትምህርት ሪፎርም ሥራዎች ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።
በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ በመለየት እንዲደራጁ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ አስተዳደራዊ ነፃነት እንዲኖራቸው ራስ ገዝ በሆነ መልኩ እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።
የትምህርት ሪፎርሙ የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጣ የተለያዩ የድጋፍና የትብብር አማራጮች እንደሚያስፈልጉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአዲስ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በመገኘቷ ከዚህ ጋር በተያያዙ አዳዲስና ተፈላጊ የትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HF5jLJ5fu/

ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል
በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል።
ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።
1. የምደባው ዋና መስፈርቶች
1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ
የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም
የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።
1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት
በዩኒቨርሲቲዎቻችን ብዝሃነትን ለማጠናከር እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
• 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤
• 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። ሙሉ መረጃውን ለየት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com

በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ና ነባር ተማሪዎች በሙሉ
በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የትምህርት ሂደታችሁ እንዳይስተጓጎልና ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል፣ በጠየቃችሁት መሰርት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እየገለጽን በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሚገለፅላቹህ ሲሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
በተለያየ ምክንያት ትግራይ ባሉት ዩኒቨርስቲዎች መቀጠል የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።
የትምህርት ሚኒስቴር

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።
የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences